ከ1997 ምርጫ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ከፈለሱት የክልል ነዋሪዎች መካከል ከ87 በመቶ በላይ የትግራይ ተወላጆች እንደሆኑ አንድ የስታትስቲክስ ባለስልጣን ባለሙያ ጠቆሙ። ቁጥሩ የሚያሳየው ባግባቡ ከሃብትና ንብረት፣ ወይም ከመተዳደሪያ ጋር የተመዘገቡትን ብቻ እንደሚያካትት ባለሙያው አመልክተዋል። ከዘጠና በመቶ በላይ ከሌሎች ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚፈልሱት የእለት ጉርስ ፍለጋ ነው።
በኢንቨስትመንት ስም በሚፈናቀሉ ዜጎች ኮቴ፣ በኮንደሚኒየም ቤቶች ዝውውር፣ መከላከያ፣ ደህንነትና ሁሉንም ዓይነት የፖሊስ ተቋማት ጨምሮ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ቅጥርና በመሳሰሉት ሰፊ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ወደ አዲስ አበባ ተምመዋል፤ እየተመሙም ናቸው። እንደባለሙያው የሌሎች ክልል ተወላጆች በስፋት ወደ አዲስ አበባ ቢፈልሱም፣ የትግራይ ተወላጆችን ልዩ የሚያደርገው “አቅም እየተፈጠረላቸው መሆኑ ላይ ነው”።
“ለምሳሌ” ይላሉ ባለሙያው “ለምሳሌ ከደቡብ ክልል በርካታ ቁጥር ያላቸው ታዳጊዎች አዲስ አበባ ይታያሉ። እነዚህ ታዳጊዎች በጫማ ማጽዳት (ሊስትሮ) እና በጉልበት ሥራ ላይ የተሰማሩ ናቸው። ኑሯቸውም አንድ ቤት በጅምላ በመከራየት ነው። በተመሳሳይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጎጃም ጎረምሶች የሊስትሮ ሳጥን ላይ ህይወታቸውን መስርተዋል”።
ንፅፅሩ ያለው የፍልሰቱ አይነት ላይ እንደሆነ ያመለከቱት ባለሙያ ይህ መሰሉ አስደንጋጭ ልዩነት በገሃድ እንዲጠናና በዳታ ተዘግቦ እንዲቀመጥ ፍላጎት አለመኖሩን አመልክተዋል። የተጠቀሰውን አኻዝ ከሌሎች የምዝገባ መረጃ (ዳታ) ላይ የተወሰደ መሆኑንንም ተናግረዋል።
ሳሪስ ከኤካፍኮ ችፑድ ፋብሪካ ጀርባ ሃዲዱን ተሻግሮ አንድ ክፍል ቤት ለስድስት ተከራይተው የሚኖሩ የደቡብ ክልል ታዳጊዎች መካከል አንዱ ሰብስቤ ይባላል። ሽምብራ እየለቀመ ነበር። ጠዋት ሽምብራ ይገዛና ለቀሞ፣ አንገርግቦ፣ ቆልቶ ወደ ገበያ ያመራል። ዓላማው ትንሽ ገንዘብ አጠራቅሞ ወደ ደቡብ አፍሪካ መሰደድ ነው።
ስድስቱ ያንድ መንደር ልጆች አዋጥተው ኪራይ ይከፍላሉ። ኪራዩ በየጊዜው እየጨመረ በግል ሁለት መቶ ብር ይደርስባቸዋል። የጎልጉል ዘጋቢ በቤታቸው ተገኝቶ እንደተረዳው አራት በአራት በምትሆነው ክፍል ውስጥ የሚኖሩት ታዳጊዎች “ልማታዊ” ተብለው የሚሰየሙበት ጊዜ በነሱ የህይወት ዘመን የሚታሰብ አይመስልም። እነዚህ ወገኖች ኢትዮጵያ ውስጥ በጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም የሚወከሉ ናቸው።
ቦሌ ወሎ ሰፈር ባንድ የጫት መቃሚያ ቤት ውስጥ ተጠገቶ እየተላላከ ይኖር የነበረውና ሯጭ የመሆን ህልም የነበረው ጎይቶም የፈለሰው ከትግራይ ነበር። አንገቱን የሚደፋውና ብዙ የማይናገረው ጎይቶም በብዛት ከኦሮሚያ ቢሮዎች ጫት “ለመብላት” የሚመጡ ይወዱት ነበር። ገንዘብም ይሰጡት ነበር። ስራም ለማስገባት ሞከረው ነበር። ተሳክቶላቸው የኦሮሚያ ሥራና ከተማ ልማት ሠራተኛ አድርገውት ነበር።
ጎይቶምን እጅግ ከሚወዱት መካከል አንዱ ነው። ስለ ጎይቶም ጥላውን እየተጠራጠረ እንዲህ አለ።
“ … ጎይቶምን አንድ ቀን ጌቱ ገለቴ ህንጻ ውስጥ ዌስተርን ዩኒየን የገንዘብ ማስተላለፊያ ቢሮ ውስጥ አገኘሁት። ፍጹም ተለውጧል። ሰውነቱ ሊፈርጥ የቀረበ ፓፓዬ መስሏል። አንገቱና እጁ ላይ ያጠለቀው የወርቅ ሰንሰለት በግድ የሚታይ ነው። ከሱ በፊት ወርቁን በመገረም እንዳየሁለት በሚረዳ መልኩ ፈገግ አለ። አቅፎ ሳመኝ። ራበኝ ሲል ስለማበላው፣ ልብሴን ስለምሰጠው፣ የሱን ኑሮ ለመቀየር ብዙ ጉዳዮችን እንጫወት ስለነበር፣ ሳይነገረኝ ድንገት መሰወሩ እንዳሳፈረው ገባኝ … ”
ጎይቶም ሁመራ ሰሊጥ ላኪ መሆኑን፣ በጫት ቤት ውስጥ ስራ እንደነበረው፣ አምስት ወር ሙሉ ጫት ቤት ምስኪን መስሎ የኖረው ለስራ እንደ ነበርና አሁን ጥሩ ሃብታም መሆኑን … ለቀድሞ ወዳጁ አጫውተው። ጎይቶም የህወሃት ሰው ሲሆን ስራውም ሰላይነት ነበር። ጫት ቤት!!
ወይዘሮ ኪሮስ በ1997 ምርጫ ወቅት በሌሊት የድምጽ መስጫ ኮሮጆ ሲሰርቁ ተይዘዋል። ባለቤታቸው ደላላ ሲሆኑ የቀበሌ ምክር ቤት አባል ናቸው። ስድስት ልጆች ሲኖራቸው ተክለሃይማኖት አካባቢ እጥርጥር ጋቢ በመሸጥ ይታወቃሉ። ዛሬ ሁሉም ልጆቻቸው ሥራ ይዘዋል። ባለቤታቸው ገልባጭ መኪና ገዝተዋል። ምንጩ በማይታውቅ ገንዘብ ቤታቸው ተፈውሷል። ጎረቤቶቻቸው ግን እንዳሉ አሉ።
መሬታቸውን በሳንቲም ካሳ አስረክበው የበይ ተመላካች የሆኑ ብዙ ናቸው። ጁነዲን ሳዶን እየረገመ፣ በቁጭት ከንፈሩን እየነከሰ ቀን እንደሚጠብቅ የሚናገረው ወጣት የለገጣፎ ነዋሪ ነው። ካንትሪ ክለብ የገነባቸውን ቪላዎች እያሳየ “መሬታችን እዚህ ነበር” አለ። “በሚሊዮኖች የሚቸበቸቡ ቪላዎችን እያየን አለን” ተነፈሰና “መሬታችንን ራሳችን በስምምነት ብንሸጥ ምን ችግር አለው?” … ዝም አለ … አቋርጦ ጀመረ። “እናም እኛም ቪላዎቹም፣ ነዋሪዎቹም፣ ጉልበተኞቹም አለን” ሲል ነበር ምሬት የተቀላቀለበት ቅሬታውን የገለጸው።
በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ከሚሰሙት ቅሬታዎች መካከል “ኢንቨስትመንቱ ሳይሆን ችግሩ አካሄዱ ነው” የሚሉት ይበረክታሉ። “ህወሃት አጥብቆ የሚፈራው የሸዋውን ኦሮሞ ስለሆነ አደህይቶ ሊያጠፋው ይፈለጋል። አስልሎ በራሱ መሬት ላይ ጭሰኛ ሊያደርገው ይተጋል” የሚሉት ክፍሎች ክልሉን በኢንቨስትመንት ስም እየተቀራመቱ ያሉት ባብዛኛው የህወሃት ሰዎች መሆናቸውን ይናገራሉ። የአየር ባየር ንግዱን ጨምሮ በባንክ ብድር የከበሩትም እነዚሁ ክፍሎች ስለመሆናቸውን ለማረጋገጥ ባንኮችን ጎራ ብሎ ማነጋገር በቂ መሆኑን ያክላሉ።
የስታትስቲክስ ባለስልጣን ባለሙያው ከሚሉት ጋር በሚስማማ መልኩ አሁን የኦሮሚያ ማስተር ፕላን በሚል ያለው ዝግጅት “ምስኪኖችን በስፋት ከአዲስ አበባ ለመንቀልና አዲስ አበባ ላይ ህወሃት በቁጥር በልጦ ፖለቲካውን እና ኢኮኖሚውን የመዘወር አቅሙን ማጎልበት ነው” የሚል አስተያየት የሚሰጡም ይሰማሉ። በምንም ይሁን በምን ከላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮችና ጠቋሚ ታሪኮች “ለማመጽ ከበቂ በላይ ምክንያቶች አሉ” የሚለውን አብይ ጉዳይ ለማመላከት ከባህሩ በቆርኪ የተጨለፉ ናቸው።
በአዲስ አበባ የባንክና የህዝብ እዳ እየጮኸባቸው ከሚታዩት ህንጻዎች መካከል የአንዱ ባለቤት ናቸው። በውል የሚታወቁ ባለገንዘብ ናቸው። ሻጭ የቀድሞ ታጋይ ናቸው ተብለው የሚታሙ፤ ጊዜ አሳምሮ የሞሸራቸው ባለሃብት ናቸው።
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በግልጽ፣ በጥቅሉ ደግሞ በድለላ ስራው ላይ ችግር ስለሚፈጠርበት “አደራ” በማለት ለጎልጉል ዘጋቢ እንዳጫወተው የሁለቱ ባለጠጎች ድርድር አስገራሚ ነበር። ሻጭ ኑሯቸውን ከአገር ውጭ ማድረግ መፈለጋቸውን እንደ ምክንያት በማቅረብ ህንጻቸውን እንደሚሸጡ ይገልጻሉ።
ቤተሰቦቻቸው ሙሉ በሙሉ አገር ቤት እንደማይኖሩና እሳቸውም ጠቅልለው የመሔድ አላማ እንዳላቸው የሚናገሩት ሻጭ፣ በዋጋው ላይ ልዩ ቅናሽ እንደሚያደርጉ ይገልጻሉ። ገዢም “አዎ አሁን እኮ ትልልቅ ግንባታ እየወረደ ነው” በማለት መደራደሪያቸውን እያቀረቡ ዋጋ እንዲቀንስላቸው ይጠይቃሉ። ሻጭ “ዋጋ አልወረደም፤ ግን ሻጭ ሊበረክት ይችላል” በማለት ትኩሳቱ እየጨመረ ስለመጣው ወቅታዊ ጉዳይ ስሜታቸውን ጠቆም አደረጉ። ሻጭ ከበዛ ዋጋ ሊቀንስ እንደሚችል ግን አልሸሸጉም።
“ከፈለክ ተጨማሪ የባንክ ብድር አስፈቅጄልህ ከዛ ልትከፍልኝ ትችላለህ” በማለት ሻጭ ሲናገሩ፤ ገዢ “ለመሆኑ ህንጻው ስንት እዳ አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። “ሞቶ” አካባቢ ነው ሲሉ ሻጭ መለሱ። አክለውም “ብድሩን እጥፍ አስደርግልሃለሁ” ሲሉ ቃል ገቡ። በግብይት የተጀመረው ጉዳይ ወደ ኢኮኖሚው ትኩሳት አመራ። በተለይም ኦሮሚያ ላይ የተከሰተው ችግር ብዙ ነገሮችን እንዳበላሸ ሻጭ ጠቆሙ። ኢንቨስትመንት አደጋ ውስጥ መውደቁን መስማታቸውን፣ በርካታ የውጭ ባለሃብቶች የስጋት ፍንጭ ማሳየታቸውን አወጉ። “አንተ ኦሮሞ ነህ፣ ችግር የለብህም …” ወዘተ በማለት ሻጭ የሳቸውንና የዘመዶቻቸውን ስጋት ተነፈሱ።
የቪኦኤ የአማርኛ ድምጽ ሪፖርተር ሄኖክ ሰማእግዜር ከሁለት ሳምንት በፊት ያነጋገራቸው የኢንቨስትመንት ኮሚሽን የበላዩ አለቃ አቶ ታደሰ አሁን የተፈጠረው “ግርግር” ምንም ችግር እንደማይፈጥር ጠቁመዋል። ሄኖክ “በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ድንጋይ የመወርውር …” ሲል አቃልሎና አንኳሶ ላቀረበው ጥያቄ ኃላፊው የመለሱት “ዓላማ የለሾች፣ ተራ …” ወዘተ በማለት ነበር። “ችግር አይፈጥርም” የተባለውና “ከድንጋይ ውርወራ” ጋር የተነጻጸረው እጅግ በርካታ ሕይወት የቀጠፈው ዓመጽ እስካሁን አልበረደም፤ የሚበርድም አይመስልም!
የበዪና የተበዪ ትዕይንቱ ቀጥሏል፤ አመጹም አላቆመም። ግፍ ተቆልሏል፤ ህወሃትም በጉልበቱ ገፍቶበታል። በመለስ ታርሶና ተኮትኩቶ የተሰናዳው “የዘር እርሻ” ጥቂቶችን እጅግ ባለጸጋ እና ባለዕድል ሲያደርግ እጅግ ብዙኃኑን ዕድለቢስና ፍጹም ደሃ አድርጓቸዋል፡፡ የማንነት ጥያቄ ኢትዮጵያን በአራቱም አቅጣጫ እየናጣት ነው፡፡ በኦሮሞ ከተሞች የቀጠለው ዓመጽና ተቃውሞ፤ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ፤ “የአማራ ተስፋፊ” እያሉ የፕሮፓጋንዳ “ጄኖሳይድ” ሲያካሂዱ የነበሩ አሁን አናሳ የነበረችውን መሬታቸውን ለሪፐብሊክነት በማዘጋጀት “አገራዊ” ቅርጽ እያስያዙ መምጣታቸው፤ በመለስና ግብረአበሮቻቸው ትዕዛዝ በዘር ማጥፋት የነደደችው ጋምቤላ ድጋሚ በዘር ዕልቂት መዘፈቋ፤ በጸጥታ እየተፈጀ ያለው የኦጋዴን ሕዝብ፤ እጅግ አስከፊ እየሆነ ከመጣው ጠኔ፤ ችጋር እና ፍጹም ድህነት ጋር ተዳምረው ኢትዮጵያን የሚፈላ አፍላል አድርገዋታል፡፡ ዘላለማዊነትን የተጎናጸፉ የመሰላቸው “ሰላም ነው፤ ህዳሴ ነው፤ ዕድገት ነው፤ ሥራ ላይ ነን፤ አይሰማም፤ …” እያሉ አልበቃ ሲላቸው ደግሞ “ልክ እናስገባለን” በማለት አሁንም ይደነፋሉ፡፡
“ከትንሹ እስከ ትልቁ ሰው፤ ሁሉም ለጥቅም የሚስገበገቡ ናቸው፤ … ሁሉም ያጭበረብራሉ፤ የሕዝቤን ቁስል እንደ ቀላል ቆጠሩ፤ እንዲፈወስም ተገቢውን እንክብካቤ አላደረጉለትም፤ ሰላምም ሳይኖር “ሰላም፤ ሰላም” ይላሉ፡፡ ስለ አጸያፊው ተግባራቸው አፍረዋል? ኧረ ጨርሶ ዕፍረት የላቸውም! ዕፍረት ምን እንደሆነ አያውቁም” እንዳለው ታላቁ መጽሐፍ የፍትሕ ሰይፍ በግፈኞች ላይ የሚመዘዝበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ የአባት ዕዳ ለልጅ ከመትረፉ በፊት ኢትዮጵያ ፈውስ ያስፈልጋታል፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
gud says
Racially motivated talk