በዋዜማ ዝግጅቶች ሲታጀብ ከርሞ፣ ቅዳሜ የተከበረውን “የብሄር ብሄረሰቦች” ቀንን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎችን በማሳተፍ “አንቀጽ 39 ለዘላለም ይኑር” ብሎናል። እኛም ለዚህ ውለታ ማንን ማመስገን እንዳለብን ለመጠየቅ ተገደድን። ለመልካሙና “የህዝቦች አብሮ የመኖር አለኝታ” ስለሚባለው አንቀጽ 39!
የሶማሌ ብሄር አባል ናቸው። አቶ አብዱላሂ አብዱራሂም ይባላሉ። ዘጠነኛውን “የብሄር ብሄረሰቦች” ቀን አስመልክቶ አስተያየት እንዲሰጡ ተጋብዘው በቴሌቪዥን ብቅ አሉ “… አቅማችሁ ካደገ በኋላ፣ ልጆቻችሁን አስተምራችሁ አቅም ስታዳብሩ ለአንቀጽ 39 ትደርሱበታላችሁ…” እንዳሉዋቸው አቶ መለስን ጠቅሰው ተናገሩ። ትዝታቸው መሆኑ ነው።
ወዲያው አቶ መለስ በወቅቱ እንገነጠላለን ያሉትን የሶማሌ ህዝቦች ሰብስበው ሲናገሩ ታዩ።እንዲህ አሉ “አስራ ዘጠኝ ዓመት የታገልኩበት አላማ እንዳይቀለበስ እፈልጋለሁ። አይቀለበስም ብዬ ቃል ስገባ እናንተን ለመደለል አይደለም። ምክንያቱም ስለመብቱ ምን አልባትም ከናንተ በላይ አስባለሁ። ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም። ከልቤ ስለማምንበት ነው” ሌላ አስተያየት ሰጪ ተከተለ። ተከተለች። “አንቀጽ 39 ለዘላለም ይኑር” ተባለ።
“የኢትዮጵያዊነት ፋይዳው በጣም ጥልቅና መሰረታዊ ነው። 80 ሚሊዮን ህዝቦች አንድ ላይ ስናጨበጭብ እንደመጣለን።ተመጋጋቢ ኢኮኖሚ አለን። ለአገራችን ደህንነትም ሃይል ነው” ይህን ምርጥ አባባልም በተመሳሳይ ፕሮግራም የተደመጠው ከቀድሞው ጠ/ሚ አቶ መለስ አንደበት ነው። በዚህ አያበቃም።
“ተበጣጥሰን የምናገኘው ቴክኖሎጂ ተሰባስበን የተሻለ አይደለም። መሰባሰቡ ጠንካራ ነገር አለው። መሰባሰባችን /አንድነታችን/ የመንደር ንፋስ የሚጠራርገውና የሚበጣጥሰው አይደለም።ስሜት አይደለም። ኢትዮጵያዊነት ጠንካራ የሚሆነው ምክንያት ስላለው ነው” አንጀት የሚያርስ አባባል። ወርቅ ንግግር። ከዚያስ?
“ነጻ ኦሮሚያ” የሚሉ ሰልፈኞች ታዩ። መለስ መጡ። አዲስ አበባ እንደገቡ ሰሞን ነው። እንዲህ አሉ “እኛ ጦርነትን በቴሌቪዥን አናውቅም። እኛ ጦርነትን በወሬ አናውቅም። እኛ ጦርነትን በተቃጠሉ ቤቶች፣ በተጨፈጨፈ ህዝብ ነው የምናውቀው። ከእንግዲህ አንዋጋም። በቅቶናል። ሰልችቶናል። ከእንግዲህ አንዋጋም” በማለት የተናገሩትን አሞጋሾችን እየቀላቀለ ኢቲቪ ትውስታ አቃመሰን።
አቶ መለስ አማራ ናቸው፣ አቶ መለስ ሃረሪ ናቸው፤ አቶ መለስ ወላይታ ናቸው። አቶ መለስ ሶማሌ ናቸው። ወዘተ የሚሉ ሰዎች መለስን ባረኩ። የሶማሌ ክልል አስተያየት ሰጪ የአቶ መለስን ፎቶ ጸሃይ ሲመታው አይተው “ፎቶም ቢሆን መለስ እኮ ነው ጥላ አድርጉለት አልኩ” ሲሉ አሁንም ኢቲቪ አስደመጠ። የሃረሪው አስተያየት ሰጪ ከጭቆናው ብዛት ከምድረ ገጽ ሳይጠፉ አቶ መለስ እንደደረሱላቸው መሰከሩ። አቶ ኩማም ኦነግን እየረገሙ አንቀጽ 39 ዋጁ። ታላቅ ገጸ በረከት እንደሆነ ደጋግመው መሰከሩ። ይብቃን!!
“የብሄር ብሄረሰቦች” ቀን ሲከበር የመጻፍ፣ የመናገር፣ የመደራጀት፣ የመቃወም፣ ህዝብ በፈቀደው መንገድ እንዲደራጅ፣ ይህ ካልሆነ እስከመገንጠል መብት አለው የሚል የተጨመቀ ዓላማ እንዳለው በተደጋጋሚ ሰምተናል። ይህንን እየሰማን አማራው መፈናቀሉ ይነገረናል። ለዓመታት ከኖሩበት እየተሰደዱ ልመና ላይ መሆናቸውን ከበዓሉ ጋር የቀጥታ ስርጭት ሆኗል። ህጻናት ለችግር ተጋልጠዋል። አባት ከጎጆው ወጥቶ የቀን ሰራተኛ ለመሆን ተገዷል። ቤተሰብ ተበትኗል። የታሰሩ አሉ። ይህ ሁሉ የሚሆነው “እገሌን ደገፍክ” በሚል የፖለቲካ ቂም እንደሆነ ሰለባዎቹ ሲናገሩ እየሰማን ነው። ለዚህ ታላቅ ብስራት ኢቲቪ ጆሮ የለውም። “ብሄር ብሄረሰቦች” እኩልነትን የተጎናጸፉበትን ክብረ በአል በቀጥታ በማሰራጨት ስራ ተጠምዷል።
ብዙ ሺህ አስረኞች “ኦነግ ናችሁ” ተብለው በአመለካከታቸው ሳቢያ እየተሰቃዩ ነው። ቅንጅን በገንዘብ ደግፋችኋል የተባሉ ከስራና ከንግድ እንዲወጡ እየተደረገ ነው። በቀረጥና በእዳ ስም የተዘረሩና የቁም ሞት የሞቱ አሉ። ጠኔ የሚቆላቸው የበይ ተመልካቾች ችግር ከጓዳ አልፎ አደባባይ ውሏል። ሃሳብን በነጻ መግለጽ የሚቻል መስሏቸውና መብቱ የተፈጥሮም በመሆኑ የተናገሩ፣ የጻፉ፣ የተቹ፣ “አሸባሪ” ተብለው ተከርችመዋል። ስለ መብት መከበርና ስለ እምነት ነጻነት የሚጠይቁ በጋሪ የሚገፋ የክስ ፋይል ተከፍቶባቸው እስር ቤት እየተሰቃዩ ነው። እነዚህ ሁሉ ሰዎች በኢህአዴግ በራሱ ቋንቋ ብሔር የላቸውም? የህዝብ አካል አይደሉም? ይህ መሰረታዊ ችግር እያለ ከበሮ ይደለቃል። ለስርዓቱ የቀለም ማስዋቢያ እንዲሆን ከየብሄረሰብ የተውጣጡ አጊጠው ሲጨፍሩ ይስተዋላል። በብሄርም ደረጃ ወርደን እንነጋገር ከተባለ በተለይ አማራ ክልል ለወገኖቹ መሟገት ሲገባው ባህር ዳር ላይ አስረሽ ምቺው መጨፈሩ ያሳፍራል። ወገኑንና የሚምልለትን ህዝብ የማይሰበስብ ድርጅት!
መራገምና ማውገዝ ሰልችቶናል። የውግዘት መንገድ ለማንም እንደማይበጅ እናውቃለን። ውግዘት ለቀጣዩ ትውልድ መርዝ የመጋት ያህል መራር ውርስ ነው። ግን ምን እናድርግ? የምናመሰግነው አጣን። ማንን እናመስግን? እንዲሁ በቅዠትና በሚያደነቁር ፕሮፓጋንዳ ኖረን እንለፍ?
“ዝናውም፣ ክብሩም፣ ሃብቱም፣ ሁሉም ያልፋል። ጊዜም ከጥላችን ይልቅ ይበራል። ደጎች ላገራቸው፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለተተኪው ትውልድ መልካም ነገር አስቀምጠው ሲያልፉ በበጎ ሲታወሱ ይኖራሉ። የክፉ ታሪክና ልምድ ማጣቀሻ ከመሆን ለአገርና ለወገን መልካም ስራ ሰርቶ ማለፍ ያኮራል” ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ድረገጽ ላይ የተወሰደ
በለው ! says
” ስለ አንቀፅ ፴፱ የምናመሰግነው ስለ ቀለሙ ብቻ ነው”
*ሁሉም እና እያንዳንዱ ሆድ አደር የፈረሙትን የቀድሞ ፕሬዘዳንት ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ አቀንቃኞች የብሔር ቱልቱላ ነፊዎች አንቀፅ ፴፱ አንብቦ ቂጡን እየመታ ሲጨፍር ሲያስጨፍር ላንቃው እስኪታይ ሲቀሳፍቱ ነበር። አሁንም ያፋሽካሉ ያምታታሉ መች ያስተምራሉ? ሁሉም ዜጎች እንዳያነብቡ፣ እንዳይጠያየቁ፣እንዳይነጋገሩ፣እንዳይወያዩ፣እንዳይረዳዱ በክልልና በራሳቸው ቋንቋ ተብትበው አሰሯቸው አጭበርብረው እኛ ስለ አንተ ታሪክ እናውቅልሃለን አንተ ብቻ “ዝም ብለህ ሸክሽክ!” ብለው ሕዝቡን ጭራ አድርገውት የግል ሀብት አከማቹ! ሥልጣን አገኙ! ቤተሰባቸውን ባለሀብት, ባለዕውቀት አደረጉ! አንዲት ትግራይ ብቻ …ትግርኛ፣ አማርኛ፣ ጣሊያንኛ፣አረቢኛ፣ኦሮሚኛ፣ፈረንሳይኛ፣ቻይንኛ መናገር ሙሉ መብት አላት ሌላው በፌዴራሉ መሥሪያ ቤት የመቀጠር ባለሥልጣን የመሆን ዕድሉ ተከለለ። ዛሬ ቻይና ሕንድ አረብ ባለልጅ ሆነ ቀጥሎም የፌዴራሉ ከንቲባ የቻይና ልጅ እንጂ ጉራጌ,ደቡቡ, ኦሮሞ ወይም አማራ አይሆንም! ዛሬ በተግባር የታየው ከአማራው ክልል ተነጥቆ መሬት ተሠጠኝ የሚለው ኦሮሞ ሕንድ፣፣አረብ፣ቻይናና ቱርክ መሬቱን ወስዶለታል። አማራው ፷ ሺህ ወጣት የሚይዝ ቂጡን የሚያለፋበት አፉን ከፍቶ የሚውልበት ስታዲየም ተሠርቶለታል፣በቀን በቀን ዘፈን ያወጣል ይሸጣል ሱሪውን ዝቅ አድርጎ ይንሳፈፋል። ጉራጌ ከንግድ ዓለም በጠረባ ተመቶ በዝረራ ወድቋል። ወይ አለህ እያለ ያኗኑራል?። ደቡቡ አካባቢውን ጥሎ ደኑን አቃጥሎ ቀዬውን አስረክቦ በቁም እሥር ባዕድ ሲበላ አይኑ ይቁለጨለጫል።ያለቅሳል!!
“ኢፈርት’በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከአፍሪካ አንደኛ ሲሆን የተመሠረተበት ገንዘብ ሳይታወቅ ዓመታዊ ገቢው ሳይታይ ሳይጠና ለሥርዓቱ ማስቀጠያ ያገባውን ድጎማ እንደመንግስት የገቢ ቀረጥ ጉራ ይቸረቸርበታል?? የወያኔ ወታደር የራሱ አስተዳደር ኢኮኖሚና የራሱን መንግስት መሥርቷል። ትግራይ በመተሳሰብ እና በመፈቃቀድ ላይ በተመሠረተ የህግ መንግስቱ አብሮ መኖር ከወሎ እና ከጎንደር መሬት ይወስዳል። ባድሜን ፹ ሺህ የመሃል ሀገሩን የድሃ ልጅ ሆን ብሎ አስፈጅቶበት በነፃ መሬቱን አስረከበ። የአሰብን ወደብ ስንጠይቅ አሸባሪዎች የደርግ ቡችሎች ትምክተኞች ስንባል እነሱ በፈለጉ ጊዜ የፈለጉትን መሬት ለጎረቤት ሀገር በመስጠት የእህል ምርት ወደ መሀል ሀገር እንዳይገባ አፍነው ግረቤት ሀገር በርካሽ ያሸጣል፣የመሀል ሀገር መብራት በፈረቃ ሲያበራ ኬንያ,ሱማልያ, ጅቡቲ,ሱዳን ሌሊቱን የጎጆ እንዱስትሪውን ሥራ አጧጡፈውታል፤ አሰፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሰሊጥ ምርት ወስደው ሽንኩርት ይልኩልናል።አቤት ሀገር አቤት ሕገ-መንግስት አልቀረብንም።ማፈሪያ ሁሉ በለው!
ለመሆኑ ይህ ሥርዓት የማን እና ለማን ነው? ህገመንግስቱ የፈታው ችግር አለ? ወይስ አሠረ? የእኛ ምሁር ዶ/ር፣ ፐሮፌሰር፣ ኢንጂነር፣ ይህንን በቲቪ እና በራዲዮ ተለጥፎ ወሬ ቢተው ምን አለበት? በዚህ ድሃ,የዋህ,ታጋሽ,ጨዋ ሕዝብ ባትሳለቁበት ባታላግጡበት ምን አለ??ሕገ መንግስቱ የአንተ አደለም! አይሆንም! ይህ ሕገ- መንግስት ከመፃፉና ከመፅደቁ በፊት ሀገሪቱ ላይ ሰው እንደነበር እውቅና አይሰጥም አንብብ ዓይንህን ግለጥ በለው!! ከሀገረ ካናዳ
Hager says
There is no means to end this suffering, nothing but war . So if we love our country, if we care for coming generation, we should fight fiercely this brutalism. Now if we say we should fight, some so called” Peace Lover” try to deceive us as War is evil.. By the way “All human knows War is evil but TPLF has not given us no choice. So war ,in our situation, is the lesser evil, otherwise we let our people to enslave by these Racist. I am happy when I see some people start recognize this…it is bitter but it is truth. So let us focus on supporting the fight against TPLF in all forms such as Economically, Psychologically, and so on
..Let us reclaim our birthright.
ababi says
This is a secret divide and rule agenda of woyane.