• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የግጭት ምንቸት ውጣ የእርቅና የሰላም ምንቸት ግባ!!

September 11, 2015 07:19 am by Editor Leave a Comment

ከልብ በመነጨ፣ ፍጹም በሆነ የወገን ፍቅር በሶማሊያ በውትድርና ላሉ ወገኖች ፈጣሪ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እንመኛለን። በማያውቁት ጉዳይ የበረሃ ጥሩር ለሚገርፋቸውና የነፍሳቸው ዋጋ በውል ለማይታወቀው ወገኖቻቸን እንኳን አደረሳችሁ ከማለት በላይ ሁሉም ወገኖች ድምጽ እንዲሆኗቸው እንጠይቃለን። በወር 30 ዶላር አበል ህይወታቸው ላለፈና አሁንም እያለፈ ለሚገኙት ሃዘናችን ትልቅ ነው። ትርጉም በሌለው ጦርነትና ለወደፊት ንጹሃን ዋጋ የሚከፈሉበት የፖለቲካዊ ቁማር ስትራቴጂ የደም ግብር ለመክፈል ሰልፍ ለያዛችሁ ፈጣሪ አሁንም ይድረስላችሁ!!

ለራባችሁም ለጠገባችሁም፡-

እንደ ልማዳችን እንኳን አደረሰን፣ አደረሳችሁ፣ እንቁጣጣሽ!! ስንል ለማለት ብቻ ባንለው ምንኛ ደስ ባለን ነበር። አዲሱን ዓመት ተቀብለን እልፍ ሳንል ባለንበት ቆመን ያረጅብናል። እኛም ያለ አንዳች ለውጥ ጎመን/አረም አሮብን የገንፎ ምንቸት ግባ እያልን በራሳችን እንደቀለድን እናረጃለን!! እኛና ዘመን እንዲህ ባለ ሂደት የጎንዮሽ እየነጎድን ነው። መለስ እንኳን ካለፉ ሦስት ዓመት አለፈ!! የክፋት ውርሳቸው ግን አሁንም አለ!!

ካሮጌውና ከጥንቱ ለመማር አንሞክርም። ያ ልባም አቀንቃኝ ቴዎድሮስ ካሳሁን “የኋላው ከሌለ የታለ የፊቱ” እንዳለው!! ምን ይህ ብቻ “የመጣንበት መንገድ ያሳዝናል” ሲል አእምሮን በርቅሶ በሚገባ የግጥም ፍሰት እየዘከርን ያለፍናቸውን ዓመታት ያመላክተናል። “አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ ለምን ይሆን የራበው ሆዴ?” እያለ “አመመኝ አመመኝ ውስጤን አመመኝ” ሲል የልቡን ስቃይ ያዜምልናል። አይገባንም። ወይም እንዲገባን አንወድም!! እውነትም አመመኝ!!

ነገሩ ሁሉ ተቃራኒ ነው። የመታደስ ፍንጭ አይታይም። ውሸቱ አይሏል። ስርቆቱ ጨምሯዋል። እንደ እንቁጣጣሽ በግና ዶሮ ዋጋ ከህደቱ ለከት አጥቷል። የሚልሱትና የሚቀምሱት አጥትው እንደጨለመባቸው ወገኖች ኅሊና የሚባለው የልቡና መብራት ተቃጥሏል፤ ጠፍቷል። ርሃብ ዘር ሳይለይ ወገኖችን እያራገፈ “የእድገት፣ የብልጽግና” ከበሮ ይደለቃል። ኅሊናቸው የቀረናባቸው “ዝናብን መቆጣጠር የቻለ አገር የለም” እያሉ የተላላኪነት ዕድሜያቸውን ያራዝሙብናል።

የአድርባይነት ተምሳሌት ተደርገው የተወሰዱት ገዢዎች የመከርቸሚያውን ሰንሰለት ከማላላት ይልቅ አደድረውታል። ዳክረው ዳክረው “የደኅንነት አገዛዝ” ትግራይ ላይ ተሰብስበው ቸንክረውብናል፤ የደኅንነት ሹሞች የአገዛዙ ቁንጮዎች ሆነዋል። “ባለ ራዕዩ መሪ” የመለመሏቸው የአፈና ማሽኖች “ውርስ ወይም ሞት” ብለው ተነስተዋል። እነርሱ አውራ ሆነው ሌሎችን ጫጩት በማድረግ ቀጥቅጦ ለመግዛት ተቧድነዋል።

ወግ ነውና በአዲስ ዓመት እንዲህ እንላለን። “አውራዎቹ” እጅግ ጥቂት፣ ጫጩቶቹ እጅግ ብዙ ናችውና ያጨለማችሁትን የልቡናችሁን መብራት አብሩት!! ለዕብሪታችሁ ገደብ አድርጉለት፤ ዓመት አልፎ ዓመት ሲተካ የትክክለኛነታችሁ ማረጋገጫ ሠርቲፊኬት ሳይሆን ምሬትን በአንድ ተጨማሪ ዓመት ማግዘፋችሁ ይታያችሁ፤ ሌሎችም ለአገራቸው የማሰብና አገራቸውን በራሳቸው የሰላም መንገድ የመውደድ መብት ይኑራቸው፤ ምሬት ጥላቻን፤ ጥላቻም በቀልን አርግዞ የግድ መውለድ የለበትም፤ የእርቅና የሰላም ምንቸት ገብቶ የግጭትና የጥላቻ ምንቸት እንዲወጣ ሁሉም ዓይነት መስዋዕትነት ይከፈል!! ኢትዮጵያችንም ትኑርልን። መጪው ትውልድም አገር አልባ አይሁን። ይመርብን።


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ®” አቋም ነው፡፡

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule