• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዕርቅና ድርድር ቢያይዋቸው፤ ቢያይዋቸው!

January 21, 2017 05:20 am by Editor 3 Comments

(ርዕሰ አንቀጽ)

ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታትና ከዚያም በፊት ስለዕርቅ ያልተናገረ የፖለቲካ ቡድን የለም ለማለት አይቻልም፡፡ ደርግ ስለ ዕርቅ ተጠይቆ አልሰማም አለ፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግም የአገዛዝ መንበሩ ላይ ከመቆናጠጡ ጀምሮ ስለ ዕርቅ ይወራል፡፡ አዳዲስ የሚፈለፈሉ የተቀናቃኝ ድርጅቶች በአገር ውስጥም ይሁን በውጪ ስለ ዕርቅ ያወራሉ፡፡ የገባውም ያልገባውም ስለ ዕርቅ ይናገራል፤ ይሰብካል፤ ያስተምራል፤ … ይህንን ሁሉ አልፎ “እኔም ያገባኛል” በማለት ህወሃትም ስለዕርቅ ያወራል፡፡ ከማውራትም አልፎ ያስተምራል፤ ያሠለጥናል፡፡ ሰላማዊ ጦርነት፤ ጥቁር ብርሃን፤ እንደሌለ ሁሉ ህወሃትና ዕርቅም እንደዚያው ናቸው፡፡

ስለ ድርድርም እንዲሁ ይወራል! አሸማጋይ፤ አደራዳሪ፤ አወያይ በሌለበት እንወያይ ይባላል፡፡ ሁሉንም የተቆጣጠረው ህወሃት የሚደራደሩ ተቃዋሚ ሳይሆኑ “ተጠቃሚ” ፓርቲዎችን ከመፍጠር ጀምሮ፤ አደራዳሪ፤ ተደራዳሪና ሸምጋይ ሆኖ ይቀርባል፡፡ ሥርዓት ያወጣል፤ በዚህ ተመሩ ይላል፤ አልመራም ያለውን ወደ እስር ቤት ይመራል፤ ድርድሩ አሁንም በህወሃት የበላይነት ያበቃል፡፡

የተቀናቃኝ ፖለቲካ አመራሮችን በየእስር ቤቱ እያሰቃዩ ድርጅቶችን ለድርድር መጥራት ምን ማለት ይሆን? መቼም ህወሃት/ኢህአዴግ እስር ቤት እየሄደ ሊደራደር እንዳላሰበ ግልጽ ነው፡፡ የፓርቲዎቹስ አመራሮች ይህችን ያህል ቀዳዳ ስላገኙ መስክ እንደተለቀቀ ጥጃ የሚያስቦርቃቸው ምንድነው? የህወሃት/ኢህአዴግ ቅድመ ሁኔታ ማንሳት? ሲጀመር ለምን ቅድመ ሁኔታ ተቀመጠ? ሲቀጥል መቼ ተነሳ? እውነት ይነገር ከተባለ ማነው ቅድመ ሁኔታ ማስቀመት ያለበት? ህወሃት/ኢህአዴግ ወይስ ተቃዋሚዎች? አመራሮቻቸው እና አባሎቻቸው በየእስርቤቱ እየተሰቃዩ፤ ጽ/ቤታቸው እየተዘጋና እየተዘረፈ፤ የመናገር፣ ሃሳብን የመግለጽ፣ የመጻፍና የማሰብ ድረስ መብታቸው በግልጽ እየተነፈገ ማነው ቅድመ ሁኔታ ማስቀመት የነበረበት?

ድርድርና ዕርቅ የህወሃት/ኢህአዴግ የሰሞኑ ዜማዎች የሆኑት ለምንድነው? ለኢትዮጵያ ሕዝብ ስለታሰበለት ነው? ህወሃት/ኢህአዴግ ለመሻሻል ስለፈለገ ነው? ይህ ከሆነ ሃሳቡ ሁሉን ነገር ትቶ ሚዲያውንና ምርጫ ቦርድን ብቻ ነጻ ያድርግ! ይልቅ ጉዳዩ ያለው ሌላ ቦታ ነው – ህወሃት በአንጋሽ ጌቶቹ ግልምጫ ስለደረሰበት ነው፡፡ እነርሱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ አስበው ባይሆንም ህወሃትን ግን ክፉኛ ስላስደነገጠውና የወደፊቱ አልጨበጥ ስላለው “ዕርቅ፣ ዕርቅ፤ ድርድር፤ ድርድር” እንዲል አስገድዶታል፡፡

ለመሆኑ ዕርቅን እንዴት እንገልጸዋለን? የቀድሞዋ የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ኮራዞን አኩዊኖ በጥሩ መልኩ ስለገለጹት የእርሳቸውን እንዋስ፤ እንዲህ ነበር ያሉት፤ “ዕርቅ ከፍትሕ ጋር መታጀብ አለበት አለበለዚያ ዘላቂ አይሆንም፡፡ ሁላችንም ስለ ሰላም ተስፋ ስናደርግ ሰላም በምንም መልኩ ይምጣ ማለት የለብንም፤ ነገር ግን በመርህና በፍትሕ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡” የህወሃት/ኢህአዴግ የዕርቅ ሃሳብ ከዚህ እውነታ ፍጹም የራቀ ነው፤ ፍትሕ አልባ፤ እውነት አልባ፤ ግልጽነት አልባ – የግፍ ዕርቅ ነው! ይህ ደግሞ ዕርቅ ሊባል ፈጽሞ አይችልም፡፡

ዜጎችን ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ከመግደል እስከ ማሰቃየት ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍ እንደፈለገ የፈጸመ፤ የልጇ አስከሬን ላይ ተቀመጪ ብሎ እናትን ያሰቃየ የወንበዴዎች ቡድን እንዴት ነው ራሱ የዕርቅ ሐዋሪያ ሆኖ፤ ራሱ የሚያዛቸውን ፓርቲዎች ለድርድር፤ ራሱ የሾማቸውን የሃይማኖት መሪዎች ለዕርቅ የሚጠራው? የሃይማኖት መሪዎችስ በየትኛው ቅዱስ መጽሐፍ የተጻፈ ዕርቅ ሊሰብኩ ነው ግፈኛ በጠራው ጉባዔ ላይ የህወሃት ሹም በከፈተውና በዘጋው ስብሰባ ስለ ዕርቅ የሚናገሩት? የተጻፈላቸውን ካላነበቡ በስተቀር በሚያስተምሩት መጽሐፍት ላይ የሚናገረው፤ ግፍ የተሰራበት ፈጣሪ አምላክ ራሱን ዝቅ አድርጎ በደል ከፈጸሙበት ጋር ሲታረቅ ነው የሚነበበው እንጂ እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ የፈለገውን ግፍ ፈጽሞ ሲያበቃ ኑ ታረቁ እያለ ሲያስገድድ አይደለም፡፡

ዴዝሞንድ ቱቱ ይህንን ብለዋል፤ “እውነተኛ ዕርቅ ርካሽ አይደለም፤ ምክንቱም በይቅርታ ላይ የተመሠረተ ስለሆነ በጣም ውድ ነው፤ ይቅርታ በተራው ደግሞ በንሰሐ ላይ የተመሠረተ ነው፤ ይህ ደግሞ ለተሰራ ስህተት ዕውቅና በመስጠትና እውነትን ግልጽ በማድረግ ተግባር ላይ የተመሠረተ ነው፡፡”

እውነት ፍርጥርጥ ብሎ ሳይነገር ዕርቅ የለም! በእውነት አጋቢነት ፍትህና ዕርቅ በአደባባይ ጋብቻ ሲፈጽሙ ካልታየ በስተቀር ግፈኛውም ግፉን ይቀጥላል፤ ዕርቅም የግፈኛው ትርከት ሆኖ ይቀጥላል፡፡


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ®” አቋም ነው፡፡

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Lusif says

    January 21, 2017 10:39 pm at 10:39 pm

    I do not care who or what that entity is, I always admire, that is consistent and loyal to its words and objectives. The ruling party has never asked for reconciliation or peace. It believes in its strength and peace can only be maintained through the barrel of the gun. Whenever the ruling party is faced with strong demands or some kind problems, it send out let us discuss invitation letters to opposition groups. The moment the opposition receive that letter, the leadership go on setting up an equation, which never get right, but that give time and space for the ruling party to breath freely, comfortably.
    So who is naive, ignorant, shortsighted? The ruling party wants to stay in power. It wants to control the economic resources. That is what it doing whether we like it or not. Look in every aspect. The ruling party is doing what takes. Look the so called opposition, let alone being strong, the opposition is not close to match up. When one compare the ratio, it is 1:70.
    That is what I said the ruling party deserves my administration. Equally and on the other hand, I despise myself and the likes for not standing firm and consistent, as a result losing the struggle.

    Reply
  2. Ezira says

    January 23, 2017 02:20 pm at 2:20 pm

    ትክክል ብላችኋል ጎልጉሎች። እውነትና ነጋት እያደር ይጠራል እንደተባለው ሁሉ ሃቅ ተደብቆ አይኖረም። እዉነቱ ይፍረጥረጥና እርቅ መጀመሪያ ከፈጣሪ ጋር ሲቀጥል ከራስ ጋር በሰተመጨረሻም ከህዝብ ጋር የሚደረግ እርቅ ብቻ ነው ራስን ነጻ የሚያውጣ እንጅ የ COMMAND POST ጋጋታ አይደለም አራት ነጥብ።

    Reply
  3. Ezira says

    January 23, 2017 02:31 pm at 2:31 pm

    ግሩም ርዕሰ አንቀጽ ብራቮ ጎልጉሎች!
    በርቱ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule