• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የ፩ኛ ዓመት መልዕክት – የሚዲያ ተሃድሶ ግድ ነው!!

September 11, 2013 09:51 am by Editor 1 Comment

ዛሬ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከተቋቋመ አንድ ዓመቱ ነው። ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ የደገፉን፣ ያበረታቱን፣ አስተያየት በመስጠት ያረቁንና በመድረካችን የተሳተፉ ያሉትን ያህል የምንሰራውን ስራ ለመቆጣጠር፣ የተመሰረትንበትን ግልጽ መስመር ለማስቀየር የሞከሩና ጨዋነት በጎደለው መልኩ የተዛለፉም አጋጥመውናል። ለሁላችም እንኳን ለአንደኛው ዓመት አደረሰን!!

“ወፌ ቆመች በሉን” በማለት ከዓመት በፊት የሚዲያውን ሰፈር በአሃዱ ብለን ከተቀላቀልንበት ጊዜ አንስቶ የሰራነውን ስራ በጥሞና ለመመልከት ሞክረናል። ሌሎች ሚዲያዎችንና ብሎጎችንም ዳሰናል። የራሳችን ደካማ ጎን ስንፈትሽ እግረ መንገዳችንን ዙሪያችንን ስንቃኝ የሚዲያ ተሃድሶ (ሪፎርም) አስፈላጊ እንደሆነ ተረድተናል። አምነናል። “መቼ” ለሚለው ጥያቄ ምላሹ ዛሬ፣ አሁን፣ አሁኑኑ የሚል ነው።

ድክመታችን

ስንጀምር በዘረጋናቸው ዓምዶች መሰረት ጊዜ በመጠበቅ መረጃ በወቅቱ አላስተላለፍንም። የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎችና ድንቃ ድንቅ ወሬዎችን የምናቃምስበት የጎልጉል ቅምሻ ዓምድ በጀመርንበት አቅም መቀጠል አልቻልንም። የግጥም ጨዋታን በተከታታይ አላቀረብንም። ጦማሮች ሲላኩ ፈጥነን ያለ መለጠፍ ችግር አለብን። እነዚህ ከድክመቶቻችን መካከል በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው። ምንም እንኳን ስራችንን የምንሰራው በበጎ ፈቃደኞች በትርፍ ጊዜ ቢሆንም በግምገማችን በድክመት አስቀምጠነዋል። አንባቢዎችንንም ይቅርታ እንጠይቃለን።

ያጋጠሙ አንኳር ችግሮች

የተሳሳተ መረጃ በመላክ ታማኝነታችንን ለማሳጣት በተደጋጋሚ ሙከራ ተደርጓል። “እነማን ናቸው፣ ከየት መጡ፣” በሚል አጀንዳ ይዘው የተወያዩ አሉ። ማንነታችንና፣ ምንነታችንን እንድናብራራ በደብዳቤ የተጠየቅንበትም ጊዜ ጥቂት አይደለም። የኤዲቶሪያል ፖሊሲያችን ከሚፈቅደው ውጪ በዘለፋ የተሞሉ ጽሁፎች በመላክ እንዲስተናገድላቸው የወተወቱን በርካታ ናቸው። በቀጥታ በአድራሻችን የማይላክልንን ጽሁፍ ስለማናስተናግድ /ወደፊትም አናስተናግድም/ ወደ አንድ መንገድ ሊያጠጋጉን የሞከሩ አንቱና አንተ የሚባሉ አጋጥመውናል። ከሁሉም በላይ በተደጋጋሚ የጋዜጠኛነት ውንብድና ተፈጽሞብናል። ይህ መረን የወጣ ችግር ማቆሚያ ሊበጅለት እንደሚገባ አጥብቀን እናምናለን። ለሙያውና ለስነምግባሩ የሚገዙ በዚህ ሃሳባችን ድጋፍ እንደሚሰጡን እናምናለን።

የሚዲያዎች ሪፎርም ለምን?

በበርካታ ሚዲያዎች እኛን ጨምሮ ህዝብን የማስተማሩን አብይ ተግባር በሚጠበቅብን መጠን የተወጣነውና እየተወጣን ያለን አይመስለንም። “ነጻና ገለልተኛ ሚዲያ አለ” ለማለት ባያስደፍርም ጭፍን ድጋፍና ውዳሴ ዞሮ አደጋው የከፋ እንደሚሆን ልምዳችን ይነግረናል። ህዝብም ይህንኑ ችግር ጠንቅቆ ያውቃል። ሚዲያዎች ሃሳቦችን በማመንጨት፣ ከህዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን በማንሳት፣ አጀንዳ በመቅረጽ፣ የክርክር መድረክ በመፍጠር ፖለቲከኞችን፣ አደረጃጀታቸውን፣ አመራራቸውን፣ ቃላቸውን፣ ተግባራቸውን፣ ራዕያቸውን፣ ግባቸውን፣ ለዴሞክራሲ ግንባታ ያላቸውን የተስፋ መጠን በመመርመር፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ነጻ የህዝብ አንደበትና መድረክ በመሆን ልናገለግል ይገባል። ከዚህ አንጻር ሲታይ አሁን ያለንበት ደረጃ “ገና ብዙ ብዙ … ” የሚለውን ዜማ ከማዜም የዘለለ አይሆንም።

ሁሉም ወገኖች እንደሚረዱት ድረገጾችና ብሎጎች ሞልተው ፈሰዋል። አባዛኛዎቹ ሙሉ በሙሉ ማለት እስከሚቻል ድረስ ጽሁፍ መዋዋስና መቀራመት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ቢያንስ ቢያንስ ርዕሰ አንቀጽ እንኳን በወጉ በማዘጋጀት አቋማቸውን ለማስቀመጥ ሲቸገሩ ይታያሉ። የራሳቸውን ሃሳብና ጥረት የታከለበት ስራ በመስራት የተመጣጠነ ሪፖርት ማድረግ ተስኗቸዋል። የሪፖርት ስራ ለጋዜጠኝነት የጀርባ አጥንቱ ቢሆንም ጽሁፍ ወደ መዘራረፍና የጋዜጠኛነት ውንብድና ተዛውረናል። በዚሁ የጽሁፍ “ጠለፋ” ሳቢያ የብዕር ባለቤቱና የድርሰቱ ዋና ጌታ ተለይቶ የማይታወቅበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

የብሎግና ድረገጽ ባለቤት በመሆን በጋዜጠኛነት ስም ምንም ልፋት ያላደረጉበትን የሌሎች ጽሁፍ ለመለጠፍ የሚጣደፉ መበራከታቸው ያስደነግጠናል። አዲስ መረጃ ወይም ዜና ሲሰማ ለመቀራመት ያለው ፍጥነት ጽሁፉን በቅጡ አንብበው ስለመቀራመታቸው ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። በሚገርም ሁኔታ ስህተትና የፊደል ግድፈት ሳይቀር እንዳለ የሚገለብጡና በራሳቸው ገጽ ላይ የሚለጥፉ ጥቂት አይደሉም። ከሁሉም በላይ ከሰው ለወሰዱት ጽሁፍና መረጃ በቂ እውቅና ሳይሰጡ የራሳቸውን የግል ፎቶ በመለጠፍ ለራሳቸው የባለቤትነት ማዕረግ የሚሰይሙትን ስንመለከት ድንጋጤያችንን ወደ ፍርሃት ይቀይረዋል። ህዝብ ከሚዲያ ስለመማሩና እንዲማር የማድረጉ ስራ አደጋ ላይ ስለመሆኑ ይሰማናል። ደረጃው ይለያይ እንጂ በዚህ መልኩ የጋዜጠኛነት ወሮበላነት ሁሉም ደጅ አለ። እኛም በተደጋጋሚ ዝርፊያው ተከናውኖብናል፤ አሁንም እየተከናወነብን ይገኛል። ማስተካከያ እንዲደረግ የተላላክናቸው መልዕክቶች በመረጃ ተቀምጠዋል።

ይህንን ስንል ጽሁፍን መዋዋስና በጨዋነት መጋራት የተከለከለ ነው ለማለት አይደለም። በጣም ውሱን ከሆኑት በቀር አድፍጦ መቀራመትና ጽሁፍ መዝረፍ በዛ፣ ልክ አጣ፣ ገደብ ይደረግለት፣ ለመረጃው ባለቤት አስፈላጊው እውቅና ይሰጠው፤ ቢያንስ ምንጩ ይጠቀስ፤ ሥርዓት ይጠበቅ ነው የምንለው። ከመቀራመት በዘለለ ሚዲያዎች የራሳቸውን ወጥ ስራ ለመስራት ይነሳሱ፣ የተለያየ አይነት ያቅም ችግር ቢኖርም ጥረቱ ይጀመር ለማለት ነው። የሚዲያዎች ተሃድሶ ያስፈልጋል የምንለውም ለዚህ ነው። አንባቢም ተቃውሞውን መግለጽ አለበት። አንባቢዎች መረጃ ሲቀበሉ እንዲህ ያሉትን የጨዋነት ጥያቄዎች የማንሳት ግዳጅ ሊኖራቸው ይገባል። ትክክለኛ መረጃ ከሚጠሉትና ከሚጠየፉት ሚዲያም ሊያገኙ ስለሚችሉ ብዙ ጊዜ ከስሜትና ከፍረጃ ራሳቸውን ነጻ ቢያደርረጉ የተሻለ ነው ለማለት እንወዳለን። አንባቢያን ይህንን ቢያደርጉ ሚዲያዎች ራሳቸውን ለተሃድሶ ፈጥነው ያዘጋጃሉና!!

በመጨረሻ

በአንድ ድፍን ዓመት ቆይታችን የተረዳነው ከራሳችን ጀምሮ በርካታ ችግሮች ያሉበትን የመረጃ መቀያየሪያ መድረክ ከችግሩ እንዲድን አስቀድመን ቃል መግባት ያለብን ራሳችን ነን “ጋዜጠኛ” የምንባለው እኛ “ጋዜጠኛ” የሚለውን ስም ከወሰድን በኋላ እየረበሽን፣ እየበጠበጥንና ህዝብን “በኩረጃ” ዘገባና በጋዜጠኛነት ውንብድና ለማንቃት የምንተጋ ከሆን ራሳችን እስከ ማቀብ የሚያደርስ ውሳኔ መወሰን ይጠበቅብናል። “እኔ እየረበሽኩ ነው፤ ከዚህ ቦታ መውጣት ይገባኛል” ማለት በራሱ ታላቅ ክብር የሚያሰጥ ተግባር ነውና ለሪፎርም ራሳችንን እናዘጋጅ። ከሚዲያዎች ብዙ ይጠበቃልና የወደፊቱን አሻግሮ በመመልከት ለመስራት ለሚተጉት ደግሞ አንባቢዎች አስፈላጊውን እውቅናና ክብር በመስጠት ለሪፎርሙ ተግባራዊነት ድምጻችሁን አሰሙ። መልካም አዲስ ዓመት!! አዲስ የሚዲያ ተሃድሶ ዘመን!!


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ®” አቋም ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው! says

    September 12, 2013 06:03 am at 6:03 am

    ***ውድ ‘ጉልጉል’ የድረ ገፅ ጋዜጣ አዘጋጆች ባለቤቶች ውድ የጋዘየታው አንባብያንና ሃሳብ ሰጭዎች ሁሉ የከበረ ሰላምታዬ አድናቆቴ ባላችሁበት ይድረሳችሁ!! የ፳፻፮ የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት የሠላም፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ አብሮ መሥራትና የመለውጥ የዕድገት ዘመን ይሁን!!እንኳንም ለመጀመሪያው አንድ ዓመት የሥራ ጊዜያችሁ በሰላም ደረሳችሁ መጪው ዘመን የተሳለውን አሠራር በተጠናከረ መልኩ ለሕዝብ በጥራት ታቀርቡ ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው። አቅም በፈቀደ ቤቱን ለማድመቅ፣ ሀሳብ ለማፍለቅ፣ ለመሞገት፣ ለተሻለ አሳማኝ የእውነተኛ የሀገር ሰውነትና ቅን አሳቢነት እንዲንሸራሸር እንወዳለን አብረንም
    እንጓዛለን። “የሚዲያ ተሃድሶ!” ታማኝነት ግልፅነት ተጠያቂነትን ያካተተ ማናቸውም መረጃና ሀሳብ ይሆናል። ግለሰቦች በሚያቀርቡት ፅሑፎች ሐሳብ ሲሰጡ የግድ የሌላውን ሃሳብ ጥላሸት በመቀባት (ስድብና ዘለፋ) የአለማወቅ መሸፈኛ ሳይሆን የተሻለውን የእርምት ሃሳብ አቅርቦ ሌላውን ለውይይት በመጋበዝ ሐሳቡን ማዳበር የሀገርም ተሀድሶ እንዲፋጥን ያደርገዋል። “ወቅታዊ እውነተኛ መረጃ የመልካም ጋዜጠኛ ሥነምግባር ነው!”

    ውድ የኢትዮጵያ ልጆች… ጉልጉል አዘጋጆች ይህ ሥራችሁ ያለክፍያ በትርፍ ግዜ በመሆኑ እክግ የሚደነቅ ነው። በአንዳንድ አጋጣሚ የምትሰጡት ፈጣን ምላሽና ማበረታቻ ሁሉ ምን ያህል ጠንካራ ቡድን እንደሆናችሁ መገመት ይቻላል። አሁንም ሥራችሁን ከጥንካሬ እስከ ድክመታችሁና የወደፊት የማሻሻያ ዕቅዳችሁ ጋር በተገቢው መልኩ አስቀምጣችሁታል። ከዚህ ላይ ማረሚአና ሐሳብ መስጠት ጉንጭ ማልፋት ይሆናል። መልካም ሥራችሁን ቀጥሉ በርቱ ሠፊው የኢትዮጵያ ወጣት እያነበበ የሚጽፍበት እየፃፈ የሚከራከርበት ሀሳቡን በነፃነትና በሰላም የሚናገርበት ቀን ዕሩቅ አይሆንም!!በተስፋ መልካም አዲስ ዘመን! በለው ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule