
ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ የጦር ኃይሎች ዋና አዛዡ ዐቢይ አህመድ ጄኔራሎቻቸውን በቅጽል ስም በመጥራት ለኢትዮጵያ የሰሩትን ውለታ በዚህ መልኩ አወድሰዋል፤
1. ድል ቁርሱ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ
2. ትንታጉ ሌ/ጀነራል አበባዉ ታደሰ
3. ነበልባሉ ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ
4. ሀገር ወዳዱ ሌ/ጀነራል ዮሃንስ ገብረመስቀል
5. የወገን አቅም ገንቢዉ ሌ/ጀነራል ሀሰን ኢብራሂም
6. ግስላዉ ሌ/ጀነራል ጌታቸዉ ጉዲና
7. አነፍናፊዉ ሌ/ጀነራል አስራት ዲናሮ
8. የጦርነት ሊቁ ሜ/ጀነራል አለምሸት ደግፌ
9. ሰዉ ሀይል አመጋጋቢ ሜ/ጀነራል ሀጫሉ ሸለማ
10. አይበገሬዉ ሜ/ጀነራል ዘዉዱ በላይ
11. ሳተናዉ ሜ/ጀነራል በላይ ሥዩም
12. ልበ ቆራጡ ሜ/ጀነራል መሰለ መሰረት
13. ሎጂስቲክስ አሳላጩ ሜጀር ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል
14. ንስሩ ሜ/ጀነራል ሹማ አብደታ
15. አርዕድ አንቀጥቅጡ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ
16. ነጎድጓዱ ሜ/ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ
17. ንስሩ ሜ/ጀነራል ብርሃኑ በቀለ
18. ካርታን እንደ ምድር አንባቢዉ ብ/ጀነራል ተስፋዬ አያሌዉ
19. ጀግናዉ ብ/ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱ
20. ጀግናዉ ብ/ጀነራል ግርማ ከበበዉ
21. ቆራጡ ብ/ጀነራል ናስር አባዲጋ እና ሌሎችም።
ይህ ማለት ሌሎች ታላላቅ ጀብድ የፈጸሙትንና የላቀ የጀግንነት ተግባር ያከናወኑትን የበታች መኮንኖች በመዘንጋት እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply