ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። ዛሬ የተሰበሰበው የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው በወንጀል የተጠረጠሩ የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል። በዚህም መሰረት፦ 1. ደብረጸዮን ገብረሚካኤል 2. አስመላሽ … [Read more...] about የበረኻ ወንበዴዎቹ ያለከመከሰስ መብት ተነሳ
Politics
የፈረሰውን የክልል መስተዳድር በፈረሰው ስሙ መጥራት ሕገወጥነት ነው
ያለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በህወሃት የሚመራውን የትግራይ ክልል መስተዳድር አፍርሶታል። ምክር ቤቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የትግራይ ክልል በክልሉ በሚገኘው እና በአገር መከላከያ ሰራዊት ስር ባለው በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነው ብሏል። ምክር ቤቱ ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ውሳኔ አሳልፏል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ያከናውናቸዋል ተብሎ ከተሰጡት ስራዎች መካከልም ሀ) አስፈፃሚ አካሉን ይመራል፣ ያስተባብራል፤ ለ) የጊዜያዊ አስተዳደሩን ኃላፊዎች ይመድባል፤ ሐ) ሕግና ሥርዓት መከበሩን … [Read more...] about የፈረሰውን የክልል መስተዳድር በፈረሰው ስሙ መጥራት ሕገወጥነት ነው
በጉጂ ዞን በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ
በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት መደምሰሳቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ኡዶ ተናግረዋል። በተጨማሪም በእርምጃው 17 የኦነግ ሸኔ አባላት መቁሰላቸውን እና የቡድኑ 13 አባላት ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልፀዋል። እርምጃው የተወሰደው የፀጥታ አካላት እና ህብረተሰቡ በጥምረት በሰሩት ስራ እንደሆነ መናገራቸውን ከኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ከአጥፊው ህወሓት ቡድን ተላላኪዎች በተለያዩ አካካባዎች የሽብር ጥቃት ለማድረስ ተልዕኮ ወስደው በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ሰር መዋላቸውን ደግሞ የጉጂ ዞን የፀጥታና አስተዳዳር ቢሮ ኃላፊ አቶ ዋሌ ዱንጎ ተናግረዋል። የዞኑ የፀጥታ አካላት በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ወረዳዎች እና ከተሞች እስካሁን ባደረጉት … [Read more...] about በጉጂ ዞን በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ
የሶስቱ ቀናት ፈታኝ ተጋድሎ በብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አንደበት
ዳንሻ ከተማ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ አምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር ካምፕ ጊቢ ውስጥ የመከላከያ መኪናዎች በጥይት ተበሳስተው ይታያሉ። መስታወታቸው ረግፏል፤ ዛፎቹም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፤ መጥረቢያ እንጂ የጥይት ውርጅብኝ የቆረጣቸው አይመስሉም። የግንብና ቆርቆሮ ቤቶች እንደ ወንፊት ተበሳስተዋል። የጥይቶች ቀላሃ እንደ ጠጠር ተብትኗል። ዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2013ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት አካባቢ በዳንሻ ከተማ ያልተጠበቀ፣ አሳዛኝ፣ አስደጋጭ ድርጊት ነው የተፈጸመው። በከተማዋ የሚገኘው የሰሜን ዕዝ የአምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር የተደገሰለትን ጥቃት አያውቅም። በመካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ስታፍ ውስጥ የሚሰሩት መደበኛ ስራቸውን ከውነው እንቅልፍ ላይ ናቸው። በዚህ ምሽት ግን የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ወደ ካምፑ ዘለቁ፤ ብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አድማሱን … [Read more...] about የሶስቱ ቀናት ፈታኝ ተጋድሎ በብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አንደበት
የሰሜን ዕዝ እንዴት ሊጥቃ እንደቻለና ወንበዴዎቹ የፈጸሙት ሰቅጣጭ ግፍ
የዓይን ምስክሮች በሰሜን ዕዝ ላይ ስለተፈጸመው ጥቂቱን ሲናግሩ እንዲህ ይላሉ፤ “ወደ ሰላሳ የሚጠጉ በሰሜን ዕዝ ውስጥ የሚገኙትን ወታደሮችን ገድለው፤ ልብሳቸውን አውልቀው፤ አስከሬናቸውን አንድ ላይ ከምረው ሌሊቱን ሲጨፍሩ አደሩ፤ አሁንም ድረስ አስከሬናቸው አልተቀበረም፤ አሞራና ጅብ እየበላው ነው።” ጄኔራል ባጫ ደበሌ ሰሞኑን አካባቢውን ቃኝተው ከተመለሱ በኋላ ሲናገሩ፤ “የታፈኑ አመራርና ወታደሮችን ጁንታው ልብሳቸውን አወላልቆ ራቁታቸውን ወደ ሻዕቢያ ሂዱ ብሎ ሰዷቸዋል፤ የባዕድ ጦር ልብስ ነው ያለበሳቸው፤ በመከላከያ ውስጥ ያሉ ትግርኛ ተናጋሪዎች የጁንታው ኔትዎርኮች ናቸው ጥቃቱን ያቀናጁት፤ … የተረሸኑ የመከላከያ አባላት ዘረኛው ጁንታ የሟቾችን አልባሳት አውልቆ ጸሃይ ላይ ለቀናት በማስጣት እንዲፈንዳዳ አድርጓል፤ የሌሎቹን አስከሬንም እንዳይቀበሩ በማድረግ ብዙዎች በጅብ … [Read more...] about የሰሜን ዕዝ እንዴት ሊጥቃ እንደቻለና ወንበዴዎቹ የፈጸሙት ሰቅጣጭ ግፍ
ህጻናትን የሚማግደው የሌቦቹ ጀርባ
አዲሱ ህወሃት በአሮጌ አቁማዳ በትግራይ መቀሌ መሽገው የ13 አመት ልጅ እየመለመሉ ስልጠና ሲሰጡ የከረሙትና ትላንት በመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት እንዲፈፀም ያደረጉት ሁለቱ ሙሰኛና የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ጄኔራሎች በፎቶው የሚታዩት ናቸው! ብ/ጄ ተክለብርሃን ወ/አረጋይ፤ የዶ/ር ዐቢይ አስተዳደር ወደ ስልጣን ሲመጣ “ተደምሪያለሁ” በማለት ጊዜ ገዝቶ፤ ሚስቱንና ሶስት ሴት ልጆቹን አሜሪካ ወስዶ፤ ቤት ገዝቶ፤ አመቻችቶ፤ እንዲሁም ከመጀመሪያ ሚስቱ የወለደው ዳንኤል የተባለውን ልጁ በካናዳ እንዲኖር ያደረገው ተክለብርሃን፤ ከአሜሪካ ከተመለሰ በኋላ ወደ መቀሌ ሸሸ። ሁለት ትላልቅ ህንፃዎች በመገናኛ ወደ ሃያት በሚወስደው መንገድ ያሉት (ተገትረው የቀሩ) በኦሮሚያ በርካታ መሬቶች የሸጠ፣ ለበርካታ ዘመዶቹ በሃብት ጥግ ያደረሰ ሙሰኛ ነው! ሁለተኛው ብ/ጀነራል ኃ/ሥላሴ … [Read more...] about ህጻናትን የሚማግደው የሌቦቹ ጀርባ
መንግሥት ከዜጎች የተግባር ድጋፍ ጠየቀ
ባለፉት 29ዓመታት ከተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆነ ከሲቪክና ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተሰምቶ በማያውቅ በሚያስብል ቁመና እና ክብደት፤ ወደፊት በታሪክ በሚጠቀስ መልኩ የዜጎችን የተግባር ድጋፍ የሚጠይቅ መግለጫ ከመንግሥት ተሰምቷል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከመንግሥት የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝቦች ከሁለት ዓመታት በፊት ግንባራቸውን ለጥይት፣ ደረታቸውን ለጦር ሰጥተው አደባባይ የወጡት የይስሙላ ፌዴራሊዝም ወገባቸውን አጉብጦት፣ ተስፋቸውን አጨልሞት ነው። ጥቂቶች ዜጎችን እያፈኑና እነርሱ እየከበሩ መምጣታቸው ቁጣቸውን አገዘፈው። ኢትዮጵያዊያን አገራቸው ሆና ለማየት ከሚያልሙት እጅግ እየራቀ መምጣት የቁጣቸውን ኃይል አገዘፈው። እውነተኛ የፌዴራል ስርዓትን ለመተግበር ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ዜጎች በጋራ የሚሳተፉበትና ተጠቃሚ የሚሆኑበት … [Read more...] about መንግሥት ከዜጎች የተግባር ድጋፍ ጠየቀ
የትህነግ አዲሱ ሤራ – አማራን በውክልና እልህ ውስጥ መክተት
* የአማራ ክልል ሰላም መሆን ለትህነግ ሤራ ስኬት ዕንቅፋት መሆኑ ተገመገመ ስብሃት ነጋ የሚባለው የትህነግ (ህወሃት) ማፊያ ቡድን አውራ ገና ወደ በረሃ ከመግባቱ በፊት አዲስ አበባ ፒያሳ ከገብረ ትንሳኤ ኬክ ቤት ዝቅ ብሎ ፍሎሪዳ ቡና ቤት መጠጥ ጠግቦ ሲወጣ ሽንት ያዘው። ከዚያም ከፍሎሪዳ እንደወጣ ያለው አደባባይ ላይ ለመሽናት አብሮት ከነበረው ባልደረባው ጋር በመሆን በሞቅታ እያወጋ ተጠጋ። አደባባዩ ላይ ሲሸና እየገለፈጠ “አማራ ላይ እንሽና” ማለቱን በወቅቱ አብሮት ከነበረው ሰው በጀብድ ሲወራ መስማቱን የመረጃ ምንጫችን ይናገራል። ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ብሎ በመሰየም አገር ሲያተራምስና ሲዘርፍ ኖሮ መንግሥት እንዲሆን ባዕዳን ኢትዮጵያ አናት ላይ አስቀምጠውት የነበረው የጥቂት ወንበዴዎች ጥርቅም ከጅምሩ የአማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት … [Read more...] about የትህነግ አዲሱ ሤራ – አማራን በውክልና እልህ ውስጥ መክተት
አዲሱ የኢንሳ አርማ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የቀድሞዉን አርማ የቀየረ ሲሆን የቀድሞውን የኤጀንሲዉን አርማ (logo) እና ብራንዲንግ ለመቀየር ዲዛይኑን ለመስራት እንደ መነሻ የተወሰዱ ሃሳብ በአዲስ መልክ ከተሻሻለዉ የተቋሙ ተልዕኮ እና ራዕይ ጋር በማዛመድ የተሰራ ነዉ። ከእነዚህም ውስጥ በዋነኝነት ጋሻ (Shield)፡ ሳይበር(Cyber Security)፡ ቁልፍ (Key)፡የንስር አይን (An Eagle Eye)፡ የትክክል ምልክት (Right sign) የሚባሉትን ሃሳቦች አካቷል። ለተመረጠው የአርማ (logo) ዲዛይን ማብራራያ እንደ ሚከተለው ቀርቧል። የቀድሞዉ አርማ 1 ጋሻ (Shield) በኢትዮጵያ ታሪክ ብሎም በዓለም አቀፍ ታሪኮች ጥቃትን የመከላከያ መሳሪያ ቀዳሚ ተደርጎ የሚወሰደው አንዱ ጋሻ ነው፤ ስለዚህም በአርማው ላይ የሚታየው ጋሻ ማንኛውም አይነት ጥቃትን በብቃት መከላከል … [Read more...] about አዲሱ የኢንሳ አርማ
ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለትግራይ የበጀት ገንዘብ አይለቀቅም
ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልሉ የሚገኙ የካቢኔ አባላት ህጋዊ ባልሆነ ምርጫ ተመርጠናል በሚል የሀገሪቱን ህገ መንግሥት በመጣሳቸው አሁን ባለው ሁኔታ የገንዘብ ሚኒስቴር ለትግራይ ክልል መንግሥት በጀት እንደማይለቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናገሩ። በትግራይ ክልል ለሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በኩል በተጠና ሁኔታ እንዲደርሳቸው ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል። ይህ ለሁለተኛው ሩብ ዓመት (ጥቅምት-ህዳር-ታህሣሥ) ከፌዴራል ለክልሎች የሚለቀቅ በጀት እንደሆነ ይታወቃል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለትግራይ የበጀት ገንዘብ አይለቀቅም










