• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ማክሰምና መሰንጠቅ – ባንዳና ባርነት

January 30, 2015 01:00 pm by Editor 2 Comments

ህወሃት በዘረፈውና በሚዘርፈው ሃብት ተጠቅሞ ለወዳጆቹ የሚያኮራ፣ ትውልድ ለሚላቸው የሚበጅ ተግባራት እያከናወነ እንደሆነ ይነግረናል፤ ይነግሩናል። ውስን ባለሥልጣናትና አበሮቻችው በሃብት ተመንድገዋል። በንዋይ ሰከረው የሚያደርጉት እስኪጠፋቸው ናጥጠዋል። የት ጋር አንደሚያበቃ ባይታወቅም፣ የተደሰቱ፣ የተከፉ፣ የተናቁ፣ የተሰረቁ፣ የሚሰረቁ፣ እየሰረቁ ያሉ፣ የተትረፈረፈላቸው፣ በስማቸው የሚነገድባቸው፣ ባሪያዎችና ባንዳዎች፣ ቀን የሚጠብቁ፣ ጥርሳቸውን የነከሱ፣ … ወዘተ “አብረው” አሉ፡፡

ዘመን፣ ወራትና ቀናት ቅዠትን በመሰሉበት ዓለም፣ ቁራሽ ለሚሞላው ከርስ ራሳቸውንና ማንነታቸውን፣ ከዚያም አልፎ የትም የማይደበቁትን ኅሊናቸውን ያቆሸሹ፣ የአገር “እንግዴ ልጆች” ወይም “ውርጃዎች” ለህወሃት የማከሰምና የመግደል ሴራ ተላላኪ ሆነው የህዝብን ክብር ሰልበው ረክሰው ያረከሳሉ። ከዚህም በላይ ነገ እንደ ውዳቂ ላንቲካ መጣላቸውን እያወቁ፣ አሽከርነት፣ ከሃዲነት፣ ውርደት፣ መለያቸው እንዲሆን መርጠው ተሳቅቀው ይኖራሉ። እነሱን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባመነበት መንገድ እንዲጓዝ ለመታገል የሚውተረተሩትን ተኩላ ሆነው ያስበሏቸዋል።

ቅንጅትን በሉት። ቅንጅትን አሳረዱት። ተቀራመቱተ። የውስጥ ችግሩ እንዳለ ሆኖ እነርሱ ግን ዕጣ መድበው ተጣጣሉብት። አየለ ጫሚሶና ባልደረቦቻቸው “የክህደት ዋንጫ” ተሞላላቸው። ከዚያም ተጣሉ።

አሁን “ምርጫ” ደርሷል፤ ድንጋጤ ጨምሯል፤ የሕዝብ ሱናሚ አስፈርቷል፤ የህንጻውና የመንገዱ ሁኔታ አልበቃም፤ የሰዉ ህይወት ከመቅለሉ የተነሳ ለሚዛን አልበቃ ባለበት አገር ህይወቱ “በቀላል ባቡር ሊቀልል” ሽር ጉድ ይባላል፤ “ሥራ ላይ ነን፤ ምርጫ ደርሷላ”፤ አስተናጋጇ ህወሃት በለመደችው መንገድ ልታባብል ብዙ ትጥራለች፤ በየማዕዘኑም እያደባች ነው፤ እስከ “ምርጫ” ቤቷን አሳምራ ቄጠማ ጎዝጉዛ፣ ፈንዲሻ ነስንሳ፣ ዕጣኗን አጫጭሳ “እንኮምር” እያለች ነው፡፡ ግን አልበቃትም፤ አላመነችም፤ ተጠራጥራለች፤ ተጨንቃለች፤ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በተለይም አንድነትን ለማጥፋት “ቡና ጠጡ” በማለት የሚላላኩላት የቦርዱ “ምሁራን” ላይ ታች እያሉ ነው። ኃላፊው ለምን ይህንን የተላላኪነት ሥራ እንደፈለጉት ባይታወቁም የቦርዱ አሽከርካሪ ምክትላቸው ግን “የዜግነት” ድርሻውን እየተወጣ ነው፡፡ “ለወገን ደራሹ ወገን” አይደል የሚባለው! ስለዚህ ህወሃት የሰፈረውን “የሚያገለማ ጽዋ” ለመጋት ርኩቻው ደርቷል። ፕሮፌሰርነት ከሚሰጠው ክብር ይልቅ “ተላላኪነት” ኩራት ሆነ!

ሶስት ዓይነት ባርነት

በአገራችን ሶስት ዓይነት ባርነት እንዳለ ይነገራል፡፡ የእነዚህ ባሪያዎች (ባንዶች) ማንነት ገፍቶ የሚወጣው “ምርጫ” በደረሰ ጊዜ ነው፡፡ አንደኛውና የመጀመሪያው ባሪያ “ምርጫ ቦርድ” የሚባለውና ሌሎች መሰል “የተቋም ባሮች” ናቸው፡፡ ሁለተኛው ባሪያ ምርጫ ቦርድን እና ተመሳሳይ ተቋማትን የሚመሩ አመራሮች ናቸው፡፡ ሦስተኞቹ ባሮች ደግሞ ህዝባቸውን ለንዋይ ሲሉ የሚሸጡ አገልጋዮች ናቸው፡፡ በሌላ ቋንቋ ህወሃት የጠፈጠፋቸው፣ ያቦካቸው፣ የሚነዳቸው፣ ሲፈልግ አዋርዶ የሚያባርራቸው ናቸው፡፡ የዘመንና የትውልድ ሁሉ ተጠያቂ ባንዳዎች!

ሰሞኑን ምርጫ ቦርድ የባርነቱን ዘመን ለማራዘም በለመደ እጁ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ላይ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ጡጫ ለማሳረፍ፣ ለመሰንጠቅ፣ ለማክሰምና ለማፍረስ ደፋ ቀና እያለ ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል ቅንጅትን በማፍረስ ታማኝ ሎሌነቱን እንዳስመሰከረ ሁሉ አሁንም ለህዝብ የእንግዴ ልጅነቱን ለህወሃት/ኢህአዴግ ደግሞ ታማኝ አሽከርነቱን ለማረጋገጥ እየተባ ይገኛል፡፡

እኛም እንደ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የባንዳዎችን ጥርቅም እናወግዛለን፡፡ ታሪክና ትውልድም ይህንን እንዳይረሱት እናሳስባለን፤ እንመዘግባለን፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ የሚዘርፉትን፣ እየዘረፉ ያሉትን፣ የተዘረፉትን፣ እየተዘረፉ ያሉትን፣ ዘርፈው የሚያደርጉት የጠፋባቸውን፣ በሃብት የናወዙትን፣ በደም የተጨማለቁትን፣ የራባቸውን፣ ምርጫ ቦርድን፣ የኢህአዴግን ሎሌዎች፣ አሽከሮች፣ ሁሉ ይዛ እየነጎደች ነው፡፡ የጥጋቡም የግፉም ማብቂያ መቼ እንደሆነ ባይታወቅም የከፋቸውና ጥርሳቸውን የነከሱ እንዳሉ ከበቂ በላይ ማስረጃ አለን፡፡ ንጹህ አገር ወዳዶችና እኛም ጎልጉሎች ያንን ቀን አንናፍቀውም፡፡ ባንዶች ግን ይህንን ቀን የማስቀረት አቅም አላችሁና ወደ ኅሊናችሁ ተመለሱ፡፡ ህዝብ ይምረጣቸው ወይም ይጥላቸው አንድነትንም ሆነ ሌሎቹን የተቀናቃኝ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ከራሳቸው ችግር ጋር ለህዝብ ውሳኔ ብትተዋቸው ይሻል ነበር፡፡ ነገርግን ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ እናንተም ዳግመኛ ባንዳነታችሁን አስመሰከራችሁ፤ ባርነታችሁንም ቀጠላችሁበት፡፡


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ®” አቋም ነው፡፡

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. helen geta says

    January 30, 2015 03:41 pm at 3:41 pm

    የኢት/ያ ህዝብ የሚፈልገው ከድህነት የሚያወጣው ኑሮውን የሚያሻሽልለት መንግስት ነው የሚፈልገው።እነሱም ይደጉ ሁሉም ይደግ ነገር ግን ወያኔ ብቻ አይደለም እየዘረፈ ያለው በሁሉም ክልል ካዲሪ የተባለ በሙሉ እየዘረፉ ነው።መቃወም ያለብን ፓሊሲው ላይ ነው።የማይጠቅም ዘረኝነት የተሞላ በመሆኑ፡ማንንም አይጠቅምም።

    Reply
  2. Tena says

    February 2, 2015 02:10 pm at 2:10 pm

    Leming anchim kililch hedesh atzerfim? Yeleloch bher bhereseboch hager mebezbez diro qere. Siamrbsh yqeral.
    Zeregnoch melisewu yezeregninet selabwochn zeregna silu yamal! Le’Ethiopia bhereseboch zarem bihon yeteleyaye yezeregn’net sim auchiwu man honena? amarawu aydel?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule