ሰሞኑን በውዴታም ይሁን በግዴታ በመቀሌ እጅግ ከፍተኛ የሚባል ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ሲጨፍሩ፣ ሲዘሉ፣ ከበሮ እየመቱ የባህላቸውን ዘፈንና ውዝዋዜ ሲያወርዱ አይተናል። ምክንያቱ በግልጽ ባይነገርም ሲደበቅ የነበረው የህወሃት ሃብትና ንብረት ውጤት የሆኑ፣ በልዩ የመንግስት ድጋፍ የተከናወኑ ግዙፍ ተቋሞች በጎዳና ለህዝብ ሲቀርቡም ተስተውሏል። ልማቱ መልካም ነው። ደስ ይለናል። ምንም ተቃውሞ የለንም። ግን መልዕክት አለን።
ለማን?
ምሬትን፣ ጭቆናና መንገፍገፍ ሲበዛ በፍቃደኛነት በቦንብ ላይ እንደሚያስሮጥ ለሚያውቀው የትግራይ ህዝብ!! የትግራይ ህዝብ ስማ!!
ሰሞኑን ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ሪፖርት የትግራይ ክልል በትምህርት፣ በኤሌክትሪክ፣ በመንገድ፣ በእርሻ፣ በደን፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ ወዘተ ከሌሎች ክልሎች ሁሉ ርቃ መሄዷን ይፋ አድርጓል። በዚህም ደስ ይለናል። አይከፋንም። ከዚህ በላይ እንዲሆን እንመኛለን። ነገር ግን አንድ መልዕክት አለን።
ለማን?
አሁንም ለትግራይ ህዝብ!!
ሓውዜን የትግራይ ወጣቶች ለትግል ግልብጥ ብለው እንዲወጡ አደረገ። ሓውዜን የደረሰው የቦንብ ድብደባ ማንና እንዴት እንደተቀነባበር ብዙ የሚባልለት ቢሆንም የምሬት ጫፍ ሆኖ ህዝብን አሸፍቷል። ዛሬ መጨቆን ያንገፈግፋል ብለው ለትግል በተነሱና በተሰው ታጋዮች ደምና አጥንት ላይ የቆሙ ሌሎች ሓውዜኖች እንዲፈጠሩ አድርገዋል። እያደረጉም ነው።
ይህ በማን ስም እየሆነ ነው? በህወሃት አማካይነት በትግራይ ህዝብ ስም!!
ኦሮሚያ ልጆቿን በእስርና በጥይት እያጣች ነው። በጨለማ ቤት እየተሰቃዩ ያሉ የኦሮሞ ልጆች ግፍ ሰፍሮ ሞልቷል። አማራው አገር አልባ ሆኖ በየጎዳናው እየወደቀ ነው። እየተለዩ ከየክልሉ እየተባረሩ ነው። የመኖር ዋስትናቸውን ተከልክለው በሞትና በጣር መካከል ያሉ ህጻናትና ነፍሰጡሮች ለቅሶ ሰማይ ደርሷል። ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎ እስር ቤት የሚማቅቁና የሚሰቃዩ ሰውነታቸውም የሚተለተል አሉ። የተገደሉ አሉ። ይህንን የሚያደርገው ደህንነቱ የተቆጣጠረውና መሳሪያ ያነገተው ኃይል ነው። ይህ ኃይል ደግሞ ህወሃት ነው። ህወሃት ይህንን ሁሉ ግፍ የሚፈጽመው በትግራይ ህዝብ ስም ነው። እያመረተ ያለው ደግሞ ብዙ ሓውዜኖችን ነው። በደልና የበቀል ስሜት ላንድ ጎሳ ወይም ሕዝብ ብቻ የተሰጠ አይደለምና ሌሎችም ሊነሱ ይችላሉ። መቼና እንዴት? አይታወቅም። በሲዳማ፣ በሶማሌ፣ በአፋር፣ … ብዙ ችግርና ምሬት አለ።
በጋምቤላ ግፍ ነዶውን እየወዘወዘ ነው። በጋምቤላ በዘመናት ወደፊት የማናገኛው የደን ሃብት እየወደመ ነው። በጋምቤላ ሰላማዊ ህዝቦች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ መሬታቸውን እየተነጠቁ ለውጪ “ባለሃብቶች” እንዲሁም ለትግራይ ተወላጆች እየተከፋፈለ ነው። በባሌ፣ በቦንጋ፣ በወለጋ፣ ድፍን ኦሮሚያና የደቡብ ክልል ደን እየተጨፈጨፈ ትግራይ በደን እየተሸፈነች ነው ብሎ መጨፈር ለትግራይ ህዝብ ኩራት አይሆነውም። ኢትዮጵያዊ ነው የሚባለው የትግራይ ህዝብ እሱ የሚጠላውና ልጆቹን የገበረለት ግፍ በሌሎች ወገኖቹ ላይ ሲፈጸም ዝም ማለቱ ለምንና ከምን የመነጨ እንደሆነ ለማወቅ የሚፈልጉ አሉና ጥያቄውን እናቀርባለን።
ስለመፈናቀል ስናወራ “የትግራይ ተወላጆች ተፈናቀሉ” ሲባልና “ተፈናቀልን” ብለው ቅሬታና አቤቱታ ሲያቀርቡ አንሰማም። ይልቁኑም የአማራን ለም መሬት ለትግራይ በመከለል በደል የሚፈጽመው ህወሃት የሚባለው በትግራይ ህዝብ ስም የተደራጀና በነጻ አውጪ ስም እስካሁን አገር የሚመራ ቡድን ነው። ይህ ሁሉ ሲደረግ የትግራይ ህዝብ ያውቃል። ቢያንስ ቢያንስ የሰው መሬት ወርረው የተቀመጡት አይክዱትም። ግን ይህ እስከመቼ ይቀጥላል? ፍርሃት አለን። ለምን? ይህ ሁሉ ሌላኛው የሓውዜን ክፍል ነዋ!!
ስለ ግብር ሲነሳ የትግራይ ተወላጆች በግብር ዕዳ፣ በባንክ እዳና እንደ ልብ ነጻ ሆኖ በመንቀሳቀስ ችግር ቅሬታ ሲያሰሙ አይደመጥም። በመላው አገሪቱ በኢንቨስትመንት ተሰማርተው በሰላም እየሰሩ ነው። ሌሎች ግን በብሔር ተለይተው መከራ ይደረስባቸዋል። ህወሃት በማንነታቸውና ባመለካከታቸው እየነጠለ ከጨዋታና ከኑሮ መስመር ያወጣቸዋል። የጭቃ ቤት፣ አርሰው የሚበሉበት ከብት፣ ዶሮና በግ ሃብት ተብሎ ይወረስባቸዋል። ይህ እውነት ለትግራይ ምሁራን የተሰወረ አይደለም። ይህም ሌላው ህወሃት በትግራይ ህዝብ ስም በሌሎች ዜጎች ላይ የሚፈጥረው የምሬት ሓውዜን ነው!!
ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ ሲነሳ የመጀመሪያው መስመር ላይ ሆነው አገሪቱን የሚያልቡት የቀድሞ ታጋዮችና የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎች ናቸው። ጤፍ ወደ ኤርትራ በማጋዝ፣ ባህር ዛፍና ቡና በማሻገር፣ የዱር እንስሳትን ቆዳና ቀንድ በመነገድ የተሰማሩት ይታወቃሉ። ብዙ እጅግ ብዙ ማለት ይቻላል። የምናነሳቸው ማሳያዎች ሁሉ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ የፖለቲካ፣ … ሓውዜኖች ናቸውና እዚህ ለጊዜው ላይ እናቁም!!
ሻዕቢያ ድንገት ወረራ አካሂዶ ድፍን ትግራይን ሲቀጠቅጥ፣ ህጻናትን በቦንብ ሲቆላ፣ አገሬ ብሎ የተነሳን ህዝብ በማያውቀው ወንጀል እየሰፈሩ ማሰቃየት ይቆም ዘንድ የትግራይ ህዝብ በቀጥታ ድምጹንና ተቃውሞውን በአግባቡ ማሳየት የሚገባው ወቅት ላይ እንደሚገኝ ይሰማናል፤ ደግሞም እናምናለን። ዛሬ “ውርሱን እንጠብቃለን” በማለት የሚጮህላቸው አቶ መለስ በወቅቱ ክህደት ሲፈጽሙ የደረሰው ዛሬ እየተነጠሉ የሚመቱትና መድረሻ ያጡ ወገኖች ናቸው። ዛሬም ቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ናቸው። በሰባና ሰማንያ ሚሊዮን ህዝብ ልብ ውስጥ የተፈጠሩት ሓውዜኖች ወደ ቁጣ ሲለወጡ አምስት አምስት ሆኖ መደራጀት፣ በስውር መታጠቅና በየሰፈሩ ያሉትን አስተባባሪዎች ስም ለቅሞ በመያዝ “ሳልቀደም ልቅደም” ብሎ መራወጥ አያዋጣም፤ ጊዜው ስለሚያልፍበት የትም አያደርስም። ሓውዜናዊ ህይወት የሚኖር ሕዝብ ከደረሰበት በላይ የሚያጣው ስለማይኖር እንኳን ስለማጣት ስለመኖርም አያስብም፡፡ በዚህ ከቀጠለ የቀን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በየቦታው ራሱ ህወሃት የፈጠራቸው ሓውዜኖች መናደፍ መጀመራቸው አይቀርም።
“ህወሓትን እናስቀድም … ጠላቶቻችንን እናጥፋ” በሚል የማያቋርጥ ጥላቻ መቀጠል ተጨማሪ ሓውዜኖችን ከመፍጠር በስተቀር “ጠላትን” ማጥፋት የማይቻል እንደሆነ ከዚህ በፊት በሕዝብ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ የወሰዱ ተሞክሮ ማስረጃ ነው፡፡ በበረሃ “ጠላትን እናጥፋ”፤ ሥልጣን ይዞ “ጠላትን እናጥፋ”፤ አገር እየመሩ “ጠላትን እናጥፋ”፤ ኢኮኖሚውን ተቆጣጥሮ “ጠላትን እናጥፋ” … 40ዓመት ሙሉ በ“ጠላትን እናጥፋ” መርህ የሚጓዘው ህወሃት “ጉድጓድ የሚምስ ራሱ ይወድቅበታል” የተባለው የተቀደሰ አባባል ሲፈጸም እንዳየነው ከ70 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለማጥፋት የሚመኘው ህወሃት የራሱ መጥፊያ የሆኑ በርካታ ሓውዜኖችን ፈጥሯል፡፡
“የ100 ዓመት የቤት ስራ ሰጥተናቸዋል” በሚል በየድረገጹ የሚለጠፉ ተራ ድንፋታና ትዕቢት የሚፈጠሩትን ሓውዜኖች ከማብዛት ውጪ ትርፍ የላቸውምና ወደ ደጉ መንገድ መመለስና ሰብዓዊነትን በማስቀደም፤ ተደጋግፎ መኖርን ማጎልበት ይሻላል ለማለት እንወዳለን። ተሳስበውና ተረዳድተው የሚገነቡት የትም ሆነ የት የአገር ነውና ሁሉም ይኮራበታል፤ ይጠብቀዋል። ተጠቃሚ ይሆንበታል። የሚያምርብንም ይህ ነው። ህወሃት አልሰማም ብሏል። የትግራይ ህዝብ ግን ስማ!! ይህ ሁሉ የሚደረገው በስምህ ነው!!
koster says
I am really ashamed about the people of Tigrai and the non-Tigrian hodams who are supporting woyane ethnic fascists. That was what Schumbasci Asres Tesemma – the grand father of fascist Meles and the grandfathers of the current ruling junta were doing when Ethiopia were invaded by fascist Ethiopia and Ethiopian heroes from Tigrai and all over Ethiopia were sacrificing their lives. Now Ethiopia is invaded by the home grown fascists from Tigrai and Tigrians and hodams are dancing about the ethnic cleansing going on and the sell of Ethiopia. Does anybody with a normal mind think this will bring lasting peace. I doubt, it may be in my life time or after my death now who are dancing or their children or grand children will pay a high price for it. My blood is boiling when I see Amharas being castrated by woyane ethnic fascists not because I am Amhara but because it is unjust. Say no to woyane ethnic fascists, ethnic cleansing and state terrorism in Ethiopia. Award winning journalist like Eskinder Nega, Eryot Alemu and political and religious leaders are languishing in woyane fascistic torture chamber to bring peace and equality for both of us including the Tigrian dancers but criminal woyane ethnic fascists will face justice sooner or later. http://vimeo.com/18242221
http://www.genocidewatch.org/ethiopia.html
http://www.ecadforum.com/2012/12/19/from-ethnic-liberator-to-national-atrocities-the-tale-of-tplf
http://www.ethiomarket.com/effort/effor_companies.htm
M. Teklu says
Unfortunately, most of Tigrai people will not listen or read to understand this article. This is not because they are dumb, but they have been filled with propoganda information and they have been brainwashed that they will not let go of this sickened mentality of holding power over all other Ethiopians because of their ethnic superiority. Some will hold on because of their needs to be loyal to their clans. The propoganda that they were subjected has been for many many years and they are refusing to listen to any other channel. Military opposition will be the only remedy to this situation.
Teshale says
Almost everything said in this article is true except that there are even more gruesome crimes committed by TPLF not mentioned in this editorial. However, the gist of this article seems to warn the people of Tigray. Why? Do they agree with what TPLF is doing… of course NO. They kept silent for the same reason that we kept silent.
Last time Woyane invaded Somalia. What did we say as Ethiopians? Nothing. What is our answer if the Somalis ask this question to the Ethiopian people. Did we agree with Woyane when it invaded Somalia…. of course NO. But we did keep silent. The name Ethiopia invading Somalia was all over the news … not the name TPLF. Woyane did use our name Ethiopia for unjust causes but let us never forget that we did keep silent because we are coward.
What would our answer be if the people of Tigray had asked this same question when Derg was bombing Tigray. We were unhappy with what Derg was doing but we did keep silent. They felt the pain and they fought and freed themselves from Derg. Unfortunately those few handling the rein were too short sighted to sustain the victory long to the fore-generations; instead they continued the Derg cycle.
So let us not kick the ball away from us so someone else could play for us. If we are feeling the real pain let us play with the ball ourselves and make it clear that the victory belongs to all including the defeated or losers. That is when even the losers will join us and the cycle will end once and for all.
TEWBEL says
Amharas are at least 30 million, and the Oromo, Southern groups and Somalis form another 50 million, why are they taking all this abuse when they could difend not only themselves but also the country? The Tigreans number about 5 million amongst which no more than 50 thousand are TPLFcadre plus some mercenariess whose loyalty is for money. With whatever force the TPLF has it can only kill it cannot defeat a determined popular force.
The problem is not the TPLF but the leaderless and disorganized opposition whose motto is to avoid serious confrontation.
Takele Tsega says
Shame on all of us the Ethiopians in general.It is us who betrayed our people for the abuse of TPLF. TPLF came to power to destroy Ethiopia that is exactly what they are doing. Wake up Ethiopia.
alebachew sekayi says
bezu ematawukut ale ene i can speak tigregna ena be tigirayi sem behiwat sem abre esebeseb neber sebsebaw emimeraw be tigregna kuankua bicha new hulem because lela tigregna emayawuk endayigebaw ena be oromo ena be amhara hizb layi eyasebut yale neger betam new emigermew ahuns kehager wotchalew america negni gin ezihem bagatami sebseba enorachew egebalew lemesmat ena emilut amharana oromo kehageritu metifat alebet lela wore yelem tigrayi melmat alebat new emilut gin bezih keketelu man yihon ethiopa eminorew?demo manim tseb mansat yefelege menesat yichilal because hulu ye tigiray hizeb mesaria astatkenewal beminabatun yiwaga eyandandu yilalu ere bizu atasleflfugn gin magegnet emfelgewun sew ke esat radio gazetegna bagegne bedenb enager neber min endemiaregu ena endet mashenef endemichal betam kelal new enihen k$%# sewoch chirashun matifat zeregna deros ke tigre men yitebekina gin tebku e/r ken alew chirash ke ethiopia yaltefu endehon….e/r ethion yimar
andnet berhane says
መልክክቱ ትክክለኛና ትገቢ የሆነ ኢትዮጵያዊነ የተላበሰ ጭዋ አቀራረብ ነው ፡ ሕዝቦች አብረው የሚኖሩ ሲሆኑ በስልጣን የተቀመጡት የሕዝብ ጠሮች ያሃገር ነቀርሶች ጊዚያውያን ናቸው፡ ለኔ ተመችቶኛል የሌለው መጨቆን እኔን አይመለከተኝም የሚለው ግብዝነት ተመላሹ አስከፊ ይሆናል፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ በተፈትሮ የተሰተው አምላካዊና ምድራዊ ነጻነት በምንም አይነት ማንም ሊቀማውና ሊከለክለው አይችልም፡ ነገርግን ወያነ በንጹሃን ዜጎዝ ደም ለፍትሕና ለእኩልነት በመታገል ሰላምና መቻቻል የሰፈነባት የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች ሃገር በቋንቋዋና በልምድ ባሕል የተሳሰረ በመተባበር በአንድነት የውጭ ወራሪዎችን የመከተ ከቅኝ ተገዥነት በትባትና በቆራጥነት አሳፍሮ የመለሰ ለአፍሪካ ኩራትና ተገን የሆነ ሕዝብ በጥቂት የትግራይን ሕዝብ ስምና ዝናን በመሸከም የባእዳውያንን ጥቅምና ፍላጎት ለመስፈጸም በተነሱ ደካማ የተሸጡ ጥቂት ግለሰቦች ለሚያደርጉት ሃገራዊና ሕዝባዊ ጥፋት የትግራይን ሕዝብ ከሌላው ወገኑ ለመነጠል የሚያደርጉት ታላቅ ሴራ በዝምታ መታለፉ ተተያቂ እንድሚያደርግህ አትዘንጋ፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባንተላይ ተነስቶም ከነኝህ እኩይ የስልጣን ጥማተኞች ጋር ወንጅሎህ አያውቅም ? ነገርግን የሚደረገው ግፍ ነገም ባንተ እንድሚፈጸም አትዘንጋ ይህ ሁሉ የሕዝብ ለቅሶና ችግር እንዳለ የሚቀትልና አንተም እንደደላህና እንድፈለግክ የምትሆንበት አይሆንም፡ ሕሊናህን ቃኘው በማመዛዘን ተመልከተው ፡ እንዲህም ብለህ አስብ ጭቆናን በመታገል መብቱን ለማስከበር የተነሳ ትግል የሕዝቦችን ትግል በመቀልበስ ጨቋኝ መሆን ምንመስሎ ይታየሃል?
እንዲሁም ለሁሉም ኢትዮፕያውያን ወንድ ሴት ወጣት አረጋውያን ለለፉት ሃያ ሁሉት ዓመታት በትግስት በፍራቻ ከዛሬ ነገ ይሻላል በመለት በሃገር ተቀምጠህ የግፍ ጽዋ ቀማሽ የሆንከው ክርስቲያን እስላም ፤ ደቡብ ሰሜን ምስራቅ ምእራብ ያለህ ኢትዮፕያዊ፡ ንብረትህ ተቀምተህ ፍርድ ያጣህ ከተወለድክበት እትብትህ ከተቀበረበት በግዴታ የተፈናቀልክ በላይህ ቤት እፈረሴብህ እንደ ባይተዋር በየመንገዱ የተጣልክ ፍትህን ለማግኘት በየ መስራቤቱ ሰሚ ያጣህ ለችግርህ መፍቻ በእጅህ በመሆኑ (ህልም ይታያል ተብሎ ሳይተኛ አይታደርም) በፍርሃት ብልኮ ተተምደህ አያቶችህ የወረሱህ ክብርና ልእልና ሲደፈር ባገርህ ጥገኛ ስትሆን ምን እየጠበቅህ ይሆን? ወያነን በጽሑፍ በመድረክ እንኳን ሊሰማህ ቀርቶ በት እቢት በንቀት የሚለውን መስማትና መልሱን በመረጠው ለመስጠት ባለመቻልህ እንድሆነ አትዘንጋ ? በጠመንጃ የያዝኩትን ስልጣን በወረቀት አልሰጥም ማለት በነፍጥ ግጠመኝ ማለ ነው፡ ሀሞትክን አፍሰህ ወርደት ለብሰህ መሳለቂያና መዘበቻ ከምትሆን በቃኝ ብለህ አንተም የሃገሪቱ እኩል ባለቤትነትክን ለማሳየት በትባት በመነሳት አንተም የነፍጥ የጦር ሜዳን አድዋ በማይጨው በኮርያ በኮንጎ ዓለምን ይስደመመ ጀግንነት እንዳለህ አሳየው፡
AW says
ንገረው ንገረው አልሰማ ካለ መከራ ይምከረው ::
“ህወሓትን እናስቀድም … ጠላቶቻችንን እናጥፋ” ለሚለን የኢዮጵያ ህዝብ ጠላቶቹን ለይቶአል
koster says
Fascist Meles lived all his life in inferiority complex due to the shamefull act of his grandfather schumbaschi Asres Tesema. Now woyane ethnic fascists may be jubilant about the Money they looted but for sure their children and Grand children will lead all their life in great shame. Those killed and brutalized by the fascists – Amharas, Oromos, Gambellans, Afars, Somalis etc. etc. for sure one day react/revenge.
http://vimeo.com/18242221
http://www.ethiomarket.com/effort/effort_companies.html
http://www.genocidewatch.org/ethiopia.html
Saba Solomon says
My problem is with Non-Woyane-Ethiopians
the Woyanes did what they belive in, im talking about the crime —
The burden of prove is on Non-Woyane Ethiopians : What are we doing to Stop the looting spree and the ongoing embarassement enslavement of our eldern our mothers brothers and sisters by this few unpopular and Un-Ethiopian Well organized and very few Eritrean-and Tigreans who call themselves TPLF(woyane) and committ crime by the name of Tigrean People
yayesh says
I strongly agreed with the above person, instead of isolating Tigreans in the name of Woyanne,
what contribution we had made to bring positive change as individual, group, and nation??,
Specially Ethiopians who are living in the western country and tested the cup of democracy, we live our lives comfortably and gather the materials, finance, and more wealth to fill our greedy emotion, put blind eyes, deaf ears when few people laid their lives for freedom and tortured, murdered? what have we done?? from simple thing petition to stand firm for freedom of our brother and sister??
Woyanne had fulfilled its plan and will continue to do so until we are able to stand together and able to show our unity to fight for justice and humanity?.
I am not Tigrean and I have no problem with Tigreans, I have issues with the person who stole from its nation, not treat his brother and sister humanely and used their power for wrong reason.
Let stop fighting each-other and work together to bring freedom for the people of Ethiopia and bring to justice for those who uses their power for wrong reason.
May Almighty god bless Ethiopia and its people.
As
አለም says
ሰሞኑን አስገደ ገ/ሥላሴ ልጄን ቶርቸር አደረጉብኝ ብሎ ኢትዮሚዲያ የለጠፈውን አንብቤ ይህን ምላሽ ልሰጥ ተገደድኩ። በቅድሚያ
እውነት ከሆነ ታሪኩ በእንግሊዝኛ ተጽፎ መለጠፍ አለበት:: እነ እስክንድር ነጋ የግፍ ፍርድ በተሰጣቸው ማግሥት መሆኑ ደግሞ አጠራጥሮኛል:: ቶርቸር ተደርጎ “ቆስሎና በስብሶ” መጣ ከተባለ ፎቶው ተነሥቶ ለሂዩማን ራይትስና መሰል ድርጅቶች መላክ አለበት:: ስለ “06” ም በእንግሊዝኛ ይጻፍ:: ሌላው ያስገረመኝ ብፈልግ ብፈልግ ይኸ ዜና አገር ውስጥ ባሉት ገጾች እንኳ አልተሰራጨም::
ቀጥሎ የተጠቀሰውን ግን ማመን አቅቶኛል::”በዛን ወቅት ምን ሆንክ ብለን ብንጠይቀው ወድቄ ነው ኣለ። እኛም ግርፋት ወይም ቶርች እነደሆነ ተረድተናል። የኋላ ኋላ ግን ቀስ ኣድረገን ጠይቀነው ግን የደረሰብኝ እንዳልነግራችሁ መርማሪዎቹና ሃላፊዎቹ ገርፈዉኛል በለህ ከተናገርክ ሂወትህን እናጠፋታለን እንዳሉትና ለወላጆቹ ኣለመናገሩ ሰግቶ መሆኑ ገልፆልናል። እኛም በግልፅ ኣቤት ለማለት ግዜ ኣልፏል ብለን ችላ ብለን ቆየን፤ መሆን ግን ኣልነበረበትም ልጄም በሰላም ስራው እየሰራ ነበር፡፡” የዚህን መሰል ዜና አቅራቢ ሁሌ ኢትዮሚዲያ ነው:: በትግራይ የሚገኙ ከሌላው የተሻለ ጥቅም እንደሚያገኙ እየታወቀ ኢሕአዴግ እንደ ሌላው ሕዝብ እያሰቃየው ነው መባሉ ነው:: የትግራይ ተወላጆች በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ሠፍረዋል; እየተዘዋወሩ ንግድ ይሠራሉ:: ሌላው ሁሉ ግን በየክልሉ ተመድቧል:: 8,000 ያህል አማሮች ከጉሙዝ ተባረሩ በተባለበት ሳምንት ይኸው አስገደ ከትግራይ 7,000 ከርስታቸው ላይ ተፈናቀሉ ብሏል:: የ”ሊስ” ጉዳይ በትግራይ ሰላማዊ ሰልፍ አስነሳ በተባለ በወሩ አዲስ አበባ ላይ ተጀመረ:: የትግራይ ወጣቶች “ኮብልስቶን” በማንጠፍ ሥራ ተሰማርተዋል; ደስ ብሎአቸው እየሰሩ ነው በተባልን በወሩ አዲስ አበባ ላይ ተጀመረ:: ብዙ የሰበሰብኩት መረጃ አለ:: ዓላማው ሌላው ሕዝብ የማሰብ ችሎታው እንደሌለውና ንቀት ያሳያል:: ይኸን የምለው በጥላቻ አይደለም:: ፍትህ እንዲኖር ከመሻት እንጂ:: አስገደ ምናልባት እየተባባሰ ያለውን ጥላቻ ለመግታት አስቦ ይሆናል:: እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ሌላው ሕዝብ በአገሪቱ ማንኛውም ክፍል በነጻነት ሰፍሮ መሥራት መብት ከሌለው ትግሬዎቹንም ከየክልሉ ማባረር ይኖርበታል:: በዘር የመካለልን አሳብ ያመጡት እነርሱው ሆነው ሳለ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገቢ አይሆንም:: በነገራችን ላይ በጉሙዝ ክልል በወርቅ, በቀርክሃ, በእርሻ, በትራንስፖርት ወዘተ ንግዱን የያዙት የክልሉ ሰዎች ሳይሆኑ ትግሬዎች ናቸው:: አይሸሹምና ሌሎች የክልሉን መሪዎች የሾሙት ትግሬዎቹ ናቸው; የሻሩአቸውም ትግሬዎቹ ናቸው:: ጉሙዝ ክልል ሆን ተብሎ ከተለያዩ አናሳ ብሔሮች ስለ ተዋቀረ እርስበርስ ተነካክሰዋልና በጋራ በሚያጠቃቸው ላይ ለመረባረብ አይችሉም:: ሌላው ጎልጉል እንደ ጠቀሰው የትግራይ ምሑራን ተግባር ነው። እነ ገላውዴዎስ፣ ጎርፉና አሳየኝ የሚጽፉትን ብትመረምሩ ምን ያህል በእኩይና ኢሰብዓዊ ተግባር እንደ ተሰማሩ ማየት ይቻላል። ለማንኛውም በተቃዋሚ ኃይላት በኩል ሆኖ ስዬ፣ ገብሩ አስራት በአንድ ፈርጅ፣ በሌላው ደግሞ ሥልጣን ጥማተኛው ዶ/ር ብርሃኑ፤ አወናባጁ ዶ/ር እሸቱና ኢትዮፕያን ሪቪው ፈቅ የማይል የተወናበደ አመራር ሲሰጡ ማየት ተስፋ አስቆራጭ ነው። በየሳምንቱ አዳዲስ ቡድኖች መመስረት ፋሽን በሆነበትና ኢትዮጵያ ሳትሆን አማራ ተፈናቀለ፣ ኦሮሞ ተፈናቀለ እያሉ የሚጮኹና የሚያጯጯሁ መብዛት ምን ያህል ለትግራይ መሪዎች እንደ ተመቻቸው ያሳያል።
Dawit G/kidan says
It is true that tigreans have celebrated during that day as u reported but u have failed to understand somethings. first, TPLF is an expert in “window dressing”. u can not blame the people of tigray per se. the majority have continued to suffer and live in poverty while few elites enjoy the national cake. i don’t think it is fair to distance from the people of tigray in the quest for freedom,democracy and prosperity where justice prevailes.
Teddy Tegaru says
Our late great and beloved leader, Meles Zenawi had taught us the Tigrayanas that the Amharas are our enemies. The Tigrayans have paid a lot of sacrifice to fight and destroy the brutal Amhara rule of Colonel Mengistu. The amaharas supported and were happy when the colonel massacred tens of thousands of Tigrayan civilians. The editor of the web site is a Tigrayan who worked for the pro-TPLF magazine, the Ethiopian reporter. But is trying to appear as an opposition for the sake of his asylum case in Norway. Deep inside he knows the crimes of the Amharas and does not defend them. All he writes is to avoid the Amhara accusations against him as a false Tigrayan asylum seeker in Norway.
desu shume' says
The people of Tegrai is part of the people of ETHIOPIA. This is the a b c of Ethiopian history. If
Ethiopia is to die because of the current disease disseminated from Tegrai, it is them who will be wiped -out first. SEWE buehle becha ainorm. Think the people of Tegrai, now or never.