• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ያብለጨለጨ ሁሉ ወርቅ አይደለም!!

January 14, 2013 06:41 am by Editor Leave a Comment

የሁሉም አለቃና የበላይ የሆነውን ሕዝብ ማስደሰት ያኮራል። የሚመሩትን ሕዝብና አገር ከልብ አክብሮ መገኘት ደግሞ ከኩራትም በላይ ነው። ይህንን በኳስ ያበደ ህዝብ፣ አገሩን ከምንም በላይ የሚያፈቀር ህዝብ መወከል ደግሞ ከበጎ ታሪክነቱ በላይ ከሽልማትና ከውዳሴ በላይ ነውና የኢትዮጵያ ልጆች ኩራታችሁ ታላቅ ይሁን። መልካም ዕድል ለአምባሳደሮቻችን!!

ኢትዮጵያዊነት እንዲህ የሚጣፍጥ፣ ማንም ሊወስደውና ሊበርዘው የማይችል ሃያል በረከት መሆኑን ምክንያት ሆነው ላሳዩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ክብር ይሁን ለማለት እንወዳለን። መልካም እድል ለአምባሳደሮቻችን ስንል በቂ ምክንያት ስላለን በፍጹም ኩራት ነው። በእግር ኳስ ፍቅር ለሚቃጠለው የኢትዮጵያ ህዝብ የደስታ ቀን ላመጣችሁ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች የምንመኘው መልካም ምኞት ካለፉት የሰላሳ አንድ ዓመታት ውድቀት ጋር የተቀበረውን የድል አድራጊነት ስሜት ስለቀሰቀሳችሁ በበጎ ታሪክ ማህደር ኢትዮጵያ አትዘነጋችሁምና ዕድለኞች ናችሁ። ለዚያውም በዛሬ ዘመን!!

አገራችንን አንቆ የያዛት የኮሙኒዝም “ሙት መንፈስ” መንግስት ያለበትን ሃላፊነት መወጣቱ፣ ዜጎች የድርሻቸውን ማበርከታቸው እንደ ታላቅ ነገር ተወስዶ “የእግር ኳሱ ውጤት የህዳሴው ስኬት አንዱ አካል” ተደርጎ መወሰዱ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ቢሆንም በሽኝታችሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ በርካታ እንግዶች በተገኙበት የተደረገላችሁ አሸኛኛት የጀግና ነውና ማለፊያ የሚያሰኝ ነው።

በመሸለማችሁና በክብር ስለተደረገላችሁ አሸኛኘት የተደሰትነውን ያህል ያዘንበትም ጉዳይ አለ። በስፖርቱ ውስጥ ተመሽገው ለእውቅናቸው የሚቧቀሱ “ጋንግስተሮች” ያየነው ባለፉት ሃያ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው። ምንጩ በማይታወቅ ሃብት ስፖርቱን የሚረዱ መስለው ፌዴሬሽኑን የከበቡ ጉልበተኞች በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲፈጽሙት የነበረው “ወራዳ” ተግባር የሚረሳ አይሆንም። ጋዜጠኞችን ከማስደብደብ ጀምሮ አገር እስከማስቀጣት የደረሱ “ማጅራት መቺዎች” ትልቅ ሰው መስለውና “ትልቅ ሰው” ተደርገው ስናይ በብሄራዊ ቡድናችን የምንኮራውን ያህል እንዲህ ዓይነት ዱርዬዎች የነገሱበት የክብር አሸኛኘት መደረጉ “ማፊያነትን” የማበረታታት ያህል ይሆንብናልና ህዝብ “ያብረቀረቀ ሁሉ ወርቅ ነው” ወደሚለው ድምዳሜ እንዳያመራ ልንመክር እንወዳለን። ሚዲያዎችም ከስሜት ያለፈውን ካሁኑ በማመሳከር መረጃቸውን እንዲያስተላልፉ ለማስታወስ እንወዳለን።

ሌላው ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስም ለመለገስ ቃል ከገቡት ሌላ “እንዳልታማ ይኸው ቼኩ” በሚል አስቀድመው እንደሚሰጡ የተናገሩትን አስር ሚለዮን ብር መድረክ ላይ መስጠታቸው ተመስገን የሚያሰኝና መጠቀስ ያለበት ነጥብ ይሆንብናል። ከባንክ ያለባቸውን እዳ በመክፈል፣ የጀመሯቸውን ፕሮጀክቶች በመጨረስ፣ አሰራዋለሁ፣ አስገነባዋለሁ በማለት ከዓመታት በፊት ከጓዳ አስከ አደባባይ የገቡትን ቃል፣ በተለይም አዲስ አበባ ስታዲየም ውስጥ “ካንድም ስምንት ስታዲየም እናስገነባለን። አፍሪካ ዋንጫን አገራችን እናዘጋጃለን” በማለት የገቡትን ተስፋና በተለያዩ ገጠሮች ክሊኒክና፣ የሙያ ትምህርት ቤት ለማስገንባት የገቡትን ውዴታ በነካ እጃቸው ለመተግበር፣ አሊያም “ትቼዋለሁ” በማለት አጀንዳውን እንዲዘጉ ለማሳሰብ እንወዳለን። ከሁሉም በላይ ለወደፊቱ ቼክ በመያዝ የፍላጎታቸውን ከማከናወን ውጪ ቃል እንዳይገቡም እንመክራለን። ሰንዳፋ አትሌቲክስ መንደር ግንባታ የዘገየው እንዲሁ ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን ለመስጠት በህጋዊ ቴሌቶን ላይ ቃል ገብተው ዝም በማለታቸው ነውና!!

ለጊዜው ይብቃን። ብሄራዊ ቡድናችን የስነ ምግብ ባለሙያ፣ የስነ ልቦና ባለሙያ፣ የጤና ባለሙያ፣ ወጌሻ፣ ስራ አስኪያጅ፣ የቡድን መሪ፣ አሰልጣኝ በመመደብና እንክብካቤ ተደርጎለት እዚህ ደርሷል። “የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች” በማለት በጀመሩት የመሸኛ ንግግራቸው ወቅት እንደተናገሩት፣ በአንድ ወቅት ገናና ከነበርንበት ስልጣኔ ወርደን የድህነት ተምሳሌት መሆናችንን በቁጭት በማንሳት፣ በአፍሪካ በጀመርነው የእግር ኳስ ውድድር ተገፍትረን ላለፉት ሰላሳ አንድ ዓመታት ተመልካች ስለመሆናችን አውስተዋል። “ቀደም ሲል ጥሩ አጥቂ፣ ጥሩ ተከላካይ፣ ጥሩ ግብ ጠባቂ ነበረን” ሲሉም ያለፈውን የነመንግስቱ ወርቁ ዘመን አወድሰዋል። በመቀጠልም ከነሱ ዘመን በኋላ ማለታቸው ነው “መፋዘዝ ነግሶ ቆይቷል” የመፋዘዙ መነሻ ብዙ ቢሆንም፣ ዛሬ ይህ ድብታ ተሰብሯል። ይህንን የውድቀት ስሜት መስበር በራሱ ታላቅ ድል ነው!! የወደፊቱን ውጤት በጸጋ እንቀበላለን። መልካም እድል!! አቶ ሃይለማርያምም ከመሪ በሚጠበቅ ደረጃ የሚመሩትን ህዝብ ደጋግመው በመጥራት ማወደስዎ ያልተለመደና የረሳነው በመሆኑ ለርስዎም ታላቅ ጅምር ለማለት እንወዳለን። በተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ ሃያ አራት ሚሊዮን ብር ስፖንሰር ያደረገውን የሔኒከን በደሌ ስፔሻል ቢራ ማሞካሸት ከተስፋዎች ሁሉ በላይ ነውና አግባብ ይሆናል እንላለን!!

በደቡብ አፍሪካ በስደት የምትገኙ ኢትዮጵያውያኖች ቡድናችሁን ለመደገፍ በስፋት መነሳሳታችሁ ተሰምቷል፡፡ ታዋቂው አርቲስት ቴዲ አፍሮም ወደዚያው እንደሚያመራ ተናግሯል፡፡ በየአቅጣጫው የወገኖቻችሁ ድጋፍና መልካም ምኞት ብርታ እንደሚሆናችሁ እናምናለን፡፡

በድጋሚ መልካም ዕድል ለዋሊያዎች!!                                                                                               (ፎቶ: ኮንሰርቫቲቭ ባይት)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule