አገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ አስር የሚሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሮች አስተዳድረዋታል፡፡ ከእነዚህ መካከል በተለየ ሁኔታ ከሚወሱት አንዱ ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ናቸው፡፡
በጣልያን ወረራ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ በአውሮጳ ያደረጉት ተጋድሎ እጅግ ከፍተኛ ለመሆኑ በተለያዩ ቦታዎች ሲጠቀስ የሚሰማ ነው፡፡ አርበኞቻችን በአገር ውስጥ የሕይወት መስዋዕትነት ሲከፍሉ አክሊሉ ሃብተወልድ በአውሮጳ የከፈሉት መስዋዕትነትና ኢትዮጵያን ለማዳን የሠሩት ሥራ ተጽፎ የማያልቅ ታሪካቸው ነው፡፡ ያላንዳች ማጋነን የዲፕሎማሲውን ሥራ ያለመታከት ከግብ ያደረሱት አክሊሉ ነበሩ፡፡
በተለይ “የአክሊሉ ማስታወሻ” በተባለው የራሳቸው ታሪክ በከፊል የተወሳበት መጽሐፍ ላይ የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆር እና የፈረንሣዩ ጠ/ሚ/ር ላቫል ከኢትዮጵያ ክፍላተሃገራት አብዛኛው የሆነው ሐረር፣ ሲዳሞና ባሌን ጨምሮ ለጣሊያን እንዲሰጥ የተቀረው ጎጃም፣ ጎንደርና ትግራይ ለኢትዮጵያ እንዲሆን በምስጢር ያዘጋጁትን “የሆር-ላቫል” ስምምነት ሰነድ አክሊሉ በለንደን በጋዜጣ ላይ ይፋ እንዲወጣ በማስደረግና በእንግሊዝ ፓርላማ ውስጥ ከፍተኛ ሙግት በማስነሳት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆር እያለቀሰ ይቅርታ የጠየቀበትና ሰነዱም ውድቅ የተደረገበት ውሳኔ ጠ/ሚ/ር አክሊሉ ለአገራችን ከሰሩት ስፍር ቁጥር ከሌለው ውለታ አንዱ ነው፡፡
ከድል በኋላም አክሊሉ በውጭ ጉዳይ ቀጥሎም በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገራቸውን ባገለገሉባቸው ዓመታት ሁሉ ከሚጠቀሰት መካከል የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ በዲፕሎማሲው መድረክ ላይ ጣሊያን በከፈተችው ጦርነት ተባባሪ በመሆን ያስቸግሩ ለነበሩት የላቲን አሜሪካ አገሮች አክሊሉ የሰጡት ትንቢታዊ ማስጠንቀቂያ ነበር፡፡ በመንግሥታቱ ማኅበር ፊት እንዲህ ነበር ያሉት፡-
“በዚህ አጋጣሚ ለባልደረቦቼ የላቲን አሜሪካ አገሮች ተወካዮች፣ በተለይም ለአርጀንቲናው ልዑክ እጅግ በጣም ከባድ ፋይዳ ስላለው ጉዳይ የማስተላልፈው መልዕክት አለኝ። ዛሬ አገሬ ከግብጽ እና ከላይቤሪያ ጋር ሆና እናንተ ከጣልያን ጋር በማደም የአፍሪቃን ሕዝቦች ለመጨቆን የምትጫወቱትን ሚና በጥንቃቄ እየተመለከትን ነው። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ግን እዚህ ያለነው ሦስት አፍሪቃውያን አገሮች በአስር እጥፍ በዝተን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ተገቢ መቀመጫችንን እንይዛለን። ያን ጊዜ እኛ እንደናንተ ሳይሆን፣ ለዓለም ሰላም ድጋፍ እና ፍትሐዊ ፍርድ ድምጻችንን እንደምናሰማ ጥርጣሬ የለኝም።”
እንዳሉትም በርካታ የአፍሪካ አገራት በያኔው የመንግሥታት ማኅበር ውስጥ አባል በመሆን የኃይሉ ሚዛን ላይ ተጽዕኖ ማድረግ ጀመሩ፡፡
ከዘመነ አክሊሉ ወደእኛ ዘመን በፍጥነት ስንመጣ የምናገኘው ህወሓት/ኢህአዴግንና መለስን ነው፡፡ ባሳለፍናቸው 21ዓመታት መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ ስፋቱም ሆነ ጥልቀቱ ይህ ነው ተብሎ ሊዘረዘር የሚችል አይመስለንም፡፡ እርሳቸው ግን የቆፈሩትን ጉድጓድ ጥልቀቱንም ሆነ ስፋቱ ሳይናገሩ እንዴት እንደሚደፈን ለባልደረቦቻቸውም ሳያሳውቁ አልፈዋል፡፡ ዛሬ ኃይለማርያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚኒስትር ወንበር ላይ እንዲቀመጡ ተሰይመዋል፡፡ አቀማመጣቸው እንዴት ይሆን?
አቶ ኃይለማርያም “ምዕራፍ” ለተሰኘ መጽሔት “ሕዝብን እና አገርን በመልካም አስተዳደር የማገልገል” የጸጋ ስጦታ እንደተሰጣቸው በተናገሩት ቃለምልልስ ላይ የሚጸጸቱበትን ውሳኔ አስተላልፈው እንደሚያውቁ ለተጠየቁት ምላሽ “አንድ ጥፋት ሰው ላይ ከሚደርስ ብዙ ጊዜ ራሴን ብጎዳ እመርጣለሁ … እስካሁን ድረስ ጎድተኸኛል ብሎ የተናገረኝ ሰው የለም” በማለት ነበር የመለሱት፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስም የባቢሎን ጠ/ሚ/ር እንደነበረው “ዳንኤል መሆን መልካም እንደሆነ” ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ ባደረጓቸው ንግግሮች ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ የመለስን ራዕይ፣ ዓላማ፣ ሃሳብ … የጋራ አመራር … የሥራ መለያቸው እንደሆነ ነግረውናል፡፡
ዳንኤል በባቢሎን በሥልጣን በነበረበት ጊዜ “ስለኃጢአታችንና (በደላችን) የሩሳሌም (እስራኤል) እና ሕዝብህ በዙሪያችን ላሉት ሁሉ መሰደቢያ ሆነዋል … ፊትህን አብራልን” በማለት ነበር በቅኝ ግዛት ሥር ስለወደቀችው አገሩ ነጻነት የማለደው፡፡
አክሊሉ ኢትዮጵያን ባገለገሉባቸው ዓመታት ከተናገሯቸው በርካታ ንግግሮች መካከል ተጠቃሽ የሆነው “የደረሰው ይድረስ ደካማ ሆኜ መታየት አልፈልግም፡፡የሀገሬን ጥቅምና መብት የሚነካ መስሎ ከታየኝ መናገሬን አልተውም” የሚለው አንዱ ነው፡፡ ይህም ከቃል አልፎ በሥራቸው ተተርጉሞ ህያው ሆኖ ይኖራል፡፡
መለስ ላለፉት 21ዓመታት ሲነግሩን የነበሩትን “ስድብ ተኮር” ቃላት መድገም ባያስፈልግም “የአዝማሪ” ያሉትን የኢትዮጵያን ታሪክ እርሳቸውም በህይወታቸው “የሚሊኒየም፣ …” እያሉ ሲያዜሙት መስማት አሁን ማስታወሻችን ነው፡፡
ኃይለማሪያምስ? እንደ አክሊሉ፣ እንደ መለስ ወይስ እንደ ዳንኤል ይሆኑ? የእኛ ምክር መጀመሪያ እንደራሳቸው እንዲሆኑ፤ ቀጥሎም እንደፖለቲከኛ እንደ አክሊሉ እንደ ሃይማኖተኛ ደግሞ እንደ ዳንኤል እንዲሆኑ ነው፡፡ እርሳቸው ግን እንዴት እንደሚሆኑት ዛሬ ጀምረውታል፡፡ ሕዝብ ማስተዋል፤ ታሪክም መመዝገብ ጀምሯል፡፡
Ta M says
Leulu Igziabher haylna tsega mastewalnm yistachew le PM Hailemariam. May the God of Moses lead his way to free all the people from oppression and new hope for the people of Ethiopia. I hope HD will not be a person of honest, respect and patient in deciding good for the people who truely needs fair and good governance.
I appreciate the article in this particular time remembering the past leaders with the newly appointed PM. Go on in providing such kind of resourceful information. May God bless you and my country forever!
Zienamarqos says
<<>>:- እጅግ:በጣም:ጥሩ:አመዛዛኝ:ጽሑፍ:ነው::”የእኛ ምክር መጀመሪያ እንደራሳቸው እንዲሆኑ፤ ቀጥሎም እንደፖለቲከኛ እንደ አክሊሉ እንደ ሃይማኖተኛ ደግሞ እንደ ዳንኤል እንዲሆኑ ነው”፡፡ያላችሁትን:ጠቃሚ: ምክር:በመለገሳችሁ:እናመሠግናለን::ሀገረችን:በዓለማት:ተደርጎ:የማይታወቅ:አስተዳደር:ውስጥ:ተዘፍቃ:እየዛቀጠች:ነው::
ከዚህም:ለመውጣት:አምላክ:ይታደግልን::በመንግሥት:ሥራ:ላይ:ሆኖ:የዜጎቿን:ተቋም:በመጋፋትና:በመንጠቅ:የሚነገድባት:
ሀገር:ኢትዮጵያችን:የመጀመሪያዋ:ናት::ሕቧም:በድንቁርናና:ረሃብ:በአንድ:ጎጠኛ:የትግሬ:ወያኔዎች:እዬተሠቃዬ፣ከቆሻሻ፡እየለቀመ፣
በትርፍራፊ፡ጉርሻ፡አንድ ግዜ፡ተመግቦ፡አዳሪ፣ተሰዳጅና፡ወደ፡ስደት፡በሚጓዝበት፡ወቅት፡በዬመንገዱ፡ሟች፡ የሆነባት፡ሀገራችን፡ኢትዮጵያ፡ በመሆኗ፡ከፍ፡ያለ፡ሐዘን፡ይሰማናል።ከዚህም፡አምላክ፡እንዲገለግለን፡ተግተን፡በኅብረት፡እንጸልይ።
mezekir zelalem says
please lets not be perenially foolish haile mariam or hagos or who ever in what ever name, will do nothing different from melles as long as the woyane anti ethiopian state machinery is in place. Lets fight to realize an all inclusive democratic system under a united Ethiopia. Let’s rise up against all kinds of ethnocenteric anti Ethiopian political forces; those who aspire to re dismantle Ethiopia by shabia style refurendum. TPLF/EPLF/ OLF ( all versions) and their running dogs in the diaspora such as Ginbot/timret…have to be stopped.
ከአዲስ ተስፋ says
መልካምና የበሰለ አስተዋይነት ያለዉ ምክር ነዉ ጠ/ሚኒስትር ሃ/ማሪያም ይደርሳቸዉ ከሆነ እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አለኝ የእኔም ምክር ያሉበት ሁኔታ በጣም ፈታኝና አስቸጋሪ እንደሆነባቸዉ እገምታለሁ ሆኖም የፈለገዉ ቢሆን እራሳቸዉን መሆኑ የሚሻል መሆኑን ላሰምርበት እወዳለሁ የእራስወት እራይ ይኑርወት እንዳለፉትም እንደወደፊቶችም እንደ ኢትዬጵያዊነትዎት በታሪክ አጋጣሚ እንጅ ከማንም በችሮታ የተሰጠወት አድርገዉ አይዉሰዱት በቅርቡ አንዳንድ ትቢተኞች ጠቅላይ ሚኒስትር መሆንወን አስመልክቶ በተናገሩት”አማራንና ኦርቶዶክስን ከስልጣን ዉጭ አድርገነዋል” የሚለዉ የስባት አባባ አማራ ባለመሆንወና ኦርቶዶክስ ባለመሆንወት የተቸረወት ለማስመሰል ተሞክሯል ይህ አባባል እርስወን ምን ለማለት እንደሆን አያጡትም የኢትዮጵያ ሕዝብም ይህን ተገንዝቧል እርስወም ከእርሰዎ የሚፈልገዉ ምን እደሆነ የሚረዱ መሰለኝ ሕዝብ ለዉጥ ይፈልጋል ስለዚህ የእራስዎትን እራይ እንጅ የሰዉ እራዬ አንጠልጥለዉ የትም አይደርሱም ስለዚህ ዘር፣ ሃይማኖት ሳይሉ ጠንካራ አገር ወዳድ ወገኖችወን ምሁራንና የአገር ሽማግሎች በዙሪያወት ያሰባስቡ ይምከሩ ከዚያም የእራስዎትን እራይ ይዘዉ ብቅ ይበሉ ይህም የተሳካ እንዲሆንልወት የኢትዮጵያ አምላክ የአባቶቻችን በእዬ እምነት ቦታወች በቤተስኪያንና በገዳማት በመስጊዶች ለፈጣሪያችን ስለአገራችን የሚያሰሙት ፀሎት ይርዳወት አሜን!
Sergute Selassie says
ሁሉንም መሆን አይችሉም። ማንነታቸው ተሰዷልና።
Birhanu Kebede says
As long as TPLF (EPRDF) is in power I don’t think the party prioritizes peace, democracy and good governance for Ethiopia rather they oppress the people to elect them for another term. I remember When Addisu Leggese was interviewed by Ethiopian TV he said, “The 2005 election has taught us that the people needed change so we should listen to the people and we should give attention to the people.” As far as I understand the 2005 election told them that they (TPLF (EPRDF)) are incapable of leading the people of Ethiopia. They should have given the power to the opposition party that had been elected by the people. In addition, prime minster Hailemariam Desalegn and Meles Zenawi are two faces of a coin so how come the current prime minister will move a step forward to listen to the people of Ethiopia. Instead, he gives a proper attention to Bereket and other TPLF (EPRDF) members whether they want him to do them a favor. Being serve as a speaking tool how much a stupid and litter job it is. As an academician it is so shame on him and his family. Please wake up the people of Southern Ethiopia you should share the blame the guy is from there. You guys tell him that he should struggle for the people not to fight to save TPLF. Tell him to look at the well known person, Obang Metho. He is from the Southern Part too. He has been doing extraordinary jobs tirelessly for his country Ethiopia