• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የህወሃት አውሬነት፣ ከውልደት እስከ ህልፈት? ወይስ አገር “እስክትፈርስ”?

July 2, 2016 12:11 am by Editor 6 Comments

* ይብላኝ ለእናንተ ለአውሬው ቀንድና ግምባሮች!

ፈቃደኛ ስለመሆኑ ባደባባይ ባልተጠየቀው የትግራይ ህዝብ ስም ራሱን ተገንጣይ ብሎ ሰይሞ አገር የሚገዛው ህወሃት፣ ከቀን ወደ ቀን ግፍ እየመከረ ነው። በአገር ስም እስከ አፍንጫው በታጠቀው ጠመንጃና በዘረፈው ሃብት በመተማመን በያቅጣጫው ንጹሃንን እየጨፈጨፈ ነው። እስር ቤት አጉሮ  እያሰቃየ ነው። ያልፈጸመውና የማይፈጽመው ሰቆቃ የለም። ህጻን፣ አዋቂ፣ አዛውንት፣ እናት፣ አባት ሳይመርጥ የጥይት አረሩን እያወረደ በያይነቱ ደም እየተጋተ ነው። ቂም እየከመረ ነው። ከቀን ወደ ቀን ደምና ግፍ የሚበቃው አይመስልም። ወዳጆቹም ሆኑ በስማቸው የሚነገድባቸውም ተው ሲሉት አይሰሙም። ምን ይሁን? ይህ አውሬነት እስከመቼ ይቀጥላል?

“በጉልበት ትግሬ ተደረግን እንጂ ፍጥረታችን ትግሬ አይደለም” ያሉ ይገደላሉ፣ ይታፈናሉ፣ ይገረፋሉ፣ እርሻቸው ይነጠቃል፣ ከመኖሪያቸው ይፈናቀላሉ። “መሬታችን ለምን ይወሰደብናል” ያሉ የኦሮሞ ልጆች በጅምላ ይፈጃሉ። በጅምላ ታፍነው አሰቃቂ ሥቃይ ይደርስባቸዋል። ታፍነው የደረሱበት የማይታወቀውን ቤትና ወላድ ይቁጠራቸው፣ የጋምቤላን ለም ምድር ለመቸብቸብ ሲባል ምንም የማያውቁ ወገኖች ተፈጁ፣ ታሰሩ፣ ተፈናቀሉ፣ ኦጋዴን ውስጥ የተፈጸመው ለሰሚው ግራ የሚያጋባ ነው። አንድ ምስኪን እናትን አራት ቀን አስከሬን አሳቅፎ ማሰቃየት ምን ማለት ነው? ከዚህ በላይ አውሬነት ምን አለ?

በያቅጣጫው የሚሰማው ለቀሶ ነው። እመጫትን በዶፍ ዝናብ ከቤት አውጥቶ መጣል ምን ማለት ነው? ህጻናትን እየገደሉ ከራባት አንጠልጥሎ አፍ መክፈትና “ጅኒ” ብሎ መዘበት በምን መስፈርት ልክ ይሆናል? እስኪ አፍቃሪ ህወሃቶች ረጋ በሉና አስቡ። በኦሮሚያ የሚሆነውና የሆነው፣ አማራ ክልል እየተደረገ ያለው፣ ኦጋዴን የሚፈጸመወና የሚፈጸመው፣ በደቡብ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የሚታየውና የሚሰማው ግፍና በየአቅጣጫው የሚሰማው የእናቶች እንባ እንዴት እርካታ ይሰጣችኋል? እንዴት ደረታችሁን ያስነፋችኋል? ይህ ሁሉ በናንተ ቤተሰቦች ላይ ቢደርስ ትወዳላችሁ? ስለምን አውሬነትን ታበረታታላችሁ? ስለምንስ ግፍ በሚፈጸምባቸው ወገኖቻችሁ ላይ ትሳለቃላችሁ? ህወሃት ነጻ ያወጣችሁ ዘንድ ፍላጎታችሁ ከሆነ ሁሉ በጃችሁ ነውና ደሃውን ህዝብ ልቀቁት!! ሂዱ። አለያ ደግሞ ድሆች ሲገደሉ፣ ሲታሰሩ፣ ሲታፈኑና ለሥቃይ ግፍ ሲዳረጉ በግልጽ፤ በገሃድ፤ በአደባባይ ተቃወሙ። ፍትህን እመኑባት!!

ከቀን ወደ ቀን እየሆነ ያለው ሁሉ የሚዘገንን ነው። የሚቀፍ ነው። ብልሆች ሲናገሩ “ውሻን ወደ ቁልቁለት አታባር፣ ሲዞር ዳገት ይሆንብሃል” ይላሉ። አዎ! ዛሬ ህወሃት ዳገት ላይ ነው። ዳገት ላይ ሆኖ የሚድኽውን፣ የሚራመደውን፣ የሚሮጠውን፣ ደካማውን፣ ህጻናትን፣ ሁሉን በጅምላ እየነዳ ነው። እየደፋ ነው። ከድንቁርና ጋር የተቀላቀለ ጥጋብና ትዕቢት አሳውሮታል። ተግባሩ ስለሚያስደነብረው ተቃውሞን አይወድም። ካልተቃውሙት ወደብ ይሸልማል። አገር ቆረሶ ይሰጣል/ይሸጣል። ሰዎች ለመብታቸው ሲነሱ መልሱ የምናየው ነው። አውሬነት ነው። በዚህ አውሬነቱ ህወሃት በደም ተጫማልቋል። የደም እዳ በዝቶበታል። አውሬነቱ ማብቂያ የሌለው ህወሃት ሰሞኑን በአቶ ሃብታሙ ላይ የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው ተግባሩ ይህንኑ አውሬነቱን ያረጋገጠ ይሆናል።

አቶ ሃብታሙ ህወሃት አጥብቆ የሚጠላው ወጣት ፖለቲከኛ ነው። በፈጠራ ክስ አሰረው። እስር ቤት አማቅቆ፣ አሰቃይቶ በመጨረሻ “ነጻ” አለው። ተመልሶ ይግባኝ ተጠየቀበት። ከዛም ይግባኙ እንዳለ ሆኖ ተፈታ። አሁን ስለሚያሰቃየው ህመም ለህብር ሬዲዮ ሲያስረዳ ታሪኩ የሚያስለቅስ ነበር። አንድ መጸዳጃ በሌለበት ክፍል ውስጥ እንዴት ያሳልፍ እንደነበር እዚህ መዘርዘሩ ባያስፈልግም ህሊና ላላቸው ሁሉ /ከአውሬዎች በቀር/ የሚያም ነው። እንግዲህ ራሱ ህወሃት በፍርድ ቤት በኩል እንዳመነው አቶ ሃብታሙ የታሰረው ያለ በቂ ማስረጃ ነበር። አፍቃሪ ህወሃቶች እስቲ አስቡት! አቶ ሃብታሙ አያሳዝንም?! ይህ ሁሉ ሳያንሰው ታይላንድ ወይም ሌላ አገር ሄዶ የመታከም መብቱ ሲገፈፍ … ሰውየው ቀብር ሄዶ ሲያለቀስ “ባክህ በቃህ” ሲሉት “ተዉኝ ለራሴ ነው የማለቅሰው” አለ እንዲሉ፣ ነግ በእኔ ነውና እንዲህ ያለ አውሬነትን መቃወም ግድ ነው።

ጎልጉል አቶ መለስ ሲሞቱ ከበሮ አልመታችም። እንደ ሰው ሞታቸው አሳዝኖናል። ነገር ግን በሰሩት የአውሬ ተግባር ህግ ፊት እንዲቀርቡ እንመኝ ስለነበር ፍርድን በሞት ማምለጣቸው አናድዶናል። እንደ ዝግጅት ክፍላችን እምነት መለስን ማስነሳት የሚቻል ቢሆን ትውልድ ሁሉ እንዲማርበት ፍትሕ ሲበይንባቸው እንዲያይ ከሞቱበት ይነሱ ዘንድ የሚፈለገውን ሁሉ እናደርግ ነበር።

እናም አቶ ሃብታሙ ዶላር አልጠየ፣ አሳከሙኝ አላለ፣ ሃኪም ቢያዝ ባያዝ፤ ቢፈቅድ ባይፈቅድ ውጪ ሃገር ሄዶ መታከም ከፈለገ እንዴት ይከለከላል? አሁን ይህንን አውሬነት አዳንቆና አወድሶ በየማህበራዊው ሚዲያዎች ማቅረብ ምን ይባላል? ያሳፍራል! ያሳዝናል! ወይስ የተፈራ ሌላ ነገር አለ? የእስሩ ግፍ ያደረሰበት የበሽታ ጉዳት እና መጠኑ ውጪ ሲወጣ በባለሙያዎች ያለጥርጥር እንዳይጋለጥ ተፈርቶ ይሆን?

ህወሃት ውስጥ የተካተቱ የሚስቶቻቸው ጥርስ ለማስሞላት፣ ልጆቻቸው ለሽርሽርና ለቶንሲል የውጪ ህክምና ተጠቃሚዎች በሆኑባት አገር … ባለስልጣናት ለወሲብ በሳምንት ሁለቴ የሚመላለሱባት ታይላንድ ብርቅ ሆና ህይወትን ለማዳን ደጇ ሲዘጋ … እንተወው!! ለሁሉም ህወሃት ተፈጥሮ ብዙም ሳይቆይ አውሬዎቹ መሪ ሆነው የወገኖቹን ደም እየጠጣ ተጓዘ። ተጉዞም እዚህ ደረሰ። አሁን በያዘው አኳኋን ደም የሚጠግብ አይመስልም። አውሬነቱንም እስከ ህልፈት ብሎ ምሏል። ወይም እሱ እንደሚመኘውና ሁሌም እንደሚያስፈራራው ኤርትራ ላይ መንግስት ለጥፎ ኢትዮጵያን እስኪያፈርስ በዚሁ አውሬነቱ ይቀጥላል። የሚያሳዝነው የአውሬ ቀንድና ሾከና ሆነው የሚያገለግሎት ባንዳዎች ናቸው። ለፍርፋሪ ተገዝተው አብሮ አደጋቸውን የሚያሳደዱት ከሃዲዎች። እኚህ ባንዳዎች ሲጣሉ የአውሬው ፈርስና እዳሪ መሆናቸውን እያዩ አለማመናቸው ይገረማል!! አዋቂዎች ሲያዝኑ “ይብላኝ ለእናንተ” እንዲሉ!!

ሕዝብን ሁልጊዜ ቁልቁለት እያባረሩ መግዛት አይቻልም፤ ሕዝብ ፊቱን ያዞረ ቀን፤ ቁልቁለቱ ዳገት ሲሆን፤ ተሳዳጁ አሳዳጅ ሲሆን፤ … ማን ይታደግ ይሆን?!


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ®” አቋም ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. gud says

    July 5, 2016 06:52 pm at 6:52 pm

    Answer from pro TPLF

    Is golgul a media or a political organization ?

    Ethiopia is a country of 100000000 people . Any
    Disturbance here and there is in avoidable .

    Finally , I urge Golgul to act as media !

    Reply
    • Editor says

      July 6, 2016 03:37 am at 3:37 am

      It depends how you define it. We are observing what you are posting for almost everything we are publishing. Unlike the the “terrorist organization” that you are tittle-tattling, scribbling and crying for daily, you have been given freedom to post what you believe on our media outlet. This defines who we are.

      Thanks for your “urge” but please pass that to the TPLF – because in the TPLF controlled Ethiopia neither the media nor political organizations practically function.

      And we “urge” you not to reply to this post.

      Editor

      Reply
  2. gud says

    July 5, 2016 06:53 pm at 6:53 pm

    Answer to your last paragraph

    Did u forget that no one was with us when we were butchered with your dada , and grand dada ?

    Reply
  3. gud says

    July 6, 2016 04:14 pm at 4:14 pm

    Editor
    Thanks for your reply .

    Please re visit your posts and you will learn how blind haters you r !

    You r no use for the current and future ethiopia .

    Reply
  4. Kebede says

    July 7, 2016 07:33 pm at 7:33 pm

    Nothing impressive. .like derg propoganda

    Reply
  5. Deribsa says

    July 8, 2016 08:01 am at 8:01 am

    Yap, they are fascists. I can explain why they have to be fascists for those tplfits. They are working towards their objective and any means is justifiable as long as it helps them to win. The Amhara, Oromo …. foot soldiers? you are practically burning your house while your children and family members are inside. When are you going to get it? How long do you think you can live in this world?
    How come you end up doing the dirty work for tplf? You are a disgrace to your family and community. To die clean is as great as to live with dignity. are you gonna to die as a foot soldier of this lowlife fascists? Think again!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule