• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች

February 11, 2020 07:53 pm by Editor Leave a Comment

የሙያው ባለቤቶችና ተመራማሪዎች ታጋቾችን ማስለቀቅ ራሱን የቻለ ታላቅ ጥበብና ስልት ይጠይቃል ይላሉ። የአጋቾችን ስነልቡና ለመስረቅ፣ ለማለስለስ፣ ወዘተ አደራዳሪዎች ፈጽሞ ሊታሰቡ የማይችሉ የሚባሉ ዘዴዎችን ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ። የአጋቾቹን ፍቅረኛ ወይም እናት ወይም ሌላ ተወዳጅ የቤተሰብ አባል ወደ ዕገታው ቦታ በማምጣት በድምጽ ማጉያ የተማጽንዖ ቃል እንዲናገሩ ይደረጋሉ። የሃይማኖት መሪዎች፣ ሽማግሌዎች፣ ሌሎች ተጽዕኖና አመኔታ ሊጣልባቸው የሚችሉ ሰዎች በዚህ እንዲሳተፉ ይደረጋል። ይህንና ሌሎች መሰል ተግባራትን በመጠቀም የታገቱት ያለ አንዳች ችግር በነጻ እንዲወጡ ሙከራ ይደረጋል። በዚህም ምክንያት ረጅም ጊዜ የሚወስድ ዕገታ በሰላም የመጠናቀቅ ዕድሉ በጣም ከፍተኛ ነው ይባላል። 

ማፈን፣ ማገት፣ ሰዎችን ያለፈቃዳቸው በቁጥጥር ሥር ማዋል፣ ወዘተ ያልተለመደ ተግባር አይደለም። በአብዛኛው የጤና ችግር ያለባቸው፣ አእምሯቸው የተቃወሰ፣ ከአእምሮ ሐኪም ቤት ያመለጡ ወይም መግባት ሲገባቸው ሳይገቡ የቀሩ፣ አሸባሪዎች፣ የጥቃት ሰለባዎች፣ ወንጀለኞች፣ እስረኞች፣ የፖለቲካ ዓላማ ያላቸው እና ሌሎችም በማገት ተግባራት እንደሚሰማሩ በየጊዜው የሚወጡ ዘገባዎች ይጠቁማሉ። የአብዛኛዎቹ ዓላማም በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ለማስከበር ያልቻሉትን እጅ በመጠምዘዝ ለማስፈጸም ሲሆን ጥቂት የማይባሉ ደግሞ ተፈጸመብን የሚሉትን ግፍ ለመበቀል የሚፈጽሙት ተግባር ሆኖ እናገኘዋለን። በየትኛውም መንገድ ቢሆን አእምሮው እጅግ የተቃወሰበት፣ የሚፈልገውን የማያውቅ፣ ካልሆነ በስተቀር አጋች ዓላማ አለው፤ በተለይ ደግሞ የፖለቲካ አጋቾች በምክንያት ነው የሚያግቱት፤ ይህንንም ዓለም እንዲሰማቸው የሚችሉትን ያህል “ይጮኻሉ”።

በዓለማችን በየቀኑ ከሁለት ሺህ በላይ ህጻናት የደረሱበት እንደማይታወቅ ይህም ከማገት ጀምሮ እስከ ሕገወጥ የሰው ዝውውር እስከ ግድያ እንደሚደርስ ዘገባዎች ያስረዳሉ። በሌላው በኩል ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ዕገታዎች ለዘመናት ሲፈጸሙ የኖሩ ሲሆን አንዳንዶቹ ከጥቂት ሰዓታት በላይ ያልወሰዱ ቢሆንም ሌሎች ብዙዎች ግን በርካታ ዓመታትን ያስቆጠሩ ሆነዋል።

ቴሪ ዌይት የተባለ የእንግሊዝ ቤ/ክ ተደራዳሪ በሊባኖስ የታገቱ አራት ሰዎችን በሽምግልና ለማስለቀቅ ወደ ሊባኖስ ካመራ በኋላ ሒዝቦላ ሰላይ ነው ብሎ በመጠርጠር አገተው። በመጨረሻም ለ1,763 (ከአራት ½ ዓመት) በኋላ ከታገቱት ጋር ተለቅቋል። “የኢራን የዕገታ ቀውስ” ተብሎ በሚጠራው ኢራን ያገተቻቸውን አሜሪካውያን ከ444 ቀናት በኋላ ለቅቃለች። ቼቺኒያ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ በነበረችበት ጊዜ በርካታ ሰዎች (ህጻናትም ጭምር) የሞቱበት የተለያዩ ዕገታዎች ተካሂደዋል፤ 800 ሰዎች የታገቱበትና ከመቶ በላይ ሞተው የተጠናቀቀው የሞስኮ ቴአትር ዕገታ እንዲሁም ከ350 በላይ ህጻናትን ህይወት የቀጠፈው የቤስላን ት/ቤት ዕገታ ጥቂቶቹ ተጠቃሾች ናቸው። በእነዚህና ሌሎች ዕገታና አፈናዎች ሁሉ አፋኞቹ ወይም አጋቾቹ ፍላጎታቸው ምን እንደሆነ በግልጽ ይናገራሉ፤ ዓለም እንዲሰማላቸውም ያደርጋሉ። 

ለበርካታ ቀናት ባልታወቁ “ሽፍቶች” የታገቱት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከታገቱ በርካታ ሳምንታት በኋላ ሚዲያውን አጨናነቀ። ባልታሰበ ፍጥነት እያደገም መጥቶ በአገርና ዓለም አቀፍ ደረጃ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አስደረገ። እጅግ በርካታ ሕዝብ በተለይ በአማራ ከተሞች ወጣ፤ አክቲቪስቶች የሚባሉቱም በሽሙጥ በለውጡ ኃይል በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትሩ አሸሞሩ፤ እርስዎን የሚጠብቀው ሪፓብሊካን ዘብ ታጋቾችን ማስፈታት እንዴት አቃተው በማለት ዕውቀትን የጾመ ልመና አቀረቡ፤ እናቶች ይጸልዩልኛል እያሉ እንዴት ሴቶች ልጆች ሲታገቱ ዝም ማለት አስቻለዎት በማለት ጠቅላዩን “ትህትና” በተላበሰ ሽሙጥ ወረፉ፤ ንጉሡ ጥላሁንም አልቀረላቸውም፤ ጸረ አማራ ተባሉ። በየማኅበራዊ ሚዲያውም ዘመቻው ቀጠለ።

ዓይን አፍጥጦ ወጥቶ የነበረ ነገርግን ሆን ተብሎ ትኩረት እንዳይሰጥበት የተደረገው ነገር ቢቢሲ አስቀድሞ ያወጣውና ከታጋች ወላጆች መካከል አንድኛው አባት የተናገሩት ነበር፤ “… ከእንግዲህ ከሷ ጋር መገናኘት እንደማልችል ነገረችኝ” ካሉ በኋላ “እና ታዲያ ምን አሏችሁ? ብዬ ስላት “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን”” አለችኝ ብለው ነበር ምስክርነታቸውን የሰጡት። ይህ ፍንትው ያለ እውነታ ለምን ትኩረት አልባ ሆነ?    

እንደሚታወቀው አጋች ዓላማ ስላለው ያገተበትን ዓላማ በመግለጽ የሚቀድመው አይኖርም። በዘመናችን እንዲያውም ያለውን ሚዲያ በመጠቀም አጋች ፍላጎቱን ዓለም እንዲሰማው ያደርጋል። በየጊዜውም ያገተውን እያስፈራራ የቪዲዮና የፎቶ መረጃ ይለቃል፤ ይህንን ካላደረጋችሁልኝ ይህንን አደርጋለሁ እያለ ይፎክራል። በደምቢዶሎው ግን ይህንን መሰሉ ድርጊት ሲፈጸም አልታየም። እንዲያውም ባልተለመደ ሁኔታ አጋቹ ዓይናፋር ይመስል መሰወርና አለመታወቅን ነው የመረጠው።

የሚፈልጉትን ባለማግኘታቸው አገራችንን ለማፍረስ እየጣሩ ያሉና ዓላማቸውንም ለማሳካት በትጋት የሚሠሩት ሩቅ ሳይሆን እዚሁ ቅርብ ያሉ ናቸው። ጽንፈኛ ብሔረተኞችና በይፋ የሚታወቁ ድርጅቶች በተለይ በአማራና በኦሮሞ ክልል የሚገኙ ከህወሓት ጋር የሚለያቸው እታገልለታለሁ የሚሉት ብሔር ስም መለየት ብቻ ስለሆነ ከህወሓት ጋር አይወግኑም፤ በአጀንዳ አይስማሙም ብሎ ማሰብ የፖለቲካ ጨቅላነት ነው።   

የታጋች አባት ያሉትን በድጋሚ እናጢን፤ “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን”!!

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ™” አቋም ነው።

Filed Under: Editorial, Right Column Tagged With: jawar massacre, Right Column - Primary Sidebar, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule