• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

Tank Man 1989

June 5, 2018 08:00 pm by Editor 7 Comments

የዛሬ 29 ዓመት በቻይና የታይናንመን አደባባይ የሆነውን ታሪክ ስናስብ “ታንክ ማን” ወይም በግልቡ የአማርኛ ትርጉም “ታንክ ሰው”ን እናስባለን። እናያለን። የወቅቱን ገድሉን እናስባለን። ወደ አገራችን ስንመለስ ምንም እንኳን ምንም ያልተባለላቸው ጀግኖች ያለመታወሳቸው ሊያሳዝነን ሲገባ፣ አሉ የሚባሉት ላይ መማማል መመረጡ በቃላት ሊገለጽ የማይችል የሃዘን አዙሪት ውስጥ ይከተናል።

ከሁሉም በላይ ደም ሰፍረን ትርፍ እንሻለን። ለአገር ክብርና ልዕልና ያለፉትን የማይተኩ ዜጎች የግብር ማወራረጃ ለማድረግ ይዳዳናል። ህወሓት “በሞተብኝ መጠን ልዝረፍ” በሚል ቀረርቶ ል27 ዓመታት ያደነቆረንና ለዚሁ ግልብ ዓላማው የጨፈጨፈን፣ የደገንብን ታንክና አፈሙዝ፣ ያሰረን፣ ያቆሰለን፣ የገረፈን ሳያንስ ዛሬም በተመሳሳይ “የእኛ ደም” በሚል ክፍያ ሲጠየቅ ሰምተናል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ አሳዛኙና አስገራሚው ስህተትን ከመቀበልና ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ማስተባበያ በመስጠት በአንድ ጀንበር ስህተት በስህተት ሲሞሸር ማየት ነው። በርካቶች ተመሳሳይ ስህተት ቢሰሩም የሰሞኑ የአቶ በቀለ ገርባ አካሄድ ጎልቶ የሚወጣ ነው።

አቶ በቀለ በበርካቶች የሚመሰገኑ፣ የሚወደዱ ናቸው። ትንሽ ትልቅ ሳይባል፣ ክልልና አድራሻ ሳይለይ ሁሉም አልቅሶላቸዋል። ዘምሮላቸዋል። ጮሆላቸዋል። እሳቸውም ከእስር ሲወጡ ይህንኑ የሕዝብ እሪታና መስዋዕትነት በወጉ አክብረው ምስጋና አቅርበዋል።

ዋሽንግቶን ዲሲ ስለኢትዮጵያ ለአሜሪካኖቹ ሲናገሩ ከቆዩ በኋላ ሚኖሶታን ሲረግጡ ቋንቋቸው ተቀየረ። ቀጥሎም አንዱን ከሌላው ስለማወዳደር እንዴት ሊያስቡና እንዴት እዚያ ጉሮኖ ውስጥ ሊገቡ እንደቻሉ ግራ በሚያጋባ ደረጃ “ተጠቃሚነትን” በኦሮሞ ልጆች ደም ሰፍረው መናገራቸው፤ “ፍቱኝ ብዬ አልጠይቃችሁም አብሬያችሁ የሠራሁበትን ጊዜ እንደውለታ ቆጥራችሁ የሞት ፍርዱን ተግባራዊ አድርጉ፤ “ሰው እየሳቀ መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ” ብሎ የተናገረን ታጋይ ለንፅፅር ማቅረብን ምን አመጣው? እንዴትስ ታሰበ? አሳዛኝ፣ አስደንጋጭ፣ ለማመን የሚያስቸግር! “እነሱ”ና “እኛ” ብሎ ማስላት!! ሰው “ውለታ ቆጥራችሁ ግደሉኝ” ሲል ደም በመስፈር ውለታን መናፈቅ!!

የትርጉም ስህተት እንደተሠራና እንዲስተባበል ቢሞከርም፣ የተባለው የትርጉም ስህተት ተፈጽሞ ቢሆንም፣ የተኬደበት የንፅፅር መንገድ አቶ በቀለን ከተቀመጡበት የክብር ማማ እንዳወረዳቸው አያጠራጥርም። ከምንም በላይ ሊገሩ የሚገባቸውን ከመግራት ይልቅ እሳቸው “የሚገሩ” ሆነው መገኘታቸው አስደምሞናል። ከአንድ የፊደል አባት፣ ከአንድ ፈጣሪውን እንደሚያምን ከሚናገር ሰው፣ ከአንድ ብሩክ ቤተስብ መውጣቱን ከሚናገር ሰው፣ አንድ አገሪቱን አሁን ከገባችበት ቀውስ አሻግራለሁ ከሚል የተፈተነ ታጋይና አታጋይ … የማይጠበቅ ተግባር በመስማታችን ማዘናችንን አጠንክረን ስንገልጽ በቂ ምክንያት አለን።

በርካታ ፖለቲከኛና አክትቪስት ነን የሚሉ ስህተት ውስጥ ገብተው ሲንቦጫረቁ ለይተን አልተናገርንም። በኦሮሚያ የተከፈለውን ዋጋ ብናውቅም በጋምቤላ፣ በአማራ፣ በኦጋዴን፣ በደቡብ፣ በሁሉም አቅጣጫ ደም መፈሰሱን፣ ግፍ መፈጸሙን፣ አሁንም ድረስ እየተፈጸመ መሆኑንን የሚከራከር ባይኖርም ደምን ለክቶና ሰፍሮ በደም የነገደ የምናውቀው ወያኔን ብቻ በመሆኑ አቶ በቀለን በግልጽ ይቅርታ እንዲጠይቁ ማበረታታት ግድ ሆኖብናል፤ “ትሳስቻለሁ” ብሎ ይቅርታ መጠየቅ ቀላልና የሰላማዊ ታጋይ መለያው ነው። ምክንያቱም ለአገራችን የሚያስፈልጉ ሰው ናቸውና! ከፈለጉ! እስኪ ወደ “ታንክ ሰው” ታሪክ እንመለስ!

በተለያዩ ስሞች ይጠራል፤ ታንክ ሰው፣ ያልታወቀው ተቃዋሚ፣ ያልታወቀው ዓማጺ፣ ወዘተ። ስሙን ያገኘው የዛሬ 29 ዓመት ነበር።

በወቅቱ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ቻይናን እየናጣት ነበር። ተማሪዎቹ ያነሷቸው ጥያቄዎች ዘርፈ ብዙ ቢሆኑም ዋንኛዎቹ ግን ከውሱን የፖለቲካ ተሳትፎ፣ ከዋጋ ንረት፣ ከኢኮኖሚ ተሃድሶ፣ ከፖለቲካ ሙስና፣ ከወገንተኝነት፣ ወዘተ ጋር የተጣመረ ነበር። በመሆኑም ዴሞክራሲ፣ ተጠያቂነት፣ የፕሬስና የመናገር ነጻነት፣ ወዘተ በቻይና እንዲሰፍን በተማሪዎቹ ጥያቄዎች ውስጥ የተካተቱ ነበር።

ለበርካታ ወራት በተቃውሞ ጥያቄያቸውን ሲያሰሙ የነበሩት ተማሪዎች የተሰበሰቡት በቤይጅንግ በሚገኘው የታይናንመን አደባባይ ነበር። አደባባዩ በተቃውሞ ሲናጥ ከከረመ በኋላ የቻይና ኮሙኒስታዊ አገዛዝ 200,000 የጦር ሠራዊቱን ወደ ወደዚያው ላከ። በዚያም በጥይት እሩምታ በርካታዎችን ገደለ፤ አቆሰለ። የሞቱትን ቁጥር እስካሁን ለማወቅ ካለመቻሉ የተነሳ የሚሰጠው ግምትም የዚያኑ ያህል በጣም የሰፋ ነው፤ ከ180 – 10,454!

ይህ እጅግ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከተካሄደ በኋላ በነጋታው ጁን ፭ ቀን ተጨማሪ በርካታ ታንኮች ወደ አደባባዩ ይላካሉ። አንድ ነጭ ሸሚዝ የለበሰና በሁለት እጆቹ ፌስታል ላስቲኮች የያዘ ሰው ቀዳሚው ታንክ ፊት ይቆማል። ከፊት ለፊቱ ሲደርስ ታንኩ ይቆማል። በቪዲዮው ላይ በግልጽ እንደሚታየው ታንኩ ወደ ግራና ቀኝ ብሎ ለማለፍ በሁለቱም አቅጣጫ ሲሞክር ሰውየው ይከላከላል። በእጁም ከዚህ ሂዱ በሚመስል ሁኔታ ተቃውሞ ያሳያል። በመቀጠልም ታንኩ ላይ ይወጣል፤ ውስጥ ካሉት ጋር የሚነጋገር በሚመስል ሁኔታ ትንሽ ከቆየ በኋላ ይወርዳል።

በመቀጠል ፊት መሪው ታንክ ለመሄድ ሲያኮበኩብ ሰውየው አሁንም በፊት ለፊት በመቆም ታንኩን ይጋፈጣል። በመጨረሻ ሁለት ሰዎች እየሮጡ ሄደው ከመንገድ ካወጡት በኋላ ታንኮቹ ጉዟቸውን ቀጠሉ። ከዚያ ወዲህ የዚህ ታንክ ያስደገደገ፤ ለብቻው ብረት ለበስ የተገዳደረ ሰው መጨረሻ አልታወቀም። አንዳንዶች በቻይና አገዛዝ ተገድሏል ይላሉ። ሌሎች ደግሞ አምልጦ ወደ ታይዋን ሄዷል ሲሉ ይህንን የማይቀበሉ ደግሞ እስካሁን የት እንዳለ አለመታወቁ እዚያው ቻይና ውስጥ ድምጹን አጥፍቶ እየኖረ በመሆኑ ነው ይላሉ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን እየታየ ለሚገኘው ለውጥ እጅግ በርካታ ታንክ ያንበረከኩ ወገኖቻችን ተሰውተዋል። ክቡርና መልሶ የማይገኝ ህይወታቸውን ሰውተዋል። ዘር፣ ቋንቋ፣ ቀለም፣ አካባቢ፣ የትውልድ ሐረግ፣ ወዘተ ሳይለይ የህወሓትን አግአዚ ፊትለፊት በመጋፈጥ ደማቸውን አፍስሰዋል፤ አጥንታቸውን ከስክሰዋል።

ሰልፍ የማይወጣላቸውና ያልተወጣላቸው፤ መዝሙር ያልተዘመረላቸውና የማይዘመርላቸው፤ በመስዋዕትነታቸው ምንም ያልተጠቀሙና ወደፊትም የማይጠቀሙ፤ ከነጻነት በስተቀር ለሚያራምዱት የፖለቲካ ርዕዮትም ወይም ወገኔ ለሚሉት ዘር ያልኖሩ፣ ያልሞቱ፤ ለዚህች ታላቅ አገር ግን የማይመለሰውን ህይወታቸውን የገበሩ ብዙ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፤ አሁንም አሉ፤ ወደፊትም ይኖራሉ። ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ ሁልጊዜ መስዋዕትነታቸው ሲታሰብ ይኖራል። እነዚህ የኢትዮጵያ “ታንክ ሰዎች” ናቸው! ከታንክም በላይ!! ደም ሰፍረው ጥቅምን በንፅፅር የማይጠይቁ!!


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ™” አቋም ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Editorial Tagged With: bekele gerba, Full Width Top, Middle Column, tank man

Reader Interactions

Comments

  1. Ezira says

    June 7, 2018 01:07 am at 1:07 am

    ያስለቅሳል !!! የኦቦ በቀለ ነገር። ያችን ሽሙንሙን ወጣት ንግሥት ይረጋንም አሰብኳት። ሽሙንሙኗ ወጣት ዕስር ቤት ወጥታ ቮኦኤ ስለ እስሯ ሁኔታ ሲጠይቃት በእግረ መንገዷ ስለ አቶ በቀለ ገረባ አንስታ ነበር። ስለሳቸውው ስታነሳ እንዲህ ብላ ነበር አቶ በቀለ ገረባን የጠራቻቸው። በተለይ አባታችን አቶ በቀለ ገርባ ብላ የጐንደሯ ልዕልት በሚጣፍጥ ለዛዋ ስትጠራቸው ፣ አንጀት ታላውስ ነበር። ሰሞኑን ግን ከ አቶ በቀለ ገርባ አንደበት የሠማነው ነገር ሆድ ይቆርጣል። ያዉም አብሯቸው በእስር ሲማቅቅ የቆየን ሰው አንስተው (ለምን ተፋታ) እስኪመስለን ድረስ አሳዝኖናል።የሰው ልጅ በሠው ሲጨቅን ከዚህ በላይ ምን ማሳያ አለ?

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    June 7, 2018 07:40 pm at 7:40 pm

    ጎልጉሎች!! ምን ይሁን ነው የምትሉት!?? እናንት ጨበርባሪዎች! ዛሬ መርካቶ፣ ነገ ኣጋሮ፣ ከነገ ወዲያ ሓዋሳ፣ከዚያም ወዲያ ወልቂጤ፣ቀና ኣለፍ ፣ሰንበትበት ስትል፣ ጥቢ ሲሆን በመስቀል ኣሳባችሁ፣ ተመልሳችሁ፣መርኬ ቁጭ ነዋ!!! ኣይደል ጭብርብሮች??

    Reply
  3. Salem says

    June 8, 2018 08:24 pm at 8:24 pm

    Dear Golgul Editors,
    Mulugeta Andargie is a cyber bully; his comments are ethnic slurs and essentially racist. By publishing them your journal is complicit and liable to censure, including loss of the privilege of using your account. I hope you understand and take your responsibility seriously. Thanks.

    Reply
    • Editor says

      June 11, 2018 08:13 am at 8:13 am

      Salem,

      Your comment is noted. We know all about him – we’ve got the needed info.

      If this comes more from our readers we can go as far as banning him from here.

      Thanks

      Editor

      Reply
      • Salem says

        June 12, 2018 07:42 pm at 7:42 pm

        Thank you for your response. I think you need to delete all comments by Mulugeta Andargie that contain ethnic slurs and report him to Google. Thanks again for your good work.

        Reply
        • Editor says

          June 13, 2018 10:19 pm at 10:19 pm

          We always monitor those – be it a comment by him or anyone else. However, if you have seen one, please let’s know.

          Thanks

          Editor

          Reply
  4. Rose says

    June 12, 2018 07:06 pm at 7:06 pm

    ልብ ላለዉ የአቶ በቀለ ገርባ የሰሞኑ ድርጊት ታላቅ ትምህርት ነዉ። ሰዉ ቋሚ አይደለም፣ ሁሌም ይሁዳዎች አሉ። ሰወችን ማጀገን እንጅ ማምለክ ማቆም አለብን። ማንንም ቢሆን።
    ልደቱ በ1995 የቤት ዉስጥ እገታ በተደረገበት ጊዜ ሂደቱ ድራማ መሆኑን ከልደቱና ከበረከት በስተቀር ማን ያዉቅ ነበር? ለዚህ ነበር የኢትዬጵያ ህዝብ ሰማዕት ሆነልኝ ብሎ ያሰበዉን ልደቱ በቁም የተነሳዉን ፎቶ፣ ፎቶ ኮፒ 10ብር (በወቅቱ10ብር ብዙ ነበር) እየገዛ ጾለት ቤቱ የሰቀለዉ። ሰወች ጥቂት መልካም ነገር ሲያረጉ ማዕረጋቸዉን ከቅዱሳን ከፍታ ጋር ማድረስ ቢቀር። ሰዉ ሲሞት ብቻ ነዉ በትክክል ስለማንነቱ መናገር የሚቻለዉ። አመሟቴን አሳምርልኝ የሚለዉ ጾለት ትርጉምም ይኸዉ ነዉ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule