• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“… የጦር ኃይል … እና የብእር ኃይል …” ሃዲስ አለማየሁ

October 19, 2016 10:13 am by Editor 3 Comments

” … ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አሁን እስካለንበት ድረስ ታሪኩን መለስ ብለን ብንመለከት በሰው ዘር ላይ ግዛታቸውን ለመዘርጋት፣ ሰውን ባካልም ሆነ በመንፈስ ለመግዛት፣ ሁለት ተቃራኒ ኃይሎች ሲታገሉ እናያለን፡፡ ከነዚህ አንዱ የሀይለኞች፣ ያጥቂዎች፣ የጦር ኃይል፣ ሁለተኛው የደራሲያን የብእር ኃይል ናቸው፡፡

“የጦር ኃይል በየጊዜው፣ በየቦታው የሚነሱ ኃይለኞች ሰራዊት አደራጅተው፣ የጦር መሳሪያ አከማችተው፣ ሰውን እየጨቆኑ ለግል ድሎታቸውና ፍላጎታቸው አገልጋይ የሚያደርጉበት እውር ሀይል ነው፡፡ የብእር  ኃይል በየጊዜው በየቦታው የሚነሱ ታላላቅ ደራሲያን ከስው ተለይተው፣ ከብእርና ከወረቀታቸው ጋር በየቤታቸው ተዘግተው፣ ምስጢረ ፍጥረትን እየመረመሩ፣ አዳዲስ ነገር እየፈጠሩ፣ ሰውን ከድንቁርና ሰንሰለት ተፈትቶ፣ ከእንሰሳ ባህርያት ጠርቶ፣ የመንፈስና የአካል ነጻነት አግኝቶ፣ ስርአት ያለው ህብረተሰብ መስርቶ፣ ፈጣሪ ከፍጥረት ሁሉ አልቆ ሲፈጥረው ለመደበለት ከፍተኛ ማእረግ ብቁ እንዲሆን የሚያደርገው ብሩህ ኃይል ነው፡፡

“እነዚህ ሁለት ተቃራኒ ኃይሎች በሚያደርጉት ትግል ምንም እንኩዋ ለጊዜው ጨቁዋኙ የጦር ኃይል ድል አድራጊ ቢመስል በመጨረሻ የእውነተኛው ድል አድራጊ የብእር ኃይል መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ የጦር ኃይል አስገዳጅ፣ የብእር ኃይል አስረጂ እንደመሆናቸው መጠን በማስገደድ የተመሰረተ እድሜው ማጠሩ፣ በማስረዳትና በማስወደድ የተመሰረተ ለሁልጊዜ መኖሩ የማያጠራጥር ነው፡፡ ለዚህም ኃይለኞች በጦር ኃይል የመሰረቱት ግዛት አንድ ባንድ እየፈረሰ፣ ያወጁት ትእዛዝ እየተደረመሰ፣ ዛሬ ዓለም የተቀበለው  ደራሲያን በየጊዜው ያወጁት የሃይማኖት፣ ያስተዳደርና የፍርድ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ኑሮ ስራት መሆኑን ታሪክ ይመሰክራል”፡፡ (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Literature, Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Ayu says

    October 20, 2016 04:17 am at 4:17 am

    Dear Editor of Golgul,
    Can you please translate this article – I link to my face book and a lots of social media -FB – users asked me.

    Kind regads

    Reply
  2. ጌታቸው፡ወልደሥላሴ says

    October 20, 2016 06:23 pm at 6:23 pm

    እንደ፡ፈረንጆቹ፡አነጋገር፡(That was in the good old days)
    አሁን፡ግን፡በብዛት፡ወጣቱም፡እናት፡አባቱም፡(Brain washed)ሆኖ፡
    እመቤታችንን፡አማላጃችንን፡ቅድስትን፡ክዶ፡በመንፈስ፡እየሞተ፡ለሥጋው፡
    እያደረ፡ነው። ያዲያቆነውም፡ሰይጣን፡ሳያቄስ፡አይቀርም፡እንደሚባለው፡
    ይሄው፡ሴይጣኑ፡ከነገሰ፡ብዙ፡ዘመናት፡አልፎአል።
    እንደድሮው፡ባሕላችን፡የባሰ፡አታምጣ፡ነው። ከዚህ፡የባሰ፡
    ምን፡እንዳለ፡እኔ፡አላውቅም።(GOD have mercy)

    Reply
  3. Tesfa says

    October 21, 2016 04:34 pm at 4:34 pm

    እውቁ ጸሃፊ አቤ ጎበኛ “ፓለቲከና ፓለቲከኞች” በተባለው ድራማዊ መጽሃፉ ላይ እንዲህ ይለናል። “ድንጋይን ማን ያናግረዋል ቢሉ ውሃ” ሆኖ አናጋሪዎች እንድናገር ስለገፉኝ የዚህን መጽሃፍ መግቢያ እንዳስፋፋው ምክንያት ሆኑኝ ይለናል። ከሽያጭና ከቅርጫ በተረፈችው በዛሬይቱ ኢትዮጵያ መኖር በዘርና በጎሳ በመሆኑ የጥቅልና የአንድነት ሃሳብ ማንሳት ነፍጠኛ ሲከፋም በጸረ ሽብሩ ህግ መሰረት ዘብጥያ ያስወርዳል። እኔንም እንዲጽፍ የሚገፉኝ አጥፊዎቹ ወያኔና ሻቢያ በህዝባችን ላይ የሚፈጽሙት ግፍ ነው። ከእነርሱ የደም ኮሮጆ እኔ ዳቦ አልሻም። ግን ዓለም እየተቀየረ ሲሄድ ዛሬም የሚያስቡበትና የሚተነፍሱበት ሳንባቸው ጫካን ተግን ያረገ መሆኑ እጅግ ያሳዝናል። ሻብያ ወንድሙን አባሮ የባህር በርን ለዓረብ!
    የቀዳማዊ ሐይለሥላሴ መንግሥት በወታደር ጭፍራ ከተተካ ጊዜ ጀምሮ ምድሪቱ የማያቋርጥ የመከራ ዶፍ ውስጥ እንዳለች የቆመ ይረዳዋል። ደርግ በሻብያ/ወያኔና በምዕራባዊያን ሴራ ከተፍረከረከ በህዋላ ሻብያ በኤርትራ ወያኔ በአዲስ አበባ አለቆች ሆነው እንሆ 25 አመታት ዘለሉ። በእነዚህ አመታት ውስጥ ይህ ነው የማይባለ ሰቆቃና ግፍ በሁለቱም መዲናዎች ተፈጽሞ አል በመፈጸምም ላይ ነው። እያደር ነገር ይሻላል በማለት ተስፋ ያረገው ህዝባችን እየቆየ ነገር እየከፋና ሃገሪቱ ጥቂቶች የትግራይ ተወላጆች መፈንጪያ መሆኑዋን ሲገነዘቡ በቃ በማለታቸው ዛሬ ላለንበት አሳር ተዳርገናል። የወያኔ ኢትዮጵያ ለወያኔ ብቻ። ሌላው ሁለተኛ ዜጋ ነው። ስትፈልግ ከተረፈው ፍርፋሪ እንካ ካልሆነ ደግሞ እሥራት፤ግርፋት፤ ሰቆቃና ሞት ድርሻህ እንዲሆን እናረጋለን እያሉ ያስፈራሩታል። የወያኔው ቆንጮ አቶ መለስ ዜናዊ ሞት ከጠራቸው ወዲህ 120 በላይ መኮንኖች የማእረግ እድገት ተለግሶአቸዋል። የሚገርመው ግን 99.9% ወያኔዎች መሆናቸው ነው።
    ሃዲስ ዓለማየሁ የኖሩበት ዘመን የጸጋ፤ የሰላም፤ ሰዎች ወደ ውጭ ለትምህርት ሲላኩ ትምህርታቸውን ጨርሰው መቼ ለሃገራቸውና ለህዝባችው ተመልሰው አገልግሎት ለመስጠት የሚናፍቁበት ወቅት ነበር። ዘርና ጎሳ ሥፍራ የሌውም። የወያኔ ብህል ሁሉም በየክልልህ በማለትና የይስሙላ የቋንቋና ውል የሌለው ክልል በማበጀት እኛ በዛ ዙሪያ ስንናከስ እነርሱ የሃገሪቱን ሃብት የሚያጋብሱበት የሳቅና የጮቤ እረገጣ ጊዜአቸው ነው። በቋንቋ እንኳን በመነጋገር እንዳንግባባ ውል አልባ የሆነ ብሄራዊነት የለለው በየጎሳው የተተለመ ባህር የማያሻገር ቋንቋን የግላቹሁ ነው ተገልገሉበት አማርኛ የጨቋኝ ቋንቋ ነው ፊደሉንም አትጠቀሙበት በማለት ገደል ከተውናል። በኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ብቻ አይደለም የሚሰቃየው። የድርና ለማዳ እንስሳትና የምድሪቱ የተፈጥሮ ደኖች ጭምር ናቸው። ወያኔና ሻብያ በምርጫ፤ በድርድር ሥልጣን ህዝብ ለመረጠው ያስረክባሉ ብሎ ማመን ራስን ማታለል ይሆናል። የተካኑት በእሳት ነው። ስልጣናቸውንም የሚሽረው እሳት ነው። የአለም ታሪካዊው እይታም ይህን ይደግፋል። ጋዳፊ፤ ሳዳም፤ ሙባረክ ሌሎችንም በህዝብ የተቀጣጠለ እሳት ነው የለበለባቸው። የወያኔና የሻቢያ እድል ፈንታም ከዚህ ቢከፋ እንጂ አይሻልም። ይብቃኝ፡፡ በዚች ግጥም ልዝጋ።

    ነበረ ይለኛል አገኘው ይመስል
    ቤት እየቆጠረ እሳት እየጫረ
    ነገርን በነገር እየተረጎመ
    ለህዝብ ቁሜአለሁ
    ለሃገር እያለ
    ትላንትን አጥላልቶ
    ዛሬን አሞካሸ
    ለራሱ አመቻችቶ
    ሌላን አባረረ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule