Partial list of Oromos that have been killed as a result of Excessive force by Ethiopian Government (TPLF's regime) armed forces during Peaceful demonstration on August 6,2016, Oromia, Ethiopia. (updated 4 September 2016) Nr Name Sex Age Zone Locality Killed by 1 Abbuu Muummee M 17 Arsii Ticho Agazi 2 Abdallaa Mohammed M - East Harageh Qobo Agazi 3 Abda Jiloo M 24 West Arsii Asasa Agazi 4 Abdaa Hasanoo M 31 West … [Read more...] about የሰማዕታት ዝርዝር በከፊል
Social
“የዛፍ ላይ እንቅልፍ!” ስደት
የመረጃ መረቡ ከሃገር ቤት በሚሰማው የህዝብ እንቢተኝነት አመጽ ተጨናንቆ እኛንም አጨናንቆን ከርሟል። በዚህ የመረጃ ቅብብሎሽ መካከል ወደ ምሥራቅ ሳውዲ ለስራ ጉዳይ አቅንቸ ነበር። ርያድ፤ ደማም፡ ጁቤል፤ ሃፍር አልበጠንን ለአንድ ሳምንት ሳካልል ከሃገር ቤት ከሚሰማው መረጃ እኩል በሳውዲ ዙሪያ ያሉ በርካታ ወገኖቸ የተለያዩ መረጃዎች በስልክ አድርሰውኛል። በተዘዋዎርኩባቸው ከተሞች ያገኘኋቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቸም የሚያመውን የስደት ህመም ሳይደምቁ አጫውተውኛል። ሁሉም አሳሳቢ ናቸው፣ ሁሉም ቢያንስ መፍትሔ ይሻሉና ዝም የማይባለውን የወገንን ድረሱልኝ ጥሪ አሳውቃችኋላሁ! ዛሬም በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተኑ ችግር የገጠማቸው ዜጎች መብት አስከባሪ አጥተው ሲንከራተቱ፣ ሲንገላቱና የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ነው! በአንጻሩ አዲስ ኮንትራት ውል ከሳውዲ አረቢያ ጋር ለመስማማት ደጋግሞ … [Read more...] about “የዛፍ ላይ እንቅልፍ!” ስደት
የበጎው ሰው፣ የጎልማሳው ህልፈት…!
በያዝነው ሳምንት ... በአብዛኛው የሀበሻ መገናኛ መንደር፣ በማህበራዊ ድህረ ገጽ ዋንኛ መድረክ በ Facebook መስኮት አንድ መሪር መርዶ ተሰምቷል! የትሁት ፣ አስተዋይና አርቆ አስተዋዩ በጎ ሰው ፣ የጎልማሳው የአቡኬ አሌክስ ህልፈት!!! የአቡኬ አሌክስ በድንገት መለየት ጥልቅ ሀዘናን ሁላችንም አንገብግቦናል! "ከሞቱ አሟሟቱ " እንዲሉ አቡኬ ባንድ ጀንበር ታይቶ በርቶ ፣ ባንዱ ጀንበር ሳይታሰብ ጠፍቶብናል! እናም በቅርብ ከሚያውቁት ፣ ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ጓደኞች እኩል በስራው በዝና የምናውቀው በሀዘኑ አዝነን ከፍቶናል! የጎልማሳው በጎ ሰው አቡኬ አሌክስ መረጃዎች የቅርብ ተከታታይ የሆነችው ባለቤቴ በህልፈቱ ጥልቅ ሀዘን የተሰማቸው መካከል አንዷ ናት ፣ ስለአቡኬ ስትገልጽ እንዲህ ብላኛለች " አቡኬ ብሩህ አዕምሮ የነበረው ፣ ኢትዮጵያውያንን በዘር በሐይማኖታዊ ሳይለየን … [Read more...] about የበጎው ሰው፣ የጎልማሳው ህልፈት…!
ደብዳቤ
ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለጓደኞቻቸው በሙሉ፤ ሰላምታዬን አቀርብላችኋለሁ፡፡ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር አገር ነች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የእግዚአብሔር ሕዝብ ነው፤ ክርስቲያኑም፣ እስላሙም፣ አረመኔውም የእግዚአብሔር ነው፤ እንደየእምነቱ በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚኖር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ጊዜ የተለየ ነው፤ ትእግስቱን ስለሚያረዝመው የተረሳ ያስመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግፍን አይረሳም፤ እግዚአብሔር ሁሌም ለአቅመ-ቢሶች ጉልበት የሚሆንበት መንገድ አለው፤ ግፍ በእግዚአብሔር በር ላይ እንደተጣለ ግም ቆሻሻ ነው፤ እግዚአብሔር ሲፈቅድ ይጠርገዋል፤ ወይም ያስጠርገዋል፡፡ እግዚአብሔር መንገዱ ብዙ ነው፤ ግፍን የሚያስከፍለው በተለያየ መንገድ ነው፤ በግፈኛው ቤተሰብ ላይ ሁሉ የግፈኛነት ጠባሳን ያሳርፍበታል፤ ሰዎች ለሥልጣናቸው ባላቸው ቅናት የእግዚአብሔርን ሥልጣን ይጋፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥልጣን መጋፋት … [Read more...] about ደብዳቤ
ጳጳሶችና ስደት
እንዲያውም ርእሱን ካህናትና ስደት ብለው ይሻላል፤ ካህናት የሁሉንም ሃይማኖቶች መሪዎችን ይመለከታል፤ ዓላማዬም ሁሉም የሃይማኖት መሪዎችን የሚነካ ነው፤ ነገር ግን የእኔ እውቀት በክርስትናው ላይ ጎላ ያለ በመሆኑ የክርስቲያኖቹ መሪዎች ላይ ያተኮርኩ ቢመስልም ሁሉንም ይመለከታል፤ በተለይ መነኩሴዎች ላይ የማነጣጥርበትም የተለየ ምክንያት አለኝ፡፡ በመጀመሪያ አንድ መሠረታዊ ነገር ላብራራ፤ እንደማንኛውም ሰው ስለፍርሃትና ስለጥቃት አውቃለሁ፤ በተለያዩ መንገዶች በመርማሪዎች የተሰቃዩ ሰዎች ሲናገሩ ሰምቻለሁ፤ የጻፉትንም አንብቤአለሁ፤ ከሁሉም በላይ ፍርሃት የግል መሆኑን አውቃለሁ፤ በዚህም ምክንያት ሰውን ለምን ፈራህ ብሎ መውቀስም አስቸጋሪ መሆኑ ይገባኛል፤ ስለዚህም ይህንን የምጽፍበት ምክንያት የተሰደዱትን ለመውቀስና እነሱን ዝቅ አድርጌ ራሴን ከፍ ለማድረግ አይደለም፤ ከቃሌ በቀር ይህንን … [Read more...] about ጳጳሶችና ስደት
“በሴትነቴ የደረሰብኝ በደል ቁስሉ ከኅሊናዬ ባይጠፋም ታሪኬ ተቀይሯል”
* “... እህታችን ታሪኳን ስትነግረኝ፣ ለፍትህ እንደምትመጥን አመንኩ” ኦባንግ “... የተረሳሁ ነበርኩ፡፡ የደረሰብኝ ግፍ ጠባሳ የሚያልፍ መስሎ አይታየኝም ነበር። ግን ብርሃን ሆነልኝ። በየትኛውም ወቅት ልረሳው የማልችለው ኦባንግ ሜቶ ችግሬን ዝቅ ብሎ አደመጠኝ። ና ባልኩት ቦታ ሁሉ ፈጥኖ እየደረሰ ፍትህ ደጅ እንድቆም ረዳኝ። ስለ እሱ ለመናገር ቃላቶች የሉኝም። ከሁለት ዓመት በፊት ያለመድሃኒት አልተኛም ነበር። ዛሬ መድሃኒት ከመቃም ተገላግያለሁ። በሴትነቴ የደረሰብኝ በደል ቁስሉ ከህሊናዬ ባይጠፋም ታሪኬ ተቀይሯል። … በየቦታው ፍትህ የተዛባባችሁ ወገኖቼ ዝም አትበሉ። ፍትህ በደጃችሁ ነው። ግን ተናገሩ። ሆን ብላችሁ ያላጠፋችሁት ጥፋት አያሳፍራችሁምና ራሳችሁን ከዝምታ ድባብ አላቅቁ...” ይህ ስሟ እንዳይነገር ከጠቀችው እህት አንደበት ነው። “... እኔ የሰራሁት ሥራዬን ነው። … [Read more...] about “በሴትነቴ የደረሰብኝ በደል ቁስሉ ከኅሊናዬ ባይጠፋም ታሪኬ ተቀይሯል”
ችጋር – የሶስት ዓመት የዞረ ድምርና የህወሃት የፖሊሲ ክሽፈት
የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የባለስልጣናት ሌብነትና ድርጅታዊ ዝርፊያ፣ የማንነት ጥያቄ፣ ድህነት፣ ስራ አጥነት፣ አድሏዊ አመለካከት፣ የሰብአዊ መብት አለመከበር፣ የማሰብ፣ የመቃወም፣ የመናገርና የመጻፍ ተፈጥሮአዊ መብቶች መጣስ፣ የዲሞክራሲ መብቶች አለመከበር የፈጠረው ስሜት ተጠራቅሞ እየገነፈለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ኢትዮጵያ የተነከረችበት ከፍተኛ እዳና የተከሰተው ችጋር አገሪቱን ወደ ከፋ ቀውስ እንዳያመራት ስጋት አይሏል። ባለፉት ስድስት ወራቶች ሰላማዊ ጥያቄ ያነሱ ዜጎች በጥይት ተደብድበው ሞተዋል። በዚሁ ሳቢያ ኦሮሚያ በእምባ ነፍራለች። ህጻናትና እናቶች በህወሃት ልዩ ታማኝ ኃይሎች ተገድለዋል። የታሰሩ ዜጎች ቁጥር በሺህ የሚቆጠር ነው። የት እንደ ደረሱ የማይታወቁ ወገኖች ስለመበራከታቸው ቤተሰቦች ስምና አድራሻ ሳይደብቁ እየተናገሩ ነው። አማራ ክልል “በግድ ትግሬ መሆን በቃን” … [Read more...] about ችጋር – የሶስት ዓመት የዞረ ድምርና የህወሃት የፖሊሲ ክሽፈት
“የልጄን ነገር አደራ…” እናት ሎሚ
የእናትን መሪር ሐዘን ሰምቸ ሆዴ ተላውሷል፣ የእናትን ጥልቅ ጭንቀቷ፣ ያለ አባት በአሳር በመከራ ያሳደገቻት የእናትን ሎሜ መሪር ሐዘን ተረድቸ ህመም መታመሜ እውነት ሳለ በዝምታ እየቆሰልኩ ማስረጃ መረጃ ፍለጋ መዋተቴ ህመሜን አክብዶታል፡፡ ከጉያዋ ወሽቃ፣ በትንፋሿ አሙቃ፣ ስታገኝ በደስታ፣ ስታጣ ተከፍታ ድሃ አደግ ቤቷን አሟሙቃ ነገን ልጆቿን ለወግ ለማዕረግ የማድረስ ምኞት ተስፋን ሰንቃ ተስፋዋን የተነጠቀች እናት እንባ ውስጤን አድምቶ አቃጥሎታል። እናት ዛሬ ማለዳ በላኩልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል “የልጀን ነገር አደራ እባክህ ነፍሴን አሳርፋት" … ሰው ሆዬ ሲጨንቀው እኔ መረጃን ከምንጩ ከማሰራጨት ባለፈ ሁሉን ማድረግ የሚቻለኝ አድርጎ ይስለኛል፤ እኔ ግን አቅሙ የለኝም! መረጃዎችን ለወገናቸው ጥቅም ቅድሚያ ከሚሰጡ የመንግስትና የድርጅት አባላት በሚስጥር፤ ከቀሩት ወገኖች … [Read more...] about “የልጄን ነገር አደራ…” እናት ሎሚ
የጥቁር ሕዝብ ኩራት!
መጪውን የአድዋ ቀን ስናስብ “እምዬ ምኒልክ ምን ዓይነት ውርስ ትተውልን ሄዱ?” ብለን እንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ በመሆኑም ወደ ጦርነት ለመግባት ሳይፈልጉ “በግድ” ወደሄዱበት የጣሊያን ጦርነት መለስ ብለን የሆነውን እንድናስብ ወደድን፡፡ ክተት፡- “እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላትን አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ እንግዲህ ብሞትም ሞት ለሁሉ ነውና ስለ እኔ ሞት አላዝንም፤ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፤ እንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር በር አልፎ መጥቷልና እኔም ያገሬ ከብት ማለቁንና የሰዉን መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡ አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት … [Read more...] about የጥቁር ሕዝብ ኩራት!
አቅም የተፈጠረላቸው ፈላሾች – ህወሃቶች
ከ1997 ምርጫ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ከፈለሱት የክልል ነዋሪዎች መካከል ከ87 በመቶ በላይ የትግራይ ተወላጆች እንደሆኑ አንድ የስታትስቲክስ ባለስልጣን ባለሙያ ጠቆሙ። ቁጥሩ የሚያሳየው ባግባቡ ከሃብትና ንብረት፣ ወይም ከመተዳደሪያ ጋር የተመዘገቡትን ብቻ እንደሚያካትት ባለሙያው አመልክተዋል። ከዘጠና በመቶ በላይ ከሌሎች ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚፈልሱት የእለት ጉርስ ፍለጋ ነው። በኢንቨስትመንት ስም በሚፈናቀሉ ዜጎች ኮቴ፣ በኮንደሚኒየም ቤቶች ዝውውር፣ መከላከያ፣ ደህንነትና ሁሉንም ዓይነት የፖሊስ ተቋማት ጨምሮ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ቅጥርና በመሳሰሉት ሰፊ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ወደ አዲስ አበባ ተምመዋል፤ እየተመሙም ናቸው። እንደባለሙያው የሌሎች ክልል ተወላጆች በስፋት ወደ አዲስ አበባ ቢፈልሱም፣ የትግራይ ተወላጆችን ልዩ የሚያደርገው “አቅም እየተፈጠረላቸው … [Read more...] about አቅም የተፈጠረላቸው ፈላሾች – ህወሃቶች