ታዋቂው የጋና ምሁር ጆርጅ አዪቴ በተደጋጋሚ እንደሚሉት ከአምባገነናዊ ስርዓት ወደ ዴሞክራሲ በሚደረገው ሽግግር የትኛውንም ዓይነት ተሃድሶ ከማድረግ በፊት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው የእውቀት ተሃድሶ ነው፡፡ ሕዝብ እንደሚገባው በእውቀት ከነቃ የዴሞክራሲና የመብቱን ጉዳይ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ይህንን ተከትሎ የሚከሰተው የእውቀት ተሃድሶ ወደ ፖለቲካዊ፣ ተቋማዊ፣ ሕገመንግሥታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ … ተሃድሶ ይመራል፡፡ የእውቀት ተሃድሶ ሳይደረግ ከአምባገነናዊ ሥርዓት ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር አንዱን አምባገነን በሌላ የመተካት ሂደት እንጂ ዘላቂ ለውጥ የሚያመጣ አይደለም ይላሉ፡፡ ሕዝብ የእውቀት ተሃድሶ ካካሄደ በሥልጣን ላይ ከተቀመጠው አምባገነን ያልተሻሉትን የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ማንነት ጠንቅቆ ማወቅ ይችላል፡፡ በፖለቲካ ብልጣብልጥነት ሊያካሂዱበት የሚችሉትን አሻጥር አስቀድሞ ያውቃል፤ ዕድልም አይሰጣቸውም ምክንያቱም ሕዝብ የሚፈልገው ትክክለኛ ሥርዓት እንዲመሠረት እንጂ አንዱን አምባገነን በሌላው ለመተካት አይደለም። ለዚህ ነው ምሁሩ ከፖለቲካ ተሃድሶም ይሁን ከሌላ ማንኛውም ተሃድሶ በፊት በቅድሚያ የእውቀት ተሃድሶ መደረግ አለበት የሚሉት፡፡ በጋና ተግባራዊ አድርገውት ውጤት እንዳመጣና ጋና ወደ ዴሞክራሲ ጎዳና ለመሸጋገር መቻሏን እንደማስረጃ ይጠቅሳሉ።
ከሰው ልጅ መሰረታዊ ባህርይ በመነሳት ሲታይ ሃያ ዓመት በአንድ ድርጅት መተዳደር በራሱ ይሰለቻል። አቶ መለስ “ሳያርፉ ሞቱ” እየተባለ እንደተነገረን መሪውን ያታክታል፡፡ የአገዛዙን ማሽን ጥርስም ይሰብራል፡፡ የሰው ልጆች ሁሌም አዲስ ነገር ይሻሉ። በተለይም እንደ ኢህአዴግ ካለ መንግስት ጋር የኢትዮጵያ ህዝብ ለሁለት አሰርተ ዓመት መዝለቁ አስገራሚ ነው። አንዳንዶች “አስማት” እንደሚሉት፤ “ኢህአዴግ ሃያ አንድ ዓመት መንበር ላይ የተቀመጠው በራሱ ጥንካሬ ሳይሆን በሌሎች ድክመት ነው” የሚሉ ቢኖሩም ኢህአዴግ በቀላሉ ሌሎች እንደሚስሉት ተገፍትሮ የሚወድቅ ድርጅት አይደለም በሚል የሚከራከሩም አሉ። በኛ እምነት ግን ችግሩ የሚቀድመውን ተሃድሶ አለማወቁ ላይ ነው።
በኢትዮጵያ ባለፉት ሃያ አንድ ዓመታት የድርጅት እጥረት አላጋጠመንም። ለቁጥር የሚታክቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቋቁመዋል። ከመንደር እሳቤ ጀምሮ እስከ ብሄራዊ ደረጃ ከተዋቀሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ምን ያህል እንደተሳካላቸው በውል ባይታወቅም ህዝብ አደራጅተናል የሚሉ አሉ። መቋቋማቸው ሳይሰማ “እንደወጡ” የቀሩ ብዙ ናቸው። እንደው ለወጉ ያህል ስያሜያቸውን እያሰሙ በመግለጫና በዘለፋ “አልጠፋንም” የሚሉም አሉ። ለዓመታት ጎረቤት አገር መሽገው ከዛሬ ነገ “መጣን” የሚሉን አሉ። መኖራቸውም መሞታቸውም ልዩነት በሌለው መልኩ የሚንከላወሱ “ሙት” ነዋሪ ፓርቲዎችም አሉ። የፖለቲካ ዓላማቸው ሌሎችን በሾኬ መጣል፤ የኢኮኖሚ ፕሮግራማቸው ሌሎቹን ማክሰር፤ የማኅበራዊ ፖሊሲያቸው ማበጣበጥ፤ የሃይማኖት አመለካከታቸው “እኛ ካልባረክነው ዉጉዝ ነው” የሚል ፕሮግራም ያላቸው የሚመስሉም አሉ፡፡ ኢህአዴግ ጥብቆ አልብሶ ያደራጃቸው “ተለጣፊ” የሚባሉትም አሉ። ቤተሰብ ሰብስበው ቃለ ጉባኤ እያጸደቁ አገርና ህዝብ ነጻ እናወጣለን የሚሉም አሉ። አጋነናችሁ ካላላችሁን ከእቁብና ከእድር ባነሰ አደረጃጀት አገር ለመምራት ተነስተናል የሚሉ እፍረት ያልፈጠረባቸውም አሉ። እየተሰነጠቁና እየተሰነጣጠሩ ኤ፣ ቢ፣ ሲ፣ ዲ፣ ኢ፣ ኤፍ፣ … የሚባሉትና ሌላም ሌላም ዓይነት፡፡ ለምን እንዲህ ይደረጋል ሲባሉ “ለአንድ ኢትዮጵያችን ብለን ነው” ይሉናል!
ታግለው የሚያታግሉ አመራሮች አሉ። ስብዕናቸው የሚወደድ መሪዎች አሉ። ከሃሳብ እንጂ ከድርጅትና ከግለሰቦች ጋር ጸብ እንደሌላቸው በማስተጋባት ያመኑበትን የትግል አቅጣጫ የሚከተሉ አሉ። በርካታ ደጋፊና ተንከባካቢ ያላቸው ዘወትር ስለመቀራረብና ስለመተባበር አስፈላጊነት የሚሰብኩ አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅት ባቋቋሙ ማግስት በትዕዛዝ የሚወገዙ፣የሚሰደቡና ቀጠሮ ተይዞ በደቦ የጥላቻ ዘመቻ የሚከናወንባቸው አመራሮችም አሉ። ደረጃ የሚወጣላቸውና የሚፈረጁም ጥቂት አይደሉም። ይህም የሚሆነው ለኢትዮጵያ ሲባል ነው ይባላል።
ድርጅት ባቋቋሙ ማግስት ሌሎች ድርጅቶችን በማውገዝ ራሳቸውን የሚያስተዋውቁ አመራሮች አሉ። በሚያራምዱት ያረጀና የነተበ ፖለቲካ ስንዝር መራመድ ሳይችሉ ቀርተው ሌሎችን በማወገዝ የተጠመዱ አመራሮች አሉ። ፓርቲን ከፖለቲካ ስራ ይልቅ ወደ ግል ማህበር በመቀየር ሲሳደቡና ሌላውን ሲያወግዙ ኖረው ለመሞት የወሰኑ አመራሮች አሉ። ምን እየሰሩ እንደሆነ የማናውቃቸው አመራሮች አሉ። እነዚህና ሌሎች ሁሉም የሚናገሩት ግን ስለ አገርና ህዝብ ነው። “ነጻ አውጪ” ስለ መሆናቸው!!
ብዙ አይነት የተቃዋሚ ድርጅቶች ደጋፊዎች አሉ። ያለአንዳች መታከት በችግርና በተስፋ መቁረጥ ውስጥ እያለፉ የሚታገሉ አሉ። ዳር ሆነው የሚያሽሟጥጡ፣ በሌሎች መስዋዕትነት የድል ክሬም ለመላስ የሚመኙ አሉ። በስድብና በዘለፋ መንግስት መቀየር እንደሚቻል አድርገው የሚናደፉ፣ ነገር ግን በተግባራዊ ድጋፍ ሲመዘኑ መስፋሪያ የማይሞሉ አሉ። አስር ዶላር በማዋጣት የሚደግፉትን ፓርቲ ሚስጥርና እንቅስቃሴ በዝርዝር በአድራሻቸው ሪፖርት እንዲቀርብላቸው የሚጠይቁ አሉ። ከሁሉም በላይ ወዴት እንደሚያዘሙ ግራ ተጋብተው ዝምታ የመረጡ አሉ። እነዚህ ዝም ያሉ ብዙሃን (silent majority) ተብለው የሚጠቀሱት ክፍሎች ትልቁን ቁጥር ስለሚይዙ ወደ ትግልና “እኔም ያገባኛል” መንፈስ ሊዛወሩ የግድ ነው። እንዴት? በእውቀት ተሃድሶ!!
ከተሃድሶዎች ሁሉ የእውቀት ተሃድሶ ካልቀደመ መሪው፣ ተመሪውና ድርጅቱ ሁሉም ተያይዘው ሲጓተቱ 21ኛው ክፍለ ዘመን ይጠናቀቃልና የሚቀድመውን ማወቅ ብልህነት ይሆናል። ለሁሉም የእውቀት ተሃድሶ በቅድሚያ! ለዲያስፖራው ሆነ ለአገር ቤቱም ወገን የእውቀት ተሃድሶ በቅድሚያ!! የእውቀት ተሃድሶ ባስቸኳይ፣ የእውቀት ተሃድሶ የዘለቀው ደጋፊና ዜጋ ሲነፍስ አብሮ በነፈሰበት አይነፍስምና!!
Christian says
I like your article.
However, I do not completely agree with the analyses.
I agree on the fact that political leaders need to have all the knowledge that they need to be better leaders. I think most of our politicians have the knowledge that is required of them. Nit all of them but most of them. Note one thing that not even all the political leaders of the democratic nations have knowledge.
If you are saying that our people (the ordinary people) need to have knowledge and if you are saying that it should come first before democracy, I have a different opinion. You need to have a democratic system to educate your people. In a country where there is no democracy and all the media outlets are pro-government, it is difficult to educate your people. I would say democracy should come first. I strongly believe that our Ethiopian people have sufficient knowledge to implement democracy.
inkopa says
God bless you!!
words like ” yewqet tehadso” and
” SILENT MAJORITY” are music to my ears.
Were says
የእውቀት ተሀድሶ ለማምጣት ምን ያስፈልጋል መልሱ ትምህት ከ ሚዛናው አመለካከት፡፡ ትምህር ሚዛናዊ አስተሳሰብ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማዳረስ፡፡ 1ኛ ትምህት ቤቶች በብዛት በጥራት መከፈት አለባቸው ተያይዞም ቤተ-መጽሐፍት 2ኛ አጫጭር ስልጠናዎች ሞያ ነክ፤ አስተዳደር ነክ፤ ቢዝነስ ነክ ወዘተ… በሁሉም እድሜ ክልል የሚሰጥ 3ኛ እውቀት ተኮር የሆኑ ሚዲያ ስርጭቶች የህዝብ ተሳትፎ ያለበት ውይይቶች የሚካሄድበት አስተማሪዎች እና ሙህራን እውቀታቸውን ሀሳባቸውን የሚያካፍሉበት፤ ሃሰብን በነጻነት የሚሸራሸርበት፤ ሃሳብን በሃሳብ ንግግርን በንግግር ክርክር የሚደረግበት፤ ንቃተህሊናን የሚያዳብሩበት ሚዲያ በሁሉም አቅጣጫ ማዳረስ፡፡ 4ኛ የስራ ፈጠራ የሚከናወንባቸው ተቋማት ስልጠና የሚሰጥባቸው ከትናንሽ እስከ ትላልቅ እንደስትሪዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ይህ ከተደረገ ከላይ የተገለጸው የኢትዮጵያ ህዝብ የእውቀት ተሃድሶ የደርጋል፡፡ ተግባራዊነቱ ላይ በዘመቻ፤ በእቅድ፤ በፍላጎት እና በግዳጅ ቢሆን በአጭር ገዜ ለውጥ ይገኛል፡፡ በግዳጅ ያልኩበት ምክንያት የመሃይምነት ደረጃው ከፍተኛ ስለሆነ መማር ማይችል እራሱን ዝቅ ያረገ ህዝብ ስላለ የግዴታ ትምህርት ያስፈልገዋል፡፡
Mulualem says
I like this analysis.
Keep up
Murad says
I also like this analysis. @Were, that would be wonderful if we can achieve it. But all in all this is what we should do
andnet berhane says
ከፖሊቲች ተሃድሶ የእውቀት ተሃድሶ ያስፈልጋል አዎን እጋራለሁ ነገር ግን መሰረታዊ አመጣጦችን በማየት በዝምናት ለመኖርና ሃገራችን ባለታሪክ የሆነችው ያለችው በግዚያዊ አዋኪያን ለደረሰባት ማህበራዊ ምጣኔ ሃብታዊ የሞራልና የፖለቲካ አለመረጋጋት ውጤቶች ካለፉት አባቶችና የትግል ውጤታቸው ያልተረዳነው ተከትለንም ተግባሩንና ውጤቱን አላጤነው አለ፡
ከሙሁር ደንቆሮ ያልተማረ ሊቅ “የሚል ብሄል አለ የተማረውን ለማጣጣል ሳይሆን ብዙ ያላያቸው ጠቃሚና ዋጋ ያላቸው ይዞቶች አሉን እነኛህም በዋናንነት ከተማረው ትምህርትና ካገኘው እውቀት ጋር በማዛመድ ለወገኖቹና ለራሱ የሚጠቅመው ሃገሩንም ለማሳደግ ባእዳንም ላሳፈር የሚያስችል ስራዎችን ባቀድን ነበር አብዛናዎቻችን ያገኘነውን ትምህርት የምንኮፈስበት በመሆኑ ካልተማረውና እድሉን ላጣው የምናደርግለት የሞራል ሆነ ስነጥበባዊ ስነልቦናዊ ደገፍ አናሳይም ይህም ከሕብረተሰቡ ጋር የተራራቅንና ከልምድና ከባህላችን የወጣን ያደርገናል፡ ማድመጥ ሳይሆን አድምጡን የሚል ራሳችንን ፍጹም በማድረግ ጥፋታችንን ለመቀበልና ይቅርታን መጠየቅና መቀበል እንድ ድክመትና እንድመሸነፍ በመውሰድ ያሉትን ሃገራዊና ማሕበራዊ ችግሮች እንድመፍታት በማስፋት በጥቅም መገዛትና ያካበቱትን እውቀት ለአገልጋይነት መጠቀም በማድረግ ያሳስባል ካልተማረው ልዩነቱ በተፈትሮ የተሰጠውን ከባሕልና ከልምድ በማያያዝ የማሕበራዊ ችግሮችን በመደማመጥ መቀራረብ በመፍጠር መፍትሄዎችን ያመጣል ያለውን ማንኛውንም የሕብረተሰቡ ችግሮችን እንደራሱ በማየት የገባበትን ኃላፊነት ይወጣል፡
አሁንም ሃገራችን የእምባገነን ሜዳ ለመሆን የበቃችው በሃገሪቱ ንጥረ ሃብት በተማሩና የራስ ወዳድነት የሃገር ክህደትና የራሳቸው ምንነት መልካም አስተዳደግና የጎደላቸው በውድድር ሳይሆን በቅናትና በተንኮል የሰከሩ የስልጣን ጥማት ያደረባቸው ትምክህተኞች ናቸው፡
እርግጥ ትምህርት አለም አቀፍ ግንኙነት ራስን ለመከላከልና እውነትና እውሸትን ለመላየት ላለመታለል ቢረዳም ባስተዳደር በኩል የሚታየውና በ ሙስና የተንሰራፉት ባአብዛኖዎቹ የተማሩና የራስ ወዳድነት የተጸናወታቸው ለመሆኑ የሚታይ ሃቅ ነው።
በቀደምት አባቶቻችን በሃገርና በግዛት አስተዳድሪነት የነበሩት መሪዎች በሙሉ በዘመናዊው ትምህርት ሳይሆን በመንፈሳዊ ትምህርት መጻፍና ማንበብ ብቻ የተካኑ እውነትን በመመርኮዝ ለገቡበት የስራ ኃላፍነት የስልጣን ተጠሪነት ለሕዝብንና ለሃገር ሲያገለግሉ እንድነበር ታሪክ ይዘክራል፡
እምባገነን ተመልሶ አይመጣም ብለን ለማረጋገጥ የምንችለው
በመጀመርያ ደረጃ ማወቅና መማር ያለብን የዘረኝነት አመጣጥ
ሀ- አድሎነት
ለ-ሕገወጥነት
ሐ-ስነስራአት ማጣት
መ-ልዩነት ማጥፋት የምንወስዳቸው እርምጃዎች ሲሆን
የአምሕበረሰቡ የስነልቦና ቅርጽና በስታና ጤናመነት
ሀ- የኑሮ ውጤቶች
ለ-ምሕበራዊ ውጤት
ሐ-ስነ አይምሮ ውጠት
እነኝህ ሦስት አብይ ጉድዮች ተግባርና ውጤቱ ጤናማነቱና ጉድለቱን በግልጽ ይመሩናል
ሀ የኑሮ ውጤት ድሕነት ተጠቂነት
ለ- ማሕበራዊ ውጤት
መደብ፤ ሥራ ፤ ዘር
ሐ-ስነ አይምሮ ውጤት
ጠባይ፤ እምነት፤ ተጸኖ፤ ስቃይ፤
እነኝህን ጥናትና መመርያ በማድረግ መፍትሄ በመፈለግ አብሮነትን በማምጣት ሕዝቦችን ማዘጋጀት ያስችላል
ነገርግን በሃገራችን ያለውን ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት የሚቻለው ሁላችንም ያለስብጥር በሃሳብና በተግባር በማበር ይቅርታን በመቀበልና በመጠየቅ ወደዋናው ሃገራዊና ሕዝባዊ ችግር ለመግባት የሚያስፈልጉት የጥናት መሰረቶች
ሀ- የችግራችን ስሮች
ለ- ግንዱን
ሐ- ቅርንጫፉን በተገቢ መንገድ በመመርመር መፍትሄ ማግኘት ያስፈልጋል