• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“መሰበር” የማይቀር ነው

July 26, 2014 04:24 am by Editor Leave a Comment

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ “በድርብ አኻዝ አድጓል፤ እያደገም ይሄዳል፣ ይቀጥላል፣ ይመነደጋል” እየተባለ “በተዘመረበት” ዓመታት ሁሉ በአንጻሩ በገሃድ ያለውን እውነታ ቁልጭ ባለ መልኩ የሚያሳዩ ዘገባዎች ሲወጡ ቆይተዋል፤ እየወጡም ይገኛል፡፡ ሆኖም እነዚህ ዘገባዎች በሥልጣን ላይ ያሉትን ሁለቴ እንዲያስቡ ሊያደርጋቸው እንደሚገባ ቢነገርም ምላሹ የተለመደው “የልማት ጸሮች” ያወጡት፣ “የአሸባሪዎች እጅ ያለበት”፣ “የኒዎ-ሊበራል አቀንቃኞች ዘገባ”፣ “የኪራይ ሰብሳቢዎች ምኞት”፣ ወዘተ ከሚል አልፎ አያውቅም።

በተደጋጋሚ የሚወጡ ዓለምአቀፋዊ መረጃዎች አገራችን በመክሸፍ ወይም በመሰበር አደጋ ላይ እንደምትገኝ ይናገራሉ። እነዚህ ጥናቶች በአብዛኛው የሚወጡት በምዕራቡ ዓለም በሚገኙ የጥናት ተቋማት በመሆናቸው ከላይ እንዳልነው “የወገኑ ናቸው”፣ “የልማታችንና የህዳሴያችን ተቃዋሚዎች ናቸው”፣ “ሚዛናዊ አይደሉም”፣ “የምዕራባዊያን ምኞት ማስፈጸሚያ”፣… ሲባልባቸው ቆይቷል። ኢህአዴግ ለዚህ ዓይነቱ ፍረጃ ቀዳሚነቱን በመውሰድ ከድቃይ የሚዲያ ተቋማቱ በተጨማሪ በተለይ “በአዲስ ራዕይ” ሲያብጠለጥላቸው በየደረጃው ያለው ካድሬ ደግሞ እንደ ገደል ማሚቶ ማስተጋባቱን ይቀጥላል።

የሚሰማው ኖረም አልኖረ የማስጠንቀቂያው ዘገባ አያቆምም ማስጠንቀቁን ይቀጥላል! ጥቂቶቹ ይህንን ይመስላሉ፡-

የዛሬ አንድ ዓመት ተኩል አካባቢ “የአሜሪካ የብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2030 የሚከሽፉ 15 መንግሥታትን (failed states) ዝርዝር” አውጥቶ ነበር። “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” ይከሽፋሉ ተብለው ከተተነበዩት የአፍሪካ፣ የእስያና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ተናግሮ ነበር። (ጎልጉል ያጠናከረው ሙሉ ዘገባ እዚህ ላይ ይገኛል)።

የዛሬ ዓመት አካባቢ “ዓለምአቀፉ የግልጽነት ድርጅት (Transparency International) በርካታ የአፍሪካ አገራት በሙስና “መበስበሳቸውን” ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ አገራት መካከል እንደምትገኝ” ዘግቦ ነበር። “በዚህ ዘገባ መሠረት በሙስና የተዘፈቁትን አገራት በመከፋፈል ባስቀመጠው ባለዘጠኝ መዘርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ከመጨረሻ ሁለተኛ መሆኗን በመግለጽ ከፍተኛ የሙስና አደጋ ውስጥ ከሚገኙ አገራት ዋንኛዋ አድርጓታል። ለዘገባው ግብዓት እንዲሆን ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል “ጉቦ ሰጥተዋል ወይ (ያውቃል)?” በማለት ለአንድ ሺህ ሰዎች ለቀረበው የናሙና ጥያቄ 44በመቶ ኢትዮጵያውያን “አዎን” በማለት መልሰዋል። ይህ የምዕራባዊ ድርጅት ዘገባ ቢሆንም “ውርሳቸውን እናስጠበቃለን” የሚባሉት ሟቹ መለስ፤ በረሃ በነጻአውጪነት፤ ከዚያም “በመንግሥትነት” ራሳቸው ስለመሩት ድርጅት የተናገሩትን የሚያረጋግጥ ነው። እንዲህ ነበር ያሉት “ከእንጥላችን ገምተናል”! (ጎልጉል ያጠናከረው ሙሉ ዘገባ እዚህ ላይ ይገኛል)።

የዛሬ ስድስት ወር ገደማ የመፈንቅለ መንግሥት ስጋት ከሚታይባቸው 40 አገራት መካከል ኢትዮጵያ በ25ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ትንበያ ተሰጥቶ ነበር። ለዚህ ትንበያ የተወሰዱት ነጥቦች “የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የእርስበርስ ግጭት፣ የነጻ ምርጫ ሁኔታ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ በየቀጣናው ያለ የመፈንቅለ መንግሥት እንቅስቃሴ፣ ወዘተ” መሆናቸው ተጠቅሶ ነበር። ይኸው ዘገባ “ከሚከሽፉ መንግሥታት” ሪፖርት ጋር በመሆን በዚህ መልኩ ተዘግቦ ነበር።

እንዲህ ዓይነቶቹን መረጃዎች በሥርዓት የሚመለከቱና የሚያጠኑ ፖሊሲ አውጪዎችና ተመራማሪዎች ወራት ጠብቀው የኢህአዴግን ፈር የለቀቀ አካሄድ ከመኮነን በማለፍ “የአፍሪካ ቀንድ ስጋት” ነው በማለት በግልጽ እስከመናገር ደርሰዋል። “በኢትዮጵያ አንድ ችግር ቢፈጠር ለማረጋጋት አስቸጋሪ እንደሚሆን፣ ህዝቡ በተለይ በህወሃቶች ላይ የሚያሳየው ጥላቻ እየተካረረ መምጣቱ፣ በአገሪቱ የሚፈጸመው ያልተመጣጠነ የሃብት ስርጭት፣ አፈናውና ሌሎች የህወሃት/ኢህአዴግ ተግባራት ተዳምረው ህዝቡን ክፉኛ ማስቀየሙ ያልታሰበ ችግር ሊቀሰቅስ እንደሚችል” ጎልጉል አንድ አሜሪካዊ ዲፕሎማት ጠቅሶ የዛሬ አራት ወር አካባቢ ዘግቦ ነበር። ዲፕሎማቱ እንደሚሉት “ህወሃቶች የቀጠናው የሰላም ምንጮች ስለመሆናቸው ለራሳቸው ምስክርነት ለመስጠት ቢሞክሩም በተግባር የሚታየው ግልባጩ ነው” ማለታቸውን በዚሁ የዜና ዘገባ ተገልጾዋል። (ጎልጉል ያጠናከረው ሙሉ ዘገባ እዚህ ላይ ይገኛል)።

የዛሬ ወር አካባቢ በኢኮኖሚው መስክ “በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ልማት ትምህርት ክፍል ሥር የኢኮኖሚ ጥናት የሚያካሂደው የኦክስፎርድ የድህነትና የሰብዕ ልማት ማዕከል (The Oxford Poverty and Human Development Initiative (OPHI)) ያወጣው የ2014 የጥናት መረጃ ደሃ ከሚባሉት 108 አገራት ዝርዝር ኢትዮጵያ ከመጨረሻው ሁለተኛ መሆኗን” ዳጎስ ያለ ጥናት ማቅረቡ ተዘግቦ ነበር። “ትምህርት፣ ጤና እና የኑሮ ሁኔታ ማለትም ኤሌክትሪክ፣ ጽዳት፣ የሚጠጣ ውሃ፣ የንብረት ባለቤትነት፣ ወዘተ” እንደ ጠቋሚ መረጃ በመውሰድ እዚህ ድምዳሜ ላይ መድረሱን ማዕከሉ አስታውቋል። ሪፖርቱ እንዳብራራው ከሆነ በኢትዮጵያ “ከ100 ሰዎች መካከል 87ቱ ድሃ ተብለው የሚጠሩ ሲሆን 58ቱ ሰዎች ግን መናጢ ደሃ ተብለው የሚጠሩ” መሆናቸውን ጠቅሶ ድህነቱ “በተለይ በገጠር እጅግ የከፋ እንደሆነ በመጠቆም ከ100 ሰዎች ውስጥ 96ቱ ደሃዎች” መሆናቸውን በግልጽ ተናገሯል። (ጎልጉል ያጠናከረው ሙሉ ዘገባ እዚህ ላይ ይገኛል)።

እነዚህ ለአብነት የጠቀስናቸው ከብዙዎቹ መካከል የተወሰኑት ናቸው፡፡ በምዕራባዊ ተቋማት በመውጣታቸው ብቻ ዘገባውን ጸረ-ኢህአዴጋዊ አያደርገውም፡፡ ምክንያቱም የምዕራብ ተቋማት የሚያወጡትን መረጃ በጭፍን የሚያጥላላው ኢህአዴግ ለራሱ ድርጅታዊ አሠራር የሚፈልገው ዓይነት ዘገባ በምዕራባዊ ድርጅቶች እያስወጣና እያሰራ ለፖለቲካው ድርሰት ሲጠቀምበትና ካድሬዎቹንም ይህንኑ ሲያዘምር በተደጋጋሚ ተሰምቷል።

በኮምፒውተር ፕሮግራም ቋንቋ “garbage in garbage out” የሚባል አነጋገር አለ፤ ፕሮግራም የሚያደርገው ሰው የሚጨምረው ኮድ “ጥራጊ” (ትርጉም አልባ) ከሆነ የፕሮግራሙ ውጤት “ጥራጊ” (ትርጉም አልባ) ይሆናል። “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” በግልባጩ እንደማለት ነው።

ከላይ የተጠቀሱትን ጥናቶች የሚያካሂዱት ተቋማት የራሳቸው አጀንዳ አላቸው ቢባልም ለዘገባቸው ግብዓት የሚጠቀሙት መረጃ ግን የሚገኘው በተግባር ከሚፈጸመውና ሕዝብ በየዕለቱ ከሚጋፈጠው የኑሮ ውጣውረድ በቀጥታ የተወሰደ ነው። እየሆነ ያለውን ነገር በየትኛውም ዓይነት ፕሮፓጋንዳ ቢሸፍኑትና ቢያጥላሉት ዕውነታውን እንዲስት ግን ማድረግ አይቻልም። የሕዝብ ሰቆቃ፣ ምሬት፣ ሃዘን፣ … ለኢህአዴግና ካድሬዎቹ ጆሮገብ ባይሆኑም የኢትዮጵያን ሰማይ ግን ጥሶ አልፎ ሄዷል። እንደፈለጉ ቢያንቋሽሹትና ቢያጥላሉትም በየጊዜው የሚወጣው ዘገባ የሕዝብን ምሬት ቁልጭ አድርጎ የሚመሰክር ነው። ኢህአዴግ ግን አሁንም “አልሰማም” በሚል ዕብሪት እንደተነፋ ነው!

ኢህአዴግ እንዲሰማ በተደጋጋሚ ከአገር ውስጥም ቢሆን ከውጭ፤ ከኢትዮጵያውያንም ይሁን ከሌሎች፤ ከተቃዋሚዎችም ሆነ ከራሱ ደጋፊዎች፤ … ቢነገረውም በተቃራኒው በሚፈጽመው ድርጊት “አልሰማም” የሚል የዕብሪት ምላሽ እየሰጠ ነው። ከውድቀት በፊት ዕብሪት እንደሚቀድም የዘነጋው ወይም እርሱንም ጭምር “አልቀበልም” ያለ ይመስላል!

አላቆም ያለው ሰቆቃ፣ እስራት፣ ግድያ፣ እንግልት፣ … የውሸት ክስ፣ የውሸት ውንጀላ፣ የውሸት ፍርድቤት፣ የውሸት ብያኔ፣ … ኅሊናን የሸጠ ዲስኩር፣ መግለጫ፣ ቃለምልልስ፣ … ጥቂቶች “አይሰማም” ቢሉም ሕዝብን እያስለቀሰ፣ እያስመረረ፣ እያንገፈገፈ፣ … ሄዷል። በሕዝብ ደምና እምባ ጸንቶ መቆም አይቻልም፤ ለዚህ ታሪክ ምስክር ነው። “ከተማን በደም ለሚሠራ ወዮለት” እንደሚል ያልተዘራ አይታጨድምና፤ “ንፋስን የዘራ ሁሉ አውሎ ንፋስን ያጭዳል”! አሁን ባይመስልም ሁሉም ወቅቱን ጠብቆ ይሆናል። እኛ የምንመኘው ወይም ከመመኘት የምንታቀብበት ቢሆንም ባይሆን “መሰበር” ግን አይቀርም! እጅግ የሚያሳስበን ግን ከዚያ በኋላ ያለው ጨለማ ነው! ሳይመሽ ጆሮ ያለው ቢሰማ መልካም ነው እንላለን!


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ®” አቋም ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule