ሰሞኑን ኢህአዴግ ጉባኤውን ሲጨርስ “አድርባይነት አሰጋኝ” ብሎናል። አባላቶቼ አድርባይ ሆነዋልና በዚህ ከቀጠልኩ እሰምጣለሁ የሚል ስጋት እንዳለበትም አስታውቆናል። ከፍርሃቻው ብዛት የተነሳ አድርባይነትን ለመዋጋትና “መድረክ ላይ ለመጥለፍ” በቁርጠኛነት እንታገላለን ብለው አቋማቸውን ነግረውናል። የሚገርመው ግን አድርባይነትን የፈጠረና ያነገሰው ራሱ ኢህአዴግ መሆኑን መዘንጋቱ ነው። ኢህአዴግ አድርባይ ሚዲያዎች አሉት። አድርባይ ባለሃብቶች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይ የኔቢጤዎች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይና የማደናገሪያ ፕሮጀክቶች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይ ድርጅቶች እንጂ ነጻ ድርጅቶች የሉትም። ኢህአዴግ አድርባይ ባለስልጣናት እንጂ ነጻ አመራሮች የሉትም። ሁሉም አድርባዮች ተጠሪነታቸው ለህወሃት ስለሆነ ተጠያቂውም ራሱ የኢህአዴግ ሾፌር ህወሃት እንጂ ሌሎች ሊሆኑ አይገባም። “ፈጣሪያቸው” … [Read more...] about ስለ አባይ ግድብ “አድርባይ” እንሁን?
Editorials
ርዕሰ አንቀጽ
የትግራይ ህዝብ ስማ!!
ሰሞኑን በውዴታም ይሁን በግዴታ በመቀሌ እጅግ ከፍተኛ የሚባል ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ሲጨፍሩ፣ ሲዘሉ፣ ከበሮ እየመቱ የባህላቸውን ዘፈንና ውዝዋዜ ሲያወርዱ አይተናል። ምክንያቱ በግልጽ ባይነገርም ሲደበቅ የነበረው የህወሃት ሃብትና ንብረት ውጤት የሆኑ፣ በልዩ የመንግስት ድጋፍ የተከናወኑ ግዙፍ ተቋሞች በጎዳና ለህዝብ ሲቀርቡም ተስተውሏል። ልማቱ መልካም ነው። ደስ ይለናል። ምንም ተቃውሞ የለንም። ግን መልዕክት አለን። ለማን? ምሬትን፣ ጭቆናና መንገፍገፍ ሲበዛ በፍቃደኛነት በቦንብ ላይ እንደሚያስሮጥ ለሚያውቀው የትግራይ ህዝብ!! የትግራይ ህዝብ ስማ!! ሰሞኑን ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ሪፖርት የትግራይ ክልል በትምህርት፣ በኤሌክትሪክ፣ በመንገድ፣ በእርሻ፣ በደን፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ ወዘተ ከሌሎች ክልሎች ሁሉ ርቃ መሄዷን ይፋ አድርጓል። … [Read more...] about የትግራይ ህዝብ ስማ!!
ቤት መኖሩን እንመን፤ ከዚያ እንግባ!
በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ1960ዎቹ በአሜሪካ የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጠንካራ ፉክክር የተደረገበት ነበር፡፡ ጆን ኤፍ ኬኔዲና ሪቻርድ ኒክሰን እጅግ ከፍተኛ ውድድር ካደረጉ በኋላ ኬኔዲ አሸነፉና ሥልጣኑን ተቆናጠጡ፤ ኒክሰን የሽንፈትን ጽዋ ጠጡ፡፡ ከኒክሰን ደጋፊዎች መካከል ቀዳሚ የነበረው የፊልም ተዋናይ ጆን ዌይን ነበር፡፡ የካው ቦይ ጫማውን አጥልቆ፤ ፈረሱ እየጋለበ፤ ሽጉጡ እያሽከረከረ፤ ጠላቶቹ በፊልም ይረፈርፍ የነበረው ጆን ዌይን ከሚከተለው የጸና የፖለቲካ አመለካከት አኳያ ሪቻርድ ኒክሰንን በመደገፍ ለማሸነፍ እንዲችሉ የተቻለውን እገዛ ያደረገ ነበር፡፡ ሆኖም ያሰበው አልተሳካም፤ የተመኘው መሪ ነጩ ቤተመንግሥት አልገባም፤ በሕገመንግሥቱ መሠረትም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አልሆነም፡፡ ጆን ዌይን ኬኔዲ ማሸነፋቸውን በተረዳ ጊዜ ግን አገር ወዳድነቱንና አርበኝነቱን … [Read more...] about ቤት መኖሩን እንመን፤ ከዚያ እንግባ!
ኢህአዴግ ሌላ፤ ኢትዮጵያችን ሌላ!!
ሚዲያ ከስሜታዊነት፣ ከስጋና ደም ድምር፣ ከችኩል ውሳኔና ግብታዊነት ነጻ ለመሆን ሌት ተቀን መስራት እንዳለበት ባለሙያዎች አበክረው የሚናገሩት ዓቢይ ጉዳይ ነው። ሚዲያ ስንል ደግሞ ሁሉንም ነው - የኅትመት፣ የምስል፣ የድምጽ፣ የድረገጽ፣ የዲጂታል፣ የማኅበራዊ ድረገጽ፣ … ። ሁሉም ሚዲያዎች አሻግሮ በማየት ህዝብንና አገርን የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው። ጋዜጠኞች ወይም እንደ ጋዜጠኛ የሚሠሩ ሁሉ ከየትኛውም ሙያተኛ በላይ ሃላፊነት ሊሰማቸውም ግድ ነው። ለዚህም ነው በጋዜጠኝነት ሙያ "አመጣጥን፣ አሁንም አመጣጥን፣ አሁንም አመጣጥን … “ባላንስ” አድርግ" የሚባለው!! ከኢህአዴግ ዓይነ ያወጣ ውሸትና ዝግነት የተነሳ ሁሉንም መረጃዎች የማመጣጠኑ ሙያዊ ሃላፊነት ለመወጣት ፈተና ቢያጋጥምም በከፍተኛ ደረጃ ጥንቃቄ ልንወስድባቸው የሚገባን ጉዳዮች አሉ። ከነዚህ ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋናው … [Read more...] about ኢህአዴግ ሌላ፤ ኢትዮጵያችን ሌላ!!
ያብለጨለጨ ሁሉ ወርቅ አይደለም!!
የሁሉም አለቃና የበላይ የሆነውን ሕዝብ ማስደሰት ያኮራል። የሚመሩትን ሕዝብና አገር ከልብ አክብሮ መገኘት ደግሞ ከኩራትም በላይ ነው። ይህንን በኳስ ያበደ ህዝብ፣ አገሩን ከምንም በላይ የሚያፈቀር ህዝብ መወከል ደግሞ ከበጎ ታሪክነቱ በላይ ከሽልማትና ከውዳሴ በላይ ነውና የኢትዮጵያ ልጆች ኩራታችሁ ታላቅ ይሁን። መልካም ዕድል ለአምባሳደሮቻችን!! ኢትዮጵያዊነት እንዲህ የሚጣፍጥ፣ ማንም ሊወስደውና ሊበርዘው የማይችል ሃያል በረከት መሆኑን ምክንያት ሆነው ላሳዩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ክብር ይሁን ለማለት እንወዳለን። መልካም እድል ለአምባሳደሮቻችን ስንል በቂ ምክንያት ስላለን በፍጹም ኩራት ነው። በእግር ኳስ ፍቅር ለሚቃጠለው የኢትዮጵያ ህዝብ የደስታ ቀን ላመጣችሁ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች የምንመኘው መልካም ምኞት ካለፉት የሰላሳ አንድ ዓመታት ውድቀት ጋር የተቀበረውን የድል … [Read more...] about ያብለጨለጨ ሁሉ ወርቅ አይደለም!!
ወሬ ይገድላል
በጎርጎሪያኑ የቀን መቁጠሪያ ለምትገለገሉ ሁሉ መልካም አዲስ ዓመት!! በአዲሱ ዓመት ከራስ ጋር በመታረቅ፣ ከህሊናና ከእዕምሮ ባርነት በመላቀቅ፣ ከይሉንታ ጥብቆ ውስጥ በመውጣት፣አካሄድን ለማሳመር ይቻል ዘንድ የተጠቀለለውን አሮጌ ዓመት ትምህርት ማድረግ ታላቅ ጉዳይ ነው። አዲሱ ዓመት ከባከኑት ዓመታቶች ጋር ተዳምሮ እንዳያጎብጠን፣ ተስፋችንን እንዳይበላውና ወደ ከፋ የፖለቲካ መሰላቸት ውስጥ እንዳይከተን መጠንቀቅ ደግሞ ከሁሉም በላይ ወሳኝ ይመስለናልና ከከንቱና የማያንጽ ወሬው ቆጠብ፣ ከተግባሩ ጨመር እናድርግ!! ወሬ ይገድላል እንዲሉ!! ይሉኝታን እንቅበር ባለፉት ዓመታት የይሉኝታ ፖለቲካ ጉዳት አድርሷል። በይሉኝታ በመነዳት የማይረሳ ኪሳራ ተመዝግቧል። በይሉኝታ ብቻ የደረሰብን የፖለቲካ ጠባሳ ሰምበሩ በያንዳንዳችን ሰውነት ላይ ይታያል። በተፎካካሪ ፓርቲዎችና ለለውጥ በተነሱ ፓርቲዎች … [Read more...] about ወሬ ይገድላል
ስለ “አንቀጽ 39” ማንን እናመስግን?
በዋዜማ ዝግጅቶች ሲታጀብ ከርሞ፣ ቅዳሜ የተከበረውን “የብሄር ብሄረሰቦች” ቀንን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎችን በማሳተፍ “አንቀጽ 39 ለዘላለም ይኑር” ብሎናል። እኛም ለዚህ ውለታ ማንን ማመስገን እንዳለብን ለመጠየቅ ተገደድን። ለመልካሙና “የህዝቦች አብሮ የመኖር አለኝታ” ስለሚባለው አንቀጽ 39! የሶማሌ ብሄር አባል ናቸው። አቶ አብዱላሂ አብዱራሂም ይባላሉ። ዘጠነኛውን “የብሄር ብሄረሰቦች” ቀን አስመልክቶ አስተያየት እንዲሰጡ ተጋብዘው በቴሌቪዥን ብቅ አሉ “… አቅማችሁ ካደገ በኋላ፣ ልጆቻችሁን አስተምራችሁ አቅም ስታዳብሩ ለአንቀጽ 39 ትደርሱበታላችሁ…” እንዳሉዋቸው አቶ መለስን ጠቅሰው ተናገሩ። ትዝታቸው መሆኑ ነው። ወዲያው አቶ መለስ በወቅቱ እንገነጠላለን ያሉትን የሶማሌ ህዝቦች ሰብስበው ሲናገሩ ታዩ።እንዲህ አሉ “አስራ ዘጠኝ ዓመት … [Read more...] about ስለ “አንቀጽ 39” ማንን እናመስግን?
አሁንም የተሃድሶ ያለህ!!!
“አንድነትን ስንመሰርት በቅንጅት ወቅት ስለሰራነው ጥፋትና የፖለቲካ ስህተት የገመገምነው ነገር የለም” ዶ/ር ያዕቆብ ሃ/ማርያም አንድነት ፓርቲን ከቅንጅት ጋር በማነጻጸር ከተናገሩት፡፡ በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲና ድርጅቶች መዋቅራዊ ጥንካሬና ደጋፊዎቻቸውን አስተባብረው ውጤት ማስመዝገብ ያለመቻላቸው ጉዳይ አነጋጋሪ ነው። ተቃውሞ በኢትዮጵያ በፓርቲ መሪዎችና በገዢው ኢህአዴግ መካከል የሚደረግ እሰጥ አገባ ካልሆነ በስተቀር በደጋፊዎች ተሳትፎ ገዢውን ፓርቲ የማስገደድና እጁን የመጠምዘዝ ደረጃ ላይ ደርሶ ሊታይ አልቻለም። ከቅንጅት መፈራረስና ልዕልናው መክሰም ጋር የህዝብ ስሜትም አብሮ ተዳፍኗል የሚለው አስተያየት ሚዛን የደፋ የሚሆንባቸው የበዙት ለዚሁ ነው። በድርጅት ደረጃ ችግሩን ተመልክተው ስለመታደስ የሚያስቡ ስለመኖራቸው ግን ለረዥም ጊዜ አልሰማንም። በኢትዮጵያ ህዝብን ለትግልና … [Read more...] about አሁንም የተሃድሶ ያለህ!!!
ከፖለቲካ ተሃድሶ በፊት [የእውቀት] ተሃድሶ በአስቸኳይ!!
ታዋቂው የጋና ምሁር ጆርጅ አዪቴ በተደጋጋሚ እንደሚሉት ከአምባገነናዊ ስርዓት ወደ ዴሞክራሲ በሚደረገው ሽግግር የትኛውንም ዓይነት ተሃድሶ ከማድረግ በፊት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው የእውቀት ተሃድሶ ነው፡፡ ሕዝብ እንደሚገባው በእውቀት ከነቃ የዴሞክራሲና የመብቱን ጉዳይ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ይህንን ተከትሎ የሚከሰተው የእውቀት ተሃድሶ ወደ ፖለቲካዊ፣ ተቋማዊ፣ ሕገመንግሥታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ … ተሃድሶ ይመራል፡፡ የእውቀት ተሃድሶ ሳይደረግ ከአምባገነናዊ ሥርዓት ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር አንዱን አምባገነን በሌላ የመተካት ሂደት እንጂ ዘላቂ ለውጥ የሚያመጣ አይደለም ይላሉ፡፡ ሕዝብ የእውቀት ተሃድሶ ካካሄደ በሥልጣን ላይ ከተቀመጠው አምባገነን ያልተሻሉትን የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ማንነት ጠንቅቆ ማወቅ ይችላል፡፡ በፖለቲካ ብልጣብልጥነት ሊያካሂዱበት የሚችሉትን አሻጥር አስቀድሞ ያውቃል፤ … [Read more...] about ከፖለቲካ ተሃድሶ በፊት [የእውቀት] ተሃድሶ በአስቸኳይ!!
እባካችሁ ይህንን “ኢትዮጵያዊነት” አክብሩት!!
ኢትዮጵያዊነት ከአጭበርባሪነት፣ ከሸፍጥ፣ ከሴራ፣ ከኩርፊያ፣ ከበቀል፣ ከተንኮል፣ ከደባ፣ ከድብቅ ዓላማ፣ ከአድማ፣ ከባንዳነት፣ ከአቃጣሪነት፣ ከከሃዲነት፣ ከተቀጣሪነት፣ ከማወናበድ፣ በተለይም ከማስመሰለና ከተራ የፖለቲካ ንግድ በላይ መሆኑንና ማንም ሊበርዘው ቢደክምም ሊሸረሽረው የማይችለው የልብ ማህተም መሆኑን ሰሞኑን አየን። ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግርኳስ ቡድን ድል እውን ይሆን ዘንድ ሠንደቅ ዓላማቸውን ለብሰው ሌሊቱን ሙሉ ላገራቸው ያዜሙ፣ በየቤታቸው ሆነው በጸሎት የማለዱ፣ በመላው ዓለም በየድረገጹ የመልካም የደስታ ምኞታቸውን ሲገልጹ የነበሩ፣ በዋናው የትግል ሜዳ የአገራቸውን መለያ ለብሰው ታሪኩን ያከወኑና የትግሉን ስትራቴጂ በመንደፍ ታሪክ የሰሩ ድርና ማግ ሆነው አገራቸውን አብርተዋታል። ብንዘገይም ለመላው የኢትዮጵያ እግርኳስ ቡድን አባላት፣ ለመላው የኢትዮጵያ … [Read more...] about እባካችሁ ይህንን “ኢትዮጵያዊነት” አክብሩት!!