• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ልጄን ገድለው በማዳበሪያ አመጡልኝ” እናት

November 5, 2016 02:47 am by Editor Leave a Comment

የለቅሶ ሳግ በያዘው አንደበት የመረረ ሃዘን ይሰማል። ተናጋሪዋ የሚሰሩት ድራማ ወይንም ዘጋቢ ፊልም ሳይሆን በትክክል የደረሰባቸውን ነው። የልጃቸው አስከሬን እንደ ምናምንቴ በማዳበሪያ ተደርጎ ነው የተሰጣቸው። ልብ ይነካል። ያማል። ጉዳዩ ከሃዘንም በላይ ይሆናል። አንድ ልጃቸው “መመኪያዬ” የሚሉት ተገደለባቸው፤ ሌላኛው ክፉኛ ተደብድቦ ታሟል፤ ሁለቱ ታስረዋል። እኚህ የ65 ዓመት አዛውንት ሲያልቅ አያምር ሆነና ባዶ ሆኑ።

“ልጄን ገድለው በማዳበሪያ አመጡልኝ” አሉ። አስከትለው አስከሬኑ መበላሸቱንና ደም ይፈሰው እንደነበር ገለጹ። ወግ አይቀር ተቀበረ። አሁን አሁን “ወዴት እየሄድን ነው” ከማለትም ያለፈ ይመስላል። ስለ ጉዳዩ የተጠየቁት የወረዳው አስተዳዳሪ “በአሁኑ ሰዓት እንዲህ ያለ ችግር የለም” ማለታቸው፣ ዋና አስተዳዳሪውና የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ምላሽ ለመስጠት አለመፈለጋቸው ሌላው አስዛኝ ጉዳይ ነው።

በምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ቦሰት ወረዳ ቆምቤ ጉግሳ መንደር ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ የ65 ዓመት፣ ባለቤታቸው የ74 ዓመት አዛውንት ናቸው። እኒህ ሁለት አዛውንቶች የደረሰባቸው ሃዘንና ግፍ ኢህአዴግን ለሚደግፉም ሆነ ለሚቃወሙ ለሁሉም ልብ የሚሰብር ነው። የወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮን ቤት መበተን ጀግንነትም አይሆንም። እሳቸው ላይ የደረሰው ሃዘን በፖለቲካ ሚዛንና ትርፍ ማየትም አግባብ አይሆንም።

“የሞተ አይመለስም” የሚሉት እናት “የተበታተኑትን ልጆቼን መልሱልኝ” በሚል ጠይቀዋል። እናም የገዢዎች ምላሽ ምን ይሆን? የሃላፊዎችስ ምላሽ ምን ይሆን?

ቀደም ሲል በወለጋ አንድ እናት የልጇ አስከሬን ላይ እንድትቀመጥ ተደርጎ የተፈጸመውን ያስታወሰው ይህ ዜና፣ አፋጣኝ ምላሽ የሚያሻው ሆኖ ተገኝቷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀና ከመታወጁ በፊት በአገሪቱ ታሪክ ክፉ የተባሉ ተግባራት ተፈጽመዋል። ይህ የሚቆምበትና ሁሉም ነገር በህግ የሚታይበት አግባብ እያለ እንዲህ አይነት የከፋ ድርጊት መፈጸም በየትኛም ጊዜ ዋጋ የሚያስከፍል፣ ለማንኛውም ወገን ገድል ሆኖ የማይቀመጥ፣ ነውና ሁሉንም ባግባቡ ማስተናገድ፣ አግባብ እንደሆነ አዛውንቶችና ነገሮችን በሰከነ መንፈስ የሚመለከቱ ይመክራሉ። (ምንጭ: ዛጎል ዜና)

የቪኦኤ ያጠናቀረው ዘገባ ከዚህ የሚከተለው ነው።

“የሞተው ልጄ ሞቷል፤ ያሉትን መልሱልኝ” ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው በምስራቅ ሸዋ ዘን ቦሰት ወረዳ የሚገኙ ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ የተባሉ እናት አንድ ልጃቸው እንደተገደለ ሁለቱ እንደታሰሩና አንዱ በእጅጉ መደብደቡን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ለስድስት ወር አስቸኳይ ጊዜ ከታወጀ አንድ ወር ሊሞላው ጥቂት ቀናት ይቀሩታል። ይህ ዐዋጅ ይፋ ከተደረገ በኋላ ሰዎች ከየቦታው እየተለቀሙ እንደሚታሰሩ በተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና በሰባዊ መብት ተሟጋቾች ጭምር ሲነገር ቆይቷል።

ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ ቆምቤ ጉግሳ በተባለ መንደር ነዋሪ እንደሆኑ ይናገራሉ። የ65 ዓመት አዛውንት ናቸው። ባለቤታቸው ደግሞ የ74 ዓመት አዛውንት መሆናቸውን ገልጸውልናል። እንደ ወ/ሮ ሎሚ ገለጻ አራት ልጆች ነበራቸው። አቢቲ ደጃሳ የተባለ የ30 ዓመት አርሶ አደር ልጅ ነበራቸው። ደምሴ ደቻሳ ወይም ደሜ እያሉ በቁልምጫ የሚጠሩት የ22 ዓመት ልጃቸው ደግሞ “አዳማ ሄዶ ሥራ ፍለጋ ሲንከራተት ተይዞ ታስሯል” ይላሉ። የት እንደታሰረ ግን አያውቁም።

ንጉሴ ደቻሳ የተባለው ልጃቸው ደግሞ ከቤት ውስጥ ተደብድቦ ተወስዶ ወለንጪቲ ተወስዶ መታሰሩን ይናገራሉ። ወ/ሮ ሎሚ በለቅሶ በታጀበ ድምጽ ረዳታቸው የ30 ዓመቱ ወጣት አቢቲ ደቻሳ ለስብሰባ ይፈለጋል ተብሎ ከቤታቸው ከተወሰደ በኋላ ጥቅምት 12 ቀን 2009 ዓ.ም አስክሬን እንደመጣላቸው ይናገራሉ።

የልጃቸው ለቅሶ ባይመጣና ቤታቸው ሐዘን ባይገባ ኖሮ ወለንጪቲ ታስሯል የተባለውን ልጃቸውን ንጉሴን ሄደው ይጠይቁት እንደነበር ገልጸዋል። “አንዱን በሞት አጣሁ። አሁን አንድ ሰው አብሮኝ የለም። ቤቴ ባዶውን ቀርቷል። ደካማ ነኝ” የሚሉት ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ “የሞተው ልጄ ሞቷል፤ ያሉትን መልሱልኝ” ሲሉ ይጠይቃሉ። የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ይህን በተመለከተ የደረሰን ሪፖርት የለም ብለዋል። (ፎቶ: New York Daily News A woman mourns during the funeral of Tesfu Tadese Biru, 32, a construction engineer who died during a stampede after police fired warning shots at an anti-government protest in Bishoftu the day before.)

የአሜሪካ ድምጽ የኦሮመኛ ቋንቋ ዝግጅት ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረችውን ዘገባ በጽዮን ግርማ እዚህ ላይ በድምጽ አቅርባዋለች።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Social Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule