ባለፈው ሳምንት ከ21/01/2014 ዓ.ም እስከ 27/01/2014 ዓ.ም ድረስ ከ44.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደ ሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን፣ የገቢ ኮንትሮባንድ 43 ሚሊዮን 12ሺ 009 ብር፤ ወጪ ደግሞ 1ሚሊዮን 437ሺ 851ብር፣ በድምሩ የ44ሚሊዮን 449ሺ 860ብር ግምት አላቸው ተብሏል፡፡ አቃቂ ቃሊቲ እና ሞያሌ የጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ ከፍተኛ የኮንትሮባንድ እቃዎች ሊያዙ ችለዋል፡፡ ከኮንትሮባንድ ቁሶቹ መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የወርቅ ማውጫ ማሽን፣ ተሽከርካሪ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ አደንዛዥ እጽ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና … [Read more...] about ከ44.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
operation dismantle tplf
34 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
34 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አዉሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ተጠርጣሪው ግለሰብ በጥቁር ፌስታል የተጠቀለለ ነገር ይዞ ሲንቀሳቀስ መደበኛ የወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነስቷል፡፡ ፖሊሶቹ ባደረባቸው ጥርጣሬ ግለሰቡን ሲፈትሹት 34 ሺህ የአሜርካ ዶላር ይዞ በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው ተብሏል፡፡ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እና መንግስት ማግኘት ያለበትን ገቢ እንዲያጣ እያደረገ ይገኛል፡፡ ወንጀል ፈፃሚዎች እና ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ አካላት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ህግን በጣሰ መልኩ እየተንቀሳቀሱ … [Read more...] about 34 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ማን እንደሚገባ፣ እንደሚወጣና እንደሚቆይ ለማንም ማሳወቅ አይጠበቅብንም
አንድ ሀገር በግዛቷ ውስጥ ማን እንደሚገባ፣ እንደሚወጣና እንደሚቆይ የመወሰን መብቷ የተጠበቀ ነው፤ የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን ውሳኔውን ለማንም ማሳወቅ አይጠበቅበትም ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ ከተልዕኳቸው ውጪ ሲንቀሳቀሱ ከአገር እንዲወጡ የተደረጉ የተመድ ሰራተኞችን በተመለከተ ለጸጥታው ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል። አምባሳደሩ በሰጡት ማብራርያ “የዛሬው ስብሰባ መነሻ ምክንያት የአንድን ሉዓላዊት ሀገር ውሳኔ የሚጋፋ የመወያያ አጀንዳ መፍጠሩ ተገቢ ካለመሆኑ በላይ ራስን በራስ በማስተዳደር በተወሰነ ውሳኔ ላይ እንዲሁም በሉዐላዊት አገር ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው” ብለዋል። በዓለም አቀፍ ህጎች መነሻነት ኢትዮጵያ ውሳኔውን መወሰኗንም አስታውቀዋል። የተለያዩ አገራት በተለያየ … [Read more...] about በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ማን እንደሚገባ፣ እንደሚወጣና እንደሚቆይ ለማንም ማሳወቅ አይጠበቅብንም
ምግብ ከባዕድ ነገሮች ጋር ሲቀላቅሉ የተገኙ 23 ተቋማት ታሸጉ
በአዲስ አበባ በ2014 በጀት ዓመት ምግብ ነክ የሆኑ ግብቶችን ከባዕድ ጋር በመቀላቀላቸው 23 ተቋማት መታሸጋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ የመድሀኒት፣ የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በምግብ እና ጤና ነክ ተቋማት ዙሪያ የቁጥጥር ሥራ እንደሚከናውን ይታወቃል፡፡ በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ በምግብ ክለሳ ላይ ሰፊ ሥራ መስራቱን አስታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት በ2014 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 146 ተቋማት ላይ በተደረገው የቁጥጥር ሥራ 23 ተቋማት መታሸጋቸውን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ የመድሀኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሙሬሳ ሚደቅሳ ተናግረዋል፡፡ ተቋማቶቹ ቂቤ፣ ማር እና የባልትና ምርቶችን ከባዕድ ነገር ጋር … [Read more...] about ምግብ ከባዕድ ነገሮች ጋር ሲቀላቅሉ የተገኙ 23 ተቋማት ታሸጉ
በአዲስ አበባ ሕገወጥ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ፍተሻ የተለያዩ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች እና ሰነዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ። በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው 32 ቀበሌ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውሰጥ ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት በተደረገ ፍተሻ የጦር መሳሪያዎች እና ሰነዶች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ላይ ጥናት በማድረግና የፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት በተደረገ ብርበራ 85 የክላሽን-ኮቭ እና የሽጉጥ ጥይቶች፣ 3 ሽጉጦች ፣ 2 ሳንጃዎች እና 1 የእጅ ቦንብ መያዙን ነው ፖሊስ የገለፀው፡፡ በተጨማሪም 10 ሺህ የኢትዮጵያ ብር እና በርካታ ፓስፖርቶችን ጨምሮ የትምህርት ማስረጃዎች በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ውስጥ መገኘታቸውን ከአዲስ ከተማ ክፍለ … [Read more...] about በአዲስ አበባ ሕገወጥ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ
በልዩ ልዩ መንገድ ለትህነግ ሢሠሩ የነበሩ ፯ የተመድ ኃላፊዎች ተባረሩ
የኢትዮጵያ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስር በተለያዩ ኤጀንሲዎች ውስጥ የሚሰሩ 7 የውጭ አገር ዜጎች በ72 ሰዓት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ ማስተላለፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢቲቪ በላከው መረጃ እንዳስታወቀው የኢትዮጵያን ድንበር ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት የመንግሥታቱ ድርጅት ባልደረቦች በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ህገ ወጥ ሥራ ሲሠሩ የተገኙ መሆናቸውም ነው የተገለፀው።የኢትዮጵያን ድንበር ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት የውጭ አገር ዜጎች የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ የዩኒሴፍ ሃላፊ አዴል ኮርድ፣ የተራድኦ ምክትል አስተባባሪ ግራንት ሊያቲ፣ የተራድኦ ምክትል አስተባባሪ ተወካይ ጋዳ ኤልታሂር ሙዳዊ፣ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ምክትል አስተባባሪ ሰኢድ መሀመድ ሀርሲ፣ ሶኒ ኦኔግቡላ የስብዓዊ መብቶች … [Read more...] about በልዩ ልዩ መንገድ ለትህነግ ሢሠሩ የነበሩ ፯ የተመድ ኃላፊዎች ተባረሩ
ለኤርሚያስ ክስ ትህነግ ወጪውን ሊሸፍን ነው
ኤርሚያስ ቃል በቃል የተናገረው ይህንን ነው፤ “ቲዲኤፍን (ስሙን የቀየረውንና በሃሺሽ ያበደውን የትህነግ ጭፍራ ማለቱ ነው) ምሳሌ ውሰዱ፤ የትግራይ ቲዲኤፍ ሕዝባዊ ኃይል ነው፤ (እነርሱ) ሳይነጋገሩ አይወስኑም፤ እንደ ቤስት ፕራክቲስ ነው የሚወሰደው፤ እደግመዋለሁ ቤስት ፕራክቲስ ነው”። ለአማራ ህዝብ እንዲተገብረው የሰጠው “ምክር” ይህንን ነው። በሌላ አነጋገር ኤርሚያስ እያለ ያለው፤ አገኘሁ ተሻገር ደብረጽዮንን፤ ጄ/ል ተፈራ ማሞ ፃድቃንን፤ ጄ/ል አዳምነህ መንግሥቴ ታደሰ ወረደን ወይም ምዕግበን፤ ግዛቸው ሙሉነህ ደግሞ ጌታቸው ረዳን መሆን አለባቸው ነው። “የህወሃት አገልጋይ” በሚል ልዩ መለያው የሚታወቅው፣ በበረከት ስምዖን አስተምህሮ ተቀርጾ የተሠራ የሚባለውና ከዚሁ ፈጣሪው ጋር ጥብቅ ትሥሥር እንደነበረው በርካታ መረጃ የሚቀርብበት ኤርሚያስ ለገሠ፤ በአበበ ገላው … [Read more...] about ለኤርሚያስ ክስ ትህነግ ወጪውን ሊሸፍን ነው
ኢትዮጵያን ለማፍረስ መስከረም 2013 በትህነግ የተዘጋጀው ሰነድ
“የትግል ልዩ ምዕራፍ እድገቶች እና የምከታችን ቀጣይ ስትራቴጂዎች፣ ስልቶች እና አቅጣጫዎች” በሚል ርዕስ ኢትዮጵያን በረቀቀ ስልት ለማፈራረስ ካልተቻለም የትህነግን ጡንቻ በማሳበጥ የመደራደር ዐቅሙን ለማጎልበት እንዲረዳ የወጣ ባለ 86 ገጽ ሰነድ እዚህ ላይ ይገኛል። “የትግል ልዩ ምዕራፍ እድገቶች እና የምከታችን ቀጣይ ስትራቴጂዎች፣ ስልቶች እና አቅጣጫዎች” Download ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ኢትዮጵያን ለማፍረስ መስከረም 2013 በትህነግ የተዘጋጀው ሰነድ
ኢትዮጵያን የምናፈርስበት “ዓመት፣ ወር፣ ቀን እና ሰዓት አሁን ነው” – ትህነግ
https://youtu.be/CImbcAqgjmc?t=304 The Special Phase of the Struggle and the Continuation of our Defense Strategies, Tactics, and Directions (TPLF’s leaked document, dated 10 October 2020), translated from Amharic to the English language) (Volume – two) Strictly confidential TPLF Secretariat October 10/2020 Mekelle Contents Introduction ……………… 3 Part One: New Developments in the International, National and Regional Political Landscape 4 1.1 ….. Developments in The … [Read more...] about ኢትዮጵያን የምናፈርስበት “ዓመት፣ ወር፣ ቀን እና ሰዓት አሁን ነው” – ትህነግ
አረንጓዴ ቢጫ እና ቀዩ ሰንደቅ የአፍሪካዊያን የነጻነት ምልክት ነው
አፍሪካዊያን አያቶቻችን የደረሰባቸው ውርደት በእኛ ምድር ላይ አይደገምም ከሚሊዮኖች ደህንነት ይልቅ የግል ስልጣናቸው በሚያስጨንቃቸው ግለሰቦች በሰጡት የተሳሳተ መረጃ የተነሳ ለሚፈጠርብን ጫና አንበረከክም፤ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መስከረረም 17 ቀን 2014ዓም ግልጽ ደብዳቤ ጽፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ደብዳቤያቸው አሸባሪው ህወሓት እንደ አገር ያደረሳቸውን ግፎችና በደሎች ዘርዝረው አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ደብዳቤያቸውም ህወሓት እንደ አገር በፈጸማቸው ግፎችና ወንጀሎች የተነሳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ቡድን ብሎ እንደፈረጀው በማስታወስ፤ ይህ ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈጸም በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት መጀመሩን ጠቅሰዋል። ከዚህ ጦርነት በኋላም ይህ አሸባሪ ቡድን በአፋር … [Read more...] about አረንጓዴ ቢጫ እና ቀዩ ሰንደቅ የአፍሪካዊያን የነጻነት ምልክት ነው










