ዛሬ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከተቋቋመ አንድ ዓመቱ ነው። ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ የደገፉን፣ ያበረታቱን፣ አስተያየት በመስጠት ያረቁንና በመድረካችን የተሳተፉ ያሉትን ያህል የምንሰራውን ስራ ለመቆጣጠር፣ የተመሰረትንበትን ግልጽ መስመር ለማስቀየር የሞከሩና ጨዋነት በጎደለው መልኩ የተዛለፉም አጋጥመውናል። ለሁላችም እንኳን ለአንደኛው ዓመት አደረሰን!! “ወፌ ቆመች በሉን" በማለት ከዓመት በፊት የሚዲያውን ሰፈር በአሃዱ ብለን ከተቀላቀልንበት ጊዜ አንስቶ የሰራነውን ስራ በጥሞና ለመመልከት ሞክረናል። ሌሎች ሚዲያዎችንና ብሎጎችንም ዳሰናል። የራሳችን ደካማ ጎን ስንፈትሽ እግረ መንገዳችንን ዙሪያችንን ስንቃኝ የሚዲያ ተሃድሶ (ሪፎርም) አስፈላጊ እንደሆነ ተረድተናል። አምነናል። "መቼ" ለሚለው ጥያቄ ምላሹ ዛሬ፣ አሁን፣ አሁኑኑ የሚል ነው። ድክመታችን ስንጀምር በዘረጋናቸው … [Read more...] about የ፩ኛ ዓመት መልዕክት – የሚዲያ ተሃድሶ ግድ ነው!!
Editorials
ርዕሰ አንቀጽ
የ“አምላካችሁ ባሮች” የሆናችሁ “ሰላማዊ ሰልፈኞች” ቅድሚ የምትሰጡት ለማን ነው?
እርቅን፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ መቻቻልን ለማውረድ የሃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች ቁልፍ ሚና አላቸው። በር ዘግተው ይጸልያሉ። ያስታርቃሉ። ይገስጻሉ። ያስጠነቅቃሉ። እንዲህ አይነት ለሌሎች ብርሃን ለመሆን የሚቃጠሉ የሃይማኖት አባቶች ያሏቸው ምንኛ የታደሉ ናቸው? በተቃራኒው የአምላክ ባሪያዎች፣ የየእምነታቸው ባሪያዎች፣ የምዕመናን መንፈስ መጋቢዎችና ጠባቂዎች፣ ወዘተ አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚወጡ በይፋ ተነገረን። "በተገንጣይ ነጻ አውጪ" ስም እየተጠራጠረና እየተጸየፈ አገራችንን ከሚመራ ከሃዲ ድርጅት ጎን ለመቆም የሃይማኖት መሪዎች መነሳታቸው ለፈረደባት ኢትዮጵያና ለህዝቧ ከዚህ በላይ ሃፍረት የለም!! ችግሩ በውስጥም በውጭም ያለውን ይመለከታል። ይህንን ስንል ምክንያታችንን ህዝብ ይረዳዋል ብለን እናምናለን። በሰማያዊውም ሆነ በምድራዊው ዓለም “መተፋት” አለ። የሃይማኖት አባቶችና … [Read more...] about የ“አምላካችሁ ባሮች” የሆናችሁ “ሰላማዊ ሰልፈኞች” ቅድሚ የምትሰጡት ለማን ነው?
የዕርቁ ካርድ እንዳይባክን!! የተደበቃችሁ ተገለጡ!!
“ከፍትህ ጋር ተቀነባብሮ ያልተፈጸመ ዕርቅ ዘላቂነት የለውም፤ ሁላችንም ሰላም እንዲሰፍን ተስፋ የምናደርግ ብንሆንም የምንመኘው ሰላም በፍትህና በሕግ ላይ የተመሠረተ መሆን ይገባዋል እንጂ በተገኘው ሁኔታ ይሁን የምንለው መሆን የለበትም” የቀድሞ የፊሊፕንስ ፕሬዚዳንት ኮራዞን አኪኖ፡፡ ወደ ሥልጣን የተጠጉና ለመጠጋት የሚያስቡ ፓርቲዎችና ግለሰቦች እንዲሁም ሥልጣንን የተቆጣጠሩ ወዘተ በአገራችን ዕርቅ እንዲመጣ ሲመኙ፣ ሲያቅዱ፣ ፕሮግራም ሲያወጡ፣ ዲስኩር ሲሰጡ፣ … ቢያንስ አራት አሥርተ ዓመታትን አስቆጥረናል፡፡ “ብሔራዊ ዕርቅ፣ አገር አቀፋዊ ዕርቅ፣ … ” እየተባለ ሲነገር የሰማነው አሁን አይደለም፡፡ እስኪሰለቸን ሰምተናል። እርቅን ያህል ታላቅ ጉዳይ "የፖለቲካ ሃይሎጋ ሆ" አስመስለው ሲጫወቱበት የቆዩ፣ አሁንም ድረስ "ባገር ሽማግሌነት" ስም የሚቆምሩ የትውልድና ያገር "ችግር ቁልፍ … [Read more...] about የዕርቁ ካርድ እንዳይባክን!! የተደበቃችሁ ተገለጡ!!
እንዴት እንኑር!
… ለመሆኑ ከየት መጣን?…. ወዴት እንሄዳለን? …እንዴትስ እንኑር? የሚሉትን የፈላስፋውን ጥያቄ ስናነሳ፣ ግሪክ አገር አቴን ከተማ የዓለም ፈላስፋዎች ሰሞኑን ተሰብስበው “ስለ ዓለም ሁኔታ ይነጋገራሉ” ብለን አልገመትንም ነበር። እኛ በዚህ እትማችን ሰለ ዓለም ሳይሆን ስለ እኛው ስለ ራሳችን ችግር ነው አንዳንድ ነገሮቸን አንስተን ከግንዛቤ ውስጥ አስገብትን መለስ ብለን ለመመልከት የተነሳነው። “…እንዴት እንኑር? ” የሚለው ጥያቄ ሲሰነዘር የሚያስቆጣቸው ሰዎች እንደሌሉ ተስፋ እናደርጋለን። አንደንድ ጊዜ ከረጅም መላ-ምትና ግራ ከሚያጋቡ ጠማማ ጽንሰ-ሓሳቦች፣ ከቲዎሪ ዎች ይልቅ ቀላልና ጥሩ ጥያቄ ማቅረብ ፣ሌላውም ጎረቤት አገር ሆነ ራቅ ያሉ ሰዎች “እነሱስ እንዴት ይኖራሉ ?”ብሎ እራስን መጠየቅ ከብዙ ድካምና መነከራተት ያድናል። ግን ደግሞ ወደፊት ዘልቃችሁ እንደምታነቡት ፣ … [Read more...] about እንዴት እንኑር!
የሚፈራው መጣ!!
ኢትዮጵያችን ታማለች። ኢትዮጵያችን ተወጣጥራለች። ኢትዮጵያችን በአደገኛ መርዝ ተበክላለች። ኢትዮጵያችን ውስጧ ነፍሯል። ኢትዮጵያችን እየቃተተች ነው። ቆዳዋ ሳስቷል። የሚሰማትና የሚደርስላት ስላጣች የያዘችውን ይዛ ልትነጉድ ከጫፍ ላይ ነች። እናም ቅድሚያ ለመቀመጫ፤ ቅድሚያ ለእምዬ ኢትዮጵያ!! ማጣፊያው ሳያጥር ሁሉም መንገዱን ይመርምር!! ኢትዮጵያ በጭንቀት ጣር ውስጥ ስለመገኘቷ ማብራሪያ የሚጠይቁ ዜጎች ያሉ አይመስለንም። ምናልባት ሳያውቁ እየተፈረደባቸው ያሉ ህጻናት ካልሆኑ በስተቀር፤ ችግር ፈጣሪውም፣ የችግሩ ሁሉ ሰላባ የሆነው ህዝብ፤ ሁሉም ከበቂ በላይ መረጃ አላቸው። ኢትዮጵያ ህመሟ ወደ "ሚድን ካንሰርነት" መቀየር የሚችል ስለመሆኑ ዜጎች ያለ "ሰበር ዜና" ይረዱታል። የሚድን ስንል በቀላል አገላለጽ ችግር ፈጣሪው ኢህአዴግ፣ የኢህአዴግ ሾፌር ህወሃት፣ የህወሃት አገልጋዮች፣ … [Read more...] about የሚፈራው መጣ!!
በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው ተጀመረ!
ሙስናው ላይ የተጀመረው ዘመቻ ሙስናን በስንጥር የሚያሰኝ ቢሆንም አቶ መለስ ያልደፈሩትን ሰፈር አቶ ሃይለማርያም ነክተውታልና በኢህአዴግ ታሪክ የሙስናን ሰፈር በማንኳኳት ግንባር ቀደሙ ሰው ያደርጋቸዋል። እኛም ጅምሩ መልካም ነው እንላለን። ግን ጥያቄም ማሳሰቢያም አለን። ለማንኛውም በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው የተጀመረ ይመስለናል። በሙስና የተጠረጠሩ ነጋዴዎች፣ ደላሎች፣ አቀባባይ የተባሉና የመንግስት ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ከተሰማ ጀምሮ ህዝብ በስፋት እየተቸ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የተደላደለውን ሙስና ህዝብ ጠንቅቆ ከነባለቤቶቹ ያውቃል። ይረዳል። ያሸታል። ባለፈ ባገደመ ቁጥር ለድህነቱ ማስታገሻ ያላምጣቸዋል። ሙስና ሲባል ሙስና ነው። ወንጀል ሲባል ወንጀል ነው። ህግ መተላለፍ ያስጠይቃል። አሁን እንደሚታየው ግን የጸረ ሙስናው ዘመቻ ሰፈር የለየ ይመስላል። ዋናዎቹ … [Read more...] about በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው ተጀመረ!
ስለ አባይ ግድብ “አድርባይ” እንሁን?
ሰሞኑን ኢህአዴግ ጉባኤውን ሲጨርስ “አድርባይነት አሰጋኝ” ብሎናል። አባላቶቼ አድርባይ ሆነዋልና በዚህ ከቀጠልኩ እሰምጣለሁ የሚል ስጋት እንዳለበትም አስታውቆናል። ከፍርሃቻው ብዛት የተነሳ አድርባይነትን ለመዋጋትና “መድረክ ላይ ለመጥለፍ” በቁርጠኛነት እንታገላለን ብለው አቋማቸውን ነግረውናል። የሚገርመው ግን አድርባይነትን የፈጠረና ያነገሰው ራሱ ኢህአዴግ መሆኑን መዘንጋቱ ነው። ኢህአዴግ አድርባይ ሚዲያዎች አሉት። አድርባይ ባለሃብቶች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይ የኔቢጤዎች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይና የማደናገሪያ ፕሮጀክቶች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይ ድርጅቶች እንጂ ነጻ ድርጅቶች የሉትም። ኢህአዴግ አድርባይ ባለስልጣናት እንጂ ነጻ አመራሮች የሉትም። ሁሉም አድርባዮች ተጠሪነታቸው ለህወሃት ስለሆነ ተጠያቂውም ራሱ የኢህአዴግ ሾፌር ህወሃት እንጂ ሌሎች ሊሆኑ አይገባም። “ፈጣሪያቸው” … [Read more...] about ስለ አባይ ግድብ “አድርባይ” እንሁን?
የትግራይ ህዝብ ስማ!!
ሰሞኑን በውዴታም ይሁን በግዴታ በመቀሌ እጅግ ከፍተኛ የሚባል ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ሲጨፍሩ፣ ሲዘሉ፣ ከበሮ እየመቱ የባህላቸውን ዘፈንና ውዝዋዜ ሲያወርዱ አይተናል። ምክንያቱ በግልጽ ባይነገርም ሲደበቅ የነበረው የህወሃት ሃብትና ንብረት ውጤት የሆኑ፣ በልዩ የመንግስት ድጋፍ የተከናወኑ ግዙፍ ተቋሞች በጎዳና ለህዝብ ሲቀርቡም ተስተውሏል። ልማቱ መልካም ነው። ደስ ይለናል። ምንም ተቃውሞ የለንም። ግን መልዕክት አለን። ለማን? ምሬትን፣ ጭቆናና መንገፍገፍ ሲበዛ በፍቃደኛነት በቦንብ ላይ እንደሚያስሮጥ ለሚያውቀው የትግራይ ህዝብ!! የትግራይ ህዝብ ስማ!! ሰሞኑን ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ሪፖርት የትግራይ ክልል በትምህርት፣ በኤሌክትሪክ፣ በመንገድ፣ በእርሻ፣ በደን፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ ወዘተ ከሌሎች ክልሎች ሁሉ ርቃ መሄዷን ይፋ አድርጓል። … [Read more...] about የትግራይ ህዝብ ስማ!!
ቤት መኖሩን እንመን፤ ከዚያ እንግባ!
በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ1960ዎቹ በአሜሪካ የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጠንካራ ፉክክር የተደረገበት ነበር፡፡ ጆን ኤፍ ኬኔዲና ሪቻርድ ኒክሰን እጅግ ከፍተኛ ውድድር ካደረጉ በኋላ ኬኔዲ አሸነፉና ሥልጣኑን ተቆናጠጡ፤ ኒክሰን የሽንፈትን ጽዋ ጠጡ፡፡ ከኒክሰን ደጋፊዎች መካከል ቀዳሚ የነበረው የፊልም ተዋናይ ጆን ዌይን ነበር፡፡ የካው ቦይ ጫማውን አጥልቆ፤ ፈረሱ እየጋለበ፤ ሽጉጡ እያሽከረከረ፤ ጠላቶቹ በፊልም ይረፈርፍ የነበረው ጆን ዌይን ከሚከተለው የጸና የፖለቲካ አመለካከት አኳያ ሪቻርድ ኒክሰንን በመደገፍ ለማሸነፍ እንዲችሉ የተቻለውን እገዛ ያደረገ ነበር፡፡ ሆኖም ያሰበው አልተሳካም፤ የተመኘው መሪ ነጩ ቤተመንግሥት አልገባም፤ በሕገመንግሥቱ መሠረትም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አልሆነም፡፡ ጆን ዌይን ኬኔዲ ማሸነፋቸውን በተረዳ ጊዜ ግን አገር ወዳድነቱንና አርበኝነቱን … [Read more...] about ቤት መኖሩን እንመን፤ ከዚያ እንግባ!
ኢህአዴግ ሌላ፤ ኢትዮጵያችን ሌላ!!
ሚዲያ ከስሜታዊነት፣ ከስጋና ደም ድምር፣ ከችኩል ውሳኔና ግብታዊነት ነጻ ለመሆን ሌት ተቀን መስራት እንዳለበት ባለሙያዎች አበክረው የሚናገሩት ዓቢይ ጉዳይ ነው። ሚዲያ ስንል ደግሞ ሁሉንም ነው - የኅትመት፣ የምስል፣ የድምጽ፣ የድረገጽ፣ የዲጂታል፣ የማኅበራዊ ድረገጽ፣ … ። ሁሉም ሚዲያዎች አሻግሮ በማየት ህዝብንና አገርን የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው። ጋዜጠኞች ወይም እንደ ጋዜጠኛ የሚሠሩ ሁሉ ከየትኛውም ሙያተኛ በላይ ሃላፊነት ሊሰማቸውም ግድ ነው። ለዚህም ነው በጋዜጠኝነት ሙያ "አመጣጥን፣ አሁንም አመጣጥን፣ አሁንም አመጣጥን … “ባላንስ” አድርግ" የሚባለው!! ከኢህአዴግ ዓይነ ያወጣ ውሸትና ዝግነት የተነሳ ሁሉንም መረጃዎች የማመጣጠኑ ሙያዊ ሃላፊነት ለመወጣት ፈተና ቢያጋጥምም በከፍተኛ ደረጃ ጥንቃቄ ልንወስድባቸው የሚገባን ጉዳዮች አሉ። ከነዚህ ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋናው … [Read more...] about ኢህአዴግ ሌላ፤ ኢትዮጵያችን ሌላ!!