• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በኦሮሚያ ከተሞች የሚካሄድ ተቃዉሞ ቀጥሏል

January 14, 2016 08:21 am by Editor Leave a Comment

ከተጀመረ ወራትን ያስቆጠረውና ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች በጭካኔ ለመገደላቸው መረጃ የሚቀርብበት ሕዝባዊ ንቅናቄ አሁንም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ቀጥሎዋል። ኢህአዴግ በአፈቀላጤዎቹ አማካኝነት “ሰልፍ የወጣ የለም፣ ከተማችን ሰላም ነው፣ የተገደለ የለም፣ . . .” በማለት የማስተባበያ ሙከራው በራሱ ሹሞች ሲጨናገፍ በተደጋጋሚ ይስተዋላል። በሌላ በኩል በፌዴራልና በአግአዚ መራር ሰቆቃ እየደረሰበት ያለው ሕዝብ “ባርነት በቃን፣ ግድያው ይቁም፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ . . .” የሚሉ መፈክሮችን እያነገበ ሰላማዊ ተቃውሞውን ቀጥሎዋል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ባለፉት ሦስት ቀናት የተከሰተውን ያቀረበው ዘገባ ከዚህ በታች ይገኛል።


ባለፈው ሐምሌ ወር ከአምቦ ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ ታስሮ እንደነበርና ታሞ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህክምና ላይ ሳለ ህይወቱ እንዳለፈ የተነገረው ተማሪ አብደታ ኦላንሳ ቀብር ዛሬ (ረቡዕ) አምቦ ከተማ ተፈጽሟል። በስልክ ያነጋግርናቸው ነዋሪ ትናንት ማታ የወጣቱን አስከሬን ለመቀበል በወጣ ህዝብ ላይ የጸጥታ ሃይሎች ድብደባ አድርሰዋል። ወደ ሰማይ ሲተኩሱም ነበር። አንድ ሰው በጥይት ተመትቶ ተገድሏል ብለዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአምቦው ነዋሪ አስከትለውም ዛሬ በቀብሩ ላይም እንዲሁ የከተማው ነዋሪ በብዛት ወጥቶ እንዳይቀብረው ለማስተጓጎል ወታደሮች በተለይ ወጣቶችን መኪና ላይ እየጫኑ ወስደዋቸዋል ብለዋል። ወደ ቀብሩ ጉዞ ላይ የነበረ ወጣት በጥይት መገደሉን ገልጸውልናል።

ትናንትና ደግሞ በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ አጠገብ የአንድ ወጣት አስከሬን ተገኝቷል ብለዋል።

የአምቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አሰፋ ሂርኮ አምቦ ውስጥ ተገደሉ የተባለውን አስተባብለዋል።

ባልደረባችን ጃለኔ ገመዳ አነጋግራቸው ነበር ። “ባለው መረጃ አምቦ ውስጥ የተገደለ ሰው የለም አዲስ አበባ ከተማ ታሞ የሞተ ሰው አአስከሬኑ አምቦ ገብቶ ዛሬ ተቀብሯል ። ለበለጠ መረጃ የአምቦ ከተማ ከንቲባውን አነጋግሩ” ሲሉ ቢመሯትም ከንቲባ ዱጋሳ ኦሉማ በእጅ ስልካቸው በተደጋጋሚ ተደውሎ አላነሱትም።

አዲስ አበባ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሞቶ ዛሬ ተቀበረ ስለተባለው ወጣት አብደታ ኦላንሳ ጉዳይ ሆስፒታሉ መዝገቡን ተመልክቶ ነገ ማብራሪያ ሊሰጥ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ሶራ ሃለኬ ባገኘው መረጃ ደግሞ ፌደራል ፖሊሶች የተማሪዎች መኝታ ቤቶች እየገቡ ጭካኔ የተመላበት ድብደባ አካሂደዋል ብዙ መቶዎች አስረው ወስደዋል።

ስሜን አትግለጡ ያለው ተማሪ፣ ተማሪዎች ያሉትን ለማጣራት ወደ ከተማዋ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ደውሎ እንዳልተሳካለት ባልደረባችን ሶራ ሃላኬ በዘገባው አመልክቷል።

በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ ደግሞ የከተማው መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች “የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት የታሰሩ ተማሪዎች ይፈቱ” “ ግድያው ይቁም” በማለት ትናንትናና ዛሬ ሰልፍ ወጥተዋል ሲሉ “ስማችንን እንዳትገልጹብን” ያሉ ተማሪዎች ለባልደረባችን ቱጁቤ ሆራ ገልጸውላታል።

በሰላም ነበር ሰልፉ የሚካሄደው የመንግሥት ሃይሎች በተኑት፣ የተወሰኑ ተማሪዎች ተደበደቡ፣ የታሰሩም አሉ ያለው ተማሪ እኔም ራሴ ከተደበደቡት አንዱ ነኝ ብሏል።

“የሃሮማያ እና የጅማ ተማሪዎች እንዲሁም በአምቦ ተማሪዎች መገደላቸውን በመቃወም፣ ድርጊቱ ይቁም ትግላችን ይቀጥላል ብለን ድምጻችንን ስናሰማ ነበር” ሲል ገልጿል።

የሻሸመኔ ከተማ የአስተዳደር እና ደህንነት ሐላፊ አቶ ስንታየሁ ጥላሁን ግን ሃሰት ነው ይላሉ ።

“ሰልፍ የወጣ የለም። ሰልፍ ማካሄድ ተፈቅዷል፣ ግን የወጣም የለም የታሰረም የለም፣ ተማሪዎች እየተማሩ ናቸው። መማር የፈለገ ይማራል፣ የማይፈልገውን ግን አናስገድድም መብቱ ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ስንታየሁ አንዳንድ ጥያቄ ያነሳ ሊኖር ይችላል ብለው ነበርና ቱጁቤ ምን ጥያቄ ነው ያነሱት? ብትል “ማለት የጠየቁት እኮ ነገር የለም ቢሯችን የደረሰው መረጃ የለም ከተማውም ሰላም ነው” እንዳሏት አክላ ጠቅሳለች።

በሌላ በኩል በምእራብ ሃረርጌ በአዳ ቡልቱም ወረዳ በዴሳ ከተማ ከትላንት በስቲያ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ሕብረተሰቡ “ባርነት በቃን” የሚል መፈክር አንግቦ ለተቃዉሞ እንደወጣ መንግስት ጥቃት እንዳያደርስብኝ ሰሜ አይገለጥ ያሉ የሰልፉ ተካፋይ ለአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል።

በቀለ ገርባና በቀለ ነጋ ይፈቱ፣ የታሰሩ ተማሪዎች  ሁሉ ይፈቱ ማስተር ፕላን ይሰረዝ የሚል በራሪ ወረቀቶች ይዘዉ ነዉ የወጡት። መንግድ ላይ የከተማዋ ካቤኒ አባል መሃመድ ሰይድ መጥቶ ወረቀቶችን ከእጃቸዉ ነጥቆ ሲበትን ሰልፈኞቹ ደበደቡት። ፌዴራል ፓሊሶችና አዳማ በታኝ ሃይሎች አሁን ያገኙትን ሁሉ እያወከቡና እያሰሩ ነዉ ፣ አግአዚዎችም ገብተዋል።

የባዴሳ ከተማ ካቢኔ አባል አቶ መሃመድ ሰይድ የበኩላቸዉን እንዲገልጹልን ሰልክ ደዉለንላቸዉ ነበር አያነሱም።

በምእራብ ሃረርጌ ሂርና ከተማ ለአንድ ሳምንት ያክል ሲካሄድ  የሰነበተዉ ተቃዉሞ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና አድማ በታኞች በወሰዱት እርምጃ ወደ ለየለት ጦርነት ተቀይሯል ይላሉ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ በመጠየቅ የኦሮሚኛ ቋንቋ ክፍልን ያነጋገሩ የሰልፉ ተካፋይ።

“ሰላማዊ ሰልፍ ነበር የተጀመረዉ። መከላከያ ሰራዊት አምጥተዉ በሰላም የጀመርነዉ ትግላችንን ወደ ጦርነት ቀየሩት። በጥይትና  በእንባ አስመጪ ጋዝ እየደበደቡን ነዉ። አጋአዚ ሁሉ አምጥተዉ ወንድ ሴት ሳይሉ በሒርና ከተማ ያለ ነዋሪ በር ሰብረዉ በመግባት እያሰሩ እየገረፉ ነዉ” ብለዋል።

በዛሬዉ የጸጥታ ሃይሎች ጥቃት ቁጥራቸዉ በዉል የማይታወቅ ሰዎች ቆስለዋል  ብለዋል የሰልፉ ተካፋይ ነኝ ያሉት የዓይን እማኝ። ካሁን በፊት በጽኑ የቆሰሉ ሶስት ሰዎች  ጭሮ ሆስፒታል እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የሂርና ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር አቦዶ በበኩላቸዉ ከተማዋ ሰላም ናት ይላሉ።

“አይ እየታሰሩ ያሉ ሰዎች የሉም። ዉሸት ሊሆን ይችላል፣ እስካሁን የታሰረ ሰዉ የለም ከተማችን እስካሁን ሰላም ናት፥ ይህ ሁሉ ዉሸት ነዉ” ብለዋል።

ትላንት በምእራብ ሃረርጌ የአሰቦት ከተማ ተማሪዎች የከተማዋ ባንክ ቤት ፊት ለፊት ቆመዉ የአዲስ አበባና የፊንኒኔ ዙሪ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተቃዉሞ ማሰማታቸዉን የቪኦኤ የአፋን ኦሮሞ ክፍል ባልደረቦች ሰልፉን የተካፈትን በማነጋገር ዘግቧል።

የከተማዋ ፖሊሶችን ባለስልጣናት ተኩስ በማሰማት ሰልፉን መበተናቸዉም ታዉቋል፣ የቆሰለ ሰዉ ግን የለም። የአፋን ኦሮሞ ክፍልን ያነጋገረ አንዱ ተማሪ በአሰቦት ከሰዓት በሁዋላ ከ6 – 9 ሰዓት ሁለተኛ ዙር በተካሄደ ተቃዉሞ ላይ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ነጋዴዎች ለገበያ የወጡ አርሶ አደሮች መቀላቀላቸዉን ገልጿል።

“ከዚያ በሁዋላ ሶስት መኪና ሙሉ የመከላከያ አባላት ወደ ከተማዋ ገብተዉ ተኩስ ከፈቱ፥ ተኩስን በመጋፈጥ ተማሪዎቹና ሕዝቡ ድንጋይ በመወርወር ተከላከል በተወረወሩ ድንጋዮች የተጎዱ የመከላከያ አባላት አሉ” በማለት በከተማዋ የነበረዉን ሁኔታ አብራርቷል። ተከትሎም የጸጥታ ሃይሎች ቤቶችን  ሰብረዉ ገብተዉ ተማሪዎችን ለቅመዉ አስራዋል ብሏል።

ትናንት  በዚሁ በምእራብ ሃረርጌ ጡጢሲ በሚባል ከተማና የዳሮ ገጠር ነዋሮዎች የተቃዉሞ ስልፍ ማከሃዳቸዉን ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ የከተማዉ ነዋሪ ገልጿል። ጥያቄአቸዉም “አቶ በቀለ ገርባ እና የታሰሩት ሁሉ ይፈቱልን ኦሮሞ የሃገር ባለቤት ነዉ በማለት ሴት ወንድ ሳይል ነዉ ሁሉም ለተቃዉሞ የወጣዉ። ተማራዎች አልተካፈሉም። አርሶ አደሮች የአገር ሽማግሌዎች ናቸዉ ልጆቻችንን አትሰሩብን” በማለት ለተቃዉሞ የወጡት።

በጡጢሲ ተቃዉሞዉ በሰላም ቢጠናቀቅም፣ ፖሊሶች ብዙዎችን ቁጥጥር ስር እንዳዋሉ ተገልጾል።

የምእራብ ሃረርጌ አስተዳዳሪ አቶ አልይ ኡመር የአሰቦት ከተማ ከንቲባ አቶ ቶፈቅ አልህ እና የከተማዋ ሰላምና መረጋጋት ሃላፊ አቶ አደም ሲራጅን ለማነጋግር የተደረገዉ ሙከራ አልተሳካም።

የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ ጌታቸዉ ረዳ በኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተጀመረ፣ ተቃዋሚዎቹ የታጠቁና የመንግስት ባለስልጣናትን፣ መሳሪያ ያልያዙ የጸጥታ ሃይሎችን፣ ገበሬዎችንና፣ ሕዝብን የሚያሸብሩ ናቸዉ ማለታቸዉን ሮይተርስ ባለፈዉ ታህሳስ አራት ዘገባዉ ጠቅሷል።

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule