• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሃት እጅ ላይ የንጹሃን ደም እየተንተከተከ ነው!! የምትኮሩ በዚህ ኩሩ

November 24, 2016 05:46 am by Editor Leave a Comment

ህወሃት የታሪኩ ካስማና ማገር ከአስከሬን ጋር የተጣበቀ ስለመሆኑ የሚመሰክሩበት የሩቅ ሰዎች አይደሉም። አብረውት በበረሃ የነበሩ፣ አብረውት አመራር ሲሰጡ የኖሩ፣ “በሚያራምዱት አቋም” ከድል በፊትና በኋላ የተለዩት በተለያዩ ሚዲያ ላይ እንደመሰከሩት ህወሃት ደም ምሱ፣ አስከሬን ትራሱ ነው። በነዚሁ የቅርብ ሰዎቹ የተሰሙት ምስክርነቶች ስም፣ ቦታ፣ ጊዜ በመጥቀስ በወቀቱ እዚያው እንደነበሩ በማረጋገጥ እንጂ እንዲሁ በመላ አልነበረም። እነሱ ለአብነት ተነሱ እንጂ ሰለባዎች በየጊዜው አዳዲስ መረጃ ይዘው ብቅ ማለታቸው የተለመደ ነው። እዚህ ላይ ሌሎችም አይረሱም። ቅድሚያ ስለ ሌሎቹ።

በቦታው የነበረ የዓይን እማኝ፤ ደደር 1983

የጅጅጋ ሆቴል ባለቤት ዓለምዘውድ እንዴት ሞተች?

ዓለምዘውድ ቁመቷ ረጅም፣ ሰውነቷ ሙሉ፣ አሣ የምትመስል ጠይም፣ ደግና ርኅሩኅ እንደነበረች የሚያውቋት ይመሰክራሉ። መሃረብ በምታክለው ደደር ከተማ በሆቴል ስራ የተሰማራችው ይህች ውብ ሴት ሁሉም ወዳጇ ነበር። በወረዳው አዳዲስ ሰራተኞች ሲመጡ፣ ዱቤ መመገብ ሲፈልጉ፣ ቤተሰብ ለመጠየቅ ገንዝብ ያጡና የቀን መዋያ የሌላቸው ዓለምዘውድ ዘንድ ከሄዱ አያፍሩም።

1983 ኢህአዴግ ወደ ደደር ከመገባቱ በፊት ደደርን ሲያስተዳድር የነበረው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግምባር (ኦነግ) ነበር። በደደር ለውጡን ተከትሎ ወዲያውኑ መሳሪያ ታጥቀው ፈላጭ ቆራጭ የሆኑ በርካቶች ነበሩ። እነዚህ በከተማዋ የሚታውቁ ሰዎች ሲታጠቁ ምን እንደነካቸው አይታወቅም አንዱን ቀን ወደ ጅጅጋ ሆቴል አመሩ። እዚያም እንደ ደረሱ ዓለምዘውድን አገኙ። እየሳቀች ስታናግራቸው እነሱ የወትሮው አይነት አልነበሩም። የአካባቢው ተወላጅ ባለመሆኗ ብቻ ገደሏት። የመጸዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ከተቷት። ይህን ያየና የሰማ የደደር ተወላጅ መምህር ይህንን ታሪክ ሲያወጋ እያነባ ነው። ገዳዮቹም እሱም እኩል ሰዎች፣ እኩል ፍጡሮች ናቸው። በደደር ሌላም ሌላም ሆኗል።

ስለ አስከሬን ሲነሳ እነዚህም ክፍሎች ሁሌም ከግንዛቤ ውስጥ የሚገቡ ናቸው። ወደ መነሻው ስንመለስ ህወሃት ለምንድን ነው ከአስከሬን ስር የሚርመጠመጠው? በረሃ በራሱ ባልደረቦች ላይ የጀመረውን የሰው ልጆችን የመብላት ታሪክ ለምን አይገታውም? ለምንስ አውሬ ይሆናል? የሚሉትና ተመሳሳይ ጥያቄዎች ይሰነዘራሉ። ከዚህም በላይ ራሱ እያፈነዳ፣ ራሱ እያቃጠለ፣ ራሱ ፈንጂ አጥምዶ እያከሸፈ በሰዎች ላጆች ህይወት ላይ እስከምቼ ይቆምራል? በሚል የሚጠይቁ ክፍሎች ለህወሃት ሰዎች፣ አምላኪዎች እንዲሁም ቅጥረኞች መልእክት አላቸው። በየጊዜው የሚያልቁት ንጹሃኖች ለህወሃት ደጋፊዎች ሃዘን የሚሆነውና “በቃ በእኛ ስም ይህን አታድርጉ” የሚሉት መቼ ነው? የሌሎች እናቶች፣ አባቶችና ቤተሰቦች እንባ ለህወሃት ደጋፊዎችና ቅጥረኞች ሃዝን ሆኖ የሚሰማቸው መቼ ነው? ሌላም ሌላም።

ረጋ ተብሎ እኮ ሲታሰብ ህወሃት በሰዎች ደም በክቷል። የንጹሃን ደም ይጮህበታል። በጋምቤላ ምንም የማያውቁ ከ400 በላይ ንጹሃንን በሁለት ቀናት በመረሸን ደማቸውን ጠጥቷል። በበደኖ ኡንቁፍቱ በሰዎች ልጆች ክቡር ህይወት ላይ የተሰራው ድራማ ህሊና ላላቸው የሚዘገንን ነው። አዲስ አበባና በተለያዩ የክልል ከተሞች አልሞ ተኳሾች በመቶዎችን ረሽነዋል። ኦጋዴን ላይ በር ተከርችሞ ያለቀውን ህዝብ ቤቱ ይቁጠረው። በኦሮሚያ ህወሃት የተጋተው ደም አይሰፈርም። አማራ ክልል እይሆነ ያለው ወደፊት ታሪክ የሚገልጠው ነው። እዛም ዜጎች አልቀዋል። እስረኞችን በእሳት እያሳበቡ በጥይት መደብደብ አዲስ ፈሊጥ ሆኗል። ምን አደከመን በአገሪቱ ዙሪያ የደም ጎርፍ ይጎርፋል። ህወሃት በዚህ ሰፊ የደም ባህር ውስጥ ተንክሮ በ“ጥልቅ ለመታደስ” ይስብካል። መቼ ነው ግን የሚያበቃው? ይህ የሁሉም ጥያቄ ነው። ሁሉም በየፊናቸው ግድያ መቼ ያበቃል በሚል ሲብሰለሰሉ ይባስ ተብሎ በአስቸኳይ አዋጅ ስም ህዝብ እየታጨደ ነው። የዚህ ሁሉ ድምር ወዴት ያመራል? አገሪቱንስ ወስዶ ወስዶ ምን ውስጥ ይጨምራታል? ለመነሻ ይብቃና አሁን ህወሃት ከአስከሬን ምርመራ ስርቻ ውስጥ መላቀቀ የማይፈልገው ለምንድን ነው? ወደሚለው ጉዳይ እናምራ!!

ህወሃትና ሚኒሊክ ሆስፒታል– የአስከሬን ምህላ

ህወሃት ከሌሎች ሆስፒታሎች በተለየ ሚኒሊክ ሆስፒታል ላይ ትኩረት የሚሰጠው ከላይ በተዘረዘረው የደም ጉዳይ ነው። አስከሬን በብቸኛነት የሚመረመረው እዚሁ ሆስፒታል በመሆኑ ህወሃት ራሱ ገሎ፣ ራሱ መርምሮ፣ ራሱ የሙት ማረጋገጫ በመስጠት እጁን ከደምና ከማይተካው የሰው ልጆች ነፍስ ዕዳ ነጻ ለማድረግ ሲል የሚኒሊክን ሆስፒታል እንደ መዥገር ተጣብቆበታል። ሰሞኑንን ኢሳትን ፈልገው መረጃ የሰጡት የህክምና ባለሙያ ሚኒሊክ ሆስፒታል ሲሰሩ በነበረበት ወቅት በአይናቸው ያዩትን በጆሯቸው የሰሙትን ይፋ ሲያደረጉ ያመላከቱት ትልቅ ጉዳይ ይህ ነው። የህወሃትን የአስከሬን መሃላ ነው ያረጋገጡት። አምፊ

ዶ/ር ካሳሁን በዛብህ ደከመኝ ያማይሉት የአገር እንቁ አሟሟት

ዶክተር ካሳሁንን የሚያውቋቸው “ሰለቸኝ” የማይሉ የህክምና ባለሙያ መሆናቸውን ይመሰክራሉ። አንዳንዶች በጥልቀት የሚያውቋቸው “ዕንቁ” ይሏቸዋል። የህክምና ህግ ባለሙያ፣ የካንሰር ህክምና ባለሙያ፣ በርካታ ጥናቶችን የሚያከናውኑ፣ እኚህ ውድ ሰው “አልታዘዝም፣ አልዋሽም፣ ሙያዬ የማይፈቅደውን አላደርግም” በማለታቸው ተሰቃዩ። መኖር ባለመቻላቸው አዲስ አበባን ለቀው ወጡ። በግል የሚሰሩባቸውን ሥራዎች አቆሙ። ቢጨንቃቸው እንደ እሳቸው የህክምና ባለሙያ ከሆኑ ወንድማቸው ዘንድ ተጠግተው መኖር ጀመሩ። የሚደረግባቸው ክትትልና ማስፈራሪያ ጠነከረ። ዕንቁው ባለሙያ ከሚኒሊክ ሆስፒታል፣ በግል ከሚሰሩባቸው ስፍራዎች ራሳቸውን አግልለው በወንድማቸው ቤት ጥገኛ ሆኑ።

በወቀቱ የሚዲያ ሰዎች ጉዳዩን ቢያውቁም የሚዘግቡት “የሚኒሊክ ሆስፒታል አስክሬን ምርመራ ሥራ አቆመ፣ የባለሙያ እጥረት አጋጠመው፣ ከኩባ ባለሙያዎች ሊቀጠሩ ነው…” የሚሉ ተራና ጉንጭ አልፋ ዜና ነበር። በዚሁ የተልፈሰፈሰ ዜና መካከል የዶ/ር ካሳሁን ሞት ተሰማ። ጉዳዩ ተረሳ። ተደፈነ። ፖሊስም ጸጥ አለ።

በ1992 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ ሻዕቢያ በጄት የደበደባቸውን የትግራይ ሃይደር ትምህርት ቤት ህጻናትን ለማስታወስ የሜጋ አምፊቲያትር ባዘጋጀው የመዝናኛ ዝግጅት ላይ ከአዲስ አበባ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተሰባሰቡ ተማሪዎች በድንገት ሞቱ ተባለ። አሟሟታቸው በኤሌክትሪክ መነሾ ቢሆንም ህወሃት የሚነዳቸው ሚዲያዎች “ተረጋግጠው ሞቱ” ሲሉ ዘገቡ። ታሪኩ ግን ሌላ ነበር።

የሚኒሊክ የአስከሬን ምርመራ ክፍል ሃላፊ የነበሩት ዶክተር ካሳሁን በወቅቱ ኤሌክትሪክ ጥብሶ የገደላቸውን ህጻናት አስመልክቶ ትክክለኛውን የህክምና ሪፖርት ያዘጋጃሉ። በወቅቱ 14ቱ ሲሞቱ 53ቱ ቆስለው ነበርና ህወሃት እንደለመደው አስከሬን ቤት ሊርመጠመጥ መጣ። ባለሙያው ያዘጋጁትን ሪፖርት እንዲቀይሩ መመሪያ ሰጠ። እሳቸው “አላደርገውም” አሉ። በዚህ መካከል ግፊቱና ጫናው ጠነከረ። ስራ ለቅቀው ወደ ሐረረ ተሰደዱ። ከዚያም አዲስ አበባ ተመለሱና ወንድማቸው ቤት ተጠጉ። ባልደረባቸው ኢሳት ዘንድ መቶ እንዳለው አንድ ቀን ፒያሳ አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ተመግበው እጃቸውን ለመታጠብ እንደሄዱ ቀሩ።(የዶክተሩን ምስክርነት እንደ ህጋዊ ማስረጃ በፍርድ ቤት መቅረብ የሚችል ነው፡፡)

ወንድማቸው ግራ ተጋብተው ወደ መታጠቢያ ቤት ሲያመሩ ዶ/ር በዛብህ አንገታቸው በስለት ተወግቶ ወለል ላይ ተዘርረዋል። በምሬትና በጭንቀት ሲገፉት የነበረው ህይወት በነፍሰበሎች ተገታ። ዕንቁው ሰው አረፉ። ይህ የተደበቀ ታሪክ የህወሃት ገድል ነው። በህዝብ ስም የሚምሉት ነፍሰበሎች ሁሌም አስከሬን ስራ ናቸው። ይህንን ያጋለጠው ባልደረባቸው የዶ/ር ካሳሁን ወንድም ገዳይ ተብለው እንደታሰሩም አስታውቋል። ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል ይሏል ይህ ነው። ይህ በህወሃት ለምትመኩ፤ የህወሃትን ቅድስና ለምትሰብኩ፤ ለህወሃት ዘብ ለምትቆሙ፤ ህወሃት ሁለመናችሁ ለሆነ፤ … ተጨማሪ ኩራት ይሁናችሁ።

በስለት የተወጉት ዕንቁ ገዳያቸው እስካሁን አልታወቀም። የተወጉበት ቢላም አልተገኘም። የተሰወረውም ወዲያው ነው። በወቅቱ ዜናውን ሲዘግቡ የነበሩ ያገር ቤት ሚዲያዎች “ራሳቸውን አጥፍተው ተገኙ” በማለት ነበር። እንደ ባልደረባችው ትንታኔ “…እኚህ ሰው የህክምና ባለሙያ ናቸው። ራሳቸውን ማጥፋት ቢፈለጉ በእንደዚህ መልኩ ሳይሆን በርካታ ቀላል መንገዶችን መጠቀም ይችሉ ነበር…” ሲል ፖሊስ የሰጠውን መረጃ ተራን ወራዳ እንደነበር ያሳያል። ይህ ባለሙያ በተደጋጋሚ ይቅርታ በመጠየቅ በሰጠው መረጃ “ኢትዮጵያ ውስጥ የባለሙያ ችግር የለም። ችግሩ በነጻነት የመስራት ነው” ሲል ለምን የአስከሬን መርማሪ ባለሙያዎች እጥረት እንዳጋጠመ አበከሮ አስታውቋል።

የኩባ ባለሙያዎች ጉዳይ

የሚኒሊክ አስከሬን ምርመራ ክፍል ተተኪ ሊያገኝ ባለመቻል ከኩባ ሁለት ዶክተሮች እንደተቀጠሩ ይፋ ሆነ። ኩባዎቹ አማርኛ ስለማይችሉ የሚፈለገው ሪፖርት እየተጻፈላቸው እንደሚፈርሙ ቢነገርም ሌላም ጉድለት እንዳለ ይደመጣል። ይኸውም ባለሙያዎቹ ብቁ ስለመሆናቸውና ሙያቸውን አክብረው ሥለመስራታቸው ቀድሞውንም ቢሆን ሃሜት ነበር። የብቃትን ጉዳይ አስመልክቶ ባካባቢያቸው ባሉ ሰዎች ትችት የሚሰነዘርባቸው ባለሙያዎች “እንለቃለን” በማለትና በተደጋጋሚ ጥቅማ ጥቅም በመጠየቅ መግባባት ባለመቻሉ የስራ መስተጓጎል ይከሰት ነበር። አስከሬን አስመርምሮ ለመውሰድ መጉላላትና ቀናትን መጠበቅ የተለመደ ነበር። በወቀቱ ሲሰጥ ከነበሩት አስተያየቶች መካከል “ህወሃት ግብግብ ውስጥ ከሚገባና ከሚሳቀቅ ለምን የራሱ የሆኑ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ የተጠመቁ ልማታዊ ሃኪሞችን አሰለጥኖ አያሰማራም” የሚለው ይገኝበታል።

በባለሙያ እጦት ሲዘጋና ሲከፈት የኖረው ሚኒሊ ክ ሆስፒታል አስመልክቶ ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም “በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተቋርጦ የነበረው የአስክሬን ምርመራ ተጀመረ” በሚል ርዕስ አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረው የምርመራ አገልግሎቱን ይሰጡ የነበሩት የውጭ ባለሙያ የኮንትራት ጊዜያቸው ማብቃቱን ተከትሎ እንደነበር አመልክቷል።

ፋና አያይዞም ዶክተር ካሳሁን የሚባሉትን የሚኒሊክ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ጠቅሶ “ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ባለሙያዎችን ማፍራት በማስፈለጉ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ለመጀመር ታስቧል” ሲል ህወሃት የራሱን ሰዎች ለማዘጋጀት መወሰኑንን ይፋ አድርጓል። ይህንኑ ተከትሎ ፖሊስና እርምጃው በቁጥር 47 እትሙ መጋቢት 15 ቀን 2008 ዓ.ም ይፋ የሚከተለውን ዜና ይፋ አደረገ።

የአስክሬን ምርመራ ውስብስብነት፤ በአደጋና በሰው እጅ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ፖሊስ አገልግሎቱን መውሰድ እንደሚገባው ተገለጸ። የዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ክበበው ወርቅነህ ጉዳዩን አስመልክቶ በጽ/ቤታቸው በሰጡት አስተያየት እንዳመለከቱት የአስክሬን ምርመራ ውስብስብ እየሆነ መምጣቱን አመልክተው የሚፈጸሙ ወንጀሎችም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረቀቁ በመምጣታቸው ለስራው ቅርብ የሆነው ፖሊስ አገልግሎቱን ቢሰጥ መልካም ነው ብለዋል።

የሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የአስክሬን ምርመራ ክፍል ከ40 አመት በላይ አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ የጠቆሙት ሃላፊው አገልግሎቱን የሚፈልጉ አካላት መብዛት፣ ወደ ሙያው የሚገቡ ባለሙያዎች አለመኖር ዘመናዊ የአስክሬን መመርመሪያ መሳሪያ አለመኖር፣ የተቋሙ ተግዳሮቶች እንደሆኑ ጠቁመዋል ሲል ፖሊስና ርምጃው ዜናውን አንደርድሮ ለባለጉዳዩ ያቀብላል። ባለጉዳዩ የፖሊስ ሆስፒታል በበኩሉ፤

“ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥያቄዎች መኖራቸውን የጠቆሙት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሸን ሪፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ረ/ኮሚሽነር ዶ/ር ግርማ በቀጣይ ጥያቄውን ለመቀበል የሚያስችል ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ አገልግሎቱን ለመስጠት ተቋሙ ዝግጁ እንደሆነና በአስክሬን ምርመራ የሰለጠነ ባለሙያም በሆስፒታሉ እንደሚገኝ ገልፀው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የአስከሬን ምርመራ በተለይ ወንጀልን የሚመለከት ምርመራ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሪፈራል ሆስፒታል ሊሰጥ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል” በማለት “ጉዳዩ እዚህ ላይ ተቋጨ” ሲል ፖሊስና ርምጃው ዜናውን “ይቋጫል”።

የአስከሬን ቁማር የማይሰለቸውን ህወሃትን ስናነሳ በተዛማጅ እንደ ዓለምዘውድ ያሉ ንጹሃን የተገደሉበትን መንገድና አገዳደሉን እያወደስን አይሆንም። በተለያዩ ስፍራዎች በማንም ትዕዛዝ ሰጪነት ቢሆንም የተከናወኑት የጅምላና የነጠላ ግድያዎች የሚዘነጉ አይደሉም። የተሠወሩ፣ እንደ ወጡ የቀሩ፣ አሟሟታቸው በውል ያልታወቀ፣ የተገደሉት በስለት፣ በመርዝ፣ በጥይት፣ በአካላዊ ስቃይ፣ … መሆኑ ሳይታወቅ ወደ መቃብር እንዲወርዱ የተደረጉ ሁሉ ቤት ይቁጠራቸው፡፡ በዚህ ድርጊት ትልቁን ድርሻ የሚወስደው ህወሃት ቢሆንም አብረውት የሚጠየቁ ጥቂት አይደሉም፡፡ ከሁሉም ወግን በደም የተጨማለቁ ዛሬም የሃዘን ስሜት አይሰማቸውም። ይልቁኑም ለሌላ ደም መፋሰስ ከበሮ ደላቂዎች ሆነዋል።

የሰው ልጅን የሚያክል ክቡር ፍጡር ለፖለቲካና ለስልጣን ስካር ማብረጃ የመጠቀም አባዜ ጎልቶ ይታያል። ህዝብ ሲስማማ ዓይናቸው ደም የሚለብስ ክፍሎች እንደገና ህዝብ መካከል ጸብን በመዝራት ተጠምደዋል። ነጻነት ያለ ህይወት መስዋዕትነት የማይገኝ ቢሆንም በአብዛኛው የሚታየው መስዋዕትነት ወደ ድል የሚያመራ አይመስልም። በመሆኑም ህወሃት በደም የሚመዘነውን ያህል ሌሎችም ከዚያው የማያመልጡበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ማመን ግድ ነው። ያደም የማይዘወረው የአገራችን ፖለቲካ ማን ይድረስለት? ሲሉ አብዛኞች የሚጠይቁት ለዚህ ነው። ሁሉም ቤት እሳት አለና። የህወሃት ግን እንደ ነበልባል እሳተ ጎመራ ይንተከተካል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Social Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule