• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኖቤል የሰላም አሻራ በኤርትራም! ባስቸኳይ!

December 13, 2019 11:53 am by Editor 1 Comment

የ2019 የዓለም የኖቤል የሰላም ሽልማት የእኛ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የእኛው ቤተሰቦች የሆኑት የኤርትራዊንም ነው ሲባል ለጎልጉል የሚገባው ሃሳቡ ወይም ንግግሩ ከመደመርም በላይ የሚታይ ስለሆነ ብቻ ነው።

እንደሚታወቀው የኖቤል ተሸላሚዎች ከሚቀበሉት ዲፕሎማ በተጨማሪ ግምቱ 10ሺህ ዶላር የሚገመት 18 ካራት አረንጓዴ ወርቅ የተለበደበት 24 ካራት ወርቅ የሚሰጥ ሲሆን ወደ 950ሺህ ዶላር የሚገመት የገንዘብ ሽልማትም አብሮ ይሰጣል። ከገንዘቡና ከወርቁ ይልቅ ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ዝናው ከሁሉ የሚበልጥ ነው።

ከዚህ በፊት በተለያዩ መስኮች የተሸለሙ በተሰጣቸው ገንዘብ ምን እንዳደረጉበት ሲናገሩ ለልጆቼ ኮሌጅ ወጪ አዋልኩት፤ አዲስ ቤት ገዛሁበት፤ በቀጥታ ወደ ቁጠባ የባንክ ሒሳቤ ነው አስገባሁት፤ ወዘተ የሚሉ መልሶችን ሰጥተዋል።

የ2019 የዓለም የሰላም ሎሬት ዐቢይ አሕመድም ሽልማቱን በወሰዱ ጊዜ ከላይ የተጠቀሰው ወርቅና ገንዘብ ተበርክቶላቸዋል። ጥያቄው ይህንን ምን ያደርጉበት ይሆናል የሚለው ነው።

Peace Research Institute Frankfurt የተሰኘው ተቋም ለሰላም ልዩ አስተዋጽዎ ያበረከቱ በሚል የ2019 (እኤአ) የHessian Peace Prize ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 25,000 ዩሮ በሽልማት መስጠቱ ይታወቃል። እርሳቸውም ይህንን የገንዘብ ስጦታ “መልካም ወጣት” በሚል ለወጣቶች ትምህርት እየሰጠ ለሚገኘው ዮናታን አክሊሉ ተቋም ማበርከታቸው ይታወሳል።

የዚህ ዓመቱ የኖቤል ሽልማት ለዶ/ር ዐቢይ የተሰጠበት ዋንኛው ምክንያት ከኤርትራ ጋር የነበረውን ውዝግብ በመፍታት ወንድማማች በሆነው ሁለቱ ሕዝብ መካከል ሰላም እንዲፈጠር በማድረጋቸው መሆኑ በስፋት ተነግሯል። እርሳቸውም በሽልማቱ ሥነሥርዓት ላይ በሰጡት ሌክቸር ውጤቱ የእርሳቸው ጥረት ብቻ ሳይሆን “አጋሬና የሰላም ጓድ” ያሏቸው ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ መሆኑን ጠቅሰው ነበር።

የ2009 (እኤአ) የኖቤል የሰላም ተሸላሚ የነበሩት ቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከኖቤል የተሰጣቸውን 1.4 ሚሊዮን ዶላር ለአስር የተለያዩ የዕርዳታ ተቋማት ማበርከታቸውን ሮይተርስ በወቅቱ ዘግቧል። ተጠቃሚ ድርጅቶቹም ለጥቁሮች፣ ለሒስፓኒክስ፣ ለአሜሪካ ኢንዲያን ስኮላርሺፕ በመስጠት ለሚተጉ ድርጅቶች ሲሆን የተቀረውም ለጦር አካል ጉዳተኞች፣ ለጤና፣ ለትምህርት፣ ለተፈጥሮ ጉዳተኞች፣ ወዘተ መርጃ እንዲሆን ነበር የለገሱት።

የ2006 የሰላም ተሸላሚ የነበሩት ባንግላዴሺያዊው መሐመድ ዩኑስ እንዲሁም የ2008 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ የነበሩት የቀድሞው የፊንላንድ ፕሬዚዳንት ማርቲ አቲሳሪ ሽልማቶቻቸውን ለማኅበራዊ አገልግሎት እንዲውል መልሰው በመስጠት የሚጠቀሱ ናቸው። ሌሎችም እንዲሁ በተሰጣቸው የገንዘብ ሽልማት ተመሳሳይ የበጎ ፈቃድ ተግባር ፈጽመዋል።   

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ትላንት አዲስ አበባ ሲደርሱ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮጵላን ማረፊያ ንግግር አድርገው ነበር። ከተናገሩት በርካታ ቁምነገሮች መካከል ሽልማቱን በኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በኤርትራ እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ በሚገኙ አገራት ስም የተቀበሉ መሆናቸውን በመናገር ከእርሳቸው ጋር በእኩል የሽልማቱ ባለቤት ኢሳያስ አፈወርቂ መሆናቸውን ተናግረዋል። በመቀጠልም ይህንን ድል አብረው አስመራ ላይ እንደሚያከብሩ ፍንጭ ሰጥተዋል።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንን የገንዘብ ስጦታ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ብቻ ሳይሆን እንዲቀጥል ዓላማው ባደረገ ጉዳይ ላይ እንዲያውሉት ሃሳብ ይሰጣል። ኢትዮጵያና ኤርትራ ሁለት አገር፤ ሁለት ህዝብ ሳይሆኑ በብዙ መልኩ የተጋመዱና የተሳሰሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን ይበልጥ የሚያጎለብት፤ ከእንግዲህ ጦርነት በቃን የሚያስብል፤ ያለፈውን ስህተታችንን እያስታወሰ ለወደፊቱ እንዳንደግመው በሚጠቅምና ልጆቻችንን በሚያስተምር ተቋም ላይ እንዲውል ቢደርጉት ምክረ ሃሳብ እንሰጣለን። ተቋሙ በአስመራ ላይ የሚገነባ ብቻ ሳይሆን በአንጻሩም አዲስ አበባ ላይ የሚኖርና በየጊዜው የሰዎች ልውውጥ የሚካሄድበት ቢሆን የበለጠ ጠቃሚ እንደሚሆን እንገምታለን።

በኖርዌይ ኦስሎ 15 የትግራይ ተወላጅ ነን የሚሉና ሌሎች በኤርትራዊያን ስም የስደት ፈቃድ ያገኙ ጠ/ሚ/ር ዐቢይን ለማንጓጠጥ ሞክረዋል። “ጥቅሜ ለምን ቀረብኝ” ከሚል ስሜትና መቀሌ የታጀለው የትህነግ አጀንዳ አስፈጻሚዎች 40ሺህ ኦሮሞ እስር ላይ ሲማቅቅና “የእስር ቤቱ ቋንቋ ኦሮምኛ” በነበረበት ወቅት የሚጮኹትን ወገኖች በዚሁ የስደት ምድር ሲያሸማቅቁ፣ ምስልና ቪዲዮ እየቀረጹ ወዳገርቤት በመላክ ሲሰልሉ፣ የነበሩ የወንበዴ ሽራፊዎች መሆናቸው ተቃውሞውን ከተራ ማንጓጠጥ ለይተን እንዳናየው ያደርገናል።

በተቃራኒው ኤርትራዊያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን፣ ቤተሰቦቻችን ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ዓለም እውቅና ለሰጣቸው ታላቁ መሪ ድጋፋቸውን፣ አድናቆታቸውንና ክብራቸውን በአስቸጋሪው የዓየር ሁኔታ ውስጥ ሆነው አቅርበዋል። ዕልልታቸውን ጧፍ እያበሩ አሰምተዋል። የወደፊት ተስፋቸውም ብሩህ መሆኑን አሳይተዋል። ለዚህም ነው ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ የኖቤል ሽልማቱ በኤርትራም የሚታይ፣ የሚዘከር፣ ትውልድን እስከወዲያኛው የሚያስተሳስር የሰላም አሻራ ሆኖ እንዲቆም ሃሳብ ያቀረበው። ሃሳቡም ነገ ዛሬ ሳይል ባስቸኳይ ይደረግ የሚለውም በዚሁ ምክንያት ነው። እናም በአዲሱ አስተሳሰብ ይህ አካሄድ መደመርና መደመር ነው።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ™” አቋም ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Editorial Tagged With: Full Width Top, Middle Column, Nobel Peace Prize Laureate Abiy Ahmed Ali

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    December 16, 2019 06:11 pm at 6:11 pm

    ሽልማት በሁለት ነገሮች ዙሪይ ይሰጣል። የመጀመሪያው ከብዙ ድካምና ትግል በህዋላ ከተወዳዳሪዎች መካከል ቀዳሚው በመባል ለምሳሌ ያህል እንደ ቅርብና የረጅም ሩጫ፤ የተማሪዎች የትምህርት ብልጫ ወዘተ ተጠቃይሽ ናቸው። ሌላው ደግሞ ለተጀመረ መልካም ሃሳብና ገና ፍሬ ላላፈራ የተተከለ ዛፍ የሚሰጥ የምስጋናና የማበረታቻ ወረቀት ነው። የጠ/ሚሩ ሽልማት ተሰራ ለተባለው ብቻ ሳይሆን ገና ለመስራት ለሚያስቡት መልካም ነገር ሁሉ ተዳምሮ የተሰጠ መልካም ሥራህን አይተናል ፍጻሜህን እንከታተላለን የማለት ያክል ነው። የፕሬዚደንት ኦባማም ሆነ አሁን በሮሂንጋ እስላሞች ላይ በዘር ማጥፋት ወንጀል መንግስቷ የተከሰሰው Aung San Suu Kyi የዚሁ የኖቤል ሽልማት ሲሰጣት ከላይ በዶ/ር አብይ ዙሪያ በታሰበው እሳቤ ታስቦ እንጂ እዚህ ግባ የሚባል ተግባር አልሰራችም ነበር። ሌሎች ተሸላሚዎችም አሉ። የሚገርመው ግን የዚህን የሰላም ሽልማት አገኛለሁ ብሎ ይቋምጥ የነበረው የአሜሪካው ፕረዚዳንት ዶላንድ ትራፕ እንደ ነበር የውስጥ ምንጮች ይናገራሉ። ይህም በሰሜን ኮሪያና በደቡብ ኮሪያ ሰላምን በማውረድ ተብሎ የታሰበ ጉዳይ ነበር። አልሆነም ያው ዶ/ር አብይ ቀንቶታል። ወደፊትም ይቅናው!
    ኤርትራን በተመለከተ እንዲህ እና እንዲያ የሚባለው ውሃ አይቋጥርም። አንዲት ሃገር የራሷ እይታ አላት። በራሷ ጊዜና ሰአት ለውጦች ከውስጥ ይመጣሉ። እንዲሁ እኛ አካባቢ ዘንቧልና እናንተም ጋም ጎርፍ ይሁን ማለት የፓለቲካ ሸፍጥ ነው። በፕረዝደንት ኢሳያስና በጠ/ሚር አብይ መካከል ጥሩ መግባባት እንዳለ እናያለን። ያንኑ ድልድይ ለማፍረስ ወዲህና ወዲያ የሚሉ የአረብ ሽብርተኞችና የሃገር ውስጥ ቅጥረኞች ሁለቱ መሪዎች በሃሳብ እስከተጣመሩ ድረስ በመካከላቸው ነፋስ አይገባም። በመሆኑም በኢትዮጵያ ሙሉ ለውጥ አለ በኤርትራ አንዳች ለውጥ የለም እያሉ ማላዘን የራስ ሲያርባት የሰው ታማስላለች እንደማለት ይቆጠራል። በአስመራ ጎዳናዎች ሰዎች አይዘረፉም፤ ቤ/ክርስቲያኖች በእሳት አይጋዪም፤ ማንም ጭፍራ ሰው ዝቅዝቆ አይሰቅልም፤ ቢለዋና ቋንጨራ ያነገቱ የዘር ሰልፈኖች የሰው አንገት አይቀነጥሱም። ጸጥ፤ ረጭ ያለ ሰላም አለ። ሃገሪቱ የፓለቲካ አሻጥር ለሚፈጽሙ ወይም ለመፈጸም ለሚያደፍጡ ሥፍራ የላትም። ባንጻሩ የአዲስ አበባ መንግስት ደግሞ ያኮረፈና ያስኮረፈን ሁሉ ኑ በማለት ወደ ሃገሪቱ በማስገባት የማዕድ ተካፋይ ካደረጋቸው ወዲህ ይህ ነው የማይባል በደል በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ ይገኛል። በመሰረቱ የዘር ፓለቲካ ወረርሽኝ ነው። አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ ሳንመልስ እያሉ የሚቀባጥሩት በዘር ፓለቲካ በመለከፋቸው ነው። ሰው በዘሩ ከተሰለፈ እንስሳ ነው። ግራም ነፈሰ ቀኝ ዲሞክራሲና ሰላም በኢትዮጵያ እንደ ሰፈነ አርጎ በመቁጠር ኤርትራን መወረፍ አላዋቂነት ነው። የኤርትራዊያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከኢትዮጵያዊያን ወገኖቻቸው ጋር አብረው ለጠ/ሚ አብይ ድጋፍ ማድረጋቸው ማለፊያ ነው። ባንጻሩ በዘሩ ተፈልፍሎ በዘሩ መዝብሮና እልፎችን ገድሎ የሃገሪቱን ሃብትና ንብረት በመቀሌ አከማችቶ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው የወያኔ ደጋፊዎች ጠ/ሚ አብይን መቃወማቸው የሚጠበቅ ነው። ጥቅማቸው የቀረባቸው የወያኔ ውሾች በአለም ዙሪያ ተዘርተው ያስጠለላቸውን ሃገር ሲያሸብሩና የማይጠረጥሩ ሃበሾችን ለመከራ ሲማግድ እንደኖሩ ጠንቅቀን እናውቃለን። ይህ ሃይል ነው አብሮ ለዘመናት የኖረን ኤርትራዊ ወገን ሃገርህ አይደለም በማለት እያፈሰ ከምድሪቱ ያስወጣው። የሙታን ፓለቲካ ሁሌ ባለፈ ነገር ላይ እንዳላዘነ የራስን የፓለቲካ ወንጀል ሸፍኖ ሌሎችን እንደ ወነጀለኛ ሲቆጥር የሚኖር በቁሙ የሞተ አስተሳሰብ አራማጆች እይታ ነው። አምናለሁ ከአሁን በህዋላ ወያኔ ኢትዮጵያዊያን እንደፈለገ የሚያደርግበት ጊዜና ሰአት አክትሟል። እርማቹሁን አውጡ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule