• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወሬ ይገድላል

January 2, 2013 10:29 am by Editor Leave a Comment

በጎርጎሪያኑ የቀን መቁጠሪያ ለምትገለገሉ ሁሉ መልካም አዲስ ዓመት!! በአዲሱ ዓመት ከራስ ጋር በመታረቅ፣ ከህሊናና ከእዕምሮ ባርነት በመላቀቅ፣ ከይሉንታ ጥብቆ ውስጥ በመውጣት፣አካሄድን ለማሳመር ይቻል ዘንድ የተጠቀለለውን አሮጌ ዓመት ትምህርት ማድረግ ታላቅ ጉዳይ ነው። አዲሱ ዓመት ከባከኑት ዓመታቶች ጋር ተዳምሮ እንዳያጎብጠን፣ ተስፋችንን እንዳይበላውና ወደ ከፋ የፖለቲካ መሰላቸት ውስጥ እንዳይከተን መጠንቀቅ ደግሞ ከሁሉም በላይ ወሳኝ ይመስለናልና ከከንቱና የማያንጽ ወሬው ቆጠብ፣ ከተግባሩ ጨመር እናድርግ!! ወሬ ይገድላል እንዲሉ!!

ይሉኝታን እንቅበር

ባለፉት ዓመታት የይሉኝታ ፖለቲካ ጉዳት አድርሷል። በይሉኝታ በመነዳት የማይረሳ ኪሳራ ተመዝግቧል። በይሉኝታ ብቻ የደረሰብን የፖለቲካ ጠባሳ ሰምበሩ በያንዳንዳችን ሰውነት ላይ ይታያል። በተፎካካሪ ፓርቲዎችና ለለውጥ በተነሱ ፓርቲዎች ውስጥ ብዙ የሚሰሙ ጉዳዮች አሉ። በየጓሮ የሚሰማው የሃሜት፣ የጀግንነትና የአሉባልታ ትግል የሚቆመው ይሉኝታ ሲሰበርና ፊትለፊት መግጠም ሲቻል ነውና የይሉኝታን አርበኝነት እንቅበር!! ይህ የአዲስ ዓመት የመጀመሪያው የቤት ስራ ይሁን!! በተግባርም ይታይ!!

ራስን ማክበር

አብዛኛውን ጊዜ ስለ ህሊናና አእምሮ ባርነት ይነገራል። ሰዎች ከዚሁ ከአእምሮ ባርነት ራሳቸውን ነጻ እንዲያደርጉ ምክር ሲሰነዘር በተደጋጋሚ ይሰማል። ምክሮቹና ትምህርቶቹ ምን ያህል ተግባራዊ እንደሆኑ ባናውቅም ባጭሩ ግን የ“ባርነት” ዋናው መሰረት ራስን አለማክበር ነውና የራሳችንን ዋጋ እንወቅ። ራሳችንን አክብረን፣ ክብራችንንና ዋጋችንን ጠብቀን፣ ስንጓዝ ከባርነት እንላቀቃለንና ለራሳችን ክብር እንስጥ። በከበርን ቁጥር ከስሜትና ከግብታዊ የፖለቲካ ትግል ራሳችንን በማረቅ አካሄዳችንን የማስተካከል እድል እናገኛለን። በእንዲህ መልኩ ስንደግፍም ሆነ ስንደገፍ አንወድቅም። በዚህ ዓይነቱ መደጋገፍ ውስጥ ተግባር እንጂ ፕሮፓጋንዳ ቦታው ያንሳል። መተማመን ይሰፍናል። ዛሬ እልል ብለን ነገ ከማዘን እንድናለን።ሁላችንም ራሳችንን ስናከብር የጋራ ራዕይና የጋራ መሪ ለመሰየም አንቸገርም። የሰየምነውንም መሪ አምኖ ለመቀበል ጊዜ አናመነዥግም። ሰባኪና ደቀ መዝሙርም አያስፈልግም። እናም ራስን ማክበር ዋጋው ታላቅ ይሆናል። ከመነዳትም ያድናልና!!

ያገባኛል

ባብዛኛው የአገራችን ጉዳይ ለተወሰኑ ሰዎች የተሰጠ ይመስላል። የተወሰኑ ሰዎች ይናገራሉ።ስለወገኖቻቸውና ስለ አገራቸው ይከራከራሉ። ህዝብ አደራጅተው ለመታገል የበኩላቸውን ሲያደርጉ የሚታዩት እጅግ ጥቂቶች ናቸው። አብዛኛው ህዝብ ግን አድፋጭ ነው። አብዛኛው ምሁር ተመልካች ነው። ህወሃት/ኢህአዴግ ክፉ መንግስት እንደሆነ ከልሒቅ እስከ ደቂቅ ሁሉም ህዝብ፣ የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ጨምሮ ያውቃሉ። ግን ዳር ቆመዋል። ባልተመጣጠነ የኢኮኖሚ ፍሰት አብዛኞች ወደ ባርነት እየተመሙ፣ ልጅ ልጆቻቸውን ለባርነት በስጦታ ለማቅረብ እየገሰገሱ ነው። ልጅ ልጆቻቸው ከተወዳዳሪነት ተለይተው የበይ ተመልካች እንዲሆኑ ሲደረግ “አያገባኝም” የሚሉ እንዴት በረከቱ? ስለ ስርዓቱ ጸያፍነትና የህዝብ ምሬት ብዙ ማለት ይቻላል። ግን አድፋጩ ለምን በዛ? የፖለቲካ መሪዎቻችን ይህንን ጥያቄ መመለስ አለባቸው።አገሪቱና ህዝቧ ያስተማሯቸው የኢትዮጵያ ልጆች ካዳፋቸው የፖለቲካ ድብታ እንዴት እንዲነቁና “ያገባኛል” በሚል መንፋስ እንዲነሱ ምን ይደረግ? “የምሁራን” መንደሮች የያዛቸው እንቅልፍና የአድርባይነት ስሜት እንዴት ይነቀል? ተወደደም ተጠላም ያገባኛል የሚል ህብረተሰብ ሊፈጠር ግድ ነውና ወገብን ጠበቅ አድርጎ መስራት ግድ ይላል።

በቃኝ

ህዝብ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚያዳምጠውና የሚከለታተለው አማራጭ ስለሚፈልግ ነው።በፉክክር ተጠቃሚ ለመሆን ነው። ህዝብ የሚጠብቀውን ማድረግ ያልቻሉ አሉ። ሰሞኑን በፓርቲዎች ክርክር ስም ቀርበው ኢህአዴግን እንሞግታለን የሚሉትን ስንሰማ አጥወልውሎናል። ህዝብ እነዚህ ናቸው ተቃዋሚ ብሎ ተስፋ እንዲቆርጥ ሆን ተብሎ የሚሰራ ስራ ቢኖርም እንዴት መናገር፣ የሚናገረውን የማያውቅ፣ ስለምን እንደሚናገር ያልተረዳ፣ እቁብና እድር እንኳን መዳኘት የማይችል ሰው ፓርቲ አቋቁሞ አገር ለመምራት ያስባል? እንዲህ ያሉ ብዙ ናቸው። የምርጫ አዳማቂዎች!! በውጪም አሉ፤ በህክምና ቋንቋ “የሼልፍ ጊዜያቸው ያበቃ” መኖራቸውም፣ መጥፋታቸውም ልዩነት የሌለው ምን አለበት “ሳናውቅ እየረበሽን ኖረናል፤ በቃን” ቢሉ? ሌላም ህይወት አለ። የሚሰሩትን ከጀርባ እየተከተሉ ጤና ከመንሳት “በቃኝ” በማለት ብቻ ለህዝብ ክብር መስጠት የሚቻል ይመስለናል።

ተግባር

ስለ ህወሃት/ኢህአዴግ ብዙ ተብሏል። እንግዳ ብንሆንም እኛን ጨምሮ በየድረገጹ ያልተነገር ነገር የለም። በተለያዩ ማህበራዊ ድሮችና ሞገዶች ዛሬን ጨምሮ ስለ ኢህአዴግ እንሰማለን።የሚሰማው ብዙ ነው። በተግባር የሚታየው ግን እጅግ በጣም፣ እጅግ ጥቂት፣ በጣም በጣም ጥቂት፣ ኢምንት ነው። ወሬው እየገዘፈ ተግባሩ ሲያንስ፣ ሲኮሰምን፣ ሲሟሟ፣ ተስፋ መቁረጥ ያስከትላልና አልሞና መትሮ መንቀሳቀስ ግድ ነው። ዛሬ የሚሰሩ ስህተቶች እስከወዲያኛው የማያገግም ጠባሳ እንዳያትምብን እንጠንቀቅ። መልካም በዓል!!

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule