• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጳጳሶችና ስደት

June 28, 2016 08:33 pm by Editor 1 Comment

እንዲያውም ርእሱን ካህናትና ስደት ብለው ይሻላል፤ ካህናት የሁሉንም ሃይማኖቶች መሪዎችን ይመለከታል፤ ዓላማዬም ሁሉም የሃይማኖት መሪዎችን የሚነካ ነው፤ ነገር ግን የእኔ እውቀት በክርስትናው ላይ ጎላ ያለ በመሆኑ የክርስቲያኖቹ መሪዎች ላይ ያተኮርኩ ቢመስልም ሁሉንም ይመለከታል፤ በተለይ መነኩሴዎች ላይ የማነጣጥርበትም የተለየ ምክንያት አለኝ፡፡

በመጀመሪያ አንድ መሠረታዊ ነገር ላብራራ፤ እንደማንኛውም ሰው ስለፍርሃትና ስለጥቃት አውቃለሁ፤ በተለያዩ መንገዶች በመርማሪዎች የተሰቃዩ ሰዎች ሲናገሩ ሰምቻለሁ፤ የጻፉትንም አንብቤአለሁ፤ ከሁሉም በላይ ፍርሃት የግል መሆኑን አውቃለሁ፤ በዚህም ምክንያት ሰውን ለምን ፈራህ ብሎ መውቀስም አስቸጋሪ መሆኑ ይገባኛል፤ ስለዚህም ይህንን የምጽፍበት ምክንያት የተሰደዱትን ለመውቀስና እነሱን ዝቅ አድርጌ ራሴን ከፍ ለማድረግ አይደለም፤ ከቃሌ በቀር ይህንን የማረጋግጥበት መንገድ የለም፤ እንዲህ ያለው ዓላማ ምንም ትርፍ የለውም፡፡

የኔ ዓላማ ሁለት ነው፤ አንደኛ የሚቀጥለው ትውልድ ሽሽትንና ስደትን እንደባህል እየወሰደው እንዳይቀጥልና የኢትዮጵያ መራቆት እንዳይባባስ እሪ! ለማለት ነው፤ እሪ! በማለት በተለይ የወጣቶቹን ትኩረት ለመሳብና ከሽሽትና ከስደት ሌላ አማራጭ እንዲፈልጉ ለማሳሰብ ነው፤ ይህንን ለማድረግ ስሞክር የማኅበረሰባዊ ግዴታዬ እስከዛሬ የተሰደዱትን ሰዎች የዜግነትም ሆነ የማኅበረሰባዊ፣ የሃይማኖትም ሆነ የታሪክ፣ የፖሊቲካም ሆነ የኑሮ ኃላፊነትን፣ ተጠያቂነትንና የወላጆችን ክብር አነሣለሁ፤ በዚህ ጽሑፍ ላይ የማተኩረው ከላይ እንደገለጽሁት በካህናት ላይ ነው፡፡

በክብረ ነገሥት ልጀምር፡–

“ለካህናትሰ ሰመዮሙ ጼወ፤ ወዓዲ ለካህናት ሰመዮሙ መኅቶተ፤ ካዕበ ሰመዮሙ ብርሃኖ ለዓለም፣ ወካዕበ ሰመዮሙ ጸሐየ ዘያበርህ ጽልመተ እንዘ ክርስቶስ ጸሐየ ጽድቅ ውስተ አልባቢሆሙ፤

ወካህንሰ ዘቦቱ ልቡና ይገሥጾ ለንጉሥ በእንተ ምግባራት ዘርዕየ ወዘኢርእየሰ እግዚአብሔር ይፈትን ወአልቦ ዘይወቅሶ፤

ወዓዲ ኢይሕምይዎሙ አሕዛብ ለጳጳሳት ወለካህናት እስመ ደቂቀ እግዚአብሔር ወሰብአ ቤቱ እሙንቱ በእንተ ዘገሠጾሙ በእንተ ኃጢአቶሙ ወጌጋዮሙ፤

ወአንተኒ ኦ ካህን ለእመ ርኢከ ዕውቀ ኃጢአቶ ለብእሲ ኢትኅፈር ገሥጾቶ ኢያፍራህከ ሰይፍ ወኢስደት፡፡”

እስቲ ዳዊት ያልደገሙት ይኮላተፉበት! ፍሬ ነገሩ ክብረ ነገሥት በመጀመሪያ ካህናትን በጣም ይክባቸዋል፤ ጨው አላቸው፤ መብራት አላቸው፤ የዓለም ብርሃን አላቸው እውነተኛው ጸሐይ ክርስቶስ በልባቸው ውስጥ ስላለ ጨለማን የሚያበራ የዓለም ብርሃን ይላቸዋል፡፡

ክብረ ነገሥት ክቦ፣ ክቦ አያቆምም፤ ይቀጥልና የካህናትን ግዴታ ይናገራል፤ ልቡና ያለው ካህን በሚያያቸው ጉዳዮች ንጉሡን ይገሥጻል፤ የማያየውን ጉዳይ ግን እግዚአብሔር ይመረምራል፤

ሕዝብ ጳጳሳትንና ካህናትን ማማት ተገቢ አይደለም፣ ስለምን የእግዚአብሔር ልጆችና ቤተሰቦች ናቸው፤

ካህን ሆይ አንተ ግን የሰውን ኃጢአት ስታይ መገሠጽን አትፍራ፤ ሰይፍም ሆነ ስደት አያስፈራህ፡፡

ዳዊትን የደገመ ሁሉ እንደሚያውቀው ፡- ኢይፈርሆ ለእኩይ እስመ አንተ ምስሌየ፤ ይላል፤ አንተ ከኔ ጋር ነህና አልፈራም ማለት ነው፤

እንግዲህ ይህ የክብረ ነገሥት ትእዛዝ በጣም ግልጽ ነው፤ የክርስቶስም ትእዛዝ በጣም ግልጽ ነው፤ ተራራውንም ማዘዝ ትችላላችሁ ይላል፤ ለደቀ መዛሙርቱ ስለእምነታቸው ጎዶሎነት ደጋግሞ ተናግሯል፤ እንግዲህ ስደት የቅንጣት ታህል እምነት መጉደል ያመጣው ፍርሃት አይደለም? ሽሽት የራስን አካላዊና መንፈሳዊ ኃይል መካድ አይደለም? “እስመ አንተ ምስሌየ”ን መካድ አይደለም? መትረየስ ፊት የቆሙትን ጴጥሮስን መካድ አይሆንም?

ወይስ የኛዎቹ ጳጳሳትና ካህናት ሌላ መመሪያ አላቸው? ወይስ አንድ አጭበርባሪ ሰባኪ ልጆቼ እንዲህ አታድርጉ፤ እንዲህም አታድርጉ እያለ ሲሰብክ አንድ በጣም የሚያውቀው ሰው ትኩር ብሎ ሲመለከተው ዓይን ለዓይን ሲጋጠሙ ማርሽ ለወጠና ልጆቼ እኔ እንደምላችሁ አድርጉ እንጂ እኔ እንደማደርገው አታድርጉ አለ ይባላል፡፡

ወደሐዲስ ኪዳንም ገብቶ ብዙ ነገር ማለት ይቻላል፤ ግን በጣም ያሳፍራል፤ በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያፈርሁት አንድ ባሕታዊ በእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተገደለና በቤተ ክርስቲያን እንዳይቀበር የተደረገው ሙከራ ነው፤ ሁለተኛው በቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የሙጢኝ ያሉትን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች  መስቀል የለበሱ ሰዎች አሳልፈው ሲሰጧቸው ነው፡፡

የተሰደዱና ያልተሰደዱ ካህናት ብሎ መለየቱ ዋጋ የለውም፤ ዋጋ የለውም የሚባለው በምእመናኑ፣ በበጎቹ፣ ዓይን ሲታይ ነው፤ በጎቹን ጥለው የሸሹትም “ስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘሀበነ ዘንተ ፀጋ በመዋዕለ ስደትነ።” እያሉ ለራሳቸው ይኖራሉ፤ ያልሸሹትም በሥጋ ነው እንጂ በመንፈስ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር መሆናቸው ያጠራጥራል፤ በአንድ በኩል ሲታይ ሁለት ሲኖዶሶች የሚባሉት በአካል የሚገኙት በኢትዮጵያና በአሜሪካ መሆናቸው ነው እንጂ በመንፈስ አንድ ናቸው፤ የዝንጀሮ ቆንጆ!

ይህች ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ልጆችን በትምህርት ስታሳድግ የኖረች፣ ደሀዎችን ስትረዳ አሮጊቶችና ሽማግሌዎችን ስትጦር፣ እናትና አባት የሌላቸውን ልጆችን እያስተማረች የምታሳድግ፣ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቅርሶች ስትጠብቅ የኖረች ዛሬ በብዙ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሚደረገውን ስትፈጽም የኖረች ነች፤ መንፈሳውያን ሰዎች በነበሩባት ጊዜ፤ ዘመናዊነት በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ እንዳልሆናት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያኒቱም አልሆናትም፤ የዛሬ ሃምሳና ስድሳ ዓመት ግድም በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት የሠለጠኑትና በኋላም ነገረ መለኮት እንዲማሩ ወደወጭ የተላኩት ሁሉ እያደናቀፋቸው ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመርዳት አልቻሉም፤ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ግን ባልተጠበቀበት መስክ ሙያተኞችን አፍርቷል፤ በሕዝብ “ደኅንነት”ና በጦር ሠራዊት ታላላቅ መኮንኖችን አበርክቷል፡፡

በአገር ውስጥ ያሉት ካህናት-ጳጳሳት “በዶልቼ ቪታ” (መለስ ታምራትን ሲያባርረው ስኳር ያለው) ተንደላቅቀው በመኖር ከአገር ውጭ ካሉት አያንሱም፤ አንዳንዶቹም ቀሚስ ለባሾች እዚያም እዚህም እየረገጡ አማርጠዋል፡፡

ወጣቱ ትውልድ ይቺን ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን ለትንሣኤ ማብቃት ያሻዋል፤ እግዚአብሔር ይርዳን!

ስደትን በሚከተሉት ቀልዶች አሳምረውታል!!!

“በሥጋ እንጅ ከቅድስት አገራችን የተሰደድነው፣ ከቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን አልተሰደድንም።”

“የክርስትና ሃይማኖት እንደ ዓለማዊ መንግሥት የግዛት ወሰን የለውምና።”

(ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

(ምንጭ: መስፍን ወልደ ማርያም ብሎግ)

ሰኔ/2008

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Social Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. tesfai habte says

    June 29, 2016 11:15 am at 11:15 am

    ሰውን በአንድ እርግ በጥሩ ለመሮጥ ኣይቻልም። ከቻለም ውጤቱ ውድቀቱ እየበዛ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ከኢጣልያኑ የአምስት አመታት የግዛት ነጻ ከወጣ እስከ አሁኑ የመጡ መሪዎች፡ ከዶላር ፍቅር የተያዙ፡ ለራሳቸው ጥቅም እንቺ ለህዝቡ ሃሳብ መምጣት የማይፈልጉ፡ የክርስትና እምነትን ወደሃላ በማድረግ፡ ደም የሚጎርፍ ውግያ መዝመት የሚቀላቸው፡ ( vampire) ከእመነታችን የወጡ የድያብሎስ ልእካን፡ ሳጥነኤሎች፡ ከዋይት ሃውስ ከሚገኘው ሳጥናኤል (ድያብሎስ) ትእዛዝ የሚቀበሉ፡ በቀል፡ ጸብ፡ ፈላጊዎች፡ (ብክሪኽ ኢትዮጵያ ማለት ጥቁር ሰው የሚኖርዋት የጥቁር ምድር ማለት ነው።) ኢትዮጵያ የጥቁሮች ማእከል ከመሆን ቀርቶ፡ የጥቁሮች ዝርያ የማጥፋት ማእከል ያደረጉት የጥቅም ሰዎች መናሃርያ ስለሆነች፡ ሁሉም የጥቁር ዘር ከአፍሪካ እተሰደደ ወደ ኤውሮፓ መጓዙን የመረጠ ዘመን እያለን መሆናችን፡ እነዚ የሳጥናኤል ተከታዮች ከልጸዳ፡ ሰላም ማግኘት ማለት የማይታሰብ ነው። vampire ደም ካልኣገኘ መኖር ስለማችለው፡ እነዚህ የቫምፔር ተከታዮች ከልተደመሰሱ መኖር ኣንችልም!—–ከቫምፔሮች ውግያው ይቀጥላል!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule