• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አንድነትን “እናኝከዋለን፤ እንገድለዋለን” – ምርጫ ቦርድ

January 30, 2015 01:13 pm by Editor 3 Comments

የዛሬ አስር ዓመት “የሕዝብ ሱናሚ” እያለ ሲምል ሲገዘት የነበረው ህወሃት ሱናሚው ወደ እርሱ እየጎረፈ ሲመጣ በረገገ፡፡ መፍትሔ በጠብመንጃ አፈሙዝና በብረት ብቻ እንደሆነ የሚያምነው ህወሃት በረሃ የለመደውን በትሩን አነሳ፤ ንጹሃንን ጨፈጨፈ፤ ደም አፈሰሰ፤ ኢትዮጵያን ወደ እስርቤትነት ቀየራት፡፡ ትዕዛዙን በቀጥታ የሰጡት “ባለራዕዩ” ለፍርድ ሳይቀርቡ “እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” ያሉትን ሰፊውን ሕዝብ ሳይጨርሱት እንደ ክዳን ቆርኪ ተስፈነጠሩት፤ ላይመለሱ ሄዱ፡፡

የዛሬ አስር ዓመት የቅንጅት አካሄድ ያስፈራው ህወሃት ጉዳዩን ለራሱ ለፓርቲውና ለሕዝብ ከመስጠት ይልቅ ደም መቃባት ውስጥ ገባ፡፡ ፓርቲው የነበረበት የውስጥ ችግር እንዳለ ሆኖ የፈሪ በትር የዘረጋው ህወሃት የገደለውን ገድሎ ከጨረሰ እና የኢትዮጵያን መሬት በደምና በእናቶች እምባ እንደገና ካጨቀየ በኋላ ቅንጅትን የማፍረስ ተግባሩን በዕቅድ ይዞ በይፋ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ግምባር ቀደም ተሰላፊው የተቋም ባንዳ “ምርጫ ቦርድን”፤ በግለሰብ ደረጃ ደግሞ በተለይ ሁለት ግለሰቦችን አሰለፈ፡፡ ዘመቻ “ቅንጅትን መግደል” ተጀመረ፡፡

በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ምንም በማያሻማ ሁኔታ በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዶናልድ ያማሞቶ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ስቴት ዲፓርትመንት) ለሚገኙት አለቆቻቸው “THE ETHIOPIAN GOVERNMENT CHEWS THE CUD” (የኢትዮጵያ መንግሥት ቅንጅትን አኘከው) በሚል ርዕስ የጻፉት እንዲህ ይነበባል፤

Over the course of the week of January 7, the National Electoral Board of Ethiopia (NEB) hammered what appear to be the final nails in the coffin of the opposition Coalition for Unity and Democracy (CUD) party. Since their surprise showing in the 2005 elections, gaining enough seats to become the second largest political party in Ethiopia, the CUD has virtually disintegrated as a result of internal power struggles and interference from the Ethiopian Government (GoE). In the latest setback, the NEB awarded the famous victory sign — the CUD symbol widely recognized by voters — to former ally turned foe, Lidetu Ayalew of the United Ethiopian Democratic Party-Medhin (UEDP-Medhin).  The NEB followed this later in the week by finally awarding registration of the reformed Coalition for Unity and Democracy Party (CUDP) party name to yet another former CUD ally turned foe Addis Ababa city council member-elect Ayele Chamisso.  Though Ayele, who is broadly viewed as having been co-opt by the GoE, has invited all faction of the former CUD to join his party, few will likely take his offer.

In a meeting with Ambassador on January 11, NEB board chairman Dr. Merga Bekana and vice-chairman Dr. Addisu Gebre-Egziabhier said that the Board still had not decided on the CUDP’s registration and would continue to consider the matter in coming weeks. Almost immediately following the meeting, however, the NEB publicly announced that it had decided that morning to award the party license to Ayele. This followed their controversial decision earlier in the week to give the CUD’s famous victory symbol to the CUD’s despised adversary Lidetu Ayalew (another person believed to have been co-opted by the GoE during the CUD’s post-2005 election struggles), and his UEDP-Medhin party.

The opposition fiercely accused the NEB of being under the influence of the GoE and of delivering votes to the ruling Ethiopian Peoples Revolutionary Democratic Forces (EPRDF) party after the opposition’s surprisingly strong showing. Since then, a new Board has been put in place, but the opposition have not altered their criticism. The NEB’s recent decisions to award the CUD party symbol and name to politicians, who are at best undeserved and at worst proxies of the GoE, has done much to reignite lingering suspicions regarding the NEB’s independence. As if to prove these suspicions, NEB vice-chairman Dr. Addisu (a Tigrayan political scientist widely believed to be the “enforcer” at the NEB) recently commented to USAID’s Senior Democracy Advisor — a former Stanford University Political Science Professor ) (strictly protect) that the NEB had decided to “kill the CUD.” The NEB decisions of the last week have effectively done exactly that.

ትርጉም

በጃኑዋሪ 7 ሳምንት ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ (ቅንጅት) ፓርቲ የሬሣ ሳጥን ላይ የመጨረሻ የሚባለውን ሚስማር መትቷል፡፡ በ2005 (1997) ምርጫ በአገሪቱ ሁለተኛው ትልቁ የተቃዋሚ ፓርቲ ለመሆን የሚያስችለውን አስደናቂ ድልና በቂ መቀመጫ ካገኘ በኋላ ቅንጅት በውስጡ በነበረው የኃይል (የሥልጣን) ሽኩቻና ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ይደርስበት በነበረው ጣልቃ ገብነት ምክንያት አለሁ ቢልም እየተፈረካከሰ ነበር፡፡ በቅርቡ በተደቀነበት ሌላ ደንቃራ ደግሞ ምርጫ ቦርድ ዝነኛውንና በብዙሃን መራጭ ዘንድ ዕውቅና የነበረውን የቅንጅትን (V) ምልክት ቀድሞ (የቅንጅት) ወዳጅ በኋላ ጠላት ለሆነው የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ፓርቲ – ኢዴፓ-መድህን ልደቱ አያሌው ሸልሞታል፡፡ በመቀጠልም ምርጫ ቦርድ ይህንን ተከትሎ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የስም ምዝገባ ቀድሞ የቅንጅት ወዳጅ በኋላ ጠላት ለሆነው የአዲስ አበባ ምክርቤት እጩ ተመራጭ አየለ ጫሚሶ ሸልሞታል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ቅጥረኛ እንደሆነ በሰፊው የሚታመነው አየለ ጫሚሶ ከቀድሞው ቅንጅት ተሸራርፈው ለወጡት ሁሉ የእርሱን ፓርቲ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቢደርግም ጥቂቶች ብቻ ጥሪውን ይቀበላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ . . .

addisu  g of neb
አዲሱ ገብረእግዚአብሔር

የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር መርጋ በቃና እና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ከአምባሳደሩ (ያማሞቶ) ጋር ጃኑዋሪ 11 ቀን ባደረጉት ስብሰባ የቅንጅትን ምዝገባ በተመለከተ ገና ውሳኔ ላይ እንዳልደረሱ እና በመጪዎቹ ሳምንታት ጉዳዩን እንደሚመለከቱት ነበር የተናገሩት፡፡ ነገር ግን ወዲያውኑ ስብሰባው እንዳበቃ ማለት ይቻላል የዚያኑ ቀን ጠዋት የቅንጅትን የስም ምዝገባ ለአየለ ለመስጠት መወሰኑን ምርጫ ቦርድ ለሕዝብ ይፋ አደረገ፡፡ ይህ የቦርዱ ውሳኔ በሳምንቱ መጀመሪያ አካባቢ የቅንጅትን ዝነኛ (V) ምልክት በቅንጅቶች ለተናቀውና የፓርቲው ጠላት ለሆነው ልደቱ አያሌውና ለኢዴፓ-መድህን ፓርቲው ለመሸለም የተደረገውን አከራካሪ ውሳኔ ተከትሎ ነው፡፡ (ልደቱ አያሌው ከምርጫ 1997 በኋላ ቅንጅት ውስጥ በነበረው ትግል ውስጥ በኢትዮጵያ መንግሥት የተመደበ ሌላው ቅጥረኛ እንደሆነ ይታመናል)፡፡ . . .

ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ መንግሥት ሥር እንደሆነ እና ተቃዋሚዎች አስገራሚ ውጤት በምርጫው ላይ ካሳዩ በኋላ (የመራጮችን) ድምጽ ለኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢህአዴግ) እንዳስረከበ ተቃዋሚ (ፓርቲዎች) አጥብቀው ይከስሳሉ፡፡ ከዚያ ወዲህ አዲስ ቦርድ የተሰየመ ቢሆንም ተቃዋሚዎች ግን አሁንም ትችታቸውን አላቆሙም፡፡ የቅንጅትን ስም እና ምልክት ፍጹም ለማይገባቸውና ለኢትዮጵያ መንግሥት የቅርብ ወዳጆች ለሆኑት ፖለቲከኞች ማስረከቡ ምርጫ ቦርድ ከአድልዎ የነጻ አለመሆኑ ላይ ያሉትን ጥርጣሬዎች እንደገና እንዲቀጣጠል አድርጓል፡፡ የምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር አዲሱ በቅርቡ ለዩኤስኤይድ ከፍተኛ የዴሞክራሲ አማካሪና የቀድሞ የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር (ስሙ እንዳይወጣ በጥብቅ የተከለከለ) ምርጫ ቦርድ “ቅንጅትን ለመግደል” ወስኖ እንደነበር መናገሩ እነዚህን ጥርጣሬዎች እርግጠኛ ያደርጋቸዋል፡፡ (የአዲግራት ተወላጅ የሆነው) (ዶ/ር አዲሱ የትግሬ የፖለቲካ ሳይቲስት ሲሆን የምርጫ ቦርድ “ፈጣሪና አድራጊ” እንደሆነ በሰፊው ይታመናል)፡፡ ባለፈው ሳምንት ምርጫ ቦርድ የወሰደው ውሳኔ (የቅንጅትን ስምና ምልክት ለቅጥረኞቹ መስጠቱ) ይህንኑ (ቅንጅትን የመግደሉን ዕቅድ) የሚያረጋግጥ ነው፡፡ . . . (ሹልክዓምድ (ዊኪሊክስ) ላይ የወጣውን ሙሉ መረጃ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

አሁንስ ማነው ባለሳምንት? በዚህኛው የምርጫ ድራማ አየለ ጫሚሶን የሚጫወተው ትዕግስቱ አወል እንደሆነ ይፋ ሆኗል፤ ልደቱንስ ማን ይተውነዋል?

ከዚህ በፊት በሰማያዊና በሌሎች ፓርቲዎች ላይ የደረሰውና አሁንም እየደረሰ ያለው እንዲሁም ሰሞኑን በአንድነት ፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ላይ የደረሰው ሰቆቃ የዘንድሮውን ሁኔታ የተለየ እያደረገው እንደሆነ ጎልጉል ከተለያዩ ምንጮች የሚደርሱት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ስለዚህም ነው “ምርጫ ቦርድ” ቅንጅትን በዕቅድ እንደገደለው አሁንም አንድነትንና ሌሎቹን ተቀናቃኞች “አኝኮ ለመግደል” ውሳኔው የሆነው፡፡

ከሕዝብ በኩል የሚሰማው የሰላማዊ ትግል ቁርጠኝነት ግን የህወሃትን የልመና ኮሮጆ በሚሞሉት ምዕራባውያንም ዘንድ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው እንደሆነ ጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ሰልፍ በተካሄደበት ወቅት በተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች ላይ ተሰራጭቶ ያገኘነውን መረጃ መጥቀሱ የቁርጠኝነቱን መጠን በተወሰነ መልኩ የሚያመለክት ነው፡፡ “በዕለቱ የደረሰበትን ጉዳት አስመልክቶ ለቢቢኤን ሬዲዮ የተናገረው የአዲስ አበባ ወጣቶች ጉዳይ አንድነት ፓርቲ ኃላፊ ስንታየሁ ቁስሉ ሳይደርቅ በወኔ እንዲህ ነበር ያለው “ወያኔ ላጠፋው ጥፋት የሚያወራርደው ሒሳብ እንዳለ ማወቅ አለበት፡፡ ለትግላችን እንሰዋለን፤ በዋዛ አንላቀቅም”፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. እምሩ ዘለቀ says

    January 30, 2015 07:42 pm at 7:42 pm

    ተቃዋሚ ድርጅት በሹመት ሆኗል፤
    አገዛዙን የሚገድፉት ምዕራባዊ መንግሥታት ዴሞክራሲ የሚሉት ለአፍሪካ ልዩ ትርጉም ተሰጥቶታል።
    ዞሮ ዞሮ ቀልዱ በኛው ላይ ሆኗል፤ መቼ ይሆን ሲወጉንም ሲረግጡንም ስያፌዙብንም የሚሰማን፧
    ሲለምርጫዉም ዉጤት ምን እንደሚሆን የጻፍኩት ነበር ብታነቡት መልካም ነው።
    ለብቻዉ እለከዋከሁ።

    Reply
    • Editor says

      January 31, 2015 03:29 am at 3:29 am

      It is published here.

      Thank you,

      አርታኢ/Editor
      ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
      http://www.goolgule.com
      editor@goolgule.com

      Reply
  2. Terminator says

    February 1, 2015 04:03 am at 4:03 am

    We don’t Have to expect a different results from pigs and rodents ,if we do then we are like them ,the best solution to eradicating wild pigs and rodents is kill them properly forever.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule