የፌደራል ዋና አቃቢ ህግ ሜቴክ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ በገዛቸው ሁለት መርከቦች አማካኝነት በህግወጥ የንግድ እንቅስቃሴ መሰማራቱን ገልፆ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ግን በሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጄ ክንፈ ዳኘው ላይ የቀረበው ክስ ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ አባይ እና ህዳሴ የተባሉትን ሁለት መርከቦች በመግዛት ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት የሀገርና ህዝብን ሃብት ያለ አግባብ አባክኗል የሚል ነው። ሆኖም ግን ለድረገፃች አዘጋጅ በደረሰው መረጃ መሠረት ሜቴክ የገዛቸው ሁለት መርከቦች እ.አ.አ. እስከ 02 – 07/-01-2016 በምስራቅ አፍሪካዊቷ የኮሞሮስ (Comoros) ደሴት ሰንደቅ ዓላማ አያውለበልቡ በህገወጥ ንግድ ተሰማርተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በቀረበው የቴሌቪዥን ዶክመንተሪ ሜቴክ እ.አ.አ. በ2014 ዓ.ም አባይ እና ህዳሴ የተባሉን መርከቦች … [Read more...] about በኮሞሮስ ባንዲራ የሚቀዝፉት የሜቴክ መርከቦች እና በካሪቢያን ስም የምትቀዝፈው የኢትዮጵያ መርከብ
Middle Column
ሌብነት፣ ውንብድ፣ ግፍና ውርደት ልክ እንደ ጌታቸው
“የእኔ ሀብት ሰውነቴ ብቻ ነው የተመዘገበው ሀብት የእኔ አይደለም” ክንፈ ዳኘው የያሬድ ዘሪሁን አሰቃቂ ድርጊት በፍርድ ቤት ተነገረ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን፣ በተጠረጠሩበት ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ ፈጽመውታል የተባለ አሰቃቂ ድርጊት በፍርድ ቤት ተነገረ። አቶ ያሬድ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ማክበርና ማስከበር ሲገባቸውና ሕዝብ እንዲያገለግሉ የተሰጣቸውን ሥልጣን ወደ ጎን በመተው፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ከነበሩት አለቃቸው አቶ ጌታቸው አሰፋ የሚቀበሉትን ትዕዛዝ ለበታቾቻቸው ኃላፊዎችና ሠራተኞች በማስተላለፍ፣ ዘግናኝና ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውንና እንዲፈጸም ማድረጋቸውን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መርማሪ … [Read more...] about ሌብነት፣ ውንብድ፣ ግፍና ውርደት ልክ እንደ ጌታቸው
የሜቴኩ ክንፈ እና የኢንሳው ተክለብርሃን በቁጥጥር ሥር ውለዋል
የቀድሞው የሜቴክ ዋና ኃላፊ የነበረው ክንፈ ዳኜው እና የኢንሳ (የህወሃት የኢንፎርሜሽን ስለላ) ኃላፊ የነበረው ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት (አብመድ) በፌስቡክ ገጹ ምንጮቹን ጠቅሶ አስታውቋል። ዋልታ እንደዘገበው ደግሞ “ሱዳን ድንበር አካባቢ የተያዙት ሁለቱ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ዛሬ (ማክሰኞ) ከሰአት ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የደረሰን መረጃ ያመለክታል”። አብመድ ግለሰቦቹን በስም ባይጠቅስም በዜናው ላይ ግን “የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) እና የኢንሳ የቀድሞ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል” በማለት ነበር የዘገበው። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ትላንት በሰጠው መግለጫ ሜቴክ ያለምንም ጨረታ የ37 ቢሊዮን ብር ግዢ የፈጸመ መሆኑን የተናገረ ሲሆን በሽብር፣ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እና በሙስና ወንጀሎች የተጠረጠሩ … [Read more...] about የሜቴኩ ክንፈ እና የኢንሳው ተክለብርሃን በቁጥጥር ሥር ውለዋል
አማራና ትግራይ ክልሎች ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ?
ሰሞኑን በአማራና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረው የመግለጫ እሰጥ አገባ ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ እንዳይቀየር ፍርሃቻ አለ። የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ ወደ አማራ ክልል ለጉብኝት መምጣታቸው በህወሓት አቀንቃኞች ዘንድ በፍርሃቻ እየታየ ነው፤ ሌሎች የዘር ፖለቲካ አራማጆች ደግሞ ጉብኝቱን ስህተት ነው ብለውታል። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅና የሱማሌው ፕሬዚዳንት ሙሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግብዣ ዛሬ በአማራ ክልል ጉብኝት ለማድረግ ጎንደር ገብተዋል። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ጉብኝት የጎንደርና አካባቢውን ታሪካዊ ቦታዎች ለመመልከትና በባህር ዳር ውበት ለለመሰጥ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በተለይ ኢሳያስ በተደጋጋሚ በትግራይ አመራር ላይ ካሉት የህወሓት ሰዎች የቀረበላቸውን የወዳጅነት ጥያቄ ችላ በማለት ከህወሓት ጋር … [Read more...] about አማራና ትግራይ ክልሎች ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ?
“ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የክልሉ ነዋሪዎች
ላለፉት ሰባት ዓመታት የጋምቤላ ሕዝብ አንድነት ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ (ጋሕአዴን) ሊቀመንበርና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ጋትሉዋክ ቱት ከፓርቲው ሊቀመንበርነታቸው “በፈቃዳቸው” ለቅቀዋል። ከእርሳቸው ጋር አብረው ምክትላቸው ሰናይ አክዎርም ከፓርቲው ምክትል ኃላፊነታቸው እንደዚሁ በፈቃዳቸው ለቅቀዋል። በምትካቸው የክልሉ የሥነምግባርና ጸረ-ሙስና ኃላፊ ዑመድ ዑጁሉ ሊቀመንበር፤ የጋትሉዋክ ሚስት ወንድም የሆኑትና የክልሉ የንግድ ቢሮ ኃላፊ ታንኩዌይ ጆክ ሮምን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። የክልሉ ነዋሪዎች ምርጫውን “የቀድሞ ደጃዝማቾች ካባቸውን አውልቀው ለሚፈልጉት በመስጠት እንደሚሾሙት ጋትሉዋክም ለዘመዱ የስልጣኑን ካባ ያጎናጸፈበት ቀልድ ነው” ሲሉ አውግዘውታል፤ ይልቁኑም ጋትሉዋክ ቱት በበርካታ ወንጀሎች የሚጠረጠሩ ስለሆነ ሌሎቹንም አመራሮች ጨምሮ ሁሉም “ለፍርድ መቅረብ … [Read more...] about “ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የክልሉ ነዋሪዎች
ሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር የአገር ስጋት ሆኗል ተባለ
ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በአገር ደረጃ ስጋት ሆኗል ተባለ። ከተለያዩ አገራት በድንበር በኩል የሚገባውን ሕገወጥ የጦር መሳሪያ አስመልክቶ ጠንከር ያለ ሕጋዊ አሰራር ሊኖር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተናግሯል። በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንዶክትሪኔሽንና ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በከተማዋ በስፋት እየተስተዋለ ያለውን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለመግታት ጠንካራ የቁጥጥር ህግ ያስፈልጋል ብለዋል። 412 ሽጉጦችን፣ ከ12 ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይቶችንና ከ9 ሺ በላይ የክላሽ ጥይቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ 5 ተጠርጣሪዎችን ፍ/ቤት በዋስ መልቀቁ ጥብቅ የሆነ አሰራር ላለመኖሩ ማሳያ መሆኑን ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል። ከህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በተጨማሪ በጦር መሳሪያ የታገዘ ዘረፋና ቤት ሰብሮ ስርቆት … [Read more...] about ሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር የአገር ስጋት ሆኗል ተባለ
የለማ መገርሣ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ትርክትና የመሐመድ አዴሞ ሹመት
የኦሮሚያ ክልላዊ ምክርቤት ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም. የበርካታ አዲስ የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች አደረጃጀትን ሲያጸድቅ የአዳዲስ ተሿሚዎችን ሹመትም አጽድቋል። ከእነዚህ መካከል የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ዋና ዳይሬክተር እንዲሆን የተሾመው መሐመድ አዴሞ ነው። የአቶ ለማ መገርሣ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” የሚለው ልብ የሚያረካ አባባል ከመሐመድ አዴሞ ለዓመታት የዘለቀ ፀረ ኢትዮጵያዊነት አቋም ጋር የሚጋጭባቸው ወገኖች የሹመቱ ጉዳይ ትልቅ ጥያቄ ፈጥሮባቸዋል። በአንጻሩ ደግሞ መሐመድን ብቃት ካለው ባለሙያ አንጻር የሚመለከቱት ሹመቱ ትክክለኛ ብቻ ሳይሆን ገጣሚም ነው ይላሉ። ለሃያ ሰባት ዓመታት በግፍ ቀንበር ሥር የነበረውን ሕዝብ በለውጥ ማዕበል ውስጥ በማስገባት “እንቁላሉን ከውስጥ የሰበሩት” የለማ ቡድን (ቲምለማ) አባላት በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ … [Read more...] about የለማ መገርሣ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ትርክትና የመሐመድ አዴሞ ሹመት
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 20ቢሊየን ብር ብድር የተበላሸና የማይመለስ ሆኗል
ያለፈው አርብ መስከረም 18፤2011ዓም የባንኩን ሁኔታ አስመልክቶ ከፍተኛ ኃላፊዎቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው ባንኩ ባለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት ካበደረው 40በመቶ የሚሆነው የተበላሸ ብድር መሆኑን ተናግረዋል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከባንኩ መረጃ አቀባዮች ባገኘው መረጃ መሠረት በሁለት ዓመታት ብቻ ባንኩ ለባለሃብቶች አበድሮ የተበላሸው ብድር መጠን 6.37 ቢሊየን ብር መድረሱን ለማወቅ ተችሏል። ይህም ካለፉት አምስት ዓመታት የተበላሸ ብድር ጋር ሲነጻጸር በከፍተኛ መጠን ያደገ ሲሆን በአምስቱ ዓመታት በድምሩ ወደ 20ቢሊዮን የሚጠጋ ብር የተበላሸ ብድር ሆኗል። የኃላፊዎቹን መግለጫ የተከታተለው ሪፖርተር እንደዘገበው “በ2007 ዓ.ም. 12.5 በመቶ የነበረው የተበላሸ የብድር መጠን በ2008 ዓ.ም. ወደ 17.7 በመቶ አድጓል። በ2009 ዓ.ም. የተበላሸ የብድር … [Read more...] about የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 20ቢሊየን ብር ብድር የተበላሸና የማይመለስ ሆኗል
የኢህአዴግ የመጨረሻ ጉባኤ…
ኢህአዴግ መሽቶበታል። አቅሙ ክዶታል። ባልሞት ባይ ተጋዳይነት አለሁ ቢልም ዘላለማዊ ዕንቅልፉ ግን የሚቀርለት አይመስልም። የሜክሲኮውን ፒ አር አይ ፓርቲ አርአያው አድርጎ ሰባ አመታትን እጓዛለሁ ብሎ የተነሳው ድርጅት ግማሽ መንገድ እንኳን ሳይጓዝ ሊፈርስ ከጫፍ ደርሷል። ገዥው ፓርቲ ውስጥ ያለው የርዕዮተዓለም ልዩነት በማይታረቅ መንገድ የአደባባይ ሙግት ጀምሯል። ኦዲፒ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ መማል ካቆመ ቆይቷል። ሊቀመንበሩ ዓብይ አህምድም (ዶ/ር) ከትናንት ጋር የተኳረፉት ለዚህ ይመስላል። ብአዴን የምመራበትን ርዕዮተ ዓለም ዳግም አጤነዋለሁ ብሎ ዛሬ መወያየቱን ጀምሯል (ይህ ዘገባ ከተጻፈ በኋላ ብአዴን አዴፓ በሚል ህወሓት የሰጠውን ቀይሮታል)። ከዚህ በአንጻሩ ህወሓት አብዮታዊ ዲሞክራሲን ብረሳ ቀኜ ትርሳኝ ብሎ ሙጥኝ ማለትን ወዷል። ደኢህዴን ሁለት ጎራ ይዞ የለየለት ፍልሚውን … [Read more...] about የኢህአዴግ የመጨረሻ ጉባኤ…
መንገዳችን በፍጥነት ይቃና!
በብዙ ዓይነት ወንጀሎች የሚታሙት የወያኔ አዛዦች ሥልጣናቸውን እንደያዙ ከሥልጣን ወረዱ ቢባል ግራ ይሆናል፤ ነገር ግን ሆነ! በሕጋዊ ምርመራ ሳይጣራና ከሳሾቹን በፍርድ ቤት ሳይሞግት የሰው ልጅ እንደከብት ከመንገድ በጉልበተኞች እየተያዘ መታሰር የቀረ መስሎን ነበር፤ አልቀረም አሉ! ጉልበተኞች በወንጀላቸው ክብደት ከሕግ ይከለላሉ ይባል ነበር፤ አሁንም ያው ይመስላል! ያነበብሁትን በትክክል ካስታወስሁት በጥንታውያን ግሪኮች ሰርቀው መያዝ እንጂ መስረቅ ወንጀል አልነበረም (የምታስታውሱ አርሙት)፤ የምንመሳሰለው በጥንታዊነት ብቻ መስሎኝ ነበር! ከዚህ ቀደም ጸጋዬ ገብረ መድኅን (ይመስለኛል) ተረግመናል ብሎ፤ ነበር፤ እኔንም መሰለኝ! ኢትዮጵያውያን መልካቸውን፣ ነብሮች ቆዳቸውን እንዴት ይለውጣሉ ያለው መልካችንን ነበር፣ ወይስ ጠባያችንን ማለቱ ነበር! ነገሬ ሁሉ የጥንቶቹን አባትና እናት … [Read more...] about መንገዳችን በፍጥነት ይቃና!










