• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ባንዶች ሀገራችሁን እንደጎዳችሁ ዛሬ ደግሞ የምትክሱበት ጊዜ ነው” ጄኔራል ለማ ገ/ማርያም

October 19, 2016 04:06 am by Editor Leave a Comment

ጄኔራል ለማ ገብረማርያም የኢጣልያ ፋሺሽቶች ኢትዮጵያን በወረሩበት ዘመን በጽንዓት ተዋግተው ከነበሩት የኢትዮጵያ አርበኞች አንደኛው ነበሩ። በፈጸሙት አኩሪ ትግል ኢጣልያዊ ስለ መማረካቸውና አሁን ደግሞ ሕይወተ ሕልፈት ያጋጠማቸው መሆኑን፤ Ethiopian Media Forum የዘገበውን ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል።

ጄኔራል ለማ ለሐገር ነጻነትና ክብር ካከናወኑት እጅግ የሚያኮራ ተግባር ውስጥ አብሮ ሊደነቅ የሚገባው አንዱ አስተዋጽኦዋቸው ቫቲካን በፋሺሽቱ ወረራ ዘመን ለፋሺሽት ኢጣልያ ላከናወነችው ያልተቆጠበ ድጋፍ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ በማመልከት ከዚህ ጋር የተያያዘውን ግልጽ ደብዳቤ ማስተላለፋቸው ነው። (ደብዳቤውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

በልጅነታቸው ጊዜ ብቻ ሳይሆን በሽምግልናቸው፤ በ97 እድሜያቸው ጭምር ጀኔራል ለማ ለሐገራቸው ያልተቆጠበ ጥረት ያበረክቱ እንደ ነበረ በማስረጃ የተረጋገጠ ነው። ለሐገራቸው ላከናወኑት አኩሪ አገልግሎትና ትግል ሁሉ ድርጅታችን ምሥጋናውን ይገልጻል።

ስለዚህ፤ ቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ የጄኔራል ለማን ነፍስ እንዲምርልንና ቤተሰባቸውንም እንዲያጸናልን እንጸልያለን።

ኪዳኔዓለማየሁ
ዋናሥራአስኪያጅ
ዓለም-አቀፍሕብረትለፍትሕ – የኢትዮጵያጉዳይ
(www.globalallianceforethiopia.org)

የጣሊያን ጀነራል የማረኩ ብርጋዴር ጀነራል ለማ ገ/ማርያም አረፉ

(ሙሉጌታ ኃይሌ)

ብርጋዴር ጀነራል ለማ ገ/ማርያም ይባላሉ፡፡ የማይጨው ዘማች ነበሩ፡፡ በተወለዱ በ99 አመታቸው መስከረም 23 2009 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ከማይጨው ዘመቻ ተርፈው እስካሁን በሕይወት ይኖሩ ከነበሩት የመጨረሻው እሳቸው ነበሩ፡፡

ከነፃነት በፊት ሜጀር የሚለው የወታደር ማዕርግ ያገኙ የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ከነፃነት በኋላም የመጀመሪያው የአባዲና ፖሊስ ምሩቅ ሆነው የፖሊስ ሠራዊትን ወደ ዘመናዊነት ከአሸጋገሩት አንዱና ዋናው ነበሩ፡፡

በዘመናቸው ከሚታወቁበት ታሪካቸው አንዱ፣ በ1934 ዓም ጎንደር ላይ የፋሽስትን የጦር መኮንኖች ለመማረክ በተደረገው የቤት ለቤት አሰሳ ላይ በአደረጉት አስተዋፆ ነው፡፡

ከነበሩበት አሳሽ ቡድን ፊት ቀደም ብለው ከሩቅ የነጭ ባንዲራ ወደሚውለበለብበት ባንኮ ዲሮማ ጠጋ ብለው በሩን ከፍተው ቢገቡ፣ የጣሊያን ከፍተኛ መኮንኖች መሠሪያቸውን መሬት ላይ አስቀምጠው ጠረጴዛ ከበው ካርታ ሲጫወቱ ያያሉ፡፡ ይሄን ሁሉ መኮንን በአንድ ጊዜ መማረክ ስለማይችሉ እርዳታ ለመጠየቅ በሌላ በር ሊወጡ ሲሉ፤ በአንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ የሸዋ ገዢ የነበረውን ጀነራል ናዚን፣ ቤተወደድ አስፋሐ ወ/ሚካኤል (ኤርትራዊው አስተርጎሚ) እና አቶ አሊ (የጀነራል ናዚ ልብስ አልባሽ) በአንድ ላይ አዝነው እንደተቀመጡ ይመለከታሉ፡፡ እነዚህን መማረክ እችላለሁ ብለው “እጅ ወደ ላይ” ሲሉ፣ ቢትወደድ አስፋሐ “እንደ ጀነራል ናዚ አይነት ከፍተኛ መኮንን በአንተ ሳይሆን በእንግሊዝ ከፍተኛ መኮንን ነው መማረክ ያለበት” ብለው ሲያንገራግሩ ወዲያው የእንግሊዝ ጦር ደርሶ ሁሉም አንድ ባንድ እጃቸውን ሊሰጡ ችለዋል፡፡

የእንግሊዝ ጦር ጄነራል ናዚን ማረከን ብለው እንዳይኩራሩ በጎንደር ከተማ ለነበሩት ለልዑል አልጋወራሽ አሰፋወሰን ኃ/ሥላሴ ምርኩኞቹ በሙሉእንዲተላለፉ አድርገዋል፡፡

ይህም ስራቸው ልዑል አልጋወራሽ ከነፃነት በኃላ የሙሉ ጄነራልነት ማዕርግ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥምይሄ ሹመት ለመጀመሪያ ጊዜ መሰጠቱ ነበር፡፡

ለዚህ ታሪክ እውነታ ቢትወደድ አስፋሐ ወ/ሚካኤል ለጀነራል ለማ በሰጡት የምስክርነት ደብዳቤ ላይ ተረጋግጦል፡፡

የጄነራል ለማ ገ/ማርያም አጭር የሕይወት ታሪክ

ጄነራል ለማ ከአባታቸው ከጎጃሙ ተወላጅ ከአለቃ ገብረ ማርያም አለምነህና ከእናታቸው ከቡልጋዋ ተወላጅ ከወ/ሮ ፋንታዬ ዘለሌ በ1910 ዓም በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ሥር በነበረችው የኬኒያ ሞያሌ ከተማ ተወለዱ፡፡ በኪኒያ የተወለዱበት ምክንያት አባታቸው በእንግሊዝና በኢትዮጵያ መሐከል የነበረውን የወሰን ክልል አስከባሪ ስለነበሩ ነው፡፡General Lemma

ጄነራል ለማ እድሜያቸው ለትምሕርት እንደደረሰ በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ገብተው በጊዜው ይሰጥ የነበረውን ትምሕርት አጠናቀዋል፡፡ በ1926 ዓ.ም. በውትድርና ተቀጥረው በምሕንድስና ትምሕርት ለሁለት ዓመት ሰልጥነው ተመርቀዋል፡፡ በ1928 ዓም የጣሊያን ጦር ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ ከመጀመሪያዎች እጩ መኮንኖች ጋር በመሆን በክብር ዘበኛ ጦር ውስጥ ማይጨው ዘምተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጦር ተሸንፎ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ፣ በመርዝ የተጎዳው ሰውነታቸው እስኪአገግም ድረስ በዘመዶቻቸው ቤት ውስጥ ተሸሽገው ተቀመጡ፡፡

የካቲት 12/1929 ዓም ግራዚያኒን ለመግደል በተደረገው ሙከራ ጣሊያን ለበለጠ በቀል የቤት ለቤት አሰሳ በሚያደርግበት ጊዜ ጄነራልበለሊት አምልጠው ወደ ጎጃም ሄዱ፡፡ ጎጃም ሲደርሱ ከአርበኛው ካሳ ብሩ እና ከራስ መስፍን ስለሺ ጋር ተቀላቅለው የአርበኝነት ሥራቸው መስራት ጀመሩ፡፡

ከእንግሊዝ ሀገር ከጃንሆይ ዘንድ የተላኩትን ፀሐፊ ትእዛዝ ሎሬንዞ መብራቱን አግኝተው አብረው ወደ ቤጌምድርና ጎጃም በመሄድ የመረጃ ስራ አሰባሰበው ተመለሱ፡፡

በመቀጠልም ሱዳን ከነበረው ከእንግሊዝ ጦር መሪ ሜጀር ቼዝማን በርካታ መሳሪያ በመረከብ እራሳቸውንና የጎጃምን አርበኞችን በተሻለ መሳሪያ አስታጠቁ፡፡

መስከረም 18/1932 ዓም በእንግሊዛዊው በጀነራል ሳንፎርድ በተቋቋመው ሚሽን 101 በተባለው የመረጃ ሰብሳቢ ኮሚቴ ውስጥ ተመድበው በሚስጥር ስራ ውስጥ ገቡ፡፡ በኮሮኔል ዊንጌት በሚመራው የጌዲዮን ጦር ውስጥ ሜጀር ተብለው የ5ሺ (እጁን የሰጠ የባንዳ ምርኮኛ) ሠራዊት መሪ ሆነው እስከ ቡሬ ከተማ ድረስ የነበረውን የጣላት ምሽጎችን አስለቀቁ፡፡

“ባንዶች ሀገራችሁን እንደጎዳቹሁ ዛሬ ደግሞ የምትክሱበት ጊዜ ነው” እያሉ የሠራዊታቸውን ሞራል ይገነቡ ጀመረ፡፡ የዚህ ምስክርነት ማስረጃ የተገኛው ክቡር አቶ ጌታሁን ተሰማ በፃፉት ማስታወሻ ላይ ነው፡፡

ብ/ጄነራል ለማ የኢትዮጵያ ነፃነት ከተመለሰ በኋላ በየቦታው ደፍርሶ የነበረውን ሰላም ለማስከበር በወሎ፣ ትግራይና ሐረር ተንቀሳቅሰዋል፡፡gen-lema-1

በተለያዩ ጊዜያት የሚከተሉትን የሀላፊነት ግዴታዎችንአከናውነዋል፡፡
1. ከ1941-42 ዓ.ም. የወሎ ፖሊስ ዋና አዛዥ
2. ከ1942-49 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የወንጀል ምርመራ ሐላፊ
3. ከ1949-50 የመላው ወህኒ ቤቶች (እስርቤት)አዛዥ
4. ከ1952-53 የኤርትራ ፀጥታ አዛዥ
5. ለጥቂት ጊዜ የመተሐራናወንጂ ስኳር ሀላፊ
6. ከ1953-1956 የሕዝብ ደሕንነት ዋና ሐላፊ (የኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ የነበረ ቦታ)

 

የ53ቱን የመንግስት ግልበጣ መሪ የነበሩትን ጀነራል መንግስቱ ነዋይን መርምረዋል (የዚህ ሙሉ ታሪክ በአቶ ታደሰ ቴሌ ሳልቫኖ በተፃፈው ገድለ መፈንቅለ መንግስት ማግኘት ይቻላል) ከዘጠኝ ዓመት በፊት በ1942 ዓም ከጀነራል መንግስቱ ነዋይ ጋር ሆነው የቤተወደድ ነጋሽ በዛብህን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራን በጋራ አክሸፋዋል፡፡ (የዚህ ሙሉ ታሪክ በአቶ በሪሁን ከበደ የአፄ ኃ/ሥላሴ ታሪክበሚለው መፅሐፍ ላይ ይገኛል) ጀነራል ለማ ከመንግስቱ ነዋይ በኋላ አራት የተለያዩ ያልተነገረላቸው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራዎችን አክሸፋዋል፡፡ “ኩዴታ ደጋግሞ ያከሸፈ መልሶ ኩዴታ ከማድረግ አይመለስም” በሚል ብሒል ጀነራል ለማ ወደ ጋምቤላ አገር አስተዳዳሪነት እንዲዛወሩ ተደርጓል፡፡

7. ከ1956-1962 ዓ.ም. የጋምቤላ አውራጃ ገዢ ሆነው ለረዥም አመታት ሠርተዋል፡፡ በአራጃው ዘመናዊ ትምህርት ቤት እና የጤና ክሊኒክ እንዲቋቋሙ አድርገዋል፡፡

ለዚህ መልካም አስተዳደራቸው የአለፋው ዓመት የጋምቤላ ፕሬዜዳንት ክቡር አቶ ኦልኤሮ ኦፒዮ በጋምቤላ በተደረገው የብሔር ብሔረሰቦች ክበረ በዓል ላይ በክብር እንዲገኙ ጥሪ አቅርበውላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን
በሐኪማቸው ትእዛዝ መሠረት በእዚህ እድሜ በአውሮፕላን መብረር አይችሉም ተብለው ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡ ታዋቂው የጋምቤላ የሥዕል ባለሞያ አቶ ሐሰን ኦፒዮ ለዛሬው ማንነቱ የጀነራል አሻራ እንዳለበት በአንድ ወቅት ሲናገር “ጀነራል ኒውሲክና ታይምስ የተባሉትን የእንግሊዘኛ መፅሔቶችን በረንዳቸው ላይ ቁጭ ብለው ሲያነቡ፣ አንድ ቀን እንደሳቸው እሆናለሁ ብዬ እመኝ ነበር” በማለት የማይረሳውን የልጅነት ትውስታውን ገልፆአል፡፡

የጀነራል ዝና ከጋምቤላ አንስቶ አዲስ አበባ ደርሶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ታሪክ ያስረዳል፡፡ እሳቸው የጋምቤላ አውራጃ ገዥ ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ በአዲስ አበባ ውስጥ ወጣቶች የጋምቤላን ተወላጅ ሲመለከቱ “ለማ!” ብለው ይጣሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡

አንዳንዶች ቃሉ ሲደጋገም ስድብ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን በጋምቤላ (በአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ) “ለማ” ለሚለው ፍቺ ካለ ጀነራል ስም በስተቀር ሌላ ፍቺ ያለው ቃልማግኘት አይቻልም፡፡

ጀነራል ለማ በ1960 ለመጀመሪያ ጊዜ የሱዳን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡበት ጊዜ ላደረጉት ከፍተኛ የሰብአዊ ርሕራሄ ሥራ የዓለም ስደተኞች ድርጅት UNHCR የልዩ እውቅና ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡

ዛሬ ከነዚህ ስደተኞች መሐከል አብዛኞቹ ዛሬ ኢትዮጵያዊ ለመሆን በቅተዋል፡፡ የዛሬ 50 ዓመት የደቡብ ሱዳን የነፃነት ታጋዮች የመረጃ አሰባሰብና የሬዲዮን ግንኙነት የተማሩት በጀነራል መኖሪያ ቤት ውስጥ እንደ ነበር የነፃነቱ መሪ የነበሩት ጀነራል ጋራንግ ስለ ኢትዮጵያ ውለታ ሲናገሩ ጠቅሰውታል፡፡

8. ከ1962-64 ዓ.ም. በሀገር ግዛት ውስጥ የወሰን አስተዳደር ም/ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል

9. 1964-68 ዓ.ም. የአሰብ አስተዳደር ዋና ሀላፊ ሆነዋል፡፡

ጀነራል ለማ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር መሪዎች የተለያዩ ኒሻኖችና ሜዳሊያዎችን አግኝተዋል፡፡ ከነዚህ በጥቂቱ

1. የዳግማዊ ሚኒሊክ ሜዳይ
2. የክብር ኮኮብ ኒሻን
3. የአጥቢያ ኮኮብ ኒሻን
4. የረዥም ጊዜ አገልግሎት ኒሻን
5. የሰብአዊ አገልግሎት ኒሻን
6. ከእንግሊዝ መንግስት የተሰጠ ሁለት በአንገት ላይ የሚጠለቅ ኒሻኖች
7. ከዩጎዝላቪያ ፕሬዚዳንት ማርሻል ቲቶ የተሰጠ ኒሻን
8. ከሱዳን መሪ ከጀነራል አቡድ የተሰጠ የሀገሪቱ ከፍተኛ ኒሻን

ጀነራል ለማ የዛሬ ሦስት ዓመትለቫቲካን መሪ ለፖፕ ፍራንሲስ የመጨረሻው ጸሎቴ በሚል ርእስ ደብዳቤ መፃፋቸው ይታወቃል፡፡ የዚህ ደብዳቤ ሙሉ ቃል ከዚህ ደብዳቤ ጋር ተያይዞል፡፡

ጀነራል ለማ ሕይወታቸው ከማለፉ አንድ ሳምንት በፊት ጤናቸውና አእምሮቸው የተሟላ በሽታ የማያቃቸው እድለኛ አዛውንት ነበሩ፡፡ ዘወትር እሁድ ቤተክርስቲያን የማይቀሩ፤ ወርሐዊ የእድር መዋጮ ለመክፈል ወደ ፓሊስ ክበብ እና የጡረታ ገንዘባቸውን ለመቀበል በየወሩ የሚሄዱ ነበሩ፡፡ (የጡረታ አበላቸው 1300.15 ሳንቲም ሲሆን በአሜሪካን ዶላር 54 ብቻ ነው፡፡ የዛሬ 45 ዓመት የጡረታ ገንዘባቸውን ማስቀመጥ ሲጀምሩ የአንድ ዱላር ምንዛሪ 2.15 ሳንቲም ነበር፤ ዛሬ 22 ወይንም 24 ብር ሆኖል፡፡) ለጀነራል መከፈል የነበረበት አበል በአሁኑ ምንዛሬ 31,200 ብር መሆን ነበረበት፡፡ ጀነራል ስለ ሆኔታው ሲገለፁ “ያልታወጀ ጦርነት በሸማገሌዎች ላይ” ይላሉ፡፡

የዛሬ አራት ወር የጀርመን ሺፐርድ ውሻቸው ወልዳ ወንዶች ቡቻላዎችን በ900 ብር፣ ሴቶቹን ደግሞ በአንድ ሺ ብር ይሸጡ እንደ ነበር ታይተዋል፡፡ ምንአልባትም በ99 ዓመት ዕድሜ ገንዘብ የሚሠራየመጀመሪያው የዓማችን ሰው ሳይሁኑ አይቀርም፡፡

እኝህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ መቶ አመት ሊሞላቸው ሦስት ወር ብቻ ሲቀራቸው በድንገተኛ ሕመም መስከረም 23 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው መስከረም 25 ቀን በጳውሎስ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን አስከሪናቸው በክብር አርፏል፡፡

እንዲህ አይነት ጀግና ሲያርፉያገለገሏት ሀገራቸው የጀግና አቀባበር ልታደርግላቸው በተገባ ነበር፤ ነገር ግን የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ያለፈው ታሪኳን እና ባለውለታዎቿን እረስታ እነሱም የዛሪቱን ኢትዮጵያ ረስተው በብቸኝነት ኖረው አንድባንድ ሁሉም በየተራ ለዘላለሙ እየተለዩን ሄዱ፡፡

ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝነሸ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!

mulugetahaile123@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Social Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule