በአድዋ ጦርነት ወቅት ለእናት ሀገራቸው ነፃነት የተዋደቁ ፈረሰኞችንና ፈረሶችን ለመዘከር በ1933 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል ጥር 23/2013 ይከበራል፡፡ዘንድሮ ለ81ኛ ጊዜ የሚከበረውን ይህ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በፈረስ ትርዒት፣ በፓናል ውይይቶችና በእደ ጥበባት ኤግዚቢሽን ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ዘውዲቱ ወርቁ ተናግረዋል፡፡ከ33 በማይበልጡ አባላት እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር በአሁኑ ወቅት ከ53 ሺህ በላይ አባላትን በማቀፍ የብሔረሰቡን ባህልና ወግ እያስተዋወቀ ነው፡፡ በዓሉ የተነቃቃ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር የጎላ ሚና እያበረከተ ነው ተብሏል፡፡ (አብመድ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል