ታዋቂው የጋና ምሁር ጆርጅ አዪቴ በተደጋጋሚ እንደሚሉት ከአምባገነናዊ ስርዓት ወደ ዴሞክራሲ በሚደረገው ሽግግር የትኛውንም ዓይነት ተሃድሶ ከማድረግ በፊት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው የእውቀት ተሃድሶ ነው፡፡ ሕዝብ እንደሚገባው በእውቀት ከነቃ የዴሞክራሲና የመብቱን ጉዳይ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ይህንን ተከትሎ የሚከሰተው የእውቀት ተሃድሶ ወደ ፖለቲካዊ፣ ተቋማዊ፣ ሕገመንግሥታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ … ተሃድሶ ይመራል፡፡ የእውቀት ተሃድሶ ሳይደረግ ከአምባገነናዊ ሥርዓት ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር አንዱን አምባገነን በሌላ የመተካት ሂደት እንጂ ዘላቂ ለውጥ የሚያመጣ አይደለም ይላሉ፡፡ ሕዝብ የእውቀት ተሃድሶ ካካሄደ በሥልጣን ላይ ከተቀመጠው አምባገነን ያልተሻሉትን የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ማንነት ጠንቅቆ ማወቅ ይችላል፡፡ በፖለቲካ ብልጣብልጥነት ሊያካሂዱበት የሚችሉትን አሻጥር አስቀድሞ ያውቃል፤ … [Read more...] about ከፖለቲካ ተሃድሶ በፊት [የእውቀት] ተሃድሶ በአስቸኳይ!!
Editorials
ርዕሰ አንቀጽ
እባካችሁ ይህንን “ኢትዮጵያዊነት” አክብሩት!!
ኢትዮጵያዊነት ከአጭበርባሪነት፣ ከሸፍጥ፣ ከሴራ፣ ከኩርፊያ፣ ከበቀል፣ ከተንኮል፣ ከደባ፣ ከድብቅ ዓላማ፣ ከአድማ፣ ከባንዳነት፣ ከአቃጣሪነት፣ ከከሃዲነት፣ ከተቀጣሪነት፣ ከማወናበድ፣ በተለይም ከማስመሰለና ከተራ የፖለቲካ ንግድ በላይ መሆኑንና ማንም ሊበርዘው ቢደክምም ሊሸረሽረው የማይችለው የልብ ማህተም መሆኑን ሰሞኑን አየን። ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግርኳስ ቡድን ድል እውን ይሆን ዘንድ ሠንደቅ ዓላማቸውን ለብሰው ሌሊቱን ሙሉ ላገራቸው ያዜሙ፣ በየቤታቸው ሆነው በጸሎት የማለዱ፣ በመላው ዓለም በየድረገጹ የመልካም የደስታ ምኞታቸውን ሲገልጹ የነበሩ፣ በዋናው የትግል ሜዳ የአገራቸውን መለያ ለብሰው ታሪኩን ያከወኑና የትግሉን ስትራቴጂ በመንደፍ ታሪክ የሰሩ ድርና ማግ ሆነው አገራቸውን አብርተዋታል። ብንዘገይም ለመላው የኢትዮጵያ እግርኳስ ቡድን አባላት፣ ለመላው የኢትዮጵያ … [Read more...] about እባካችሁ ይህንን “ኢትዮጵያዊነት” አክብሩት!!
ከሞት በፊት እውነተኛ ክብር
“… ከሁሉ አስቀድሞ ማሸነፍ የሚኖርብን በውስጣችን ያለውን ፍርሃት ነው። ለህወሃት/ኢህአዴግ ታማኝ ሊሆኑ የሚችሉት የጦርና የፀጥታ ኃይሎቹ እንዲሁም የስለላ ተቋሙ የህዝብ ድጋፍ የሌላቸው የጥቂት ዘረኞች ስብስብ በመሆኑ የሕዝብ እምቢተኝነት ሲጠናከር በቀላሉ ይመክናሉ። አመራሮቹ አስተሳሰባቸው በጣም ጠባብ፤ ብቃታቸውም እጅግ ዝቅተኛ ነው። በመሆኑም እነዚህ ኃይሎች ሁሉንም ነገር እንደተቆጣጠሩት አድርጎ ማሰብ ራስን ማዋረድ ነው። ስለዚህም መሸሽ ሳይሆን በየጊዜው ልንፈታተናቸው፣ ልንጎነትላቸውና ልንፋለማቸው ይገባል። ስለሆነም ካሁን በኋላ ሥራው ህወሃት/ኢህአዴግን ከውስጥ ሆኖ የመበታተንና የማፍረስን ሥራ ነው። የነጻነት ኃይሎችም መዋቅራቸውን በማስፋትና በርካታ ህዋሶችን በመፍጠር በትጋት እየሠሩ ይገኛሉ። የህወሃት/ኢህአዴግን የመዋቅር ስፋት በነፃነት ኃይሎች የመዋቅር ስፋት መጋፈጥ ይቻል ዘንድ … [Read more...] about ከሞት በፊት እውነተኛ ክብር
ኃይለማርያም ደሳለኝ – እንደ ዳንኤል፤ እንደ አክሊሉ ወይስ እንደ መለስ?
አገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ አስር የሚሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሮች አስተዳድረዋታል፡፡ ከእነዚህ መካከል በተለየ ሁኔታ ከሚወሱት አንዱ ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ናቸው፡፡ በጣልያን ወረራ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ በአውሮጳ ያደረጉት ተጋድሎ እጅግ ከፍተኛ ለመሆኑ በተለያዩ ቦታዎች ሲጠቀስ የሚሰማ ነው፡፡ አርበኞቻችን በአገር ውስጥ የሕይወት መስዋዕትነት ሲከፍሉ አክሊሉ ሃብተወልድ በአውሮጳ የከፈሉት መስዋዕትነትና ኢትዮጵያን ለማዳን የሠሩት ሥራ ተጽፎ የማያልቅ ታሪካቸው ነው፡፡ ያላንዳች ማጋነን የዲፕሎማሲውን ሥራ ያለመታከት ከግብ ያደረሱት አክሊሉ ነበሩ፡፡ በተለይ “የአክሊሉ ማስታወሻ” በተባለው የራሳቸው ታሪክ በከፊል የተወሳበት መጽሐፍ ላይ የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆር እና የፈረንሣዩ ጠ/ሚ/ር ላቫል ከኢትዮጵያ ክፍላተሃገራት አብዛኛው የሆነው ሐረር፣ ሲዳሞና ባሌን ጨምሮ … [Read more...] about ኃይለማርያም ደሳለኝ – እንደ ዳንኤል፤ እንደ አክሊሉ ወይስ እንደ መለስ?
ከመጥበብ ቅድሚያ ለ “እምዬ ኢትዮጵያ”
የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል በወገኖቹ የሚፈቀር፣ የሚከበርና አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ የሚደረግለት የህዝብና የአገር አለኝታ ነው። ክቡር ህይወታቸውን ሳይሳሱ ላገራቸው ሲሉ አሳልፈው የሚሰጡትን ውድ የኢትዮጵያ ልጆች የምናከብራቸውና ልንከባከባቸው የሚገባው ልክ ያይናችን ብሌን ያህል ነው። “ክቡር ለውድ ኢትዮጵያዊ ሰማዕታት” ሲባል እንዲሁ መፈክር ለማለት ሳይሆን ከልባችን፣ ከውስጣችን፣ የመስዋዕትነታቸውን ክብር ከቶውንም ልንዘነጋው የሚቻለን ባለመሆኑ ነው። ሌላ ምክንያት የለውም። በቃ!! የምንኮራበት መከላከያ እንዲኖረን አጥብቀን ስለምንመኝ ያገር ኩራት የሆነው መከላከያችን በክልል፣ በዞንና በጎጥ አንሶና የተዋረደ ስብዕና ተላብሶ እንዲዋቀር ኢትዮጵያውያን አይፈቅዱም። አገራችን ከምትገኝበት የጂኦ ፖለቲካል አቀማመጥ አንጻር ብሄራዊ ስብዕና ያለው፣ ህዝብንና አገርን የሚያስቀድም የመከላከያ … [Read more...] about ከመጥበብ ቅድሚያ ለ “እምዬ ኢትዮጵያ”
ወፌ ቆመች በሉና!!
መረጃ ለአንድ ማህበረሰብ ከምንም በላይ አስፈላጊና አንገብጋቢ አጀንዳው ነው። ይህ የሚሆነው በአግባቡ ሚዛኑን ጠብቆ ሲራመድ ብቻ ነው። ስርዓት ጠብቆና በተቻለ መጠን ሙያዊ ስነምግባሩን ተከትሎ መራመድ የሚችል ሚዲያ የወደፊቱን በማየት ህብረተሰብን ያነቃል፣ ያሳስባል፣ ያዘጋጃል፣ የተለያዩ ሃሳቦችን ገደብ ሳያደርግ ያስተናግዳል። በዚህ እሳቤ ላይ ተመስርቶ ለመስራት የተስማማው የጎልጉል ኤዲቶሪያል ቦርድ በአገራችን አዲስ ዓመት ዋዜማ ለንባብ ሲውል ቀዳሚ ጥሪው ያደረገው ለመቆም የሚውተረተር ህጻን የሚበረታታበትን “ወፌ ቆመች” የሚለውን ባህላዊ ቃል ነው። ወፌ ቆመች!! ሚዲያ እንደ ንፋስ ከነፈሰና በስማ በለው ከነጎደ ስቶ ከማሳቱ በላይ ማህበረሰብን ሚዛን በሌለውና በተራ አሉባልታ በማዥጎርጎር ቀላል የማይባል የስሜት ግሽበት ያስከትላል ብለው ከሚያምኑት ክፍሎች ተርታ ራሳችንን እንመድባለን። … [Read more...] about ወፌ ቆመች በሉና!!