ሠልፍ፣ ተቃውሞ፣ መፈክር፣ … ያለፉት 50ዓመታት መለያችን ሆኖ ቆይቷል። በተለይ ባለፉት 27ዓመታት ዘመነ ፍዳ ወወያኔ ደግሞ በተለይ በአውሮጳና አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን “ሼም ኦን ዩ …” ሳይሉ የሚያልፍ ወር አልነበረም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለዚህም ይመስላል “አሜሪካ አገር ኋይት ሃውስ ደጃፍ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ” ስትል ብትውል ማንም የሚነካህ የለም ሲባል የሰማው ክበበው ገዳ “እኛስ ሃገር ቢሆን አራት ኪሎ ቤተመንግሥት በር ላይ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ!” እያልክ ብትጮህ ማን ይነካሃል?” በማለት የቀለደው። ይህ “ማንም አይነካኝም” የሚለው አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን የሰልፍ ሱሰኛ እስኪመስሉ ድረስ ለሁሉም ችግር ሰልፍን ብቸኛ አማራጭ ሲያደርጉ የሚታዩት። ያለፉት 27ዓመታት የተወጣው ሰልፍ ውጤት አላመጣም ለማለት አይቻልም። የተወጡም ሰልፎች … [Read more...] about የተቃውሞ ሠልፍ “ሱስ”?!
Editorials
ርዕሰ አንቀጽ
ተመልሰናል!
የጎልጉል ርዕሰ አንቀጽ በቅድሚያ ለጎልጉል ወዳጆችና አንባቢያን እንዲሁም ጠላቶች ለመጥፋታችን በርካታ አጥጋቢ ምክያቶች ቢኖሩንም በቅድሚያ ይቅርታ ለመጠየቅ እንወዳለን። መረጃ ከእኛ ለማግኘት ፈልጋችሁ ለበርካታ ወራት ሳታገኙ በመቅረታችሁ እናዝናለን። “የት ጠፋችሁ?” በማለት በተደጋጋሚ ስትጠይቁን ለነበራችሁ ቅኖች ምስጋናችን የላቀ ነው። የእናንተን መሰሉ ቅንነት ወደፊትም በብርታት እንድንቀጥል የሚያደርገን ነውና መልካምነታችሁ ወደፊትም አይለየን። በመጥፋታችን ደስ ብሏችሁ የነበረ የበለጠ ደስ ይበላችሁ እንደወጣን አልቀረንም፤ መጥተናል። አገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ስንመለከተው በርካታ ተስፋ ሰጪ ተግባራት ሲደረጉ ብንመለከትም ያንን የሚያፈርስ እኩይ ተግባር ሲፈጸምም እናያለን። የተደፈውን ቀዳዳ መልሰው የሚቆፍሩ ክፉዎች የመኖራቸውን ያህል ላገራቸው ምንም ጩኸት ሳያሰሙ … [Read more...] about ተመልሰናል!
ሕዝብ ከስሜትና ከተራ ብሽሽቅ በመራቅ በያለበት የአገሩ ዘበኛ ይሁን!
ቀደም ሲል በሃዋሳ፣ ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ በተቀነባበረ ሁኔታ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ፣ በቤኒሻንጉል በተለያዩ ቦታዎችና በተለይም በአሶሳ የደረሰንና እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥራት ጭፍጨፋ፣ ሕዝብ ወደ ምሬት እንዲሄድ ሆን ተብሎ የሚደረግ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ በጥሞና ለምትከታተሉ ሁሉ፤ በባህር ዳር ለጠቅከላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ቀና ተግባርና የለውጥ ሩጫ እውቅና ለመስጠት የተጠራውን ሰልፍ ለማወክ ከወዲሁ ቦንብ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውን ለሰማችሁ፣ የደኅንነት ኃይሉን ትብትብ በወጉ ለምትረዱና ለምትገነዘቡ፤ በተለያዩ የአገሪቱ የልማት ተቋማት ላይ የሚፈጸመውን የኢኮኖሚ አሻጥር በውል ለምትከታተሉ፤ ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጋጨት የሚሸረቡ ተንኮሎችን ለምታጤኑ፤ ለውጡ እንዲኮላሽና አገሪቱ ወደ ትርምስ ውስጥ እንድትገባ በተሸናፊነት ውስጥ ሆነው ለጥፋት የሚመደበውን በጀት ለምትሰሙ … [Read more...] about ሕዝብ ከስሜትና ከተራ ብሽሽቅ በመራቅ በያለበት የአገሩ ዘበኛ ይሁን!
Tank Man 1989
የዛሬ 29 ዓመት በቻይና የታይናንመን አደባባይ የሆነውን ታሪክ ስናስብ “ታንክ ማን” ወይም በግልቡ የአማርኛ ትርጉም “ታንክ ሰው”ን እናስባለን። እናያለን። የወቅቱን ገድሉን እናስባለን። ወደ አገራችን ስንመለስ ምንም እንኳን ምንም ያልተባለላቸው ጀግኖች ያለመታወሳቸው ሊያሳዝነን ሲገባ፣ አሉ የሚባሉት ላይ መማማል መመረጡ በቃላት ሊገለጽ የማይችል የሃዘን አዙሪት ውስጥ ይከተናል። ከሁሉም በላይ ደም ሰፍረን ትርፍ እንሻለን። ለአገር ክብርና ልዕልና ያለፉትን የማይተኩ ዜጎች የግብር ማወራረጃ ለማድረግ ይዳዳናል። ህወሓት “በሞተብኝ መጠን ልዝረፍ” በሚል ቀረርቶ ል27 ዓመታት ያደነቆረንና ለዚሁ ግልብ ዓላማው የጨፈጨፈን፣ የደገንብን ታንክና አፈሙዝ፣ ያሰረን፣ ያቆሰለን፣ የገረፈን ሳያንስ ዛሬም በተመሳሳይ “የእኛ ደም” በሚል ክፍያ ሲጠየቅ ሰምተናል። ከሁሉም በላይ ደግሞ አሳዛኙና … [Read more...] about Tank Man 1989
ጥያቄው አሁንም ግልጽ ነው!
ያለ ሕዝብ ፍላጎትና ምርጫ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) በማለት የሰየመ የአሸባሪ ወንበዴዎች ቡድን አሁንም የውንብድና ተግባሩን እየፈጸመ ይገኛል። ይህ በዓለምአቀፋዊ የአሸባሪዎች መረጃ ቋት ውስጥ በአሸባሪነት የተመዘገበ ድርጅት በነጻ አውጪ ስም ሕዝብ ሲጨፈጭፍ፣ ሲያዋርድ፣ ሲያስር፣ ከአገር ሲባርር፣ ሲያፈናቅል፣ … የኖረ ድርጅት አሁንም በዚሁ ተግባሩ ቀጥሏል። ዓላማ ብሎ የተነሣለትን አገር ማፍረስ የተቃወሙ፣ ሃሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ የገለጹ በሙሉ አሸባሪ፣ ጸረ ልማት፣ ጸረ ህዝብ፣ … በማለት ሲገድልና ሲያሰቃይ ኖሮ አሁን ደግም “አላሰርኩም” ሲላቸው የነበረውን እስረኞች “እፈታለሁ” ብሏል። ይህ በህወሓት/ኢህአዴግ ስለተነገረው መግለጫ ጥቂት ነጥቦች ብቻ እናንሳ፤ በመጀመሪያ ኃይለማርያምና ጓደኞቹ በኢትዮጵያ ስም እና ስለ ኢትዮጵያ … [Read more...] about ጥያቄው አሁንም ግልጽ ነው!
ኃይለማርያም ከየት ይለቃል? ያልነበረ “ፓርላማ” ወዴት ይበተናል?
ከወራት በፊት የመልቀቂያ ደብዳቤ ያስገባውን አባዱላ ገመዳ የኢህአዴግ ሥራአስፈጻሚ ጥያቄውን አጽድቆለታል ተብሏል። ከዚህ ጋር ተከትሎ በቀጣይ ኃይለማርያም ከ“ሥልጣን” ይወርዳል የሚለው ጉዳይ በስፋት በሁሉም ዓይነት ሚዲያ እየተስተጋባ ነው። በተያያዘ ወሬ አዲስ አበባ ላይ ያለውና ሰሞኑን በመጠኑ ሥራውን መሥራት የጀመረውን “ፓርላማ” ህወሓት ሊበትነው እያቀደ ነው የሚል መረጃ ተሰምቷል። ከዚህ በተጨማሪም ከትግራይና ሌሎች ታማኝ ክልል/ሎች በስተቀር በክልል የሚገኙ ምክርቤቶችን በሙሉ ህወሓት ሊበትናቸው አሢሯል የሚል መረጃ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ እየተሰማ ነው። ከገቢ አንጻር የሰበር ዜና ልክፍት የተጠናወተው ሚዲያ ይህ መሰሉን “መረጃ” ሲያስተላልፍ ከመረጃው ጋር ሕዝብ ማወቅ ያለበት ምንድነው የሚለውን ኃላፊነት የዘነጋው ይመስላል። ኃይለማርያም ደሳለኝ በሟቹ መለስ ተመልምሎ ወደ … [Read more...] about ኃይለማርያም ከየት ይለቃል? ያልነበረ “ፓርላማ” ወዴት ይበተናል?
የህወሃት አጀንዳ + የዘር ፖለቲካ + የሜንጫ ፖለቲካ – መጨረሻው ተያይዞ …
የኢትዮጵያ ህወሓት ሰራሹ “ፌደራሊዝም” ወደ ተፈራው ቀውስ እየተንደረደረ መሆኑንን የሚያሳዩ የዜና ዘገባዎች የተሰሙት ገና ከጅምሩ ነበር። በርካታ ባለሙያዎችና የተቀናቃኝ ፖለቲካ መሪዎች በተደጋጋሚ ስጋታቸውን ቢገልጹም ተቀባይነት ሊያገኙ ባለመቻላቸው የጎሣና የብሄርተኛነት በሽታ እያደር ኢትዮጵያን እየበላት አሁን ያለችበት ደረጃ አድርሷታል። ችግሩ አለመስማትና አለማወቅ ብቻ ሳይሆን ዓላማ ያለው፣ በቅጥረኝነት አገሪቱን የማፈራረስ ተልዕኮ የማሳካት ጉዳይ በመሆኑ የመከሩ፣ የዘከሩ፣ ያስጠነቀቁ፣ ስጋታቸውን አደባባይ ያወጡ ዜጎች ወንድ ሴት ሳይባል ተፈጅተዋል። አገሪቱ ምትክ የሌላቸውን ልጆቿን እንድትከስር ተደርጋለች። ግድያውና አፈናው ብቻ ሳይሆን መላውን የአገሪቱን ህዝብ እርስ በእርስ ጎሣና ጎጥ ለይቶ እንዲናከስ እየተወተወተና እየተገፋ አገሪቱ ቆዳዋ በልጆቿ ደም እንዲለወስ ሆኗል። ዛሬ … [Read more...] about የህወሃት አጀንዳ + የዘር ፖለቲካ + የሜንጫ ፖለቲካ – መጨረሻው ተያይዞ …
የህወሓት ፕሮግራም፤ የመለስ ሌጋሲ – ዜጎችን ማፈናቀል፤ ማጋደል!
ገና ከመነሻው በበረሃ ያወጣው ፕሮግራሙ በግልጽ እንደሚያመለክተው የህወሓት ዋንኛ ዓላማ ኢትዮጵያን አዳክሞና በጎሣ ከፋፍሎ ትግራይን ታላቅ በማድረግ ሪፑብሊክ መመሥረት ነው። ባለፉት 26 ዓመታት ይህንን ለማሳካት በኢትዮጵያ ውስጥ ያልፈነቀለው የጎሳ ድንጋይ የለም፤ ያላጋጨው ሕዝብ፤ ያላጋደለው ወገን የለም፤ ትግራይን ሳይጨምር! ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ሳያስበው አስፈነጠረው እንጂ የመለስና ዋናዎቹ የህወሓት መሥራቾች ዕቅድ ይህንኑ ለማሳካት እንደሆነ ሰሞኑን በተከታታይ በምናትመው የአቶ ገብረመድኅን ጽሁፍ በግልጽ የተቀመጠ ሐቅ ነው። የወቅቱ የፍጅት ዓላማ ደግሞ ኦሮሞን ከሶማሊ ወገኖቹ ጋር በማጋጨት የአገዛዝ ዘመኑን ማራዘም፤ ሁለቱን ጎሣዎች በማይረሳ ቂምና ጥላቻ ውስጥ ማስገባት፤ ይህንንም እስካሁን በሌሎቹ ጎሣዎች መካከል ከፈጠረው ጥላቻና ቁርሾ ጋር ተዳምሮ የኢትዮጵያን ኅልውና አጥፍቶ … [Read more...] about የህወሓት ፕሮግራም፤ የመለስ ሌጋሲ – ዜጎችን ማፈናቀል፤ ማጋደል!
ፍትህን ሰቀለው በፍትህ ስም የፕሮፓጋንዳ ዳንኪራ – የጨለማው ሳምንት!!
የ“ፍትህ” ወይስ የጨለማ ሳምንት? (ርዕሰ አንቀጽ) “ገንዘብ ሲናገር ፍትህ ጸጥ ይላል!” ይህ የተጻፈው በአንድ የጎንደር እስር ቤት ውስጥ ነው። የተጻፈው በግድግዳ ላይ ሲሆን በብዕር ወይም በቀለም አይደለም። ፍትህ ከተጓደለባቸው አንዱ የእጁን ጣት በመብጣጥ በደሙ ነው። ፍትህ የተዛባባቸው ይህንኑ አባባል ልክ እስር ቤት እንደገቡ ይሳለሙታል። በብዙ የአገሪቱ ማጎሪያዎች ውስጥ ተመሳሳይ ስሜት ገላጭ ሃረጎች ይጻፋሉ። ፍትህን አደባባይ ሰቅለው በምስኪኖች ህይወት ለሚጫወቱ ይህ ሁሉ ስላቅ ነው። ፍትህን አደባባይ ሰቅለዋት፣ በፍትህ ስም እየማሉ በድግስ ሊያሽካኩ ይወዳሉ። ፍትህ የዜጎች ሁለንተናዊ ህይወታቸው ትርጉም የሚያገኝበት ውድ ጉዳይ ነው። ይህንን ሃቅ የበረሃው አባዜው አልለቅ ያለው ህወሃት ጥንቅቆ ያውቀዋል። ሊክደውም አይችልም። ለዚህም ነው “ህገ መንግስት፣ ህግ፣ አዋጅ፣ የሰብዓዊ … [Read more...] about ፍትህን ሰቀለው በፍትህ ስም የፕሮፓጋንዳ ዳንኪራ – የጨለማው ሳምንት!!
ህወሓት: በነፃ ፕሬስ መቃብር ላይ የቆመ አገዛዝ!
ኢትዮጵያ በፕሬስ ነፃነት ከዓለም 150ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች! አገሪቱ የነፃ-ሚዲያ ባለቤት የምትሆነው በህወሓት መቃብር ላይ ነው! ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና ድጋፍንም ሆነ ተቃውሞን ምክንያታዊ በሆኑ ነገሮች መግለጽ የሚችልና ፖለቲካዊ ንቃት ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚደረገው ትግል፤ ካለ ነፃ ፕሬስ ተዋፅኦ ስሙር ሊሆን የሚችል አይደለም፡፡ ገዥው ኃይል የግሉ ፕሬስ ለአገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና አሳታፊነት ያለው የፖለቲካ ሥርዓት እንዲፈጠር የራሱን በጎ ሚና እና አበርክቶ እንዲወጣ ምቹ የሥራ ምህዳር ከመፍጠር ይልቅ በትዕግስት አልባ ባህሪው የተነሳ በነፃ ፕሬሱ ላይ የተለየ ሃሳብና የፖለቲካ አመለካከት በተንፀባረቀ ቁጥር በመደንበር ሚዲያዎቹን በመዝጋት፣ በግልፅ የተደነገገውን ህግ በህብዑም ሆነ በግላጭ ሲንደው ታይቷል፡፡ በውጤቱም፤ በየዓመቱ የዓለም … [Read more...] about ህወሓት: በነፃ ፕሬስ መቃብር ላይ የቆመ አገዛዝ!