• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በ2030 ከሚከሽፉ መንግሥታት አንዷ ኢትዮጵያ ነች”

January 16, 2013 09:29 am by Editor 18 Comments

የአሜሪካ የብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2030 የሚከሽፉ 15 መንግሥታትን (failed states) ዝርዝር አውጥቷል፡፡ “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” ይከሽፋሉ ተብለው ከተተነበዩት የአፍሪካ፣ የእስያና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች፡፡

እጅግ የነጠረ፣ ያልተዛባና የተጠና ዘገባ ለአሜሪካ የስለላ ተቋማት፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አውጪዎችና ለዓለምዓቀፍ ግንኙነት ተመራማሪዎች በማውጣት የታወቀው የአሜሪካ ብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት ከተቋቋመ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ምክርቤቱ በሚያወጣቸው ዘገባዎች የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ የተለያዩ መ/ቤቶች ተጽዕኖ እንደማያደርጉበት የሚናገር ሲሆን፤ ዘገባዎቹንም ከአድልዎ እና ከአሜሪካ መንግሥት አቋም ነጻ በመሆን እንደሚያዘጋጃቸው ይናገራል፡፡

የም/ቤቱ ዘገባ በተለይ ምርጫ ከተካሄደ በኋላ ለመጪው ፕሬዚዳንት የወደፊቱን የዓለማችን መልክ ምን እንደሚመስል የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ አስተሳሰቦች እና ዓለምአቀፋዊ ዝንባሌዎች ላይ አቅጣጫ የሚጠቁም ትንበያ ያደርጋል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ ዓለምአቀፋዊ የደኅንነት ዘገባ ያቀርባል፤ ለብሔራዊ የጸጥታ ምክርቤት እና ለአገር ውስጥ ደኅንነት መ/ቤት ምክር ያቀብላል፤ በአጠቃላይ የአሜሪካን የስለላና የደኅንነት ማኅበረሰብ ሊከተል በሚገባው ጉዳይ ላይ አቅጣጫ የሚያስይዝ ሃሳብ ያቀርባል፡፡

በዚሁም መሠረት ባለፈው የታህሳስ ወር “በ2030 የዓለም አቅጣጫ፡ አማራጭ አገራት” በሚል ርዕስ አንድ ዳጎስ ያለ ጥናት አቅርቧል፡፡ ይኸው 160ገጽ ያለው ዘገባ የዛሬ 17ዓመት የዓለማችን ገጽታ ምን እንደሚመስል ከየአገራቱ በተወሰደ ጥናትና እዚያው በሚገኙ ተመራማሪዎች የሰበሰበውን ያካተተ ነው፡፡ ዓለማችን የምታዘነብልባቸው ቀዳሚ ሁኔታዎች አንዱ ሰዎች በራሳቸው አነሳሽነት ድህነትን ለመቀነስ፣ በትምህርት ለማደግ፣ በቴክኖሎጂና በህክምና ለመራቀቅ እንዲሁም በገቢም የመካከለኛው መደብ ላይ ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቀሱት አንዱ አቅጣጫ ጠቋሚ ነው፡፡

ሌሎቹ ዓለምን አንድ አድርጎ በመዳፉ ሥር የሚገዛ ኃይል የማይነሳ መሆኑ ከሚታዩት ከፍተኛ ዝንባሌዎች ተጠቃሽ ሲሆን አሜሪካ ምንም እንኳ “የዓለም ፖሊስ” የመሆኗ ሁኔታ የሚቀንስ ቢሆንም የዓለምን አቅጣጫ መቆጣጠሯ ይቀራል ማለት እንዳልሆነ ይጠቁማል፡፡ የዓለም የሕዝብ ቁጥር ከመጨመሩ አኳያ “እያረጁ” የሚሄዱ አገራት የኢኮኖሚ ዕድገታቸው እንደሚያሽቆለቁልና ከገጠር ወደከተማ ፍልሰት እንደሚጨምር፤ 60በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ በከተሞች አካባቢ ኑሮውን እንደሚያደርግ ይተነብያል፡፡ በዚህም ምክንያት የውሃ፣ የምግብና የኃይል (ኤነርጂ) ፍላጎት ከሕዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያድግ ይናገራል፡፡ የቴክኖሎጂ ምጥቀትና የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎትም የዓለማችንን አቅጣጫ እንደሚቀይር ያስረዳል፡፡

የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት በስፋት እንደሚቀጥልና በበርካታ ፈርጆች ትብብርና ስምምነት እየፈጸሙ ሰፋ ያለ ዓለምአቀፋዊ ኅብረት እንደሚያደርጉ የሚናገረው ይህ ሪፖርት በየአገራቱ እየሰፋ የመጣው በድሃና በሃብታም መካከል ያለው ክፍተት የማኅበራዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ይጠቁማል፡፡ ይህም ቀውስ በአንዳንድ አገራት ውስጥ እየሰፋ በመምጣት ለተባባሰ ግጭትና ክስረት እንደሚያጋልጥ የኑሮ ልዩነቱም የማኅበራዊ ቀውሱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያደርሰው ይተነትናል፡፡ የሃይማኖት ሚና እንደሚጨምር የጠቆመው ዘገባ ይህንኑ ተከትሎ መካረርና ግጭት እንዲሁም አሸባሪነት ለመስፋፋት ሃይማኖት ምክንያት እየሆነ እንደሚሄድ ይናገራል፡፡

በዘገባው ከተነገረው በተጻጻሪ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ ወዲህ እስካሁን በ44 አገራት ጉዳይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ጣልቃ በመግባት ጦርነት ያካሄደችው አሜሪካ የዓለም ኃያል ሆና እንደምትቀጥል በመናገር ሪፖርቱን የሚያጣጥሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ እንደማስረጃም አድርገው አሜሪካ በተለያዩ አገራት ያላትን 737 የወታደራዊ ተቋማት ይጠቅሳሉ፡፡ ስለሆነም ዘገባው የአሜሪካ የበላይነት የመቀነሱን ጉዳይ አንስቶ የተናገረውን አይቀበሉም፡፡

እኤአ በ2030 የሚክሽፉት 15ቱ መንግሥታት (ፎቶ: ጂአይ)

ዘገባው የዓለማችንን የወደፊት ሁኔታ ሲተነብይ በዋንኛነት ከጠቀሳቸው ጉዳዮች አንዱ በ2030 የሚከሽፉ መንግሥታትን ዝርዝር ሰጥቷል፡፡ “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” የሚከሽፉ መንግሥታት ተብለው ከተጠቀሱት 15 አገራት መካከል ኢትዮጵያ እንዷ ስትሆን አፍጋኒስታን፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ፣ ቻድ፣ ኒጀር፣ ማሊ፣ ኬኒያ፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ፣ ማላዊ፣ ሃይቲና የመን የተቀሩት ናቸው፡፡

ይሁንና ይኸው ም/ቤት እኤአ በ2015 ፓኪስታን የምትከሽፍ አገር ትሆናለች በማለት ትንቢት ሰጥቶ ይኸው እስካሁን አለች በማለት ዘገባውን የሚያጣጥሉ ክፍሎች ኢትዮጵያም ሆነ ሌሎቹ አገራት ለመክሸፋቸው በቂ ማስረጃ የለም በማለት የዘገባውን ጥቆማ ይቃረናሉ፡፡ በሌላ በኩል እንዲህ ያለው የመክሸፍ ሁኔታ ሊዋጥለት የማይችለው ኢህአዴግ “ህዳሴ፣ ውዳሴ” ከማለት ይልቅ ይህንን ጉዳይ አጥብቆ ሊያስብበት እንደሚገባና የሥርዓት መበስበስ አመላካች የሆነውን “የመንግሥት ሌቦች” መበራከት መፍትሔ ሊያበጅለት እንደሚገባ ደጋፊዎቹና አመራሩ በየጊዜው የሚያነሱት ነጥብ ነው፡፡

በዚሁ የኢትዮጵያ እንደ አገር የመክሸፍ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው አሁን ካላቸው ተግባር አኳያ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በአውሮጳ የሚገኙ የፖለቲካና ዓለምአቀፋዊ ግንኙነት ተመራማሪ “ችግሩ የኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን የተቃዋሚውም ነው” ይላሉ፡፡ “በአገር ውስጥ ያለው ተቃዋሚ ከውስጥ የሥልጣን ሽኩቻና ከስብሰባ/ውይይት ጋጋታ ባለፈ መልኩ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ሊያደርግ የሚችል የተቀናጀና ውጤታማ ተግባር ሊፈጽሙ ይገባቸዋል” የሚሉት ምሁር በውጭ ያለውም “ከጊዜያዊና ጥቃቅን የራስ ክብር የመፈለግ አካሄድ በመላቀቅ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ጡንቻውን በወያኔ ላይ ማሳረፍ ይጠበቅበታል” ብለዋል፡፡ “የደኅንነት ተቋሙ ባወጣው ዘገባ ላይ በግልጽ እንደተነበየው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ የመጨመሩ ያህል በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ይህንኑ ለውጥ ማምጣት የሚችል የዘመኑ ቴክኖሎጂ ለአሉባልታና ተራ የፖለቲካ ወሬ ከመጠቀም ይልቅ አገር ለማዳን ተግባር ሊጠቀምበት ይገባል” በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል፡፡

የደኅንነት ምክርቤቱ ያወጣው ሙሉ ዘገባ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Dawit says

    January 16, 2013 10:21 am at 10:21 am

    እንደ አገር የመክሸፍ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው አሁን ካላቸው ተግባር አኳያ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በአውሮጳ የሚገኙ የፖለቲካና ዓለምአቀፋዊ ግንኙነት ተመራማሪ “ችግሩ የኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን የተቃዋሚውም ነው” ይላሉ፡፡ “በአገር ውስጥ ያለው ተቃዋሚ ከውስጥ የሥልጣን ሽኩቻና ከስብሰባ/ውይይት ጋጋታ ባለፈ መልኩ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ሊያደርግ የሚችል የተቀናጀና ውጤታማ ተግባር ሊፈጽሙ ይገባቸዋል” የሚሉት ምሁር በውጭ ያለውም “ከጊዜያዊና ጥቃቅን የራስ ክብር የመፈለግ አካሄድ በመላቀቅ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ጡንቻውን በወያኔ ላይ ማሳረፍ ይጠበቅበታል” ብለዋል፡፡ “የደኅንነት ተቋሙ ባወጣው ዘገባ ላይ በግልጽ እንደተነበየው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ የመጨመሩ ያህል በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ይህንኑ ለውጥ ማምጣት የሚችል የዘመኑ ቴክኖሎጂ ለአሉባልታና ተራ የፖለቲካ ወሬ ከመጠቀም ይልቅ አገር ለማዳን ተግባር ሊጠቀምበት ይገባል” በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል፡፡

    Reply
  2. sisay says

    January 16, 2013 04:58 pm at 4:58 pm

    this is trash ይሄ ያልተጨበጠ የ ህልም ትንበያ ነው በኣማርኛ ህልም አንደፈቺው ነው አንደሚባለው ስለዚህ አኢትዮጵያ በ ኣሜሪካእኣስተሳስብ ሳይሆን በ ጌታ ኣስተሳስብ ነው የምትኖረው መዖሃፍ ቅዱስ ላይ ኣሜሪካ አጆችዋን ወደ አግዚኣብሄር ት ዘረጋለች ሳይሆን አኢትዮጵያ ነች አጆችዋን የምትዘረጋው አባካቹ መጀመሪያ የራሳች ሁን ችግር ፍቱና ዜጎቻጩን ስራ ኣስገቡና ስለ አፍሪካ ኣስቡ ገና ድሮ ስለ ኣፍሪካ ጥሩ ኣመለካከት የሌላት ሃገር ኣሜሪካ ኣሁን አፍሪካ ከ ቻይና ጋር በመሆን አድገት ላይ ባለችበት ጊዜ አንዲ ኣይነት ትንበያ look short sited

    Reply
    • yigermal says

      September 17, 2013 10:15 pm at 10:15 pm

      በርግጥም ለሃገራችን የጠለቀ ችግር መፍትሄ ሳንፈልግለት እንዲያው በደፈናው “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደእግዚአብሄር ትዘረጋለች” እያልን ማናፋቱ ዋጋ የለውም:: ኢትዮጵያ እጆቿን በርግጥ እየዘረጋች ነው ወይ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ አይደለም ነው:: ምክንያቱም ጉራው(በዘር: በመልክ ወዘተ መፎከሩ ): አንዱ ላንዱ ጉድጓድ መቆፈሩ: ምቀኝነቱ: ሌብነቱ: አንዱ ሃይማኖት ተከታይ ሌላውን መጥላቱ: ስግብግብነቱ: ወዘተ… ውስጣችንን እየቦረቦረ ልባችንን አደንድነን ተቀምጠን መፍትሄ ከላይ ይመጣል ማለት ዘበት ነው:: ይልቅስ እርስ በርሳችን ከምንንቆራቆስ ልባችንን አጥርተን መከራችን በቅቶናል ማረን! ካላልን በስተቀር ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ከካርታ ላይ እስከምትጠፋና እንደሩዋንዳ እርስበርሳችን እስክምንጫረስ ድረስ ለራሳችን ፍቃድ አሳልፎ ሊሰጠን ይችላል:: የኢትዮጵያ ህዝብ እጣ ፋንታው በአምላክ እጅ ነው:: ነገሮች ከድጡ ወደማጡ እስከሚሆንብን ድረስ ከመጠበቅ አሁኑኑ እጃችንን ወደእግዚአብሄር በትህትናና በተዋረደ መንፈስ ካላነሳን መጨረሻችን አለማማሩ በርግጥ እውነት ነው:: እግዚአብሄር ድንጋዩንና በጥላቻ የተሞላውን ልባችንን ይቀይርልን! አሜን::

      Reply
  3. Gudu Kassa says

    January 16, 2013 06:37 pm at 6:37 pm

    This is game on the minds of Africans!!!!!

    Reply
  4. ብስራት says

    January 17, 2013 03:47 am at 3:47 am

    ፓ! ጥሩ ያሟርታሉ! ወረኞች ሁላ! ካወሩ መች አነሳቸው! እድሜ ልካቸውን ኢትዮጵያ ላይ ሲያሟርቱ ይኖራሉ!! እነሱ ስለእኛ ሺህ ጊዜ ቢያጠኑ እና ቢያነቡ የማይረዷቸው ሺህ ነገሮች አሉ! ወረኛ ሁላ!

    Reply
  5. Wey wey Ethiopia says

    January 17, 2013 04:48 am at 4:48 am

    Surprised to not see Eritrea on the map. Contrary to what Woyane wants us to believe, of course.
    It is not Ethiopia that will fail by the way. Woyanie is in a ‘failed state’, not Ethiopia. The country will be rescued from this ugly prediction by its sons and daughters that are deeply opposed to the minority regime, a regime that only represents 3 million Tigrays.

    Reply
  6. ሙስጠፋ says

    January 17, 2013 09:59 pm at 9:59 pm

    ምን ነው? ምን ነው? ጎልጉሎች ምን የመሳሰለ ወሳኝና ጠቃሚ መረጃ ስታቀርቡ የነበራችሁ በሳሎች በእነዚህ በማይረቡ አሜሪካውያን ጠንቋዮች የሚጻፍ እንቶ ፈንቶ ላይ ጊዜአችሁን፣ እውቀታችሁ እና ገንዘባችሁን በከንቱ ማባከናችሁ? እኔ እነሱ እሚያወጧቸውን ጥናት ተብዬ አልፎ አልፎ እከታተላቸዋለሁ፤ ሆኖም ከተነበዩት ውስጥ ባብዝሃኛው ከመሆኑ አለመሆኑ ያመዝናል። ምክናየቱም እነሱ ለአለማችን አገሮች ያላቸው እይታ በጥናት ላይ ሳይሆን በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ነው። ባይሆን አጥፍቶ መጥፋትን እንዴ ፖሊሲ የሚጠቀመውን ወያኔን ሳያጠፋን አስወግደን አገራችን እናሳድጋታለን። ምናልባት እነሱ ይከሽፋል ያሉት ወያኔን ከሆነ ትክክል ሆነው ሳለ ግዜው 2030 ሳይሆን 2013 ሊሆን ይችላል።

    Reply
  7. AleQa Bru says

    January 18, 2013 07:21 pm at 7:21 pm

    The original report says quite different from what GolGul is saying:

    In 2008, Ethiopia ranked 10th (Risk of Failing state) and the report forecasts that Ethiopia will rank 15th in 2030. So this is an improvement. According to the report Ethiopia will be more stable.

    Reply
    • Editor says

      January 19, 2013 12:58 am at 12:58 am

      AleQa Bru
      Well said. You wanted to pick on us but you end up conflicting yourself. Regardless of the rank, Ethiopia is still in the rank of 15 countries. 15 ሰዎች ወደ ገደል እየተደፉ በተራ በተራ ቢጣሉ 10ኛ ይሁን 15ኛ መሆን ከመደፋት አያድንም:: የሚያድነው ከዝርዝሩ ውስጥ አለመሆን ነው:: What we wrote here is not our own OPINION but a NEWS article. There is a huge difference between the two. And just for the record, according to the report, Ethiopia’s rank is not 15th but 14th.
      We appreciate your comment. Please keep on doing it.

      አርታኢ/Editor
      ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
      http://www.goolgule.com
      editor@goolgule.com

      Reply
  8. ዱባለ says

    January 19, 2013 07:06 am at 7:06 am

    Quick point here. Why did some people look disappointed with this report? The report is actually re-enforcing what Ethiopian scholars predicted probably six to seven years back in Ethiopian Economic association, a workshop proceeding edited by Dr. Birhanu et al, if I’m not mistaken. The scholars predicted, if Ethiopia continues in the same trend, Ethiopia by 2020 will be not only in failed states category but will end up fragmented into ethnic conflict like Somalia. Since then things are not getting better in Ethiopia but spiraling in downward trend. So, we should not be surprised by this report prediction, we should be surprised why they are so behind and fail to predict what the Ethiopians scholars predicted six to seven years before.

    Reply
  9. AleQa Bru says

    January 19, 2013 10:32 pm at 10:32 pm

    Hi Admin thank you for your reply. I am actually surprised to have the admin reply to my very first comment at this blog.
    Anyways, you are right about Ethiopia ranking 14 (not 15) in the list of 15 countries the report projects to have “some kind of state failure” by 2030.

    The article says also the following about Ethiopia (page 15):

    “In Africa, Egypt, Ethiopia, and Nigeria have the potential to approach or surpass South Africa in overall national power, but the key will be better governance to further economic growth and social and human development.” It would have been balanced if you also mentioned this instead of focussing only on the negative.

    I would like to point out 2 mistakes in your review of the report:

    1. The title you gave to the review is not inline with the intention of the report. You give the impression that “Ethiopia is doomed to fail as a nation by 2030” while the original report literally says the following: “The table above lists countries that are projected to have a high risk of instability, conflict, or some other type of state failure in 2030 because of their poor human ecology and resilience.” Big difference….!!!! (not to mention the ranking improvement between 2008 and 2030 that you conveniently ignored to mention!)
    2. The authors of this report say the following at the beginning of the Executive Summary:”this report is intended to stimulate thinking about the rapid and vast geopolitical changes characterizing the world today and possible global trajectories during the next 15-20 years. As with the niC’s previous Global trends reports, we do not seek to predict the future—which would be an impossible feat—but instead provide a framework for thinking about possible futures and their implications.” On the other hand your understanding of the report seems to me (specially reading your reply to my comment) that things mentioned in this report ARE GOING TO HAPPEN.

    My point in all this is simple and as follows: Just because you believe the Ethiopian government will look bad, DO NOT trash your country and people. Be a responsible journalist. EVERY ONE of us is responsible for Ethiopia’s rise or fall.

    Regards,
    AleQa Bru

    Reply
    • Editor says

      January 21, 2013 02:31 am at 2:31 am

      Dear AleQa Bru,

      Thanks for your reply. Don’t be surprised for receiving a reply from us because we value our readers’ comments more than anything else. We do not reply to every comment posted but only to those that question our professionalism and integrity which, we believed, is stated on your previous comment. However, we don’t want to be engaged in a perpetual back and forth dialog type of commenting. As we have tried to explain it to you in our previous comment, what we wrote here is not an opinion but a news article. A correspondent may report a homicide committed by his own son. When he reports it he is a reporter but outside his line of duty he is a sympathetic father of a troubled kid. As far as balancing, reporting, … this news article about failed states has it all for we know what we did. We do not just copy/paste stuff and call it a news. But here we’d like to inform you again that there is a HUGE difference between writing an opinion vs writing a news. Misunderstanding this critical issue affects not only reporters but readers as well.

      So what we advice you here is to write an article about this news we reported – something like Op-ed and we will be glad to post it.

      Regards,

      አርታኢ/Editor
      ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
      https://www.goolgule.com
      editor@goolgule.com

      Reply
  10. Dagmawi Gudu Kassa says

    January 22, 2013 12:39 pm at 12:39 pm

    Nice dialog between golgul and one of its readers. I enthusiastically read all comments, with a special focus on those two arguing parties. It is good to speak our minds and come to a common ground that unifies us at the end. We don’t have to necessarily insult or badmouth each other as a tradition; we should bring ourselves off the path of the Woyannes and some riffraff ignoramuses in the opposition who prioritize their political interests and economic advantages. We should come to our conscience and emulate the positive experiences of the so called civilized world wherein mutual understanding based on equality and civility is the common feature that binds citizens in harmony.

    Reply
  11. ዱባለ says

    January 22, 2013 07:30 pm at 7:30 pm

    AleQa Biru said
    “Just because you believe the Ethiopian government will look bad, DO NOT trash your country and people. Be a responsible journalist. EVERY ONE of us is responsible for Ethiopia’s rise or fall.”
    No, we the people, the 80 million, who are oppressed and have no say in the political and economic affairs of the country are not responsible. It is those in the leadership position of the government and their blind supporters who are responsible for demise of the country and should be held accountable. The reality on the ground is….Woyane is an incompetent government who is controlling every sector of Ethiopia’s economy through Tigre’s cartel of EFFORT. Those who are benefiting from the illegally amassed wealth by EFFORT and its subsidiaries could take responsibility just like AleQA Biru did, I do not think the the rest of us should.

    Reply
  12. Oumer says

    January 23, 2013 06:38 am at 6:38 am

    Mn aynet tnat new benatachhu keze behuwal 17 ere ydebral

    Reply
  13. meretework says

    March 15, 2013 03:23 pm at 3:23 pm

    Hi our Brother and sister! what we need unity to come togher to kick our ——and we need to trust each other from now on to have peace! and work toghter ,yenesu tenbite lrasachw new! bezu sera ytebeqebenal hizibache batam tegosaqulale ,tesfa yemiyaskorete wore meinm ayseram, derom endich yebalale- libelate yesebaten kokqe doro neche yelatal, egziabiher serawn siyakom yemifesemewn yemiyaweke esu becha new,”For neither from the east” nor from the west,”Nor from the south “is there an exalting.-For God is the judge,”This one he abases, and that one he exalts.”so we do not give up our good work!!!!!!!!!!!

    Reply
  14. aman says

    April 1, 2014 09:57 pm at 9:57 pm

    you stupid american you alredy feild not my mama ETIOPIAN

    Reply
  15. aman says

    April 1, 2014 10:00 pm at 10:00 pm

    that was your drime. but we will stand wolke and runn.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule