“አንዳንዱ ነገር ድራማ ይመስላል” የኦነግ ቃል አቀባይ ቀጄላ መርዳሳ በህዳር ወር 2012 የመጨረሻ ሳምንት ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ጋምቤላ ከተማ በመጓዝ ላይ ሳሉ በአጋቾች እጅ የገቡት ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል። እስከ አሁን ባለው መረጃም ተማሪዎቹ የአማራ ክልል ነዋሪ እንደሆኑ በመገለፁ አዲስ ማለዳ የአማራ ክልል የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙን አነጋግራለች። ኮሚሽነሩ ምንም እንኳን በጉዳዩ ላይ በቀጥታ ለመሳተፍ የህግ ገደብ ቢኖርባቸውም የታገቱት ተማሪዎች ከተያዙ እለት ጀምሮ የልጆቹን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉት አንደሆነ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። “የስልጣን ገደብ ቢኖርብንም ልጆቻችን ናቸው እኮ፣ መቶ በመቶ ቅድሚያ ሰጥተን እየተከታተል ነው” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ዛሬ አመሻሹ ላይ ገልጸዋል። “ጉዳዩ የኛ ጉዳይ ነው፣ ነገር ግን መዋቅር … [Read more...] about “ልጆቻችን ናቸው እኮ” ኮሚሽነር አበረ አዳሙ
olf
“የመረራን ፓርቲ የተቀላቀልኩት የሸዋን ድምጽ ለመሰብሰብ ነው”
መረራ - ሲያልቅ እጅ ሰጡ!! ኦነግን ይዞት በነበረው አቋም አማካይነት ፍጹም እንደማይነሳ አድርገው የቀጠቀጡት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ናቸው። “ኦሮሞ ግንድ እንጂ ቅርንጫፍ አይደለም ” ሲሉም የኦሮሞን አካታችነትና ታላቅ ሕዝብነት በማስረገጥ የጎጥ ፖለቲካ ረብ የለሽ መሆኑንን በጥናት አስደግፈው ኦነግን ያኮሰሱት መረራ፤ ኦነግ ውጤት እንደማያመጣም ተናግረው ነበር። ዛሬ ግን “ተመልሰው ለኦነግ እጅ ሰጡ” ሲሉ ወዳጆቻቸው ሳይቀሩ እየወቀሷቸው ነው። የአምቦ ክፋይ በሆነችው ጊንጪ የተለኮሰው የኦሮሞ ትግል አድማሱን አስፍቶ ወደ ሌሎች ክልሎችም ተስፋፍቶ በጥምረት ለውጤት ሲበቃ፣ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ሲንከላወስ የነበረውና ተፈረካክሶ በየአቅጣጫው የተበተነው የኦነግ አመራሮች ወደ አገር ቤት “በጀግንነት” የመግባት ዕድል ተጎናጸፉ። እናም የድል አጥቢያ አርበኛ ሆነው የጠመንጃውንና … [Read more...] about “የመረራን ፓርቲ የተቀላቀልኩት የሸዋን ድምጽ ለመሰብሰብ ነው”
ከኦነግ የተገነጠለው ኦዴግ ከኦዴፓ ጋር መቀላቀል ኢህአዴግን እና ግንቦት 7ን ወዴት ያመራቸዋል?
“አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ ለመመስረት ተነስተናል። የቀድሞው የትግል ስልት አያዋጣም” በማለት “የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር” (ኦዴግ) ODF የሚባል አዲስ ግንባር መጋቢት 22፤2005ዓም (ማርች 31/2013) ያቋቋሙት የቀድሞው የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች የቀድሞውን ኦህዴድ የአሁኑን ኦዴፓን ተቀላቅለዋል። ከኦነግ ተገንጥሎ ኦዴግ የሆነው የሌንጮ ለታ ፓርቲ ኦዴፓን መቀላቀሉና በኢህአዴግና በግንቦት 7 ላይ የሚያስከትለው የፖለቲካ ተጽዕኖ ገና አልጠራም። ከዳውድ ኢብሣ ኦነግ ጋር እቀላቀላለሁ ያለው የመረራ ጉዲና ኦፌኮም መጨረሻው አልታወቀም። የዛሬ አምስት ዓመት አካባቢ ከብሪታንያ፣ ከስዊትዘርላንድ፣ ከካናዳ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጀርመንና ከተለያዩ አገራት የተሰባሰቡ ቁጥራቸው 400 የሚጠጋ ተሰብሳቢዎች ባካሄዱት ውይይት ላይ ስለ ኦዴግ ማብራሪያ የሰጡት ሌንጮ አስፈላጊ የተባሉ ጥያቄዎች … [Read more...] about ከኦነግ የተገነጠለው ኦዴግ ከኦዴፓ ጋር መቀላቀል ኢህአዴግን እና ግንቦት 7ን ወዴት ያመራቸዋል?
ፅንፈኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞች (ልሂቃን)
ከዝግጅት ክፍሉ፤ ይህ ጽሁፍ ለጎልጉል የተላከውና የቀረበው “መልስ ለዶ/ር በያን አሶባ ቃለ መጠይቅ” በሚል ርዕስ ለቀረበው ጽሁፍ ድጋፍ ሆኖ ነው። በዚህ ጽሁፍም ሆነ በመጀመሪያው ላይ አስተያየት ወይም የተቃውሞ ጽሁፍ ለማቅረብ የሚፈልጉ (editor@goolgule.com) በሚለው የኢሜይል አድራሻችን እንድትልኩ ይሁን። ከዚህ ቀጥሎ የማቀርበው ሃሳብ ከኦሮሞ ህዝብ መሃል ስለወጡና በተለያዩ ምክንያቶች በተሳሳተ አፍራሽ አመለካከት ተመርዘው በፅንፈኛነት ሃገርና ህዝብን ስለሚያተራምሱ በየዘመናቱ የነበሩ የኦሮሞ ፖለቲከኞች፣ ልሂቃንና የጎሳ መሪዎች እንጂ ወገኔ ስለሆነው የኦሮሞ ህዝብ እንዳልሆነ በቅድሚያ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ። ባለኝ የግል ልምድና ግንዛቤ አንጻር እንደተረዳሁት አብዛኛዎቹ የኦሮሞ ፅንፈኛ ፖለቲከኞች ወይም ልሂቃን በዋናነት የሚያመሳስላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ አለመረጋጋት፣ … [Read more...] about ፅንፈኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞች (ልሂቃን)
መልስ ለዶ/ር በያን አሶባ ቃለ መጠይቅ
የተከበራችሁ አንባቢያን፤ ይህችን መጣጥፍ ለመከተብ የተነሳሁት የዶ/ር በያን አሶባን (የኦሮሞ ዴሞክራሲ ግንባር ቃል አቀባይ) ቃለ መጠይቅ ካደመጥኩ በኋላ ነው፤ አመለካከታቸው ብዙ መልካም አስተሳሰቦችን በውስጡ ያካትታል፤ መልካም የምላቸው አመለካክቶች የኢትዮጵያ ችግር መፈታት ያለበት እዛው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑ፤ መሰረታዊ ለውጥ ማስፈለጉ፣ በሙሉ እከሌ ከእከሌ ሳይባል የፖለቲካ እስረኞች የመፈታትን ሃሳብ፣ የውጭው ትግል አጋዥነት እንጂ መሪ ቦታ መያዝ እንደማይገባው፤ የሚሉትን ሲሆን ትልቁ ተቃውሞዬ ወያኔን የሽግግሩ አካል ማድረጉ ላይ ነው፤ (በሰላምና እርቅ ሰበብ) ፍራቻቸው ወያኔ አጓጉል አወዳደቅ ከወደቀ አገሪቱ የማትወጣበት ችግር ውስጥ ትገባለች ነው፤ {አገሪቱ የማትወጣበት ችግር ውስጥ ከገባች ሰንብታለች}። ወደ በያን አሶባ ማንነት ስመለስ ለዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በመለሱት ደብዳቤ … [Read more...] about መልስ ለዶ/ር በያን አሶባ ቃለ መጠይቅ
“… አንድ ኮማንዶ…”
ጊዜው የጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ሕመማቸውና ሞታቸው በፈረቃ ተቃዋሚንም ሆነ ደጋፊን ዥዋዥዌ ሲያጫውቱት የነበረ ጊዜ ሲሆን፤ በተቃዋሚ በኩል መለስ ሲሞቱ ቢሯቸው ክፍት ስለሚሆን፤ ስልጣን የሚጠብቃት እረኛ በማጣቷ፤ ከቤተመንግሥስት ወጥታ ስትበር በወጥመድ ለመያዝ ያሰፈሰፈ ይመስል ነበር ቢባል፤ ብዙ የሚያሳማ ግንዛቤ አይመስለኝም። በዚያው ሰሞንም ነበር ጥምረትና ኦነገ (የጄ/ል ከማል ገልቹም) አሊያንስ ፈጠሩ ተብሎ የተወራው፤ ነገር ግን ወሬውን አጣጥመን ሳንጨርስ፤ በነሃሴ 1ቀን 2004 ዓ.ም. የተቋቋመው ስብስብ (ሰንጠረዥ ‹‹ለ››) ውስጥ ሁለቱ የአሊያንስ አባል ድርጅቶች ተነጣጥለው ገብተው እናገኛቸዋለን፤ ከዚያ ወዲህም የአሊያንስ ጉዳይ ኮሽታው ይጠፋል። (ሙሉው ጽሑፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about “… አንድ ኮማንዶ…”