• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ህወሃት በእስረኞች ላይ አጥንት የሚያመነምን መርዝ ይጠቀማል” እማኝ

October 11, 2016 10:03 am by Editor Leave a Comment

በኢትዮጵያ እስረኞች አጥንትን ቀስ በቀስ በሚያፈርስ መርዝ እየተጠቁ መሆኑን ታውቁ ኖሮዋል?

ከጥቂት ዓመታት በፊት የግንቦት ሰባት መሪዎች እና አባላት መታሰራቸው ይታወሳል። ብዙዎቹ ቃሊቲ የሚገኘው እስር ቤት ነበሩ። በእስር ቤት እያሉ በደረሰባቸው ያልታወቀ ሕመም ምክኒያት ሕይወታቸውን ያጡ መሪዎችም ነበሩ።ታዲያ አንዴ ከሜክሲኮ ወደ ሃያሁለት በታክሲ ተሳፍሬ ስሔድ በግምት የሃያ ዓመት ዕድሜ ያለው ልጅ ታክሲው ውስጥ ገብቶ አጠገቤ ተቀመጠ።

ታክሲው ሞልቶ መሔድ ሲጀምርም ወንድሜ ይቅርታህን የታክሲ ትከፍልልኛለህ ብሎ ጠየቀኝ። ዞር ብዬ ያየሁት ይህን ሲል ነበር። ድንጋጤ እና መሸማቀቅ ይነበብበት ነበር።ልቤ በጣም አዘነለት። ምን ሆነህ ነው? ከዬት ነው የምትሔደው፤ወዴት ነው የምትሔደው ብዬ ጠየኩት። እርሱም ከቃሊቲ እስርቤት ዛሬ መለቀቄ ነው አለ። ለምን ታሰርክ እንዴትስ ተለቀቅህ ስለው የቦሌ ሁለተኛ ደረጃ  ት/ቤት ተማሪ እንደ ነበረ እና ከመንገድ አፍሰው ወደ እስር ቤት እንደጣሉት ነገረኝ። የግንቦት ሰባት አባል እና ደጋፊ ናችሁ ብለው ቀን ከለሊት ሲገርፉን፤ ሲያስርቡን፤ መዓት መከራ ደርሶብናል፤ እንደምታዬው አእምሮዬ ራሱ ልክ አይደለም። ነገርግን በጣም ጤነኛ ልጅ ነበርኩ ብልህ አታምነኝም፤ ድሮም ትንሽ እብድ ነገር ነበርክ ብለህ ብታስብ አይገርመኝም አለ።

ፍርድቤት የሚባል ነገር አይተን አናውቅም።

መጀመሪያ ላይ ቤተሰብ እንዲጠይቀን ተፈቅዶላቸው ይጠይቁን የነበረ ሲሆን በኋላ ግን ተከለከሉ። ቤተሰቦቼን በአይኔ ካየሁ ሁለት ዓመት ሊሆነኝ ነው አለ። ከዚያም ወዲያው ስለ ራሱ ትቶ ሁላችንም ስለምናውቃቸው እና በግንቦት ሰባት ሰበብ እስርቤት ተጥለው ስለ ነበሩ መሪዎች ይነግረኝ ጀመር። እነ አቶ እከሌ እኛ ጋ ነው ታስረው የነበሩት። እንላላካቸውም ነበር። ምንም እንኳን እነርሱ እንደ እኛ ወደ ውጪ ብዙውን ግዜ እንዲወጡ ባይፈቀድላቸውም ፀሐይ እንዲሞቁ በሚያወጡዋቸው ሰዓት እየተላላክን የሚፈልጉትን እንገዛላቸው ነበር። ከቆይታ በኋላ እነ አቶ እንትናን እና አቶ እንትናን ከሌሎች ለይተው ሌላ ክፍል ውስጥ አሰሯቸው። በኋላም አይናችን እያየ ሰውነታቸው መፈራረስ ጀመረ። አፍንጫቸው፤ ጆሮዋቸው፤ አይናቸው ጣታቸው የስጋ ደዌ እንደያዘው ሰው ይፈራርስ ጀመር። አንድ ቀን ሊልኩኝ ሲጠሩኝ በድፍረት ምን ሆናችሁ ብዬ ስጠይቅ እንደ ፍሊት ያለ መርዝ እየረጯቸው መሆኑን ነገሩኝ። መድሃኒቱንም እድሜ ለቻይና እናንተን የማሰናበቻ ቀላል መንገድ ተገኘ እያሉ ይፎክሩብናል፤ ይስቁብናል፤ የውሸታቸውን ሆስፒታል ይወስዱናል። ለቤተሰባችን ታመዋል ብለው ይነግራሉ ብለው ነገሩኝ አለ።

ከዚያስ በኋላ ስለው ቀስ በቀስ መንቀሳቀስ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደረሱ። በሚያስጠላ ሁኔታ ሰውነታቸው እየፈራረሰ ስለነበረ መሸፋፈን ጀመሩ። መጀመሪያ ወደዚያ ክፍል ከገቡት መካከልም እነ አቶ እንትና ሞቱ። ታመው ሞቱ ተብሎ ሲነገር ሰማን አለ።

ቤተሰብ እንዳያያችሁ ለምን ተከለከለ ብዬ ስጠይቀው፤ ምክንያቱን አላወቅንም ነበረ። በኋላ ግን ቤተሰባችን እንዳያዬን ከከለከሉ በኋላ ምግብ ያመጡልን ጀመረ አለ። ምግባቸውን መብላት ስለቀፈፈን የበላን እያስመሰልን እንደፋ ነበረ፤ ወደ ውጪ የመውጣት እድል ስናገኝም የሌሎች እስረኞችን ትራፊ እንበላ ነበር።ከቆይታ በኋላ ግን ምግቡን እንድንበላ አስገድደው እንቢ ስንል የሆነ መርፌ ወጉን። ቀስ በቀስ ሰውነታችን እየደከመ ሔደ፤ ቀስ በቀስ አእምሯችንም እየጨለመ ሲሔድ ይታወቀን ጀመር።

አንዳንዶቹ ልጆች ከሌሎቻችን በበለጠ መልኩ እንደ እብድ የለየላቸው ሆኑ። ታመው ነው እያሉ ሆስፒታል ይወስዷቸዋል። የአእምሮ ጭንቀት ነው እያሉ የስነልቦና ጠበብት መጥተው እንዲጎበኟቸው ያደርጉ ነበር። ከዚያ አውጥተው መንገድ ላይ ይጥሏቸዋል። ስንቶቹን ቤተሰብ እንዳገኛቸው እግዚአብሔር ብቻ ያውቃል አለኝ።

ሰፈሩን ያውቅ እንደሆነ ስጠይቀው በጣም ደስ አለው። አዲሳባ ሃያሁለት ተወልጄ ያደኩ መሆኑን እና ቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እንደነበርኩ ነግሬህ ቤቴን እንደማውቅ ስትጠይቀኝ ችግሬ በጣም ገብቶሃል ማለት ነው አለኝ። እስከ ቤተሰቡ ቤትም ሸኘሁት። ያ ልጅ ምን ላይ እንደደረሰ አላውቅም። ነገርግን እግዚአብሔር በጥበቡ ካልደረሰለት በስተቀር በሕይወት አለ ብዬ አልገምትም።

ይህ ነገር ወደ አእምሮዬ የመጣው ትላንት የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮን ዜና ስከታተል አንድ ብሔሩ ኦሮሞ የሆነ ኮማንደር በሰበታ የታሰሩ ልጆችን በተመለከተ የአጋዚ አዛዦች ስብሰባ ጠርተውን ለታሰሩት ልጆች ከምግብ ጋር መርዝ እንድንሰጣቸው መመሪያ ተላልፎልናል ብለው በመቆርቆር ሲናገሩ ስሰማ ነው። ከምንምግዜ በላይ አሁን አደጋ ላይ መሆናችን አሳሰበኝ። በየእስርቤት የታጎሩ የኦሮሞ እና የአማራ ልጆች እጣ ፈንታ ይሔው የተባለው መርዝ መሆኑ እረፍት ነሳኝ።

አሁን ሊበሉን ተነሱ ማለት ነው። አሁን ቤተሰብ ለልጆቹ መድረስ ይኖርበታል።ልጆቹ በእጁ እንዲገቡ እስኪያደርግ ድረስ ቤተሰብ መተኛት የለበትም። ይህ እንዲሆን ደግሞ ቤተሰብ ሚስጥሩን መረዳት ይኖርበታል።

ይህ ዜና እንዲሰራጭ ማድረግ አንዱ የመከላከያ መንገድ ሊሆን ስለሚችል እባካችሁ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ዘገባችሁን አጠናክሩ።

ወደ ሕዝቡ ሊደርስ በሚችልበት በማንኛውም መንገድ ይህ ዜና ይሰራጭ። እውነት መሆኑን ማመን ቢያቅታችሁም እንኳን በማሰራጨታችሁ የምትጎዱት ነገር ግን የለም።

(ለደህንነታቸው ስንል ይህንን መረጃ የላኩልን ማንነት ከማውጣት ተቆጥበናል፡፡ ፎቶው ለማሳያነት የተወሰደ ነው)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions, Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule