“አንድነትን ስንመሰርት በቅንጅት ወቅት ስለሰራነው ጥፋትና የፖለቲካ ስህተት የገመገምነው ነገር የለም” ዶ/ር ያዕቆብ ሃ/ማርያም አንድነት ፓርቲን ከቅንጅት ጋር በማነጻጸር ከተናገሩት፡፡
በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲና ድርጅቶች መዋቅራዊ ጥንካሬና ደጋፊዎቻቸውን አስተባብረው ውጤት ማስመዝገብ ያለመቻላቸው ጉዳይ አነጋጋሪ ነው። ተቃውሞ በኢትዮጵያ በፓርቲ መሪዎችና በገዢው ኢህአዴግ መካከል የሚደረግ እሰጥ አገባ ካልሆነ በስተቀር በደጋፊዎች ተሳትፎ ገዢውን ፓርቲ የማስገደድና እጁን የመጠምዘዝ ደረጃ ላይ ደርሶ ሊታይ አልቻለም። ከቅንጅት መፈራረስና ልዕልናው መክሰም ጋር የህዝብ ስሜትም አብሮ ተዳፍኗል የሚለው አስተያየት ሚዛን የደፋ የሚሆንባቸው የበዙት ለዚሁ ነው። በድርጅት ደረጃ ችግሩን ተመልክተው ስለመታደስ የሚያስቡ ስለመኖራቸው ግን ለረዥም ጊዜ አልሰማንም።
በኢትዮጵያ ህዝብን ለትግልና ለእምቢተኝነት የሚያነሳሱ ጉዳዮች ሞልተው የፈሰሱ ቢሆንም ህዝብ በስርዓቱ ከመበሳጨት የዘለለ እንቅስቃሴ አለማድረጉ ስርዓቱ ከዘረጋው የአፈና መዋቅር ጋር የሚያገናኙት ቢኖሩም በዋናነት የተቃዋሚዎች ድክመት ጎልቶ እንደሚታይ አሁን አሁን ይፋ እየሆነ ነው። በተለይም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሰሞኑን “የግል አስተያየቴ ነው” በማለት ያቀረቡት ጽሁፍ የችግሩ ቁልፍ ነውና ሁሉም ወገኖች አሰራራቸውን ሊፈትሹ እንደሚገባ ይሰማናል – አሁን!!
“ከኔ አመለካከት ጋር የማይስማሙ እንዳሉም እገነዘባለሁ፡፡ በበኩሌ ከኔ ጋር የማይስማሙትን አከብራለሁ፡፡ ሃሳባቸውንና አመለካከታቸውን ባልጋራና ባልስማማባቸውም እነሱንም ሆነ ሃሳባቸውን፣ አመለካከታቸውንና አቋማቸውን አዳምጣለሁ። አከብራለሁ፡፡ የመረጃ ስህተት ካለ ስህተቴን ለመቀበልና ለማረም ዝግጁ ነኝ፡፡ የኔን ሃሳብ፣ አመለካከትና አቋም የማይጋሩት ግን እንዲያዳምጡኝና እንዲያከብሩልኝ አደራ እላለሁ” ሲሉ የወቅቱን የአገራችንን ሁኔታና የወደፊቱን የትግል አቅጣጫ በተመለከተ ለመወያየት በተጠራ ስብሰባ ላይ የአንድነት ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ባቀረቡት ንግግር የተናገሩት ነው። ሌላስ ምን አሉ?
“ኅብረሰባችንን ስናይ ብሶተኛና የማጉረመርም ደረጃ ላይ እንጂ ተናድዶ ንዴቱን በእንቅስቃሴ ለማሳየት ዝግጁ የሆነበት ደረጃ ላይ የደረሰ አይመስልም፡፡ ብዙ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ችግሮች አሉበት፡፡ ይህንን ሰቆቃውንና ብሶቱን ያማርራል፡፡ በይፋና በአደባባይ አይገልጽም፡፡ ብሶቱ በማጉረምረም ደረጃ የሚገልጽ ነው እንጂ በአጠቃላይ ወደ ኅብረተሰባዊ ንዴት አልተለወጠም፡፡ የተናጠል ንዴቶች አልፎ አልፎ ቢገለፁም ሠፊና የአጠቃላይ የኅብረተሰቡ አልሆኑም፡፡ እነዚህ የተናጠልና ትናንሽ ንዴቶች ወደ ተደራጀና የተቀናጀ ሕዝባዊ እምቢተኝነት እና የእምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች አልተለወጡም፡፡ በሌሎች አገሮች በዳቦ ወይም በነዳጅ ዋጋ ላይ ትንሽ ጭማሪ ከታየ የኅብረተሰቡ ንዴት ይገነፍላል፡፡ በኛ ህዝብ ዘንድ ግን ይህ አይታይም፡፡ ምልክት ከታየም ጥቂት፣ የተናጠል፣ ያልተደራጁና ያልተቀናጁ ናቸው” ነበር ያሉት።
አዎ!! ያለመደራጀት ችግር፣ የግንዛቤ ችግር፣ ደጋፊን አሳምኖ የመምራት ችግር፣ ከስህተትና ከውድቀት ያለመማር ችግር፣ የተሃድሶ ችግር፣ የእውቀት ተሃድሶ ችግር፣ የራዕይ ችግር፣ በስድብና ተቃውሞ ላይ ያተኮረ ትግል፣ ፍረጃና ማግለል ላይ የተንጠለጠለ የትግል ጉዞ፣ ካለፈው ያለመማርና ይሉኝታን ያዘለ ትግል፣ በግልጽ ራስንና ተሞክሮን ያለመገምገም ችግር፣ የተድበሰበሰ አቅጣጫ የመከተል ችግር፣ እንደኔ አስብ የሚል አባዜ፣ ድርጅትህን አፍርሰህ እኔ ጋር ተጠቃለል የሚል ሌላውን ያለማክበር ችግር፣ እኛ ያልባረክነው የተቃውሞ መንገድ ውግዝ ነው የሚል የትምክህት ስሜት፣ በተመሳሳይ አጀንዳ እየተመሩ መቧደን፣ ማነስ፣ ትንንሽ መሆን፣ ከትግልና ከትግሉ መስመር ይልቅ ወንበርና ስልጣን መናፈቅ፣ ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ በውይይት ከማስወገድ ይልቅ በሃሜትና በማሳጣት መስመር መረባረብ … የሚጠቀሱት በሽታዎች ናቸው። በተግባር እንደታየውና ሁሉም እንደሚመሰክሩት እነዚህ ችግሮች የተቃዋሚውን ጎራ ጨረቃ ላይ ጥለውታል። ባለበት እንዲረግጥ አድርገውታል። በዚህም ሳቢያ አብዛኞች ከየትኛው ወገን እንደሚሆኑ መወሰን አቅቷቸዋል። በኛ እምነት ይህኛው የኅብረተሰብ ክፍል ታላቅና ሃይል ያለው ስለሆነ በእውቀት ተሃድሶ ወደ ትግሉ የሚገባበት መንገድ መቀየስ አለበት። የተከፈለው ዋጋ ተከፍሎ!!
“እውቀት የሌለው፣ መረጃ የማያገኝ ህዝብ፣ የተደራጀና የተቀናጀ አደረጃጀቶች የሌለው ሕዝብ ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፡፡ ከፖለቲካ ድርጅቶች የሚጠየቀውና የሚጠበቀው የተናደደ ኅብረተሰብን መፍጠር ሳይሆን መረጃ የሚያገኝ፣ እውቀት ያለው፣ የተደራጀና ድርጅቶቹ የተቀናጁ ኅብረተሰብ መፍጠር ነው” ሲሉ አሰተያየታቸውን ያሰፈሩት ዶ/ር ነጋሶ ደግ ብለዋልና ጆሮ ላላቸው ታላቅ መልዕክት ነው።
ስለሆነም የወደፊት የትግል አቅጣጫችንን የማሳወቅ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የማደራጀትና፣ ድርጅቶችን የማቀናጀት ሥራን ማዕከል ያደረገ መሆን እንዳለበት ልምዳቸውንና በግልጽ የተመለከቱትን አስታከው ያቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ በስፋት መድረክ ሊሰጠው የሚገባ ነው ብለን እናምናለን። በእውቀት ላይ የተመሰረተ ትግል እንደገለባ መንሽ በተመለከተ ቁጥር አይቦንም፤ እውቀቱም ቀላል ነው። በየወቅቱ የሰለቸንን የመቡነን አደጋና ከድርጅት ወደ ድርጅት የመገላበጥ እንዲሁም ስም እየቀየሩ ብቻ ለቁጥር የሚያዳግት ድርጅት መመስረት የሚቆመው ይኸው የእውቀት ተሃድሶ ተግባራዊ ሲሆን ነው። እውቀቱ በኮሌጅ ወይም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጥ አይደለም። በእውነተኛነትና በቅንነት ላይ የተመሠረት እውቀት ነው፡፡ ከራስ በራስ የሚቸር ቀናነትን መሰረት ያደረገ ለራስ የመታመን ጥያቄ ነው። ሰው ምን ይለኛልን አውሎቆ የጣለ እውቀት ነው፡፡ በጥቅምና በወዳጅነት የሚደለል ሳይሆን በሐቀኝነት ዓለት ላይ በመተማመን ጸንቶ የቆመ እውቀት ማለት ነው፡፡ ለራሱ የሚታመን የትግል መስመርና ታጋይ ራዕይ አለው። ለለውጥ ንቅናቄ መሪውን አይጠብቅም፡፡ ያነገበው ራዕይ እያንደረደረ የድሉ በር ላይ ያደርሰዋል። ከሁሉም በላይ የነቃና በመረጃ የታጠቀ ህዝብ ድርሻውን ያውቃል። መብቱን ለማስከበር የትኛውንም ወገን የማስገደድ አቅም ያዳብራል። እንዲህ ያለ ህዝብ በተፈጠረ ቁጥር የአምባገነኖች ጡንቻ እየሰለለ ይሄዳል። ልባቸውም ይርዳል። እንዲህ ያለው የእውቀት ተሐድሶ ከድርጅት ወይም ከፓርቲ አይመጣም፡፡ በስብሰባ ብዛትና በጥናትና ምርምር ምጥቀት አይከሰትም፡፡ ግንኙነት ማድረግ በሚቻልበት አጋጣሚ ሁሉ ወሬ በመውቀጥ በተዓምር ብቅ አይልም፡፡ እንዲያውም ይህንን ዓይነቱ አካሄድ በሙሉ የራስ ማንነትን በማጥፋት በአጀብ፣ በቡድን ተግበስብሶ ለመመራት ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ ተሃድሶው ከራስና በራስ መጀመር አለበት፡፡ እያንዳንዱ ሰው የሚፈልገውን በደመነፍስ ሳይሆን በእርግጠኝነት ማወቅ አለበት፡፡ ስለዚህ ከመምራትም ሆነ ከመመራት፤ ከመደራጀትም ሆነ ከማደራጀት በፊት እውቀት ይቀድማል! ለዚህ ደግሞ ተሃድሶ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም አሁንም ደግመን የምንለው ቅድሚያ ከራስ የሚጀመር ተሃድሶ ባስቸኳይ!!
bibi says
ኅብረሰባችንን ስናይ ብሶተኛና የማጉረመርም ደረጃ ላይ እንጂ ተናድዶ ንዴቱን በእንቅስቃሴ ለማሳየት ዝግጁ የሆነበት ደረጃ ላይ የደረሰ አይመስልም፡፡ አዎ ግን መቼም ተናድዶ ንዴቱን በእንቅስቃሴ ለማሳየት እንደማይነሳ ደሞ መታወቅ አለበት፡፡
የኛ ህዝብ ምንም እንኳን የመረረ ኑሮ እየኖረ ቢሆንም: የባሰ እንዳይመጣ ስለሚፈራ ብቻ አለማመጽን ይመርጣል፡፡ This is Habesha and you can’t help it.
dawit says
Exactly true.
……..በእውቀት ላይ የተመሰረተ ትግል እንደገለባ መንሽ በተመለከተ ቁጥር አይቦንም፤ እውቀቱም ቀላል ነው። በየወቅቱ የሰለቸንን የመቡነን አደጋና ከድርጅት ወደ ድርጅት የመገላበጥ እንዲሁም ስም እየቀየሩ ብቻ ለቁጥር የሚያዳግት ድርጅት መመስረት የሚቆመው ይኸው የእውቀት ተሃድሶ ተግባራዊ ሲሆን ነው። እውቀቱ በኮሌጅ ወይም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጥ አይደለም። በእውነተኛነትና በቅንነት ላይ የተመሠረት እውቀት ነው፡፡ ከራስ በራስ የሚቸር ቀናነትን መሰረት ያደረገ ለራስ የመታመን ጥያቄ ነው። ሰው ምን ይለኛልን አውሎቆ የጣለ እውቀት ነው፡፡ በጥቅምና በወዳጅነት የሚደለል ሳይሆን በሐቀኝነት ዓለት ላይ በመተማመን ጸንቶ የቆመ እውቀት ማለት ነው፡፡ ለራሱ የሚታመን የትግል መስመርና ታጋይ ራዕይ አለው። ለለውጥ ንቅናቄ መሪውን አይጠብቅም፡፡ ያነገበው ራዕይ እያንደረደረ የድሉ በር ላይ ያደርሰዋል። ከሁሉም በላይ የነቃና በመረጃ የታጠቀ ህዝብ ድርሻውን ያውቃል። መብቱን ለማስከበር የትኛውንም ወገን የማስገደድ አቅም ያዳብራል……..
MINILIK SALSAWI/FACEBOOK says
ከተሃድሶዎች ሁሉ የእውቀት ተሃድሶ ካልቀደመ መሪው፣ ተመሪውና ድርጅቱ ሁሉም ተያይዘው ሲጓተቱ 21ኛው ክፍለ ዘመን ይጠናቀቃልና የሚቀድመውን ማወቅ ብልህነት ይሆናል። ለሁሉም የእውቀት ተሃድሶ በቅድሚያ! ለዲያስፖራው ሆነ ለአገር ቤቱም ወገን የእውቀት ተሃድሶ በቅድሚያ!! የእውቀት ተሃድሶ ባስቸኳይ፣ የእውቀት ተሃድሶ የዘለቀው ደጋፊና ዜጋ ሲነፍስ አብሮ በነፈሰበት አይነፍስምና!!
http://minilik-salsawi.blogspot.com/2012/11/blog-post_4274.html
koster says
Talking about how KINIJIT disintegrated is taboo. If one asks they say let us move forward but without the truth it is difficult to have trust, unite and move forward.
ዱባለ says
ሕዝብን መውቀስ አንዴት ይቻላል? ማን ነው ሕዝቡን አንውጣና ብሶት አናስማ ያለው? ማነው ሕዝቡን ያደራጀው? ማነው ሕዝቡን ታጋይ ታስሯልና ወጥተን አንቃወማ ያለው? ማነው ሕዝቡን ፍርድ ተዛብቷልና አብረን ተቃውሞ አናድርግ ያለው?
አውነትን ተናግሮ የመሽበት ማደር ይላል ያገሬ ሰው:: የተቃዋሚ ፕለቲካ መሪዎች ፈሪዎች ናቸው:: አንዴ ታስረው ትምህርት አግኝተዋል ሁለተኛ መታስር አይፈልጉም:: አነሱ ናቸው በውስጣቸው ንዴት የሌላቸው; ቆራጥነት የጎደላቸው:: ለዚሕም ስራ ስሌላቸው በስባራው በስንጣራው መስዳደብና መክፋፈል የሚታየው::
የአስልምና ተካታዮች ሕዝብ ብለን ከቆጠርናቸው መሪ ያለውና የቆረጠ ታጋይ ካለ ሕዝብና መተባበር አንደሚችል አሳይተዋል:: ዶክተር ነጋሶ ስራ ይስሩ ብቻዎትንም ቢሆን ወጥተው የተቃውሞ ስልፍ ያድርጉ አንበላቸው:: ህዝቡ አስኪመራቸወ አይጠብቁ አንበላቸው::
በነገራችን ላይ አኔን ላስተዋውቃችሁ የመጨራሻ ፈሪ ሰው ነኝ:: የተቃዋሚ መረዎች ክአደኔ ያለው አጅግ በጣም ይሻላሉ:: አንግባባ!!!
Germame Newaye says
The main problem of your editorial is your preconception of what you call “opposition” and assume the former CUD(kINIJT) as the most important and even at times ONLY viable “opposition” force. Of course CUD(KINIJT) has played an important role with in the bounds of the so called “constitution”(Made in Woyane). The nature and essence of the organization is pan Ethiopian and galvanized the latent feelings of the populace..its form of struggle ( its tactic) is parliamentarian-to take over power via election is a gross miscalculation and political naivety against a determined ,well organized,totalitarian woyane regime. All the commentators from the reformist( orgs. who are “Legal” under the auspices of the woyane constitution.) seldom pass the buck on the victims of the woyne repression-the Ethiopian people, as the culprit for lack of will and sense of outrage. And also as your editorial lamented the weak opposition as a result of internal squabbles. All these by itself is not the fundamental problems of the political crisis including within woyne regime. All these are symptoms or collateral damages of the the root causes of the Ethiopian body politics. Ethiopia as nation-state or the sum of ethnic groups is the fundamental benchmark of political outcome/school of thought. Any political prescription,the endgame flows from these two points of departure. Hence,opposition organizations that are mostly mushroomed post woyne regime are the result of or in response to the prevailing state policy that maintains and protects its interest in terms of ethnic nationalist elites. The other veteran opposition org. are established around pan Ethiopian and pro democratic principles are for total transformation of the nation institutions and its attendant forces under democratic and republican constitution. In other words to radically transform that political legitimacy and political power emanates by the consent of the people,or sovereign power of the people.
Wrong diagnostic of the the sickness lead to wrong prescription ..instead of solving it might complicate the ills even cause death.. so is in politics..
I still enjoy your contribution and keep up the good work..!!
Editor says
Dear Germame Newaye,
Thanks for taking your time and send us this comment. We really appreciate it.
We think both you and us have said the same thing but in different ways. You mentioned about radical transformation that “emanates by the consent of the people or sovereign power of the people”. We also stated pretty similar idea in our previous editorial entitled “ከፖለቲካ ተሃድሶ በፊት [የእውቀት] ተሃድሶ በአስቸኳይ!!” “… የእውቀት ተሃድሶ ሳይደረግ ከአምባገነናዊ ሥርዓት ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር አንዱን አምባገነን በሌላ የመተካት ሂደት እንጂ ዘላቂ ለውጥ (አያመጣም)፡፡ ሕዝብ የእውቀት ተሃድሶ ካካሄደ በሥልጣን ላይ ከተቀመጠው አምባገነን ያልተሻሉትን የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ማንነት ጠንቅቆ ማወቅ ይችላል፡፡ በፖለቲካ ብልጣብልጥነት ሊያካሂዱበት የሚችሉትን አሻጥር አስቀድሞ ያውቃል፤ ዕድልም አይሰጣቸውም ምክንያቱም ሕዝብ የሚፈልገው ትክክለኛ ሥርዓት እንዲመሠረት እንጂ አንዱን አምባገነን በሌላው ለመተካት አይደለም። …” In this editorial we reiterated the similar idea by expounding this concept of “intellectual reform” and how it can be achieved and who should be the owner of this reform. Here we also said ” … በየወቅቱ የሰለቸንን የመቡነን አደጋና ከድርጅት ወደ ድርጅት የመገላበጥ እንዲሁም ስም እየቀየሩ ብቻ ለቁጥር የሚያዳግት ድርጅት መመስረት የሚቆመው የእውቀት ተሃድሶ ተግባራዊ ሲሆን ነው። እውቀቱ በኮሌጅ ወይም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጥ አይደለም። በእውነተኛነትና በቅንነት ላይ የተመሠረት እውቀት ነው፡፡ ሰው ምን ይለኛልን አውሎቆ የጣለ እውቀት ነው፡፡ በጥቅምና በወዳጅነት የሚደለል ሳይሆን በሐቀኝነት ዓለት ላይ በመተማመን ጸንቶ የቆመ እውቀት ማለት ነው፡፡ ለራሱ የሚታመን የትግል መስመርና ታጋይ ራዕይ አለው። ለለውጥ ንቅናቄ መሪውን አይጠብቅም፡፡ ያነገበው ራዕይ እያንደረደረ የድሉ በር ላይ ያደርሰዋል። ከሁሉም በላይ የነቃና በመረጃ የታጠቀ ህዝብ ድርሻውን ያውቃል። መብቱን ለማስከበር የትኛውንም ወገን የማስገደድ አቅም ያዳብራል። እንዲህ ያለ ህዝብ በተፈጠረ ቁጥር የአምባገነኖች ጡንቻ እየሰለለ ይሄዳል። ልባቸውም ይርዳል። እንዲህ ያለው የእውቀት ተሐድሶ ከድርጅት ወይም ከፓርቲ አይመጣም፡፡ በስብሰባ ብዛትና በጥናትና ምርምር ምጥቀት አይከሰትም፡፡ ግንኙነት ማድረግ በሚቻልበት አጋጣሚ ሁሉ ወሬ በመውቀጥ በተዓምር ብቅ አይልም፡፡ … ስለዚህ ተሃድሶው ከራስና በራስ መጀመር አለበት፡፡ … ስለዚህ ከመምራትም ሆነ ከመመራት፤ ከመደራጀትም ሆነ ከማደራጀት በፊት እውቀት ይቀድማል! ለዚህ ደግሞ ተሃድሶ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም አሁንም ደግመን የምንለው ቅድሚያ ከራስ የሚጀመር ተሃድሶ ባስቸኳይ!!”
However, we want to make it clear to you and all others that in this editorial we didn’t preconceive, assume and/or insinuate “the former CUD (kINIJT) as the most important and even at times ONLY viable “opposition” force.” And it is because of that we are able to diagnose and pin point the problem and offered a “prescription” which we believe it to be “Intellectual Reform”.
Again, we are grateful to read yours and all others’ comments and have this discussion amongst our people. That is what a media outlet can do.
Regards,
አርታኢ/Editor
ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
Germame Neway says
Dear Editors,
I really appreciate for taking your precious time to respond for my critical comment. I hope and pray others follow your precedent in paying attention readers/followers had to say. Indeed, you could be sited as a stellar example of the fledgling free press. KEEP UP THE GOOD WORK!!!
Best regards,
Editor says
Dear Germame Neway
We are grateful to you as well. Keep sending us your comments and we’d like to encourage you and all our readers to confront and/or challenge us by writing op-eds to our editorials. By entertaining all kinds of views and debating on the issue in a civilized and thoughtful manners we will be able to educate ourselves and grow to benefit our country.
Thanks again
አርታኢ/Editor
ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
http://www.goolgule.com
editor@goolgule.com
ዱባለ says
Germame
We cannot dismiss the opportunity to throw out the incumbent at that time was there after the opposition “won” the election, at least gained significant seats in the parliament. The fallacy is what follows after that. The incumbent outwit the opposition, what ever tactic it used. They were able to dump down the political temperature by playing some psychological games that I think the opposition leadership easily fell to it. The intent of peaceful opposition was misunderstood by the opposition leadership. When they were supposed to fire up the people with anger and rage for stealing election, they dampened it by engaging in useless dialogue, which the government used to buy time and mobilize its forces. Thousands of people went to jail peacefully instead of resisting arrest, there goes for killing rage and anger that would have shake the power of the incumbent. The political divide you described between ethnic advocates Vs Ethiopian nationalist will remain to be the political reality of Ethiopia, unless another contending political realities surfaces. That is very unfortunate.
yilma says
Dear editors,
I agree what is lacking is personal responsibility. Knowledge is not valued while smart talk and short cut is celebrated. We are all responsible for that. Change starts with oneself and it is not easy. It is a timely editorial to remind us of our responsibility as citizens. Again before embarking to change others it is always better to make sure we do not carry unnecessary baggage full of such sickness as intolerance, hate, ethnicity and other disease.