• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከሞት በፊት እውነተኛ ክብር

October 10, 2012 02:14 am by Editor 1 Comment

“… ከሁሉ አስቀድሞ ማሸነፍ የሚኖርብን በውስጣችን ያለውን ፍርሃት ነው። ለህወሃት/ኢህአዴግ ታማኝ ሊሆኑ የሚችሉት የጦርና የፀጥታ ኃይሎቹ እንዲሁም የስለላ ተቋሙ የህዝብ ድጋፍ የሌላቸው የጥቂት ዘረኞች ስብስብ በመሆኑ የሕዝብ እምቢተኝነት ሲጠናከር በቀላሉ ይመክናሉ። አመራሮቹ አስተሳሰባቸው በጣም ጠባብ፤ ብቃታቸውም እጅግ ዝቅተኛ ነው። በመሆኑም እነዚህ ኃይሎች ሁሉንም ነገር እንደተቆጣጠሩት አድርጎ ማሰብ ራስን ማዋረድ ነው። ስለዚህም መሸሽ ሳይሆን በየጊዜው ልንፈታተናቸው፣ ልንጎነትላቸውና ልንፋለማቸው ይገባል። ስለሆነም ካሁን በኋላ ሥራው ህወሃት/ኢህአዴግን ከውስጥ ሆኖ የመበታተንና የማፍረስን ሥራ ነው። የነጻነት ኃይሎችም መዋቅራቸውን በማስፋትና በርካታ ህዋሶችን በመፍጠር በትጋት እየሠሩ ይገኛሉ። የህወሃት/ኢህአዴግን የመዋቅር ስፋት በነፃነት ኃይሎች የመዋቅር ስፋት መጋፈጥ ይቻል ዘንድ ትግሉ ተፋፍሟል…

“… ስለዚህ ፍትሕ፣ ሰላም፣ አንድነትና ዕርቅ የሚሰፍንባትን “አዲሲቷን ኢትዮጵያ” በጥቅም ተደልለው ወይም በፍርሃት ነፃነታቸውን አሳልፈው በሚሰጡ ሰዎች መገንባት አይቻልም። የሕዝብ እግዚኦታ፣ ለቅሶና ምሬት ወደ ተግባር ሲለወጥ የማሳሰቢያ፣ የንሰሃ ወይም የጥሪ ጊዜ አይኖርም፡፡ ከላይ እንደጠቆምነው አሁን እየቀረበ ያለው ጥሪ የኢትዮጵያ መሆኑን ልብ ይበሉ:: ይህንን ጥሪ ንቆ ነገ “እኔኮ ትዕዛዝ ፈጻሚ ነበርኩ” የሚሉ ሁሉ ይህ ጥሪ ራሱ የወንጀላቸው ማስረጃ ሆኖ እንደሚቀርብባቸው መገንዘብ አዋቂነት ነውና ይህንን እየራደ የሚገኝ ሥርዓት “እንቢ!” ያሉ ወገኖቻችን የሚኖራቸውን ሞገስና ክብር፤ ከማይቀረው የኢህአዴግ ውድቀት በኋላ ተባባሪዎቹ ላይ ከሚደርስባቸው ውርደት ጋር በማነጻጸር ዛሬ ለእውነት እንቁም፡፡ ወደ ልባችን እንመለስ!! ለጥሪውም ምላሽ እንስጥ!!”

ይህ ከላይ የተቀመጠው መልዕክት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ “ደወል” በሚል ርዕስ ለስርዓቱ ታዘዦች በተከታታይ ካስተላለፈው መልዕክት ሁለተኛው ቁጥር ላይ የተቀነጨበ ነው። ሃሳቡን ቀንጭበን የወሰድነው ነገር ለመድገም ፈልገን ሳይሆን የወቅቱን ሁኔታ ለማሳሰብ ያህል ነው። ስጋታችንን ለመጠቆም ነው።

ኢህአዴግ ላለፉት ሃያ አንድ ዓመታት እንዴት ኖረ? ብለን ስንጠይቅ መልሱ በስለላ፣በወታደራዊ ሃይል፣ በድርጅታዊ አቅም ግዝፈቱ ሳይሆን የተቃዋሚው ጎራ ቁልፍ ድክመትና ራዕይ አልባነት እንዳለ ሆኖ፣ በ“የነጻነት ተፋላሚዎች” የተሸናፊነት ስሜትና በውስጣቸው ባለ ፍርሃት ሳቢያ ነው። ዛሬ ኢህአዴግ ያለበትን ትክክለኛ ትኩሳት መረዳት ለሚችሉ ስርዓቱ “በስብሷል፣ ሸትቷል” በማለት ከቁጥር በላይ ማስረጃዎች ራሳቸውን መጥቀስ ይቻላል። ስጋታችን የሚነሳው ከዚሁ ከመበስበስ አደጋ ላይ ይሆናል።

ኢህአዴግ ባለስልጣናቱ በሙስና የገለሙ፣ ከድሃ ህዝብ ላይ በመዝረፍ አጥንቱን የሚግጡ፣ አገርን ከመምራት ይልቅ በተራ ዝርፊያና በረከሰ ወንጀል የተጨማለቁ፣ የስብዕናቸው እድፈት ሊደበቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ የደረሰባቸው፣ የሸተተ ስርዓትና አመራር አገርናና ህዝብን ተቆጣጥረው እንደሚኖሩ አድርጎ ማሰብ ከላይ እንደተገለጸው ራስን የማዋረድ ያህል ቢሆንም ከሁሉም በላይ እኛን የሚጨንቀን የአገራችን የወደፊት ጉዳይ ነው።

አሁን ባለው የመቧደንና የመሰነጣጠቅ አዝማሚያ፣ ስርዓቱና ባለስልጣኑ ከደረሱበት የመሞሻለቅ አፋፍ ላይ እንደ ቆምን ይሰማናል። ባለን መረጃና በያቅጣጫው ከሚታዩት ምልክቶች አንጻር የሚፈርስ ስርዓት ስለመኖሩ መጠራጠር አቁመናል። ይህንኑ የመፈራረስ አደጋ ለማስታገስ እንደተለመደው ስታሊናዊ ርምጃዎች በቅርቡ እንደምንሰማም አይታበልም። በዚህ ሁሉ መደነባበር ውስጥ አገራችንን የሚሉ የቁርጥ ቀን ልጆች ከወዲሁ ዝግጅታቸውን ሊያደርጉ ይገባል እንላለን።

ታሪክ ሰርቶ ማለፍ በደልን ሁሉ ያስረሳልና ለአገራችን ሲባል፣ ለህዝብ ሲባል፣ ለራስ ሲባል፣ ለራስ ልጅ ልጆች ሲባል፣ ማለፍም ስላለ ኢህአዴግ በቅድሚያ አገራችንን የሚታደግ ርምጃ ቢወስድ ሁሉንም ያቀለዋልና አገርና ህዝብ ደስ እንደሚላቸው ጥርጥር ለውም። ተቃዋሚዎችም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ትግልንና ዓላማን ወደ መሬት ለማውረድ ሊረባረቡ የሚገባቸው ወቅት ላይ እንደ ሆኑ ቢያውቁትም ልናስታወሳቸው እንወዳለን። በየደረጃው ያለን የኢትዮጵያ ልጆች ወቅቱ የሚጠይቀውን ሁሉ በማስተዋል ልናደርግ ይገባልና አገርን ለሚጠቅም አጀንዳ ሁሉ በመነዳት ሳይሆን አስተዋይነት በተሞላው መንገድ ተባባሪነትን ማሳየት እንደሚጠበቅ እንጠቁማለን። ለማንኛውም የፖለቲካ የአየር ትንበያ ባለሙያዎች ያስፈልጉናል። ባለሙያዎቹ የንስሃን ጊዜ ሲያበጁ ከሞት በፊት ንስሃን ይፈጥን ይሆናል!! ህዝብ ይቅር ካለ አገርም ትጠቀማለች። መጪው ትውልድም ባለው ለመቀጠል ይታደላል። ግን ባስቸኳይ ይሁን!!

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Kibba says

    October 26, 2012 10:15 am at 10:15 am

    ህወህት/ኢህአዴግ እስክሁን የቋየው በስለላ፣በወታደራዊ ሃይል፣ እና በድርጅታዊ አቅም ግዝፈቱ ሳይሆን በተቃዋሚው ጎራ ያለው ድክመትና ራዕይ አልባነት እንዳለ ሆኖ፣ በ“የነጻነት ተፋላሚዎች” የተሸናፊነት ስሜትና በ መላ ኢትዮጵያውያኖች በውስጣቸው ባለው “ፍርሃት” ሳቢያ ነው።
    ዛሬ ኢህአዴግ ያለበትን ትክክለኛ ትኩሳት መረዳት ለሚችሉ፡ ስርዓቱ “በስብሷል፣ ሸትቷል” ለዚህም ከቁጥር በላይ ማስረጃዎችን መጥቀስ እና ማቅረብ ይቻላል።
    ጥየቂችን ግን ይህን የመበስበስ ሥርዓት ለማሽነፍ የህዝበችንን “ፍርሃት” እንዴት ማሽነፍ እንችላለን ነው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule