ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለጓደኞቻቸው በሙሉ፤
ሰላምታዬን አቀርብላችኋለሁ፡፡
ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር አገር ነች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የእግዚአብሔር ሕዝብ ነው፤ ክርስቲያኑም፣ እስላሙም፣ አረመኔውም የእግዚአብሔር ነው፤ እንደየእምነቱ በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚኖር ነው፡፡
የእግዚአብሔር ጊዜ የተለየ ነው፤ ትእግስቱን ስለሚያረዝመው የተረሳ ያስመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግፍን አይረሳም፤ እግዚአብሔር ሁሌም ለአቅመ-ቢሶች ጉልበት የሚሆንበት መንገድ አለው፤ ግፍ በእግዚአብሔር በር ላይ እንደተጣለ ግም ቆሻሻ ነው፤ እግዚአብሔር ሲፈቅድ ይጠርገዋል፤ ወይም ያስጠርገዋል፡፡
እግዚአብሔር መንገዱ ብዙ ነው፤ ግፍን የሚያስከፍለው በተለያየ መንገድ ነው፤ በግፈኛው ቤተሰብ ላይ ሁሉ የግፈኛነት ጠባሳን ያሳርፍበታል፤ ሰዎች ለሥልጣናቸው ባላቸው ቅናት የእግዚአብሔርን ሥልጣን ይጋፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥልጣን መጋፋት የግፍ ግፍ ነው፤ ታሞ በእግዚአብሔር እጅ ባለ ሰው ላይ ጉልበተኛ መሆን በእግዚአብሔር ሥልጣን መግባት ነው፤ የግፍ ግፍ ይሆናል፤ ለእናንተም፣ ለቤተሰቦቻችሁም፣ ለአገሪቱም፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብም የሚበጅ አይደለም፡፡
ሀብታሙ አያሌው በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እግዚአብሔርን አትፈታተኑ፡፡
ደጉን ያስመልከታችሁ!
የግዛታችሁ ነዋሪ
መስፍን ወልደ ማርያም
gud says
This man became religious over night
Repent for having 60 elderly h Silase officials
Murdered !