• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም!”

October 12, 2016 11:23 pm by Editor 1 Comment

ኢትዮጵያ ድንቅ አገር ናት። ይህ ማስደነቋ ደግሞ ከሕዝቧ መደበላለቅ ጋር ውበቷን እጅግ አጉልቶታል። ከዛሬ 40ዓመት በፊት የተጀመረው ጎሣ፣ ዘር፣ … ላይ ትኩረት ያደረገው ገዳዳ የግራ ፖለቲካ ኢትዮጵያ አላት የተባለውን የፖለቲካ ችግር ሲፈታ ሳይሆን ይበልጡኑ ሲያወሳስበውና ሕዝብን ግራ ሲጋባ እዚህ ደርሰናል። በዚያ ርዕዮት የተጠመቁ ሕዝብን ሲያስፈጁ እንጂ ለሕዝብ ጥቅም ሲያመጡ አልታዩም፤ በዚያ የጎሣ ፖለቲካ ጥርሳቸውን የነቀሉም እስካሁን የማይሠራ ነገር በመሞከር በሽታውን ለአዲሱ ትውልድ እንደ ስጦታ አስረክበውታል።

ለነጻነት በሚደረገው ትግል የሁሉም ኢትዮጵያ ወገኖች በአንድነት ብሶታቸው፣ ምሬታቸው፣ … ሊሰማ ይገባል እንጂ በተናጠል “ፍትህ ለኦሮሞ፣ ፍትህ ለአማራ፣ ፍትህ ለኦጋዴን፣ …” የሚለው አካሄድ የትም የሚያደርስ አይመስለንም፡፡ የተጨቆንነው ሁላችንም ነን፤ የትግራይ ተወላጆችንም ጨምሮ! የምንታገለውም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆን ይገባዋል፤ ትግራዮችንም ጨምሮ! “ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም!”

ትላንት #የኦሮሞአቢዮትና #የአማራተጋድሎ ዓለምአቀፍ የትብብር ሰልፍ በሎንዶን ተካሂዶ ነበር፡፡ በሰልፉ ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ ወገኖች ይወክለናል የሚሉትን ሠንደቅ ዓላማ ይዘው ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር፡፡ የታየው ኅብረትና አንድነት ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ መፈክሮች በተለያዩ ቋንቋዎች ሊነገሩና ዓለም እንዲሰማው ሊደረግ ይችላል፡፡  በህወሃት ለ25 ዓመታት የተዘራውን ክፉ የጎሣ ፖለቲካ ማሸነፍ የግድ ነው፡፡ መነጋገር፣ መወያየት፣ አብሮ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት በይበልጥ ሊበረታታ የሚገባ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሁላችንም ቤት ስለምንላት ኢትዮጵያ በአንድነት እንድናስብ የሚረዳን ነው፡፡ የመደበላለቃችንን ውበት የምናይበት አስደናቂ ትዕይንት ነው፡፡

omoከዚህ ጋር ተያይዞ በትላንቱ ሠልፍ ላይ ከተሰሙት መፈክሮች መካከል “ህወሃት ወደ ትግራይ TPLF to Tigray” የሚለው መፈክር ወደፊት ልንኖርባት የምንመኛትን አገር ስዕል የማያሳይ ሆኖ ነው ያገኘነው፡፡ ከዚያም ሲያልፍ “ፍትሕ ለኦሮሚያ፣ ነጻነት ለኦሮሚያ፣ (Justice for Oromia, Freedom for Oromia) ፍትህ ለአማራ፤ ነጻነት ለአማራ፤ …” እየተባለ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሲነገር የነበረው መፈክር ትብብርን የማያሳይ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በተነገረው መፈክር መሠረት ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ሶማሊያ፣ ኦጋዴን፣ ሲዳማ እና ጋምቤላ ብቻ ናቸው ፍትሕና ነጻነት የተጠየቀላቸው፡፡ በበርካታ ቀውስ ውስጥ ያለው የኮንሶ ወገናችንስ? የህወሃት ታጣቂዎች እጅግ በሚዘገንን መልኩ እጅና አንገታቸውን በገመድ አስረው ወደ አልታወቀ ቦታ የወሰዷቸው የሱርማ ወገኖቻችንሰ? ፍትህና ነጻነት አያስፈልጋቸውም? ሌሎቹስ? በዚህ ዓይነት አፈካከርስ ስንቱን የኢትዮጵያ ጎሳ ጠርተን ልንጨርሰው ነው?

ከሁሉ በላይ ግን “ህወሃት ወደ ሄግ (TPLF to the Hague)” ተብሎ በተነገረበት ሰልፍ ላይ “ህወሃት ወደ ትግራይ TPLF to Tigray” የሚለው መሰማቱ ጥቂትም ይሁኑ ብዙ ከእኛ ጋር ህወሃትን እየታገሉ ያሉ የትግራይ ወገኖቻችን አገር ማሳጣት ይሆናል ብለን እንገምታለን፡፡ የህወሃት ሹመኞች የትግራይ ህዝብ ህወሃት ነው፤ ህወሃት የትግራይ ሕዝብ ነው እያሉ የሚደሰኩሩትን ትክክል ነው የማለት ሆኖ ነው የተሰማን፡፡ በሰልፉ ላይ እንደተባለው ትግሉ ህወሃትን ለፍርድ ማቅረብ ነው እንጂ ወደ ትግራይ መወርወር ነው ብለን አናምንም፡፡ በህወሃት ልባቸው ቆስሎ ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን በርካታ ነቀፋና መገለልን እየተቀበሉ ያሉትን ጥቂት የትግራይ ወገኖቻችንን ማሳዘንና መሸሸጊያ ማሳጣት መስሎናል፡፡ ለህወሃትም የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ጥሩ መጠቀሚያ መሆን መስሎ ተሰምቶናል፡፡

ስለዚህ የሰልፍ አስተባባሪዎች በእንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ ቢያደርጉ እንመክራለን፡፡ ወቅቱ “የፖለቲካ ተኩላነት” የሚጠይቅ ስለሆነ ወደፊት በየትኛውም የዓለም ክፍል በሕዝብ ስም በሚደረጉ ሠልፎች ላይ ይህንን መሰል መፈክር ከማሰማት መቆጠብ ተገቢ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ታላቁ መጽሐፍ እንዳለውም “እንደ እባብ ብልህ” መሆን እያንዳንዳችን ይጠበቅብናል፡፡ ጥላችንና ትግላችን ከህወሃት ሥርዓት ጋር መሆን አለበት እንጂ ከአንድ የኅብረተሰብ ክፍል ወይም ጎሣ ጋር መሆን አይገባውም፡፡ ሥርዓቱን ስንታገል ከሥርዓቱ ጋር አልላቀቅም ብለው የሙጥኝ ያሉትን ምርጫቸው ወደሚፈልጉት እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል፡፡ በኅብረተሰብ ክፍል ላይ ጥላቻን የሚያነሳሱ ተግባራትን ከመፈጸም መታቀቡ ለኢትዮጵያችን መልካም ነው፡፡

“ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም!” (ፎቶና ጥቅስ: አኢጋን)

smne banner


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ®” አቋም ነው፡፡

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Lusif says

    October 14, 2016 06:59 pm at 6:59 pm

    All countries are being led and governed by ” ELITES “. Most elites are calculated narcissists.narrow ideologiest, partisan tyrants who always try to impose their groups’ mentality on other groups. They are fearful to the power of unified people and are cowards.
    In spite of this, no wonder the elites placed themselves in their particular corner and undermine each other. The elite dream is always how much he gets out of all the disunity and suffering of the people. Such group of people can never think of giving, instead they calculate how much they can get.
    Currently, our country is deep trouble. Innocent lives are being lost, way of life is in shambles, no more peace, only confrontations.
    Every where we see tribal leaders foul crying in the name of their respective tribe. How the Ethiopian people then triumph over tyranny.?
    The Ethiopian people particularly the youth has spoken. The Youth has already brought down the dividing wall that made it weak the last quarter of century.
    The so called ” Elites ” never paid attention to the call of the Ethiopian citizens. At this moment they seem struggling among each other.
    The struggle for freedom, equality, justice, and democratic way of life is underway. Each day it is getting fiercer and stronger.
    The Ethiopian elites were supposed to get together, forge a national agenda and strategy, creat a national center that can be ran and managed by national figures. Such inability of so called “Elites” is a dismal failure, tantamount to betrayal. To be honest, to me, it is like a treasion.
    Such parochial tendency is the greatest problem. The good news is the Ethiopian youth is determined to face tyranny by bringing its effort together, dispute lack of a national strategist, reinforcements and suppliers. This is really, really sad, but triumph and peace are closer.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule