እንደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አህዛዊ መረጃ በመዲናዋ ውስጥ 1671 የሚሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ መረጃው ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ኮሌጅ መሰናዶ ድረስ ያሉትን የግል ትምህርት ቤቶች የሚያጠቃልል ሲሆን ፤ ትምህርት ቢሮው በ2006 የትምህርት ዘመን መጨረሻ ወራት ላይ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ፣ በግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) የሚሆኑ ተማሪዎች ይማራሉ፡፡ ትምህርት ቢሮው የ2007 የትምህርት ዘመን አጠቃላይ አህዛዊ መረጃ አጠናቅሮ በድረ ገፁ ይፋ ባያደርግም ቁጥሩ ካለፈው የትምህርት ዘመን ሊልቅ እንደሚችል ይገመታል፡፡ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2015 ዓ.ም ከሚጠናቀቀው የሚሊንየሙ የልማት ግቦች አንዱ የሆነውን ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ዕድሜቸው ለትምህርት ለደረሱ ህፃናት የማዳረስ ዕቅድ ያላት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የሚሊንየሙን የልማት ግቦች … [Read more...] about የሸገር ወላጆች ምሬት Vs የግል ት/ቤቶች ቅሬታ
Social
ክብር ከደቡብ አፍሪካ ለደራርቱ ቱሉ
በኢትዮጵያም ሆነ በጥቁር አፍሪካ ኦሊምፒክ ታሪክ ሁለት ወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው ደራርቱ ቱሉ ባለፈው ሳምንት ከደቡብ አፍሪካው ዌስተርን ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተቀበለች፡፡ ከኦሊምፒክ በተጨማሪ በዓለም ሻምፒዮንም ሆነ በተለያዩ አህጉርና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ቁንጮ በመሆን ታላቅነቷን ማስመስከሯ ይታወሳል፡፡ ደራርቱ ለመጀመርያ ጊዜ በባርሲሎና ኦሊምፒክ (1984 ዓ.ም.) በ10,000 ሜትር ተወዳድራ የወርቅ ሜዳልያውን ያገኘችው የቅርብ ተፎካካሪዋንና የዓለም አቀፍ ውድድሮች ልምድ የነበራትን ደቡብ አፍሪካዊቷን ኤሌና ሜየርን በረዥም ርቀት ጥላት በማሸነፍ ነበር፡፡ ፎቶግራፉ ደራርቱ የክብር ዶክትሬቷን ከተቀበለች በኋላ ከዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ሐኔኮም (በግራ) እና ከዩኒቨርሲቲው ሬክተር ፕሮፌሰር ብሪያን አ ኮኔል ጋር ሆና ያሳያል፡፡ ሁለተኛው ፎቶ በባርሴሎና ኦሊምፒክ … [Read more...] about ክብር ከደቡብ አፍሪካ ለደራርቱ ቱሉ
ምሽት ዳንኪራ ከዲያስፖራ
ያለሁት ካናዳ፤ ቶሮንቶ ነው፡፡ ከጥቂት ሳምንታት ቆይታ በኋላ ትላንት ማታ አንዱ የኢትዮጵያ ምግብና ዳንኪራ ቤት ለማምሸት ከዘመድ እና ሰሞኑን ከተዋውቅኳቸው ጥቂት ሰዎች ጋር ሄድኩ፡፡ ቤቱ በአንድ ሰሞን በአንድ ዜማ እጅግ ታዋቂ ሆኖ በነበረ ወጣት ድምፃዊ የሚተዳደር ነው፡፡ ስገባ ወጣቱን ድምፃዊ አየሁት፡፡ እንግዶቹን ዞር ዞር እያለ ሰላም ይላል፡፡ ከማውቀው ወፍሯል፡፡ ዘመናዊም ባህላዊም ዘፈን በዲጄ ሲለቀቀቅ ጠባቧ ቤት ንዝረቷ ይጨምራል፡፡ ከምሽቱ አምስት ሰአት ገደማ ቤቷ ሞላች፡፡ ከሀበሻ ውጪ ሌላ ዘር ያለው ሰው ግን አላየሁም፡፡ ስድስት ሆነን ከተቀመጥንበት ጠረጴዛ ጀርባ ባለጌ ወንበርና ጠረጴዛ ላይ አንዲት በህንድ ዘዬ የተሰራ “እዩኝ እዩኝ” ሆደ- ግልብ ብልጭልጭ ልብስ የለበሰች ረጅምና ቀጭን፣ ቆንጅዬ ልጅ ተቀምጣ ቢራ ትጠጣለች፡፡ አላግባብ ተከምሮ ሳር ከጫነ መኪና … [Read more...] about ምሽት ዳንኪራ ከዲያስፖራ
የዛፍ ጥላ ስር ትምህርት ቤቶች
ጠመዝማዛ ባላዎች ላይ የቆመው ክፍል በደደሆ ዛፍ ቅጠል የተሠራ ጣሪያ አለው፡፡ ክፍሉ ውስጥ ከ20 የማይበልጡ ትንንሽ ድንጋዮች ላይ ኩርምት ኩርምት ብለው የተቀመጡ ተማሪዎች ይታያሉ፡፡ ደብተሮቻቸውን በየጉልበታቸው ላይ አድርገው ከፊት ለፊታቸው ያለውን መምህር ያዳምጣሉ፡፡ ከመሬት ብዙም የማይርቀው የክፍሉ ጣሪያ መምህሩን ጐንበስ ብሎ እንዲያስተምር ግድ ብሎታል፡፡ መምህሩ ለማለቅ በተቃረበ ነጭ ጠመኔ ያረጀ ሰሌዳ ላይ ቁጥሮች እየጻፈ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሒሳብ ያስተምራል፡፡ የክፍሉ ጣሪያ በሳሳበት አቅጣጫ የተቀመጡ ተማሪዎች ጸሐይ ይመታቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ድንጋዩ ጐርበጥ ሲያደርጋቸው ወደ አንድ ወገን ገደድ እያሉ ለመመቻቸት ይጣጣራሉ፡፡ እነዚህ በዛፍ ጥላ ስርና በዳስ የሚማሩ ተማሪዎች የመኪና ድምጽ በሰሙ ቁጥር አንገታቸውን አጠማዘው ይመለከታሉ፡፡ ግድግዳ በሌለው ክፍላቸው አቅራቢያ … [Read more...] about የዛፍ ጥላ ስር ትምህርት ቤቶች
ለነዋሪዎች አማራጭ የለም!
በአዲስ አበባ ያለው የመጸዳጃ ቤት ችግር ከልክ ያለፈና መሆኑን የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ዘገበ። ሐሙስ በወጣው የጋዜጣው ድረገጽ ላይ እንዳስነበበው ከ3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በሚኖርባት አዲስ አበባ ውስጥ ለሕዝብ መገልገያነት የዋሉት መጸዳጃ ቤቶች 63 ብቻ መሆናቸውን ዘግቧል። አማራጭ ያጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ ከተማዋ ወደ መጸዳጃ ቤትነት እየተለወጠች መሆኗን በምሬት ገልጸዋል። ጋርዲያን “Wash Ethiopia Movement” የተባለ አገር በቀል ድርጅት ጠቅሶ እንደዘገበው በከተማዋ ከ10 ቤተሰቦች 9ኙ የጉድጓድ መጸዳጃ ቤት እንደሚጠቀሙና መቀመጫ ባለው መጸዳጃ ቤት የሚጠቀሙት ከ25 ቤተሰቦች አንዱ ብቻ መሆኑን ተናግሯል። በዘገባው መሠረት የከተማዋ ባለሥልጣናት የዛሬ ዓመት ይገነባሉ በሚል የ100ሚሊዮን ብር ዕቅድ የተያዘላቸው መጸዳጃ ቤቶች እንዳሉ መናገራቸውን … [Read more...] about ለነዋሪዎች አማራጭ የለም!
የሴት ልጅ ግርዛት ጎጂ ወይስ ጠቃሚ?
ጥናታዊ ጽሑፍ! በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ አንዳች ጥናት ቢጤ ማድረጌን አምና በግብረ ሰዶማዊያን ጉዳይ ላይ በጻፍኩት ጽሑፍ ሳይቸግረኝ ጠቆም በማድረጌ ብዙኃን መገናኛዎችን የሚከታተሉ ሰዎች በኢሜይልና በስልክ በአካልም ጭምር በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያዘጋጀሁትን ጥናታዊ ጽሑፍ ለንባብ እንዳበቃላቸው እጅግ ወተወቱኝ፤ አይ ረጅም ነው ለመጽሐፍ እንጅ ለዚህ ዓይነት መስተንግዶ አይሆንም ረዘመ ትላላቹህ ብልም ሊቀበሉኝ አልቻሉም ጨቀጨቁኝ እንግዲህ ካልተውኝ ምን አደርጋለሁ ብየ አቀራረቡን ግን ለብዙኃን መገናኛ በሚሆን ቀየርኩትና ተዛማጅ የሆነ ጠቃሚና አስፈላጊ ጉጋይ አክየበት ጽፌላቹሀለሁ ያውላቹህ፡- ይሄንን ጥናት ያደረኩት ከስድስትና ከሰባት ዓመታት በፊት ነበር፡፡ በዚህ ጥናት ከ800 ያላነሱ ሰዎች በቀጥታ በሽዎች የሚቆጠሩ በተዘዋዋሪ የጥናቴ ግብአት በማድረግ ተጠቅሜያለሁ፡፡ ጥናቴን … [Read more...] about የሴት ልጅ ግርዛት ጎጂ ወይስ ጠቃሚ?
አዲስ አበባን የተጫናት ፍልሰት
ዕቃ የጫኑ ታክሲዎችና ሌሎች መኪናዎች በሚያራግፉባቸው ማቆሚያዎች ሰብሰብ ብለው ሮጠው ዕቃ ማውረድ፣ ከሚጫንበት ስፍራም መጫን የለት ተዕለት ሥራቸው ነው፡፡ አሠሪዎች በተለይም በግንባታው ዘርፍ ያሉት የቀን ሠራተኞችን ከሚወስዱበት መገናኛ፣ ሃያሁለት፣ መሪ ሳሪስ አየር ጤናና ሌሎችም ሥፍራዎች በጠዋቱ ተሰባስበው መታየታቸው አመሻሽ ላይም በየሃይገሩና ባሱ ተጨናንቀው ወደየማደሪያቸው መጓዛቸውም እንዲሁ፡፡ ታዳጊ አዋቂ ሳይል በየገበያ ስፍራው የሸክም አገልግሎት ለመስጠት የሚሯሯጡትም ጥቂት አይደሉም፡፡ በመልካም አስተዳደር እጦትም ይሁን ከራስ በመነጨ ፍላጐት ትምህርት አቋርጠውና በእርሻውም ሆነ በሌላው የሚያግዙዋቸውን ቤተሰቦቻቸውን ትተው ወደ አዲስ አበባ የሚነጉዱት የየክልሉ ነዋሪዎች ተበራክተዋል፡፡ በዋና ዋና መንገዶች፣ በአደባባዮችና በትራፊክ መብራቶች፣ በእምነት ሥፍራዎች በማሳለጫ … [Read more...] about አዲስ አበባን የተጫናት ፍልሰት
ምርቃት ወዲህ ሥራ ወዲያ
አሁን ላይ በሐገራችን የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ደረጃዎች የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ጨምሯል፡፡ በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርትን በነባርና አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች በኩል ትምህርታቸውን ተከታትለው እየተመረቁ የሚወጡ ተማሪዎች (ምሩቃን) ቁጥር በዚያው ልክ እያደገ ይገኛል፡፡ በዚህ አመት ብቻ እንኳ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተመራቂዎች ቁጥር ከ60 ሺህ በላይ እንደሆነ ይፋ ሆኗል፡፡ ይህ ቁጥር በግል ኮሌጆችና በተለያዩ መለስተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን የተከታተሉትን አይጨምርም፡፡ የትምህርት ተቋማትም ሆነ በእነዚህ ተቋማት ገብተው ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ቁጥር መጨመሩ ይበል የሚያሰኝ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ዳሩ ግን እነዚህ ተማሪዎች በምን ሁኔታ ትምህርታቸውን ተከታትለው እንደሚወጡ ሲታይና ከምረቃ በኋላም ያለውን የሥራ ጊዜ … [Read more...] about ምርቃት ወዲህ ሥራ ወዲያ
የረመዳን ወግ
ወቅቱ ረመዳን ነው፡፡ እነሆ ለረመዳን የሚሆን (አንድ ወግ) ልጋብዛችሁ፡፡ ኸሊፋው ዑመር ኢብን አል-ኸጣብ ዘወትር እንደሚያደርገው የነዋሪዎቹን ሁኔታ ለመታዘብ በምሽት በመዲና ጎዳዎች ላይ ይንጎራደድ ነበር፡፡ ወደ አንድ ሰፈር ሲደርስ በስካር መንፈስ የሚለፈልፍ ሰው ድምጽ ሰማ፡፡ ወደ ቤቱ ተጠግቶ በመስኮት ቢያይ ሰውዬው የወይን ጠጅ እየጠጣ ዓለሙን ሲቀጭ አገኘው፡፡ ዑመር አላስቻለውም፡፡ በመስኮት ዘሎ ገባና ሰውዬውን “አንተ ምን መስራትህ ነው?… ከሰው ብትደበቅ ከአላህ መሰወር የምትችል መሰለህ?… ወይን ጠጅ ለምንድነው የምትጠጣው?” በማለት ተቆጣው፡፡ ሰውዬው እንግዳውን ትክ ብሎ ቢያይ ዑመር ነው፡፡ በጣም ደነገጠ፡፡ ስካሩ በአንድ ጊዜ ለቀቀው፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ተረጋጋና ዑመርን እንዲህ አለው፡፡ “ኸሊፋው ልክ ነዎት! ወይን ጠጅ መጠጣቴ ሐጢአት ነው፡፡ ይሁንና እኔ አንድ … [Read more...] about የረመዳን ወግ
ሕገወጥ ደም ሻጮች የከሰሩበት
ከአንድ ዓመት በፊት አንድ ህመምተኛ ለሚደረግለት ህክምና ደም የሚያስፈልገው ከሆነ፣ ቤተሰብ አሊያም ወዳጅ ዘመድ ምትክ ደም ሰጥቶለትና የሚያስፈልገው የደም አይነት ከደም ባንክ ወጥቶለት ይታከም ነበር፡፡ ይህ አሠራር ግን በርካቶች የሚያስፈልጋቸውን ደም በቀላሉ እንዳያገኙ የሚያደርግ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ቤተሰብ አሊያም የታካሚው የቅርብ ወዳጆችም ‹‹ደም ለግሱና ደማችሁ ተተክቶ ለታካሚው ሌላ ደም ይሰጠው›› የሚለውን ሐሳብ ሲሰሙ ሃሳቡን ይሸሻሉ፣ ከልገሳው ያፈገፍጋሉ እንዲሁም ይፈራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ደማቸው ተወስዶ እምብዛም ጥቅም ላይ መዋል የማይችል ግለሰቦች በደላሎች አማካይነት በሽያጭ ደም ይለግሳሉ፡፡ ደም ባንክ የእነዚህን ሰዎች ደም በምትክ ወስዶ ከባንኩ ለታካሚዎች ደም ቢሰጥም፣ በሕገወጥ መንገድ ተሸጦ ገቢ የተደረገው ደም ከሞላ ጎደል ይወገድ እንደነበር ባንኩ … [Read more...] about ሕገወጥ ደም ሻጮች የከሰሩበት