“ዕድገት”፣ “ትራንስፎርሜሽን”፣ “ህዳሴ”፣ “የመለስ ውርስ (ሌጋሲ)”፣ … በሚመሯት ኢትዮጵያ ሙስና እየከፋ መሄዱ ታወቀ፤ ከመቶ ሰዎች ውስጥ ከ40 በላይ የሚሆኑት ጉቦ የሚሰጡ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡
ሰሞኑን ዓለምአቀፉ የግልጽነት ድርጅት (Transparency International) ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በርካታ የአፍሪካ አገራት በሙስና “መበስበሳቸውን” ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ አገራት መካከል እንደምትገኝ ዘግቧል፡፡
ከዚህ በፊት በያዝነው ዓመት ጥር ወር የሙስና አደጋ የተጋረጠባቸው አገራትን ዝርዝርና የአደጋውን መጠን በሰባት ደረጃ በመከፋፈል ይኸው ድርጅት ባወጣበት ጊዜ ኢትዮጵያን በከፍተኛ የሙስና አደጋ ውስጥ ከሚገኙ አገራት ዝርዝር ውስጥ አስገብቷት ነበር፡፡ በዚህ ዘገባ መሠረት በሙስና የተዘፈቁትን አገራት በመከፋፈል ባስቀመጠው ባለዘጠኝ መዘርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ከመጨረሻ ሁለተኛው ውስጥ አካትቷታል፡፡
ሰሞኑን የወጣው ዘገባ ይህንን እንዲል ያስቻለው አንዱ መረጃ “ጉቦ ሰጥተዋል ወይ (ያውቃል)?” በማለት ለአንድ ሺህ ሰዎች ያቀረበውን ናሙና መሠረት በማድረግ ነው፡፡ በጥያቄው መሠረት በኢትዮጵያ 44በመቶው “አዎን” በማለት መመለሳቸውን ዘግቧል፡፡
ጥናቱ የ3በመቶ የስህተት ገደብ ያደረገ ቢሆንም፤ የነጻ ሚዲያ፣ በነጻነት የመናገር፣ ያለፍርሃትና ዛቻ ሃሳብን የመግለጽ፣ ወዘተ መብት በተረገጠባት ኢትዮጵያ የዘገባው ቁጥር ከዚህ በላይ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፡፡ በቅርቡ ራሱ ኢህአዴግ በሙስና ላይ ዘመቻ ጀምሬያለሁ በማለት የወሰደው እርምጃ ጎልጉል “ሙስናን በስንጥር” በማለት የዘገበው ቢሆንም ዓለምአቀፉ የግልጽነት ድርጅት ካወጣው መረጃ ጋር ሲነጻጸር “የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀውንና የሚኖረውን ብታውቁና ብትኖሩ ኖሮ” የሚያስብል ነው፡፡
ከህዝቧ ግማሽ በላይ ሥራአጥ በሆነባት (የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ነው)፣ 86በመቶ ምንጥ ያለ ድሃና 80በመቶ በግብርና የተሰማራ ችግረኛ ሕዝብ በሚኖርባት አገር፤ ዘገባው ያወጣው አኃዝ ጉዳይ ከሚያስፈጽመው ሕዝብ መካከል ግማሽ ያህሉ ጉቦ መስጠት ግዴታው መሆኑ፤ ድሃው ሕዝብ ጉዳዩን ለማስፈጸም ጨርሶ አቅቶታል ወይም ጉዳዩን ከማስፈጸም ተቆጥቧል የሚያስብል ነው፡፡
ለ5ዓመታት በአዲስአበባ ኃላፊነት ከቆዩ በኋላ ሰሞኑን ወደ ጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት “ማቀዝቀዣ” የገቡት ኩማ ደመቅሳ በስንብታቸው ወቅት በኢህአዴግኛ “ኪራይ ሰብሳቢነት” አሁንም የከተማዋ አሳሳቢ ችግር እንደሆነ አምርረው ተናግረዋል፡፡ ይህ ሁኔታና አሁን የወጣው ዘገባ “ውርሳቸውን እናስጠበቃለን” የሚባሉት ሟቹ መለስ፤ በረሃ በነጻአውጪነት ከዚያም በመንግሥትነት ራሳቸው ስለመሩት ድርጅት የተናገሩትን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት “ከእንጥላችን ገምተናል”!
Liberalism says
Liberalism