• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ተሰባሪ መንግሥታትና የመሰበራቸው ምክንያቶች

July 24, 2014 09:23 am by Editor Leave a Comment

በዓለማችን የመክሸፍ አደጋ የሚታይባቸውን አገራት ዝርዝር በየዓመቱ በማውጣት የሚታወቀው የውጭ ፖሊሲ መጽሔት ሰሞኑን አደጋው የሚታይባቸውን አገራት በዝርዝር አውጥቷል። በዚህ የ178 አገራትን ዝርዝር በያዘው ዘገባ መሠረት ቁጥር አንድ የአደጋው ተጋላጭ ደቡብ ሱዳን ስትሆን ኢትዮጵያ ደግሞ 19ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ጠቁሟል።

ባለፈው የአውሮጳውያን ዓመት 2013 መረጃ ላይ ተመርኮዙ የወጣው ዘገባ 12 መስፈርቶችን በግብዓትነት የተጠቀመ መሆኑን አስታውቋል። እነዚህም፤

  1. የስነሕዝብ ተጽዕኖ፡ ከህዝብ ብዛት ጋር በተያያዘ የምግብ ዕጥረት፣ የሟቾች ቁጥርና ፍጥነት፤
  2. ስደተኞችና በአገር ውስጥ የሚፈናቀሉ፡ በስደት ወደ አገር የሚገቡና በአገር ውስጥ ከየቦታው የሚፈናቀሉ፤
  3. የቡድን (የሕዝብ) ሃዘን፡ በአገር ውስጥ ባሉ ቡድኖች መካከል ያለው ውጥረትና ጠብ፤
  4. አገር ጥለው የሚሄዱና የምሁር ስደተኞች፡ ከአገር ውስጥ ወደ ውጭ የሚሰደዱ ዜጎችና ምሁራን፤
  5. ሚዛናዊ ያልሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት፡ በአገር ውስጥ በሚገኙ ብሔሮች ወይም የሃይማኖት ቡድኖች ወይም ክልሎች መካከል የሚታይ ያልተመጣጠነ (ሚዛናዊ ያልሆነ) የኢኮኖሚ ዕድገት፤
  6. ድህነትና የኢኮኖሚ ውድቀት፡ የድህነት መጠንና የኢኮኖሚው አፈጻጸም፤
  7. የመንግሥት ህጋዊነት፡ ሙስና እና ሌሎች እንደ ምርጫ ሂደት፣ መልካም አስተዳደር፣ የመንግሥት ሥርዓት አፈጻጸም፣ ወዘተ የመሳሰሉ የዴሞክራሲ ብቃት መለኪያዎች፤
  8. የሕዝብ አገልግሎቶች፡ ትምህርት፣ የጤና አጠባበቅ፣ የንጽህና አጠባበቅ፣ እና ሌሎች ሕዝባዊ አገልግሎቶች፤
  9. ሰብዓዊ መብቶችና የሕግ የበላይነት፡ የሰብዓዊ መብቶች ከለላና እነዚህ መብቶች እንዲጠበቁ የሚደረግ ትጋት፤
  10. የደኅንነቱ አሠራር፡ የአገር ውስጥ ግጭቶችና ከመንግሥት ቁጥጥር ውጪ ያሉ የታጣቂዎች ቁጥር መጨመር፤
  11. የልሒቃን ወገናዊነት፡ በየአካባቢውና በብሔራዊ ደረጃ የሚገኙ ልሒቃንና መሪዎች መካከል የሚካሄድ ፉክክርና ግጭት፤
  12. የውጭ ጣልቃገብነት፡ ከውጪ የሚገባ ዕርዳታ መጠንና በውጭ ኃይላት የሚደረግ የማዕቀብና የወታደራዊ ጣልቃገብነት ተጽዕኖ ናቸው።

ዘገባው የ2013ን መረጃ በመጠቀሙ አሁን በየአገራቱ ከሚታየው ሁኔታ ጋር በመጠኑም ልዩነት የሚታይ ቢሆንም በመጪው ዓመት ግን ይኸው ከግምት ውስጥ ገብቶ ማሻሻያ እንደሚደረግ ገለጾዋል። ሆኖም በየዓመቱ የሚደረገው የደረጃ ጉዳይ እምብዛም ለውጥ የማያሳይ እንደሆነ አክሎ አስታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ በየአመቁ የሚጠቀምበትን “failed states” (የከሸፉ መንግሥታት) ከሚለው መጠሪያ ይልቅ “fragile states” (ተሰባሪ መንግሥታት ወይም ክሽፈት ያነጣጠረባቸው መንግሥታት) በሚል መቀየሩን በዘገባው ላይ አመልክቷል።

በተለይ ከአንድ እስክ ሃያ አምስት ያሉትን አገራት ስንመለከት አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት መሆናቸው አኅጉሩ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የሚጠቁም ነው። ከዚህ ዝርዝር ውስጥ 1ኛ ደቡብ ሱዳን፣ 2ኛ ሶማሊያ፣ 3ኛ ማዕከላዊ የአፍሪካ ሪፑብሊክ፣ 4ኛ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ 5ኛ ሱዳን፣ 6ኛ ቻድ፣ 11ኛ ዚምባብዌ፣ 12ኛ ጊኒ፣ 14ኛ ኮትዲቯር፣ 16ኛ ጊኒ ቢሳው፣ 17ኛ ናይጄሪያ፣ 18ኛ ኬኒያ፣ በእኩል የ19ኛ ደረጃ ኢትዮጵያና ኒጀር፣ 21ኛ ብሩንዲ፣ 22ኛ ዑጋንዳ፣ 23ኛ ኤርትራ፣ 24ኛ ላይቤሪያ ናቸው።

failed states 1በዚህ መረጃ መሠረት ከ25ቱ አገራት መካከል የአፍሪካውያን ቁጥር ከ70በመቶ በላይ ሲሆን የምስራቅ አፍሪካ አገራት ብቻ ደግሞ ከ30በመቶ በላይ የሚሆነውን የሚያካትቱ መሆናቸው በእርግጥ የአፍሪካ ቀንድ በከፍተኛ አደጋ ውስጥ የሚገኝ ቀጣና መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው። በተለይ በቀጣናው ባሉ አገራት ላይ የበላይነትን ተጎናጽፌአለሁ የሚለው ኢህአዴግ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት መሆኑን በዚሁ ዓመት የመጋቢት ወር ጎልጉል አንድ አሜሪካዊ ዲፕሎማትን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወቃል።

ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ባተመው በዚህ ዜና መሠረት “ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ብቸኛ ተዋናይና ፊት አውራሪ አድርጎ ራሱን የሾመው ኢህአዴግ ለቀጠናው ስጋት” መሆኑን ጠቁሟል። ዘገባው ሲቀጥልም “ህወሃት ያቋቋማቸው ጥቃቅን መንግሥታት ከህዝብ ይልቅ ለህወሃት የወደፊት እቅድ ታማኝ በመሆን መጓዛቸው ከቀን ወደቅን የፈጠረው ስሜት ኢህአዴግን እየበላው እንደሆነ የጠቆሙ የዜናው ምንጮች፣ ኢህአዴግ የምስራቅ አፍሪቃ የሰላም አባት ሊሆን ቀርቶ የራሱንም ችግር መፍታት ወደማይችልበት የቁርሾ ማሳ ውስጥ እንደሚገኝ” ጠቁሞ ነበር።

ሟቹ አቶ መለስ በየትኛውም አገር ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ በመሄድ እጅግ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ኤርትራ እንድትገነጠል በይፋ ከለመኑና በትጋት ከሰሩ በኋላ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ቁጥር እየጨመረ ሄዷል። በመቀጠልም ህወሃት/ኢህአዴግ የምስራቅ አፍሪካ አገራትን እንደፈለገው በመዘወር በሶማሊያ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሲያማስል ቆይቶ አገሪቱን በመከፋፈል የራሱን አሻንጉሊት አስተዳደር አስቀምጧል። በሱዳንም እንዲሁ በማድረግ ደቡብ ሱዳንን የግል ቤቱ በማድረግ ከፖሊስ እስከ መከላከያና የደኅንነት ሥልጣኑን በእጅ አዙር ከተቆጣጠረ በኋላ በአሁኑ ጊዜ ደቡብ ሱዳን በዓለም ላይ መረጋጋት ከሌለባቸው (ከከሸፉ) መንግሥታት መካከል የመጀመሪያው ሥፍራ ላይ ትገኛለች።

ከአንድ እስክ ሃያ አምስት ያሉት አገራት አብዛኛዎቹ ከአፍሪካ መሆናቸው አህጉሪቱ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የሚጠቁም ነው። ለአገራቱ ተሰባሪነት ወይም መክሸፍ ምክንያት ተብለው የተዘረዘሩትን ምክንያቶች አሁን ካለው የአገራችን ሁኔታ ጋር የሚጣጣሙ ሆነው እናገኛቸዋለን። ኢህአዴግ ኢትዮጵያን መግዛት ከጀመረበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው ስልት እየዋለ አድሮ ያመጣቸው ጣጣዎች የመክሸፍ መንስዔ ተደርገው ከቀረቡት መካካል ይገኛሉ። በየጊዜው ተጨባጭ ምክንያት በማቅረብ የሚወጡ ሪፖርቶችን በመግለጫ ከመቃወምና፣ በጭፍን ድጋፍ ከማጣጣል ውጪ ነገሮችን ረጋ ብሎ የመመርመር ችግር በመኖሩ ችግሩ ከቀን ወደ ቀን እየገዘፈ ነው።  አብዛኞች እንደሚሉት በጥናት የሚቀርቡ ሪፖርቶች በ24 ሰዓት የሚከናወኑ ሳይሆኑ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ “አዋጆች” ናቸው። በዚሁ አዋጅ መሰረት ችግር ውስጥ ያሉ አገሮች የኢህአዴግን አገዛዝ ጨምሮ ለራስም ሆነ ለአገር ሲባል የችግሮችን መልክ ለመቀየር መስራት አለባቸው። የመክሽፍ ወይም የመሰበር አደጋ ያስከትላሉ ተብለው የቀረቡትን ጭብጥ መረጃዎች ከቀነሱና ካስወገዱ በኋላ “እኔ አልከሽፍም፣ አልሰበርም” ማለት ተገቢ ሊሆን ይችላል። ይህንን ሳይፈጽሙ ግን በችግሮች የተካበ ማማ ላይ ቆሞ “ማስተባበልና ማላዘን” በከንቱ ፕሮፓጋንዳነት ለጥቂት ጊዜ ሕዝብን ለማታለል “ከመጥቀም” በላይ ላለመሰበር ዋስትና በጭራሽ አይሆንም!!

ዘገባው እዚህ ላይ ይገኛል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule