የፌደራል ዋና አቃቢ ህግ ሜቴክ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ በገዛቸው ሁለት መርከቦች አማካኝነት በህግወጥ የንግድ እንቅስቃሴ መሰማራቱን ገልፆ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ግን በሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጄ ክንፈ ዳኘው ላይ የቀረበው ክስ ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ አባይ እና ህዳሴ የተባሉትን ሁለት መርከቦች በመግዛት ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት የሀገርና ህዝብን ሃብት ያለ አግባብ አባክኗል የሚል ነው። ሆኖም ግን ለድረገፃች አዘጋጅ በደረሰው መረጃ መሠረት ሜቴክ የገዛቸው ሁለት መርከቦች እ.አ.አ. እስከ 02 – 07/-01-2016 በምስራቅ አፍሪካዊቷ የኮሞሮስ (Comoros) ደሴት ሰንደቅ ዓላማ አያውለበልቡ በህገወጥ ንግድ ተሰማርተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በቀረበው የቴሌቪዥን ዶክመንተሪ ሜቴክ እ.አ.አ. በ2014 ዓ.ም አባይ እና ህዳሴ የተባሉን መርከቦች … [Read more...] about በኮሞሮስ ባንዲራ የሚቀዝፉት የሜቴክ መርከቦች እና በካሪቢያን ስም የምትቀዝፈው የኢትዮጵያ መርከብ