• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጥምቀትና ጎንደር Vs የትዝብት ወግ

January 19, 2016 08:59 pm by Editor Leave a Comment

“ጥምቀትን በጎንደር መታደም መባረክ ነው” ይህ የብዙሃኑ የእምነቱ ተከታዮች የምስክርነት ቃል ነው፡፡ ጥምቀትና ጎንደር የገጠሙ እለት እንኳንስ ለጎብኝዎች ለነዋሪዎችም ታይተው አይጠገቡም፡፡ የጎንደር ጥምቀት በዓል ከመላ ኢትዮጵያ አከባበር የሚለይባቸው በሁለት ተያያዥ ምክንያቶች ይመስለኛል፡፡ ከቀድመው የመሳፍንት እና የአፄዉ ስርዓት ጋር በተያያዘ ከተማዋ  ለረዥም ዓመታት መናገሻ ከተማ ሆና መቆየቷ፣ በጊዜው የነበረው ኃይማኖታዊ መንግስት በመሆኑ አብዛኛው ነዋሪ ጥብቅ የኦርቶዶክስ ክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ከሌላው አካባቢ (ከተማ) በተለየ መልኩ “የአርባ አራቱ ታቦታት” መገኛ መሆኗ የመጀመሪያው ምክንያት ሲሆን፤ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በአስራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ከአፄ  ፋሲል ቤተመንግሥት ምስረታ በኋላ ከቤተ መንግሥቱ በስተ ምዕራብ በኩል አራት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በ18 ሺህ ካሬ ሜትር ምድረ ግቢ ውስጥ በግሩም የስነ ሕንፃ ውበት ለጥምቀተ ባህር መዋኛና ታቦታት ማደሪ ተብሎ በአፄ ፋሲል የተሰራው የፋሲለደስ መዋኛ መገኘቱና ለበዓሉ ድምቀት የጎላ ተፅዕኖ ማሳደሩ የጎንደርን የጥምቀት በዓል የተለየ ያደረገው ይመስላል፡፡ የፋሲለደስ መዋኛ ስፋት 50 ሜትር በ30 ሜትር ሲሆን፣ ጥልቀቱ ደግሞ 2.5 ሜትር ይሆናል፡፡ እንደዚህ አይነት ስፋት ያለው መዋኛ ገንዳ በዛ ዘመን መገንባቱ በራሱ ድንቅ ነው፡፡

በዓሉን በከተማዋ ለማሳለፍ ብዛት ያላቸው የአገር ውስጥና የባህር ማዶ ጎብኝዎች በበዓለ ጥምቀቱ ላይ መታደማቸው ከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች በተጨማሪነት የጎንደርን ጥምቀት ከሌላው አካባቢ አከባበር የተለየ ያደርገዋል፡፡ በእናቱም የጥምቀት በዓል የአደባባይ በዓል በመሆኑ ጎንደሬዎች ለአደባባይ በዓል የተመቹ ናቸው፡፡  ለዚህም ይመስላል የሰሞን ልጅ በረከት ፋታ ከሚነሳው የፓርቲው የሴራ ፓለቲካ ለአፍታም ቢሆን ተነጥሎ በዓለ ጥምቀትን በየዓመቱ በጎንደር የሚያልፈው፤ ምናልባት የማርክሰን ንድፈ ሀሳቦች ማነብነብ ከመጀመሩ በፊት በልጅነቱ ያየው የነበረው የጥምቀት በዓል ትዕይንት ውል እያለበት ይሆናል በዓሉን በጎንደር የሚያሳልፈው፡፡ በዓሉ ላይ ማንነቱን ፈልጎ ባያገኘው እንኳ የልጅነት ትወስታውን የሚያጣው አይመስልም፡፡ የበረከት ማንነት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጉድጓድ ላይመለስ የተቀበረ  ቢሆንም የልጅነቱ ትውስታው ግን ጨለጨል በሆነ እይታ ጥምቀትን አስታኮ የሚያየው ይመስላል፡፡ 11

በነገራችን ላይ በጎንደር አካባቢ ሁሌም ቢሆን ሦስት ነገሮች በጉጉት ይጠበቃሉ፡፡ በዓል ጥምቀት፣ የሰሊጥ ምርትና ዶላር፡፡ ሦስቱም ነገሮች ለጎንደርና አካባቢው ነዋሪዎች የነፍስም የስጋም እርካታን የሚያጎናፅፍ በረከቶች ናቸው፡፡ በጣም የታደለው የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ሦስቱም ነገሮች ይኖሩታል፡፡ በከፊል የታደለው ደግሞ ከሦስቱ ሁለቱን አያጣም፡፡ በጣምም ሆነ በከፊል ከታደከሉት መሀል የሌለበት የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ “ጥምቀት” የተባለ የአደባባይ በዓል ይኖረዋል፡፡

ግማሽ ደርዘን የሚሆን የቤተሰቦቿ አባላት ሰሜን አሜሪካ አለያም እስራኤል ውስጥ የሚኖሩ ተጧሪ ልጃገረድም ሆነች በአስር ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በየምርት ዘመኑ የሰሊጥ ምርት የሚያመርተው የናጠጠ ሃብታም አባወራ …. ቤሳ ቤስቲን ከሌለው መናጢ ደሃ ጋር እኩል እየተጋፉ የሚያከብሩት የአደባባይ በዓል ጥምቀት ብቻ ይመስለኛል፡፡የመስቀል በዓል የአደባባይ በዓል ቢሆንም ጎንደርና አካባቢው ላይ የጥምቀትን ያህል የሚደምቅ አይደለም፡፡ ኃይማኖት ያዛመዳቸው አማኞች ከከተራ በዓል እስከ ጥምቀት ባህር መልስ (የሚካኤል ንግስ) ድረስ ታቦቱን አጅበው ይጓዛሉ፡፡ በያሬዳዊ ዜማም አምላካቸውን ያመሰግናሉ፡፡ በዓለ ጥምቀትን አስታከው የሚመጡ ለዘብተኛን ኢ-አማኞች ደግሞ ልጃገረዶችን አጅበው ይተማሉ፡፡ ስለ ልጃገረዶቹ ጡትና ዳሌ ስጋዊ ዜማ ያሰማሉ፡፡ ከሁለቱም የሌሉበት በሺዎች የሚቆጠሩ የባህር ማዶ ጎብኝዎች ደግሞ ትዕይንቱን እየተከታተሉ በካሜራና በብርሃን አሰናስለው ይቀርፃሉ፡፡ በግል ማስታወሻቸውም ይከትባሉ፡፡

12 - Copyኃይማኖት ያዛመዳቸው አማኞች በቡድንና በተናጠል ጧፍ፣ ዘቢብና መሰል ስጦታዎችን በታቦቱ ፊት ሲጥሉ፣ የነርሱ ተቃራኒዎች ደግሞ በልጃገረዶች ደረት ላይ ሎሚ መወርወር ይቀናቸዋል፡፡ በአጭሩ ጥምቀት ለኃይማኖቱ ተከታዮች ከኃጢያታቸው የሚነፁበትና አምላካቸውን የሚያመሰግኑበት ኃይማኖታዊ በዓል፣ ለለዘብተኞችና ኢ-አማኞች ደግሞ መልካም የስሪያ አጋጣሚ፣ ለባህር ማዶ ጎብኝዎች ታይቶ የማይጠገብ ልዩ ባህለ- ኃይማኖታዊ የትዕይንት መድረክ ነው፡፡

የጎንደርን ጥምቀት በልዩ ድምቀት ከሚያከብሩ የፊት መስመር ተሰላፊዎች ውስጥ የሚመደቡት ያለም አጫዋቾች (አዝማሪዎች) ሲሆኑ፣ የበዓሉ ቀን እግዚሃርን የሚያመሰግኑ ዘለሰኛ ግጥሞችን ቢጫወቱም የማታ ማታ የማህበራዊ ሞገድ ሰለባ ናቸውና እግዚሃርን ባመሰገኑበት መሰንቆ ስለ ሽንጥና ዳሌ ሲገጥሙ ሌሊቱን ያጋምሳሉ፡፡  ቀን ለነፍስ፣ ማታ ለስጋ ይሉሃል ይሄ ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ፣ ጥምቀትን አስመልክቶም ሆነ አላስመልክቶ ወደ ጎንደር የምትዘልቁ የአገር ውስጥም ሆነ የባህር ማዶ ጎብኝዎች የጎንደር አዝማሪ ቤቶችን እንድትጎበኙ ይመክራል፡፡ አልያማ ስለ ከተማዋ ሙሉ ምስል ልታገኙ አትችሉም፡፡ ነዋሪዋም ቢሆን ጭፍራ ነፍሱ ነው፡፡  ዘመነኛ የሸገር ልጃገረዶች ሁለት አይነት ሆቢ አላቸው፡፡ ሳልሳ ዳንስ መደነስና ሾፒንግ፡፡ የጎንደር ልጃገረዶችም “ድስቃና ዋንጫ ልቅለቃ” የተባሉ የባህላዊ ውዝዋዜ ሆቢዎች አሏቸው፡፡ ይብዛም ይነስም የሸገር ልጃገረዶች ሆቢያቸውን የሚፈጽሙት የወንድ ልጅ ኪስ በማጠብ ነው፡፡ የጎንደር ልጃገረዶች ስለ ሆቢያቸዉ ላብን እንጂ ኪስ አያራግፉም፡፡ ‹ላቤን ጠብ አድርጌ እጨፍራለሁ› የሚል ጎረምሳ ወደ ጎንደር ጥምቀት ይዝለቅ፡፡ ከአንዷ ልጃገረድ ጋር ዋንጫ ልቅለቃውን ይሞክረ፣ እርሱ ባይሆንለት እንኳ ድሰቃው አለለት፡፡ ድሰቃን ሞክሮ ያልተሳካለት የጥምቀት ጎረምሳ ከቶ ያለ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ለድሰቃ ላብህን እንጅ ኪስህን ማራገፍ አይጠበቅብህም፡፡13 - Copy

ከልጅነት እስከ አስተውሎት ዘመኔ ድረስ ስታዘበው የኖርኩት ባህለ – ኃይማኖታዊ ክዋኔዎችን በወግ መሰል ትርክት ቁንፅል በሆነ መልኩ ለመግለጽ ሞከርኩ እንጂ፣ የጎንደር ጥምቀት በዓል አከባበር ትልቅ ጥራዝ ሊወጣው የሚችል የአደባባይ በዓል ነው፡፡ ለሁሉም ለመንፈሳዊያኑ መልካም በዓል፣ ለስጋዊያን ደግሞ መልካም የዋንጫ ልቅለቃና የድሰቃ  ጊዜ ይሁንላችሁ፡፡ በነገራችን ላይ “ዋንጫ ልቅለቃና ደሰቃ” የባህል ጭፈራ ዓይነት መጠሪያዎች  ብቻ ሳይሆኑ የዘመኑን መንፈስ የሚገልጡ የውስጠ ወይራ አንጓዎች ናቸው፡፡ አሁን ማን ይሙት ከጥቂት ለነፍሳቸው ካደሩ ገዳማዊያን መነኮሳት ውጭ ጥምቀትን ዋንጫ ሳይዝና ሳይለቀልቅ የሚያሳልፍ “ኃይማኖተኛ” ቀርቶ የኃይማኖት መሪ አለ?! ድሰቃን በዋዛ የሚያሳልፉትስ ስንቶች ናቸው?! የሎሚ ውርወራው ተከታይ ድሰቃ መሆኑ ከማን የተሰወረ ነው?! … ግን የእየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ላይ በ”መተጫጨት” ስም የስሪያ መድረክ ማዘጋጀት ተገቢነት አለው? ኃይማኖታዊ ይዘቱንስ አያጎፈድዉም? … ለዚህና መሰል ጥያቄዎች የኃይማኖት ሊሂቃኑ ምላሽ እስኪሰጡን ድረስ የቻልን በአርምሞ ያልቻልን ግን በዋንጫ ልቅለቃና ድሰቃ በዓሉን እናሳልፍ፡፡ (ፎቶዎቹን የላኩልን ጸሃፊው ናቸው)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዛሬ ‘ኃያል ነን’ የሚሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ በሚዲያ /በመረጃ/፣ በዲፕሎማሲ፣ በሳይበር እና በተልእኮ የተቀነባበረ ‘ግራጫ ጦርነት’ እያካሄዱባት ነው” ጠ/ሚ ዐቢይ July 7, 2022 10:03 am
  • የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት አብን ጠየቀ July 6, 2022 01:38 pm
  • “አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ July 6, 2022 01:53 am
  • “በኢትዮጵያዊያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሀገሪቱን ማተራመስ አለብን” አይማን አብድልአዚዝ ግብጻዊው ፖለቲከኛ July 5, 2022 12:57 pm
  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule