• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ችጋር – የሶስት ዓመት የዞረ ድምርና የህወሃት የፖሊሲ ክሽፈት

April 14, 2016 08:45 am by Editor 5 Comments

የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የባለስልጣናት ሌብነትና ድርጅታዊ ዝርፊያ፣ የማንነት ጥያቄ፣ ድህነት፣ ስራ አጥነት፣ አድሏዊ አመለካከት፣ የሰብአዊ መብት አለመከበር፣ የማሰብ፣ የመቃወም፣ የመናገርና የመጻፍ ተፈጥሮአዊ መብቶች መጣስ፣ የዲሞክራሲ መብቶች አለመከበር የፈጠረው ስሜት ተጠራቅሞ እየገነፈለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ኢትዮጵያ የተነከረችበት ከፍተኛ እዳና የተከሰተው ችጋር አገሪቱን ወደ ከፋ ቀውስ እንዳያመራት ስጋት አይሏል።

ባለፉት ስድስት ወራቶች ሰላማዊ ጥያቄ ያነሱ ዜጎች በጥይት ተደብድበው ሞተዋል። በዚሁ ሳቢያ ኦሮሚያ በእምባ ነፍራለች። ህጻናትና እናቶች በህወሃት ልዩ ታማኝ ኃይሎች ተገድለዋል። የታሰሩ ዜጎች ቁጥር በሺህ የሚቆጠር ነው። የት እንደ ደረሱ የማይታወቁ ወገኖች ስለመበራከታቸው ቤተሰቦች ስምና አድራሻ ሳይደብቁ እየተናገሩ ነው። አማራ ክልል “በግድ ትግሬ መሆን በቃን” በሚል ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖች ታስረዋል፤ ተገርፈዋል፤ የሞቱም አሉ። በተወለዱበት ቀዬ መኖር ተስኗቸው የተሰደዱና ዱር ቤቴ ያሉ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ይህንኑ ተከተሎ ያኮረፉና የተበሳጩትን ቤት ይቁጠራቸው። በደቡብ ክልልም በተመሳሳይ ችግሩ የተወሳሰበ መሆኑንን ከስፍራው የሚወጡ ሪፖርቶች ያስረዳሉ።

famine ethይህ ሁሉ የተቆለለ ችግር ሳያንስ ሲሸፋፈን ቆይቶ የተገለጠው ረሃብ በተለይም በምስራቁ የአገሪቱ ክፍል ለሶሰት ተከታታይ ዓመታት የከረመ ድምር እና የክሽፈት ውጤት መሆኑ ይፋ እየሆነ ነው። “መቶ በመቶ የሕዝብ ድጋፍ” አግኝቻለሁ በሚል አገሪቱን በነጻ አውጪ ስም የሚገዛው ህወሃት/ኢህአዴግ፣ ተገድዶ ያመነው ችጋር ያስከተለው ጉዳት ትክክለኛ መረጃ እስካሁን ይፋ ባይሆንም አደጋው ዘግናኝ ስለመሆኑ መከራከር በማይችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል። የህወሃት ሹመኞች “ራሳችን እንወጣዋለን” ሲሉ እንዳልነበር ዛሬ የርዳታ ያለህ ጩኸት እያሰሙ ነው።

ጠኔው እየገፋ ሄዶ የአገሪቱን የህወሃት ውላጅ ሚዲያዎች በየቀኑ መንታ ምላስ ባደረገበት ባሁኑ ወቅት፣ “ነጻ” የሚባሉት የወረቀት ሚዲያዎች ጉዳቱ የደረሰበት ስፍራ ሄደው በወጉ ሽፋን አለመስጠታቸው ታሪካዊ ትዝብት ፈጥሯል።

የአውሮፓ ኮሚሽን በድረገጹ እንዳሰፈረው ከ10 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተርቧል ሲል፤ ህጻናትን አድን የተሰኘው ድርጅት ደግሞ ከ6ሚሊዮን በላይ ህጻናት በረሃብ አደጋ ላይ መሆናቸውን ይፋ ያደረጉት አሳሳቢ የተባለው ችግር አለበት ቦታ ድረስ ሄደው ካዩ በኋላ ነው።

እንደ ኮሚሽኑ አተያየት የወቅቱ የኢትዮጵያ ችጋር አምስት አንኳር እውነታዎች የሚከተሉት ናቸው፤

  • በሃምሳ ዓመታት ውስጥ ከተከሰቱት አስከፊው ድርቅ ነው፤
  • በድርቁ በጣም በተጎዱት አካባቢዎች ከ50 እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ሰብል መና ሆኗል፤ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ከብቶች አልቀዋል፤
  • 100 ሚሊዮን ከሚጠጋው አጠቃላይ የአገሪቱ ህዝብ ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ይሻሉ፤
  • ከ100 ሺህ በላይ ህዝብ ተፈናቅሏል፤ ከምግብ በተጨማሪ መጠለያ፣ ውሃ፣ ንጽህና አጠባበቅና የህክምና ርዳታ እጅግ አንገብጋቢ የሚባሉት ናቸው፤
  • የአውሮፓ ኮሚሽን ካለፈው ዓመት ጀምሮ 170 ሚሊዮን ዩሮ ለአስቸኳይ ርዳታ እጁን ዘርግቷል።

ኮሚሽኑ 125.5 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚሰጥ ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ የገባውን ስጋት ደጋግሞ ጠቁሟል።

በመከረኛው ኢል ኒኞ የሚላከከው ችጋር በሴፈቲ ኔት የታቀፉትን ወገኖች ጨምሮ 18 ሚሊዮን የሚጠጉ ወገኖችን ተፈታትኗል። በተለይም ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት ያሉበት አሳሳቢ ሁኔታ እረፍት የሚነሳ ሆኗል። “… አሳሳቢ የሆነው ጉዳይ ነው፤ አሁን ማድረግ ያለብንን ፈጥነን ካላደረግን የፈራነው እውን መሆኑ አይቀሬ ነው” ሲሉ ከጉብኝታቸው በኋላ ስጋታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የተናገሩት የህጻናት አድን ዋና ኃላፊ ናቸው።

በቅርቡ የምጣኔ ሃብት (ኢኮኖሚክስ) ፕሮፌሰር የሆኑት አለማየሁ ገዳ ይፋ ባደረጉት ጥናታቸው አገሪቱ ከሰላሳ ቢሊዮን ዶላር በላይ እዳ ይጮህባታል። የብድሩ መብዛት ብቻ ሳይሆን አከፋፈሉ እንዲሁም የገቢና የወጪ ንግዱ አለመጣጣም መጪውን ጊዜ አሳሳቢ እንደሚያደርገው አሰገንዘበዋል።

በሌላ በኩል ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ባወጣው ሪፖርት በ2009 ብቻ ከኢትዮጵያ ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተዘርፎ ካገር እንዲወጣ ተደርጓል። ሪፖርቱ እንዳለው በድምሩ ባለፉት ሰባት አመታት ከአገሪቱ ተዘርፎ ወደ ውጭ የወጣው ገንዘብ ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ስለመሆኑ ምስክርነቱን መስጠቱ የሚያስታውሱ ወገኖች የተዘረፈውን ዶላር “ይህ ብር ምን ያህል ሰፋፊ የእርሻ ልማት ይገነባበት ነበር” ሲሉ ይጠይቃሉ። በገፍ የተወሰደውን ብድር አስመልክቶ “በሌብነትና በከሸፈ ፖሊሲ ላይ የተበተነ ያገሪቱ የመጪው ትውልድ ቁልል እዳ” ይሉታል። አቶ መለስ አፈር ሳይውጣቸው “መሃይምም ቢሆን የድርጅታችንን ዓላማ እስከተቀበለ ድረስ…” በማለት ራሳቸውን ለማግዘፍ ዙሪያቸውን የዕውቀት ድርቅ ባጠቃቸው በመክበብ ሹመት እየሰጡ ሚኒስትር ማድረጋቸው አሁን እየተከሰተ ላለው ክሽፈት በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው።

ለበርካታ ጊዜያት የሚላስ የሚቀመስ በማጣት የራሳቸውን ሥጋ “እየበሉ” ሲኖሩ የቆዩ ወገኖች መሞት የሚጀምሩት ከወራት በፊት እንደሆነ በኢትዮጵያ ችጋር ላይ ከበቂ በላይ ጥናትና ምርምር ያደረጉት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ይናገራሉ። ተፈጥሮ ፊቷን በምታዞርበት ጊዜ በችጋር አፋፍ ላይ የሚገኙት ገበሬዎች ወደችጋሩ ገደል መግባት ይጀምራሉ የሚሉት ፕ/ር መስፍን “ችጋር ሕዝብን በጅምላ የሚጨፈጭፍበት ጊዜ ከስድስት እስከ ስምንት ወራት ይፈጃል” ይላሉ። በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ በተመለከተ የሚያስከትለውን አስከፊ ሁኔታ ሲያስረዱም “ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ተከሰተ የተባለው ድርቅ ሰዎችን በችጋር መረፍረፍ የሚጀምረው በሚያዝያና በመጋቢት ነው፤ ገበሬዎቹ ከአሁን ጀምሮ እስከ መጋቢት ምንም ሰፊና ትልቅ ዘላቂ እርዳታ ካላገኙ በመጋቢትና በሚያዝያ ሰው እንደቅጠል የሚረግፍበት ጊዜ ይሆናል” በማለት “ስለ ችጋር” በሚል ርዕስ በኅዳር 2008ዓም ባስነበቡት ጦማር ትንታኔ ሰጥተው ነበር።famine

በነጻ አውጪ ስም ላለፉት 25ዓመታት ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ህወሃት “አገር የመምራት ብቃት ፈጽሞውኑ” የሌላቸው ግለሰቦች ስብስብ መሆኑን አስቀድመው እንደተናገሩት እንደ ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ የህወሃት/ኢህአዴግ ሰዎች ይህንኑ ትንቢታዊ ንግግር ከ25ዓመታት በኋላ በማያሻማ መልኩ ዕውን አድርገውታል፡፡ ሕዝብ ወድዶን መቶ በመቶ ተመርጠናል ከማለት ጀምሮ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በድርብ አኃዝ እያደገ ዓለምን አስደምሟል በማለት ህወሃት የዕውቀት ጠር በሆኑት ሹሞቹ ሕዝብን ሊያሳምን የጣረው ሁሉ አልሠራ ብሎት ምዕራባውያንን “ብትረዱን ይሻላችኋል” በማለት ትዕዛዛዊ ማስፈራሪያ እየሰጠ ይገኛል፡፡ ምርጫን መቶ በመቶ አሸነፍኩ፤ ሕዝብ ይወደኛል፤ … ለማስባል ተሸፋፍኖ የከረመው የዓመታት ችጋር አሁን ያለበት ሁኔታ ከሚገመተው በላይ እንደሚሆን እየተነገረ ነው፡፡ በጠኔ ተጠብሰው ከሞት ጋር ፊት ለፊት የተጋፈጡት ወገኖች የመጨረሻውን እስትንፋስ ላለመተንፈስ እየተገዳደሩ ቢሆንም ቀን የከዳቸው ይመስላል፡፡ ሕጻናት ያለ አሳዳጊ፣ ወላጆች ያለ ጧሪ የሚቀሩበት ጊዜ ጀምሯል፡፡ የበርካታ ትውልድ የወደፊት ተስፋ ጽልመት ጋርዶታ፣ የሕይወት መስመር ተቋርጦ አለመኖር በመኖር ላይ እየነገሠ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ አልፎ ለመኖር የሚበቃው ወገን የተስቦ ወረሽኝ ገና ይጠብቀዋል – ድርብ ድርብርብ ክሽፈት! (ፎቶዎቹ ከኢንተርኔት የተገኙ ናቸው)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Social Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. geresu says

    April 14, 2016 10:24 am at 10:24 am

    ተው ተነስ ወገኔ ተው ተነስ ወገኔ ገና በቁመናህ ሳይበላህ ወያኔ! ተው ተነስ ወገኔ ተው ተነስ ወገኔ በ66ቱ በአባትህ ወኔ! ተው ተነስ አማራ ተው ተነስ ኦረሞ የገረሱ ዱኬ የሀይለማሪያም ማሞ እንስራው ተሰብሮ ሳይባል ገመሞ እገረፈህ ነው ወያኔ ለጉሞ!!

    Reply
  2. geresu says

    April 14, 2016 10:56 am at 10:56 am

    ተይ ተነሽ አገሬ ተይ ተነሽ አገሬ ጨርሼ ሳልሸጥሽ መንዝሬ መንዝሬ!! ተው ተነስ ወገኔ ተው ተነስ ወገኔ ሂትለር ነው ሞሶሎኒ አይምርም ወያኔ!! ይቅር በለኝ መንጌ እጅህ ከሙስና እጂግ የፀዳ ለሀገር ክብር የማታወላዳ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ነፍስ የምታስከፍል 50 የሱዳን ነፍስ!! አዬ መንጌ ጉድ አየህ በቁምህ የወያኔ ባንዳ አገር ሲሸጥልህ!! ተው ስትለን አልሰማ ብለንህ እግር ከወርች ታስረን ተገረፍንልህ!! መለዮአችንም መለመኛ ሆነልህ የአንተ አንድ ስህተትህ በአደባባይ መግደልህ ከወያኔ የሚለይህ!! ሌላ ምንም እንከን የለህ !!! ቻው !ቻው! ወያኔ ይብቃው!

    Reply
  3. Yikir says

    April 14, 2016 02:16 pm at 2:16 pm

    PM H/MARIAM “ZELALEMAWI KIBIRINA MOGES LE meles zenawi”yihun alu.mehayimochu shumegnoch degimo meles almotem yemilu alu. GIN EWINET LIHON YICHILAL .SATAN /SETAN ,DABILOS YIMOTAL WEY ? .KETEKEBERU YEGODANA TEDADARIWOCH “ZELALEMAWI WURIDETINA KILET lemeles zerawi” enilalen.

    Reply
  4. ሸመልስይማም says

    April 25, 2016 03:18 pm at 3:18 pm

    ህወሀትኢሀዴግወይምባንዳየባንዳደቃላወችየኢትዮጵያጠላቶችናቸው

    Reply
  5. tesfai habte says

    June 23, 2016 02:49 pm at 2:49 pm

    ወያኔ ሰው መብላት ብቻ ነው የቀረው! የኢትዮጵያ ህዝብ ለምን እስከ ኣሁን ያለምክንያት ዝም ብሎ ይጠብቃል። ይሄ የሳጥናኤል ውጤት፡ ግብረ-ሰዶም የተቀበለ ወስላታ ዘረኛ ወያኔ ብሃይሊ እንጂ ብሰለማዊ መንገዲ መንደራደር ኣያዋጣም!—-ተነስ!—-ተነስ!—ለህልውናህ፡ ለመብትህ፡ —–ብረት ኣንግበህ ተነስ!—–ጭራሲን መጥፋት ዛሬ ተነስ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule