• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“አውሬነት” – ለማንም አይበጅምና ጠንቀቅ!!

May 2, 2014 11:35 pm by Editor 2 Comments

አሁን ከኢህአዴግ ጋር ገድለሃል አልገደልክም የሚል ክርክር የለም። ራሱ ባንደበቱ “ገድያለሁ” ብሏል። ነፍስ ማጥፋቱን አውጇል። ያልገለጸው በጸጥታና በስም እንጂ አንጋቾቹ ህይወት መቅጠፋቸውን አረጋግጧል። ግድያው በዚህ ስለማብቃቱ ማረጋገጫ አልተሰጠም። ተቃውሞውም እየቀጠለ ነው። ከዚያስ? በደም እየታጠቡ፣ ወንጀልን እያባዙና የደም ጎርፍ እየጎረፈ “ህግ” ማስከበር እስከመቼ ያስኬዳል። ያዋጣልስ? የህዝብ እንባስ እንዲሁ ከንቱ ይቀራል?

በርግጥ ህግ ማፍረስ አይደገፍም። ህግ መከበር አለበት። ከሁሉም በላይ ደግሞ ህገመንግስት ክቡር የመተዳደሪያ ዋስትና በመሆኑ ሊናድ አይገባውም። ህግን የማክበርና የማስከበር ጥያቄ አይለያዩም። ኢህአዴግ እንዳሻው የሚምልበትን ህገ መንግሥት እየጨፈላለቀና እየጎራረደ ሌሎች ህግ እንዲያከብሩ መጠየቅ ለምዶበታል። ሰዎች መብታቸውን እንዲለማመዱ አይወድም። ይህ ችግሩ በደም የታጠበ፣ የደም እዳ ያለበት፣ ታሪኩ ሁሉ ከደም ጋር የተሳሰረ እንዲሆን አድርጎታል። እስኪ ወደ ዛሬው ጉዳይ እናምራ!

አልታደልንም

ህዝብን የሚያከብር፣ ለህዝብ ቅድሚያ የሚሰጥ፣ በህዝብ የሚምል፣ ህዝብ ውስጥ የሚኖር፣ ህዝብ እውቅና የሰጠው፣ ህዝብ የሚያምነው፣ ሲፈልግ የሚቀጣው፣ ሲፈልግ የሚያሞግሰው አስተዳደር አጋጥሞን አያውቅም። የቀደመውን ኮንኖ የሚመጣው ከቀደመው የማይሻል፣ ደም የጠማው፣ ጠመንጃ አምላኩ የሆነ አገዛዝ ነው። አገሪቱም፣ ትውልዱም፣ የወደፊቱ እንግዳ ዘርም ሁሉም በስህተት ቅብብል በርግማን ይኖራሉ። ነፍጠኛ፣ ትምክተኛ፣ ጎጠኛ፣ ጠባብ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ አንጃ … ቃላት እንደ ፋብሪካ ምርት እየተፈበረኩልን ስንሰዳደብ እንኖራለን። የሁሉም አስተሳሰብ አንድ ብቻ ነው – የራሱን ህልውና ለማስፈን የሚቃወሙትን ሁሉ መደምሰስ! “በጠላቶቻችን መቃብር ላይ …” የሚለው መፈክር ደርግ ቢለውም የራሱ በማድረግ አንግቦ የሚዞረው ግን እጅግ በርካታ ነው፡፡police12

ኢህአዴግ ተቃውሞና የተቃውሞ ድምጽ ያስበረግገዋል?

አዎ!! ኢህአዴግ የተቃውሞ ድምጽ ሲሰማ ይርዳል። የተቃውሞ ድምጽ ሲሰማ ይንቀጠቀጣል። ሲቃወሙት የበረሃ ወባው ይነሳበታል። ከድንጋጤው የተነሳ ይበረግጋል። ይደነብራል። ለምን? ቢባል በደም የተለወሰ ፓርቲ ስለሆነ ነው። ኢህአዴግ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ነፍስ ያላጠፋበት ስፍራ የለም። በመሀል አገር ክቡር የሰው ልጆችን ገሏል። የሚደመደም ነገር ባይኖርም በበላዮቹ ትዕዛዝ ኢህአዴግ ባፈሰሰው ደም መጠን ጠላት አፍርቷል። ወዳጁና አጋሩ ጠብመንጃና በደም የለወሳቸው አባላቱ ብቻ ናቸው። ሌላ ወዳጁ እንዳሻው የሚዘራው የአገሪቱ ሃብት ነው። የህዝብ ሃብት ህዝብን ለማፈን ማዋል!! ሌላው ስጋቱን ለመጥቀስ እንጂ ከዝርፊያ ጋር የተቆራኘውን ታሪኩን ለመዘርዘር አይደለም። ስለዚህ ህዝብ ሲቃወም ያጥወለውለዋል። ይጓጉጠዋል። አውሬ ይሆናል። ህግና ስርዓት አፍርሶ የጫካ ደንብ ይተገብራል። ባጭሩ ይገላል!!

ኢህአዴግ በበረገገ ቁጥር እንሰጋለን!!

ኢህአዴግ የኢትዮጵያ ገዢ ነኝ ካለበት ጊዜ ጀምሮ ህዝብን ያስቀየሙ፣ ያሳዘኑና፣ ያሳፈሩና ቂም ያስቋጠሩ ተግባራትን በግልጽና “በድብቅ ግን የሚታወቅ” አከናውኗል። በተለያዩ ጊዜያት በተግባሩ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማፈን ሃይል ተጠቅሟል። አልሞ ተኳሾችን አሰማርቶ ዜጎችን ልባቸውና ግባራቸው አየተመታ እንዲገደሉ አድርጓል። የሚችለውን ያህል አስሯል። ገርፏል። ራሱ ክስ መስርቶ ራሱ እየፈረደ ወህኒ ወርውሯል። ነጻ ፕሬስን ሰቅሎታል። ሃሳብን በነጻ ማራመድን በህግና ህግ በማይጠቀስበት አግባብ አግቷል።

አሁን ኦሮሚያ ላይ የተነሳውን የተቃውሞ አመጽ ተከትሎ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ በጥበብ ከማስተናገድ ይልቅ ብረት አንስቶ መግደልን መርጧል። ኢህአዴግ በገደለ ቁጥር አገሪቱ ስጋቷ እየጨመረ፣ የህዝብ ስሜት እየተበላሸ ነው። ይህ እንደሚዲያ ያስጨንቀናል። ኢህአዴግ የዘራው የቂም ዘር በየአቅጣጫው ፍሬው እየጎመራ መሄዱ ያሳዝነናል። ከሁሉም አቅጣጫ መፍትሔ የሚፈልግና ችግር የሚያረግብ አይታይም። አገሪቱ አስተዋይ በማጣቷ በስጋት ደመና እየነፈረች ነው። የአንዱ ለቅሶ ለሌላው ደስታ እየሆነ ነው። ከዚህ በላይ የሚያስጨንቅ ምን አለ? አማራው፣ ደቡብ ክልል ያሉ ዜጎች፣ ኦጋዴን፣ ሶማሌ፣ ሁሉም ጋር ብሶት አለ። የኑሮ ችግር የጠበሳቸው የበይ ተመልካቾች መሯቸዋል። ያልመረራቸው ቢኖሩ ከቁጥር የማይገቡ ባለጊዜዎች ብቻ ናቸው። ይህም ታላቅ ስጋት ነው!!

ምን ይደረግ?

አሁን በኦሮሚያ የተነሳውን የባለቤትነት ጥያቄ ማክበር አማራጭ የለውም። ጸረ ሰላም ሃይሎች ከአመጹ ጀርባ አሉ በሚል መፎከርና ችግሩን ማድበስበስ አያዋጣም። የድሃውን መሬት መቀራመትና መቸብቸብ ይቁም። አርሶ አደሩ በመሬቱ ላይ ብቻ የተመሰረተው የመኖር ተስፋው ይከበርለት። ይህ ሁሉ የኢህአዴግ የመሬት ፖሊሲ ጣጣ ያመጣው ነውና ይታሰብበት። ኢህአዴግ የድሃውን ገበሬ መሬት ከመሸጥ ይቆጠብ። መቃወም ህጋዊ መብት ስለሆነ ኢህአዴግ ተቃውሞን ከመፍራትና እመራቸዋለሁ የሚላቸውን ወገኖች ከመግደል ይልቅ ህዝብን የሚያስቆጣ ተግባር ከመፈጸም ራሱን ያቅብ። “አዲስ የልማት ዘዴ ዘይጃለሁ” ሲል የጉዳዩን ባለቤት በቅድሚያ ያሳምን። ህዝብ ተቃውሞውን ሲገልጸ እየበረገጉ በደም መታጠብ ቆይቶም ቢሆን ዋጋ ያስከፍላልና ይታሰብበት። የጠብ መንጃ ሰላም ዋስትና ቢኖረው ኖሮ ኢህአዴግ እስካሁን ያፈሰሰው ደም በበቃው ነበር። እናም ቅድሚያ ለህዝብ ክብርና ለህግ!! ታሪክ በግልጽ መስክሯል – አውሬነት ለማንም አይበጅምና!!


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ®” አቋም ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. andnet berhane says

    May 7, 2014 04:27 pm at 4:27 pm

    ይህ ስርዓት ከመሰረቱ በንጹሃን ደም የጨቀየ በውሸትና በአሉባልታ የተጠመቀ በመሆኑ፡ ከዚህ እኩይ ተግባሩ መቆም የሚቻለው ሕዝቡ የራሱን እርምጃ ማቀድ ሲችል ብቻ ነው፡ ወያነ ከመሰረቱ ካባቱ ከሻእብያ በመመሳጠር የኢትዮጵያን ሕላዊነት ለማጥፋት የተነሳ ኃይል ነው፡ ነገርግን አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ሊያየውና ሊረዳው ያልቻለ አንድ ትልቅ ውዥምብር ፡ ሁለቱን የጥፋት ኃይሎች ጠበኞች አርጎ በማየት አንዱን ጠላት አንዱን የሃገር ጠባቂ በማለት መስዋእትነት ከፍሏል ፡ ለመሆኑ ይህን እኩይ ዘራዊ አስተዳደር በዚህ አይነት ለመቆየት ያስችለዋልን? ይህ የሁሉም ዜጎች መልስ ይጠይቃል፡እስከመቼ በኢሃደግ ከፋፍለህ ግዛ ምስለኔዎች የልብ ትርታ የሚታወከው ፡ ምርጫው አንድ ነው፡ ሕዝብ መብቱን ለማስከበር ሃገሩን ለመጠበቅ ዋጋ መክፈል ያስፈልጋል እስከመቼ ኢሓዴግ በመግደል እኛም በሞሞት ይቀጥላል። አማራእጭ አለን በሰላምና በውይይት እምቢ ያለውን በመረጠውና በተመካበት መሄድ ሕዝባዊ ግዴታ ነው፡ የጠፋን ልንኖር የማይቻል በመሆኑ ፡ሁሉም ዜጎች ባንድነት የአበው ፈለግ በመከተል ወያነን በታሪክ ብልሹነቱና በሃገር ከዳተኛነቱ ሕዝባዊ እርምጃ መውሰድ ስራአቱን ተገን በማድረግ በጭካኔ የንጹሃን ዜጎች ሕይወት የቀጠፉ ያስቀጠፉ ወደፍርድ ማቅረብ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። በዚህም መሰረት እየጠፋን አንኖርም ታሪካችን የአበው አደራ አጥንታቸው አያስችለንም፡
    ሀገር አለን እያልን ታሪክ ያከበራት፡
    ህዝብ አለን እያልን በደም የገነቧት፡
    ለዘመናት የኖርን ብሄሮች ከበዋት ፡
    በጭቁን መስዋእት ሃገር የሚሸጧት፡
    ታድያ እስከመቼነው እየጠፋን ልንኖር።
    መናገር ተነፍገን መኖር ተበታትነን ፡
    በስራት በስደት መብታችን አጥተን፡
    ወገኔ ተባበር በጽናት ባንድነት፡
    ይወገድ ይህን ስራዓት ተቀዳጅ ነጻነት፡
    ታድያ እስከመቼ እየጠፋን ልንኖር።
    ላለፈው ሁለት ዘመን ያየኸው መከራ፡
    ቤትክን ሲያፈርስ እርሻህን ሲቀማ ፡
    ድበርክን ሲያስደፍር አያት አባት ሲያደማ፡
    ዝምታው ምንይሆን ምነው ስታቅማማ፡፡
    ታድያ እስከመቼ እየጠፋን ልንኖር
    በመንደር ተደራጅ ፍራቻው ይወገድ፡
    በትር ምሳር አንግት ጠላትህ ይታረድ፡
    ሞት ለማይቀር ታፍነህ ከምትወድቅ ፡
    አንገቱን ቀንጥሰው ጠላትነ ይወቅ ።
    ታድያ እስከመቼ እየጠፋን ልንኖር
    ዓለም የሚሰማው ጥቃት ስትሰነዝር፡
    አንተም እንድነሱ ጡንቻህን ስትገትር፡
    በሰላም ለመጣል ተባብረህ ሰልፍ ውጣ፡
    እደ ዩክሬን ትግል እንደ ታይላድ ቅጣ።
    ታድያ እስከመቼ ነው እየጠፋን ልንኖር
    ፈራ ተባ አትበል ቆርጠህ ተነሳ፡
    ዛሬውን አታስብ ነገንም አታውሳ፡
    ባገርህ ባንተላይ የተነሳ ጠላት ፡
    ማንነትክን ክዶ ሲሰነዘ ጥቃት፡
    ታድያ እስከመቼ ነው እየጠፋን ልንኖር
    ቀደምት አባቶችህ የተውልህ ብቃት ፡
    ጋሻው ጦሩ ጎራዴ ከሰገባው አውጣት፡
    እንዲማር ወያኔ ለዘመናት ቅጣት ፡
    አባረህ አውጣው ይህን ያገር ጥፋት፡
    ታድያ እስከመቼ ነው እየጠፋን ልንኖር
    ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወጣት አዛውንቱ ፡
    ያባት የናት ሃገር ድንበሯን ሲገፏት፡
    ሃገርና ክብር አንተነት በድፍረት ፡
    አዋርደው ሲሸጡህ ለአረብ ባርነት፡
    ታድያ እስከመቼነው እየጠፋን ልንኖር
    ወያኔ ጥጋቡ ቦንድ ገዢ ሲያጣ ፡
    ሳአኡዲን ተስማማ ኢትዮጵያዊ ይውጣ፡
    አዋርደው አራክሰው እንደንሰሳ ገለው ፡
    ሴቶችን በወሲብ እንድውሻ ሰረው፡
    ታድያ እስከመቼ ነው እየጠፋን ልንኖር
    አባት የሌለው ቤት ገቢው የበዛበት፡
    ሙስና ገነን ዘራፊው ምንገዶት፡
    ለህዝብ ያልቆመ ለግሉ ተጠምዶ ፡
    መንግስት ባይ ለማኝ የሚኖር ተዋርዶ፡
    ታድያ እስከመቼነው እየጠፋን ልንኖር

    Reply
  2. wassihun says

    May 20, 2014 09:56 pm at 9:56 pm

    arif new ketlubet woyane asmerironal yabay calkefelachihu hager likequ eyetebalne new minew wone tefa

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule