(ርዕሰ አንቀጽ) ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታትና ከዚያም በፊት ስለዕርቅ ያልተናገረ የፖለቲካ ቡድን የለም ለማለት አይቻልም፡፡ ደርግ ስለ ዕርቅ ተጠይቆ አልሰማም አለ፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግም የአገዛዝ መንበሩ ላይ ከመቆናጠጡ ጀምሮ ስለ ዕርቅ ይወራል፡፡ አዳዲስ የሚፈለፈሉ የተቀናቃኝ ድርጅቶች በአገር ውስጥም ይሁን በውጪ ስለ ዕርቅ ያወራሉ፡፡ የገባውም ያልገባውም ስለ ዕርቅ ይናገራል፤ ይሰብካል፤ ያስተምራል፤ … ይህንን ሁሉ አልፎ “እኔም ያገባኛል” በማለት ህወሃትም ስለዕርቅ ያወራል፡፡ ከማውራትም አልፎ ያስተምራል፤ ያሠለጥናል፡፡ ሰላማዊ ጦርነት፤ ጥቁር ብርሃን፤ እንደሌለ ሁሉ ህወሃትና ዕርቅም እንደዚያው ናቸው፡፡ ስለ ድርድርም እንዲሁ ይወራል! አሸማጋይ፤ አደራዳሪ፤ አወያይ በሌለበት እንወያይ ይባላል፡፡ ሁሉንም የተቆጣጠረው ህወሃት የሚደራደሩ ተቃዋሚ ሳይሆኑ “ተጠቃሚ” ፓርቲዎችን … [Read more...] about ዕርቅና ድርድር ቢያይዋቸው፤ ቢያይዋቸው!
Editorials
ርዕሰ አንቀጽ
የአጋንንት ፖለቲካ – ውጣ!!
ልብ ማለት ያቃተን ለምን ይሆን? የማንሰለጥነውስ ለምንድን ነው? በፖለቲካ ትግል ውስጥ ዕድሜ ገፍተን የማንበስለው እስከመቼ ነው? አድሮ ቃሪያ፣ አድሮ ጥሬ ... እንዲሉ በጫጫታ ትውልድን የምናሰቃየው ስለ ምንድን ነው? ብዙ ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል። ይህ በድህነትና በችጋር የሚቃጠለው ህዝብስ ማን ያስብለት? ማን ይድረስለት? በእነማን ብርሃን ይመልከት? ማን ከጨለማ እንዲወጣ ይምራው? ሩብ ምዕተ ዓመት እንደተባላን እንቀጥል? ያሳዝናል? ያስለቅሳል፣ እጅግ ያንገበግባል ... ንስሃ የማያውቅ የአጋንንት ፖለቲካ ይሏል እኛ ነን!! ችግሩ አንድ ወገን ዘንድ ብቻ አይደለም። ችግሩ ሁሉም ዘንድ በውጭም በውስጥም ነው። በውስጥ የተመቸ የመፎካከሪያ ሜዳ የለም። እያደር ይሻላል ሲባል ጭራሹኑ ህወሃት/ኢህአዴግ ሌሎችን “አያገባችሁም” አለና አረፈው። ይህ አልበቃ ብሎ ምክንያት እየተፈለገ ማሳደድና … [Read more...] about የአጋንንት ፖለቲካ – ውጣ!!
“ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም!”
ኢትዮጵያ ድንቅ አገር ናት። ይህ ማስደነቋ ደግሞ ከሕዝቧ መደበላለቅ ጋር ውበቷን እጅግ አጉልቶታል። ከዛሬ 40ዓመት በፊት የተጀመረው ጎሣ፣ ዘር፣ … ላይ ትኩረት ያደረገው ገዳዳ የግራ ፖለቲካ ኢትዮጵያ አላት የተባለውን የፖለቲካ ችግር ሲፈታ ሳይሆን ይበልጡኑ ሲያወሳስበውና ሕዝብን ግራ ሲጋባ እዚህ ደርሰናል። በዚያ ርዕዮት የተጠመቁ ሕዝብን ሲያስፈጁ እንጂ ለሕዝብ ጥቅም ሲያመጡ አልታዩም፤ በዚያ የጎሣ ፖለቲካ ጥርሳቸውን የነቀሉም እስካሁን የማይሠራ ነገር በመሞከር በሽታውን ለአዲሱ ትውልድ እንደ ስጦታ አስረክበውታል። ለነጻነት በሚደረገው ትግል የሁሉም ኢትዮጵያ ወገኖች በአንድነት ብሶታቸው፣ ምሬታቸው፣ … ሊሰማ ይገባል እንጂ በተናጠል “ፍትህ ለኦሮሞ፣ ፍትህ ለአማራ፣ ፍትህ ለኦጋዴን፣ …” የሚለው አካሄድ የትም የሚያደርስ አይመስለንም፡፡ የተጨቆንነው ሁላችንም ነን፤ የትግራይ … [Read more...] about “ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም!”
ለህወሃትና አገልጋዮቹ “አንቱታን” ነፈግን
የኢትዮጵያ ልዩ መጠሪያዎች ከሚባሉት መካከል “ሰው አክባሪነት” አንዱ ነው፡፡ በበርካታው የአገራችን ባህል ሰዎች በዕድሜያቸው የአንቱነትን ማዕረግ ይጎናጸፋሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በሥራቸው፣ በሙያቸው፣ በሕዝብ ዘንድ ባላቸው ከበሬታ ይህ የአንቱነት ማዕረግ ይሰጣቸዋል፡፡ በዕድሜያቸው በጣም ልጆች የሆኑ እንኳን ባላቸው መንፈሣዊ አገልግሎት ወይም ልዕልና በታላላቆቻቸው ሳይቀር አንቱ ይባላሉ፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናትን አንቱ ብሎ መጥራት ለኢትዮጵያዊ የሚነገረው ወይም የሚማረው ግብረገብ አይደለም፡፡ እንደ ህወሃት ዓይነቱን ግን “መንግሥት”፣ “አስተዳደር” ብሎ መጥራት በሕዝብ መቀለድ ነው፡፡ የሕዝብ ይሁንታ የሌለው፤ ሕዝብ አንቅሮ የተፋው፣ በግድ መቶ በመቶ እወደዳለሁ ብሎ ሥልጣን በአፈሙዝ የነጠቀ ወንበዴና የወንበዴዎች ስብስብ “አገዛዝ” መባል ሲበዛበት ነው፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ለሕዝብ … [Read more...] about ለህወሃትና አገልጋዮቹ “አንቱታን” ነፈግን
የጻድቃን “መፍትሔ ሃሳቦች” – ልመና? ጥገና? ወይስ ህወሃት ቁጥር 2?
የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅና አለአግባብ ለመበልጸግ ያሰቡ አውሮጳውያን በአሜሪካ አካባቢ ያሉትን አገሮች በጥጥና በሸንኮራ አገዳ እያለሙ መጠነሰፊ ሃብት ለማጋበስ በሰላም የሚኖሩ አፍሪካውያንን በግፍ እያጋዙ ዓለማችን እስካሁን ዓይታ የማታውቀውን ዓይነት የባርነት ሥርዓት ለበርካታ ዓመታት አካሂደዋል፡፡ ከአፍሪካ ወደ አሜሪካ በግፍ የተጋዙት ወገኖች በመንገዳቸው ያሳለፉት መከራና ከዚያም ለማሽን እንኳን የሚሰጠው ዕረፍትና ጥገና እነርሱ ተነፍገው ለመቶዎች ዓመታት ከምንም ጋር የማይወዳደርና የማይነጻጸር ሰቆቃ አሳልፈዋል፡፡ የዚህ መራራ ግፍ ውጤት አሁንም አብዛኛውን የዓለማችንን ክፍል እየናጠው ነው፡፡ በዚህ አስከፊ ዘመን በባርነት ሥር የሚማቅቁት እንደ ንብረት ይቆጠሩ ስለነበር በምርጫ አይሳተፉም ነበር፡፡ ሆኖም ካላቸው ከፍተኛ የህዝብ ብዛት አኳያ ባሪዎችን አስቆጥረው በርካታ የምክርቤት … [Read more...] about የጻድቃን “መፍትሔ ሃሳቦች” – ልመና? ጥገና? ወይስ ህወሃት ቁጥር 2?
የህወሃት አውሬነት፣ ከውልደት እስከ ህልፈት? ወይስ አገር “እስክትፈርስ”?
* ይብላኝ ለእናንተ ለአውሬው ቀንድና ግምባሮች! ፈቃደኛ ስለመሆኑ ባደባባይ ባልተጠየቀው የትግራይ ህዝብ ስም ራሱን ተገንጣይ ብሎ ሰይሞ አገር የሚገዛው ህወሃት፣ ከቀን ወደ ቀን ግፍ እየመከረ ነው። በአገር ስም እስከ አፍንጫው በታጠቀው ጠመንጃና በዘረፈው ሃብት በመተማመን በያቅጣጫው ንጹሃንን እየጨፈጨፈ ነው። እስር ቤት አጉሮ እያሰቃየ ነው። ያልፈጸመውና የማይፈጽመው ሰቆቃ የለም። ህጻን፣ አዋቂ፣ አዛውንት፣ እናት፣ አባት ሳይመርጥ የጥይት አረሩን እያወረደ በያይነቱ ደም እየተጋተ ነው። ቂም እየከመረ ነው። ከቀን ወደ ቀን ደምና ግፍ የሚበቃው አይመስልም። ወዳጆቹም ሆኑ በስማቸው የሚነገድባቸውም ተው ሲሉት አይሰሙም። ምን ይሁን? ይህ አውሬነት እስከመቼ ይቀጥላል? “በጉልበት ትግሬ ተደረግን እንጂ ፍጥረታችን ትግሬ አይደለም” ያሉ ይገደላሉ፣ ይታፈናሉ፣ ይገረፋሉ፣ እርሻቸው ይነጠቃል፣ … [Read more...] about የህወሃት አውሬነት፣ ከውልደት እስከ ህልፈት? ወይስ አገር “እስክትፈርስ”?
የግጭት ምንቸት ውጣ የእርቅና የሰላም ምንቸት ግባ!!
ከልብ በመነጨ፣ ፍጹም በሆነ የወገን ፍቅር በሶማሊያ በውትድርና ላሉ ወገኖች ፈጣሪ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እንመኛለን። በማያውቁት ጉዳይ የበረሃ ጥሩር ለሚገርፋቸውና የነፍሳቸው ዋጋ በውል ለማይታወቀው ወገኖቻቸን እንኳን አደረሳችሁ ከማለት በላይ ሁሉም ወገኖች ድምጽ እንዲሆኗቸው እንጠይቃለን። በወር 30 ዶላር አበል ህይወታቸው ላለፈና አሁንም እያለፈ ለሚገኙት ሃዘናችን ትልቅ ነው። ትርጉም በሌለው ጦርነትና ለወደፊት ንጹሃን ዋጋ የሚከፈሉበት የፖለቲካዊ ቁማር ስትራቴጂ የደም ግብር ለመክፈል ሰልፍ ለያዛችሁ ፈጣሪ አሁንም ይድረስላችሁ!! ለራባችሁም ለጠገባችሁም፡- እንደ ልማዳችን እንኳን አደረሰን፣ አደረሳችሁ፣ እንቁጣጣሽ!! ስንል ለማለት ብቻ ባንለው ምንኛ ደስ ባለን ነበር። አዲሱን ዓመት ተቀብለን እልፍ ሳንል ባለንበት ቆመን ያረጅብናል። እኛም ያለ አንዳች ለውጥ ጎመን/አረም አሮብን … [Read more...] about የግጭት ምንቸት ውጣ የእርቅና የሰላም ምንቸት ግባ!!
ይህ ረሃብ “ፖለቲካዊ ችጋር” ነው!!
ህወሃት ለአገራችን የቀመመው የበቀልና የተላላኪነት ፖለቲካ ገና ጦሱ አልጀመረም። ግን ሊመጣ ግድ ነው። በንጉሡ ወቅት ተርበናል። በደርግ ጊዜ ተርበናል። ኢህአዴግ ከመጣ ጀምሮ የታዩት ርሃቦች ግን ለየት ያሉ ናቸው። ስለዚህ ርሃቡም ሆነ ችጋሩ ፖለቲካዊ ነው ቢባል ያስማማል። ኢሣ የግጦሽ ሳር ሲያጣ ወደ ጎረቤቶቹ ያመራ ነበር። አፋር ተመሳሳይ ችግር ሲገጥመው ከብቶቹን እየነዳ ችግርን አሳልፎ ይመለስ ነበር። መጠነኛ አለመስማማት /በግጦሽ መሬት/ ከመፈጠሩ ውጪ “እገሌ ነህ” በሚል ጎጥ ለይቶ ሲጋደል አልተሰማም። ዛሬ ህወሃት ሌሎችን እንደራሱ ለማሳነስና ለመበጣጠስ ሲል በዘርና በጎሳ መባላትን በአዋጅ ደንግጎ፣ በህግ አጽድቆ፣ ባገር ሚዲያ ጥላቻን እየሰበከ ተፋቅረው የኖሩትን አባልቷቸዋል። እያባላም ነው። ብዙ ሳይቆይ ራሱንም ጨምሮ የሚበላውን እሳት በየቀኑ እያጋመውም ይገኛል። እናም ሰሞኑን … [Read more...] about ይህ ረሃብ “ፖለቲካዊ ችጋር” ነው!!
“ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንሞክራለን”
እንደ ሚዲያ ወይም እንደ ጋዜጠኛ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊ ፍጡር ይህን እንጽፋለን፡፡ እንደ ክርስቲያን ወይም እንደ ሙስሊም ሳይሆን እንደ አንድ ሰው ይህን እንናገራለን፡፡ ሰብዓዊነት ከሙያ በላይ ነው፡፡ ሰብዓዊነት ከሃይማኖት በላይ ነው፡፡ ሰብዓዊነት ከዘር በላይ ነው፡፡ ሰብዓዊነት ከምን ዓይነት መጠሪያ በላይ ነው፡፡ በሊቢያ የሚገኘው የአይሲስ ተወካይ ቡድን 30 ኢትዮጵያውያንን አረደ፤ በጥይት ረሸነ፡፡ የዓለም ዜና ማሰራጫዎች ዘገባውን አቀረቡ፤ ኢትዮጵያውያን መታረዳቸውን አወጁ፤ ዓለም ቪዲዮውን ተመለከተው፤ ዜናውን አነበበው፡፡ እኛም በሃዘንና በእንባ አንብበነዋል፤ ተመልክተነዋል፤ (ፎቶም ሆነ ቪዲዮውን እዚህ ላይ አንለጥፍም)፡፡ ኋይት ሃውስ እንኳን መግለጫ ሰጠ፤ ድርጊቱን ኮነነ፤ ከሰብዓዊነት በታች፤ ዘግናኝ፣ ፍጹም አረመኔያዊ፣ ጨካኝና ስሜት አልባ በማለት አወገዘው፡፡ ኢትዮጵያውያኑ … [Read more...] about “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንሞክራለን”
ማክሰምና መሰንጠቅ – ባንዳና ባርነት
ህወሃት በዘረፈውና በሚዘርፈው ሃብት ተጠቅሞ ለወዳጆቹ የሚያኮራ፣ ትውልድ ለሚላቸው የሚበጅ ተግባራት እያከናወነ እንደሆነ ይነግረናል፤ ይነግሩናል። ውስን ባለሥልጣናትና አበሮቻችው በሃብት ተመንድገዋል። በንዋይ ሰከረው የሚያደርጉት እስኪጠፋቸው ናጥጠዋል። የት ጋር አንደሚያበቃ ባይታወቅም፣ የተደሰቱ፣ የተከፉ፣ የተናቁ፣ የተሰረቁ፣ የሚሰረቁ፣ እየሰረቁ ያሉ፣ የተትረፈረፈላቸው፣ በስማቸው የሚነገድባቸው፣ ባሪያዎችና ባንዳዎች፣ ቀን የሚጠብቁ፣ ጥርሳቸውን የነከሱ፣ ... ወዘተ “አብረው” አሉ፡፡ ዘመን፣ ወራትና ቀናት ቅዠትን በመሰሉበት ዓለም፣ ቁራሽ ለሚሞላው ከርስ ራሳቸውንና ማንነታቸውን፣ ከዚያም አልፎ የትም የማይደበቁትን ኅሊናቸውን ያቆሸሹ፣ የአገር “እንግዴ ልጆች” ወይም “ውርጃዎች” ለህወሃት የማከሰምና የመግደል ሴራ ተላላኪ ሆነው የህዝብን ክብር ሰልበው ረክሰው ያረከሳሉ። ከዚህም በላይ … [Read more...] about ማክሰምና መሰንጠቅ – ባንዳና ባርነት