• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢህአዴግ ሌላ፤ ኢትዮጵያችን ሌላ!!

February 16, 2013 04:25 am by Editor 11 Comments

ሚዲያ ከስሜታዊነት፣ ከስጋና ደም ድምር፣ ከችኩል ውሳኔና ግብታዊነት ነጻ ለመሆን ሌት ተቀን መስራት እንዳለበት ባለሙያዎች አበክረው የሚናገሩት ዓቢይ ጉዳይ ነው። ሚዲያ ስንል ደግሞ ሁሉንም ነው – የኅትመት፣ የምስል፣ የድምጽ፣ የድረገጽ፣ የዲጂታል፣ የማኅበራዊ ድረገጽ፣ … ። ሁሉም ሚዲያዎች አሻግሮ በማየት ህዝብንና አገርን የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው። ጋዜጠኞች ወይም እንደ ጋዜጠኛ የሚሠሩ ሁሉ ከየትኛውም ሙያተኛ በላይ ሃላፊነት ሊሰማቸውም ግድ ነው። ለዚህም ነው በጋዜጠኝነት ሙያ “አመጣጥን፣ አሁንም አመጣጥን፣ አሁንም አመጣጥን … “ባላንስ” አድርግ” የሚባለው!!

ከኢህአዴግ ዓይነ ያወጣ ውሸትና ዝግነት የተነሳ ሁሉንም መረጃዎች የማመጣጠኑ ሙያዊ ሃላፊነት ለመወጣት ፈተና ቢያጋጥምም በከፍተኛ ደረጃ ጥንቃቄ ልንወስድባቸው የሚገባን ጉዳዮች አሉ። ከነዚህ ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋናው የሃይማኖት ጉዳይ ነው። እውነት ለመናገር አሁን ባለው የሃይማኖት ውዝግብ ህዝብ ግራ ተጋብቷል። መሰላቸቱንም እየገለጸ ነው። ሲመረው “አረ መግዱ” ሊል ይችላል። ይህንን የሚለው ደግሞ የማይደግፈው ብቻ ሳይሆን እየተደገፈና እየተሞካሸ ያለው ሊሆን ይችላል፡፡ ሁሉም ወገን!!

እንደሚታወቀው አገራችንን ሊጠብሳት እያዘጋጃት ያለው የ”ጎሳ ፖለቲካ” ደራሲውና ቀማሚ በሞት ቢለዩም የሚያበርደው አስተዋይ መሪ አልተገኘም፡፡ በማስተዋል ማርከሻውን ለሚቀምሙም በቂ ጆሮ አልተሰጣቸውም – ጩኸቱ እጅግ ያደነቁራልና። ከውጪም ከውስጥም የሚረጨው የጎሳና የ”ደም” መርዝ ሳያንስ አሁን ደግሞ በሃይማኖት ተንተርሶ የተጀመረው አለመግባባት አስደንጋጭ ይዘት እንዳለው አያጠያይቅም። ተወደደም ተጠላም ያስፈራል። ኢህአዴግ ባቀናበረው “የድርሰት” ፊልም መነሻ ሳይሆን በበርካታ መረጃዎች የተደገፈ ማሳያ ማቅረብ ይቻላል።

ሁሉም ችግሮች በሰለጠነ መንገድ መፈታት የሚችሉ ቢሆንም ኢህአዴግ በሚከተለው “የደንቆሮና ድንቁርና የወለደው (አስፈሪ) የፍርሃት ፖለቲካ” ሳቢያ ነገሮች እየተካረሩ አገርና ህዝብ ላይ ሲያነጣጥሩ ማየት ተለምዷል። በሌላ አነጋገር በኢህአዴግ ግትርነትና “ያለ እኔ” በሚል በሚከተለውና ራሱም ባመነበት “የበሰበሰ አስተሳሰብ” የተነሱ ችግሮች ተጠራቅመው መጨረሻቸውን ህዝብና አገር ላይ አድርገዋል። በተለያዩ ቦታዎች የደረሰውን አሰቃቂ መከራ፣ ግድያና መፈናቀል አንዘነጋውም። ኢህአዴግ አልሰማ ብሎ ኤርትራን ከኢትዮጵያ በላይ አፍቅሮ የማይረሳ የታሪክ ዋጋ አሳጥቶናል። ተቆጥሮ የማያልቅ የኢኮኖሚ ኪሳራ አድርሶብናል። በወንድሞቻችንና በጭቁን ህዝብ ደምና አጥንት ፈርዷል። ብዙ፣ ብዙ፣ እጅግ ብዙ፣ … ኢህአዴግ ክፋቱና አረመኔነቱ ተዘርዝሮ አያልቅም። በበርካታ ምክንያቶች ኢህአዴግን እንቃወማለን፤ አጥብቀን እናወግዛለን፤ ለሥርዓቱ መለወጥ እና ለፍትሕ እንታገላለን። በኢትዮጵያችን ግን አንጫወትም። በኢህአዴግ መወገድና ማስወገድ ሰበብ ግን በጭፍን በኢትዮጵያችን ላይ አንቀልድም። ኢህአዴግ ሌላ፤ ኢትዮጵያችን ሌላ!!

ከላይ የዘረዘርናቸው ችግሮች ደጋግመን እንደምንለው፣ ሌሎች አገሮች እንደሚያደርጉት በቀናነትና በመቻቻል ሊፈቱ የሚችሉ ነበሩ። በገዢውም ሆነ በተቃዋሚዎች ውስጣዊ አደረጃጀትና ውስጠደንብ የተለየ አመለካከት ማራመድ ወንጀል ባይሆን ኖሮ፤ በልዩነት ላይ በመከራከር ምርጫው ገና ድሮ የህዝብ እንዲሆን በተደረገ ነበር። ግን አልሆነም። ተጀምሮ ነበር፤ ከሸፈ። በመጨረሻም አሁን ለሰለቸንና ላንገፈገፈን  “የጋለሞታ ፖለቲካ” ተዳረግን። እንዘርዝረው ቢባል ስፍራውም ጊዜውም አይበቃምና አሁን አሳሳቢ ስለሆነው ጉዳይ እንቀጥል፡፡

“መብታችን ይከበር” በሚል የተነሱት የእስልምና እምነት ተከታዮች ጉዳይ አንገብጋቢ እንደሆነ ከሚሰማቸው ክፍሎች ተርታ ነን። “ድምጻችን ይሰማ” በሚል የተጀመረው ትግል ዓመት ቢሞላውም ከመርገብ ይልቅ የመወሳሰብ አዝማሚያ እየያዘ ነው። አዳዲስና የከረሙ፣ ዓመት ያስቆጠሩ መረጃዎችም እየተሰሙበት ነው።

በእኛ እምነት የፖለቲካዊ፣ የሃይማኖታዊ፣ የማኅበራዊ፣ የጾታዊ፣ … “ድምጻቸው እንዲሰማላቸው” የጠየቁም ሆነ መጠየቅ የሚፈልጉ “ድምጻቸው ሊሰማ” ይገባል ብለን በአጽዕኖት እናምናለን። አሜሪካዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ “በአንዲት ቦታ የሚፈጸም ኢፍትሃዊነት በሁሉም ቦታ ለሚገኝ ፍትሃዊነት አደጋ ነው” ብለው የተናገሩትን ቃል በሙሉ ልብ ተቀብለን የምናስተናግደው ብቻ ሳይሆን በአገራችን ተግባራዊ እንዲሆንም የምንታገልለት ነው፡፡ እንዲሁም “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም” የሚለውን የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ መፈክር እኛም በሚቻለን ሁሉ ከፍ አድርገን የምንፈክረውና የምንሟገትለት ነው፡፡ ሆኖም የሰው ልጅ መብት ሊገፈፍ እንደማይገባ ስናምንና ለዚሁም ተግባራዊነት እገዛ ስንሰጥ ግን እስካሁን እንዳደረግነው አሁንም ጥንቃቄ እናደርጋለን። ይህም ለመብት መከበር ካለን የጸና እምነት ባልተናነሰ ዋጋ የምንከፍልበት አቋማችን ነው። ግልጽ እናድርገው፡፡

የሙስሊም ወንድሞችና እህቶች ጥያቄ በፊት ለፊት የተቀመጡት ሶስቱ ጉዳዮች ከሆኑ ከየአቅጣጫው እንደሚባለው ችግር የለውም። “መብቴ ይከበርልኝ፣ እርዱኝ” ተብሎ የሌላውን መብት የመጎሸም አዝማሚያ ካለ ግን “ጠርጥር ከገንፎ ውስጥም አለ ስንጥር” እንላለን፤ ካስፈለገም “ወራጅ አለ” እንላለን፤ ካለብን ኃላፊነት በመነሳት ሌሎችም እንዲወርዱ እንመክራለን። ቆም ብለን እንድናስብ እንገደዳለን።

በተለያዩ መገናኛዎች ኢትዮጵያ ላይ በአምላክ (ስሙን በየትኛውም ሃይማኖት በመጥራት) ሲዛት እየሰማን ነው። ኢትዮጵያን በመቆጣጠር ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ወይም ኢህአዴግ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ያስምል እንደነበረው በዚያ መልክ መንግስት ለመመሥረት ዓላማ እንዳላቸው ባደባባይ የሚናገሩትን እያዳመጥን ነው። ጉዳዩ በዴሞክራሲና በህዝብ ፈቃድ ቢሆን ባልከፋ ነበር። አሁን የሚሰማው ፉከራ “ድምጽን አሰምቶ መብትን በማስከበር” አቀባባይነት “እንትኖችን … እናጠፋለን” የሚሉና ለዚህ ዓላማ መሳካት ሁሉም ዓይነት ዝግጅት ያደረጉ የመኖራቸው ጉዳይ ነው። ይህንን ከሚሰብኩት አንዳንዶቹ እስከመመለክም ደርሰዋል። ምንም እንኳ ይህ አመለካከት “የጥቂቶች ወይም የተወሰኑ ግለሰቦች ነው” የሚል መከራከሪያ ቢሰጥበትም፣ “የግለሰቦች” አስተያየት ውስጥ ካለው የክፋት መጠን የተነሳ አገርና ህዝብ ላይ በሚያነጣጥሩ ጉዳዮች ላይ ዝምታን መምረጥ የክህደት ያህል ሆኖ ይሰማናል። አንድም ሰው ቢሆን አገራችን ላይ ሲዝት ማረቅ ይጠበቅብናልና። የጠላነው የሃይልና የማስፈራራት መንገድን ነውና!! በዛቻ፣ በመሃላ፣ … መብትን ማስከበር ወይም ለማስከበር መነሳት ውጤቱ ምን እንደሚሆን ኢህአዴግ ለ21 ዓመታት አሳይቶናል፤ አሁንም እያየን ነው፡፡ በየትኛውም መልኩ ይሁን እንዲደገም አንፈልግም!

ሃይማኖት ያላቸውም ሆኑ ሃይማኖት የሌላቸው … ተደራጅተው አገር ለመምራት የህዝብና የፓርቲያቸውን ፈቃድ ካገኙ እሰየው ነው። ሁሉም ዜጎች የሚናፍቁት ነው፡፡ ከዚህ መንገድ ውጪ ኢህአዴግን ስለምንጠላ በሚል የሳሳ ስሌት አገርንና ህዝብን ታሳቢ ሳናደርግ መጋለብ አንመርጥም። ኢህአዴግን መቃወምና አገርን መጥላት ለየቅል ናቸው። ኢህአዴግ ሌላ፤ ኢትዮጵያችን ሌላ!!

(ፎቶ፡ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Islampeace says

    February 17, 2013 03:45 am at 3:45 am

    No i dont think so!islamic People asked let our voice heard be cause they were clearely made voiceles and theire religion were clearely attemted to be altered (by dirty eprdf,dr shiferaw and mejlise)hence dont try to let others think our agenda is more than protecting our religion fredom.we love our ethiopia and our christian brothers!

    Reply
  2. Ibn Teymiyyah says

    February 17, 2013 06:38 am at 6:38 am

    Yasazinal zarem ye hagerin fikir be mateb ye mitasela be mehonih azignalehu.be ethiopia ke 1 amet belay selamawi teqawomo be madreg ye selamin tirgum meret lay yaweredut eko ethiopiawian muslimoch nachew.yih degmo ye mejemriyaw tarik new.le ezih ewqina le mestet alfelegkim.gin ante yemitilewun hager Lela ehadeg Lela silet eko muslimoch qedmewuh gebtwachew be tegbar eyasayuh new. Be facebook le hager teqorqwari meslo metayet eko qelal new. Muslimochu gin ehadegin be nech bandira mertat chilewal.ye hager guday be mateb ayselam fiqrum be zer ena eminet aygedebim.ewqina ke mestet yiliq gunch alfa ameknyo atigotit.

    Reply
  3. Islampeace says

    February 17, 2013 12:28 pm at 12:28 pm

    I strongly ask the editer to rethink about this article and recommend him to check his information about this islamic protest and remove this (hidden fire) article.ethiopia belongs to all ethipians not for certain religion,race or group.hopefully the writer will read about eprdf sponsered new islamic sect ahbash( organized by dr shiferaw ,berekt “simogn”, sibhat nega) which is imposed on the rest of us forcefully.what about terrerism issue does the writer consider it this is eprdfs one strategy to get support from us and others on expense of poor ethiopian muslims.what about its interferance on orthodox church! We need freedom more than food free mind can cultivate…remember “the truth shall set you free” one love for our mother land ethiopia diversity is beauty!

    Reply
  4. Elias says

    February 17, 2013 09:00 pm at 9:00 pm

    አህባሽ በግድ አይጫንብን ማለት ከመቼ ጀምሮ ነው እስላማዊ መንግስት ማቋቋም የሆነው ደግሞ? መስጂዳችንን እንኳ ራሳችን መምራት ያልተፈቀደልንን ህዝቦች እስልማዊ መንግስት ሊያቋቁሙ ነው ብሎ ሽብር መንዛት ምንኛ ክፉ ሃሳብ ነውስ!

    እኛ ሙስሊሞች ዎያኔችዎች እና ፕሮቴስታንቶች ራሳቸው እንኳ የማያምኑበትን አህባሽ ከሚጭኑብን እንደ አጼ ዮሃንስ ወደ ሚያምኑበት ክርስትና ቢጠምቁን እንመርጣለን። ሁለተኛው አማራጭ ቢያንስ አስገዳጃችን እንኳ ለሰማይ ቤቴ ይሆነኛል ያለው ዕምነት ነውና ደማችንን እያፈሰሰ የሚጭንብን።

    የተበደልነው እኛው፣ ኩላሊታችን እስኪፈነዳ የምንቀጠቀጠውም እኛው፣ የምንገደላውም እኛው ያውም ምንም ሳንላችሁ ከመሬት ተነስታችሁ አህባሽ ሁኑ ብላችሁን። አሁን ደግሞ ጭራሽ ለገዛ ሃገራችን ስጋት ናችሁ ትሉናላችሁ? የኛም የናንተም ሃገር ነው! ስለምም ሆነ ጦርነት የምንጠቀመውም የምንጎዳውም አብረን። ለቀን እንሂድ ብንል እንኳ የት እንሄዳለን። አህባሽ ካልሆናችሁ ብላቹ ብታርዱንም የትም አንሄድ። ያው አርዳችሁ ትጨርሱን እንድሆን እናያለን።

    ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አሉ ዎይዘሮዋ። የምድሩ አንሷችሁ የሳማይ ቤታችንንም ለመንጠቅ መሞከራችሁ ነው እኮ የሚገርመው ነገር።

    Reply
  5. inkopa says

    February 18, 2013 01:35 am at 1:35 am

    Thank you Golgul!!

    Reply
  6. Islampeace says

    February 18, 2013 11:00 am at 11:00 am

    By the way this protest will never end unless eprdf stops its interferance and release these innocent scholars.but shame on those who try to use this islamic wise, deciplined ,neverseen ,protest to have 4killo palace.we ethiopian muslims never stop unless they stop touching us.shame on those ,who live miserable life under this government. we muslim ethiopians at least are able to show our real stand!bravo ethio muslims show to the others how to seek freedom!those brothers who always complain eprdf and do nothing take your notes.

    Reply
  7. ዱባለ says

    February 19, 2013 03:58 am at 3:58 am

    ወያኔ በምንም መልኩ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ያስባል ብሎ መገመት አስቸጋሪ ነው፡: የመሪዎቹ ዋናው እምነት ስልጣን ላይ መቆየት የሚችሉት ሀዝብን ከህዝብ በማናከስ እንጂ ህዝብ አንድ ሲሆን ነው በለው አይደለም:: ለዚህም ነው አገር ወዳድ በሙሉ የወያኔ መሪዎች ለአገር ያላቸውን ተአማኒነት የሚጠራጠረው:: በተለይ መለስ ዜናዊ የተባለ ጎዶሎ ኢትዮጵያን በመውደድ አይታማም:: አሁንም ያሉት መሰሪዎች ስብሐት ነጋን የመሳሰሉ እንዲሁ የስለጣን ጥም ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የመጥላት ስሜታቸው ከፍተኛ መሆኑን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሳይገልጡ አላለፉም:: አሁንም በሙስሊሙ ሕብረተሰብ ላይ የሚያደርጉት ወከባ ይሄንኑ ፍላጎታቸውን ለማራመድ ይሆን ወይንም የአክራሪነት ጥንስስ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሶ ይሁን ማወቅ አይቻልም:: ነገር ግን ድርጊታቸው ግልጽ የሆነ የመብት ጥሰት ነው:: ርምጃቸው ግን አክራሪነትን የሚጠናክር እንጂ የሚያጠፋ አይመስልም:: የተቀረው ህብረተሰብ ትልቅ አጣብቂኝ ውስጥ ነው ያለው:: አክራሪዎች የሉም ብሎ ሸምጥጦ መካድ አይቻልም:: ህብረተሰቡ መፍትሄ ለመስጠት ግን አቅምም ሆነ ግብአት የለውም:: አሁን ብቅ ብቅ እያሉ የሚታዩት የሙስሊም አክራሪዎች ከአገሬ በፊት ሀይማኖቴ እያሉ የሚፎክሩ ከንቱዎ ች በጣም አሳሳቢ ብቻ ሳይሆኑ አስፈሪም ናቸው:: የሙስሊሙ ህብረተሰብ ይህንን ለይቶ ተረድቶ መንግስት መብታቸውን እንዲያከብር መታገል በተጓዳኝም አክራሪዎች ትግላቸውን ወዳልታሰበ አቅጣጫ እንዳይወሰዱት ነቅተው በመጠበቅ አክራሪዎችን ማጋለጥ አስፋላጊ ይመስለኛል:: በአጭሩ የጎግል ማሳሰብያ ነገሮች ፈር ሳይለቁ መስመር ማስያዙ ወቅታዊ ነው::

    Reply
    • Islampeace says

      February 19, 2013 11:11 pm at 11:11 pm

      No sign of tererrism,extrimism dubae ,how could u be sure.remember actualy there is no evidence except jahidawi harekat ,false tape.dont bark like dog!

      Reply
  8. ዱባለ says

    February 20, 2013 09:29 pm at 9:29 pm

    ወንድሜ Islampeace
    ማንም በንጽሁ አእምሮ የወያኔን ፕሮፓጋንዳ አይቀበለም:: ወያኔማ የተጨበጠ ማስረጃ ማቅረብ ስላልቻሉ በመንግስት ገንዘብ ይቀልዳሉ:: ነገር ግን ነጻ ሚዲያው ለሽብርተኞች መኖር የተሻለ ማስረጃ ካለው ወያኔን ለመቃወም ሲባል ብቻ ከህዝብ ጆሮ ማንኛውንም ዜና መደበቅ ወይም ማጣመም የለበትም ነው እየተባለ ያለው:: ይህንን አባባል በበኩሌ እስማማበታለሁ::

    Reply
  9. Daniel Hein says

    February 22, 2013 01:01 am at 1:01 am

    Ethiopins Musslems and chrstian are one bloud exept our Faith, No one can tell us rebish story.

    We know echather and we Love echather.Good love all of us.

    Reply
  10. SALAHADIN ABDUREHMAN says

    March 12, 2013 11:25 pm at 11:25 pm

    Ethiopian muslims are not terrorists but we are showing way of peacefull demonstration to EPDRF & peoples who want to learn from us.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule