“ስብሃትን “አቦይ” አልላቸውም … እንዲህ ዓይነት አባት አልመኝም” ጄኔራል ባጫ የጁንታው ፈጣሪና መሪ ስብሃት ነጋ በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶ ሲስቁ ታይተዋል። በርካቶችም ስብሃት ምን አሉ በሚል ሲነጋገሩ ነበር። ሌፍተናንት ጄኔራል ባጫ ደበሌ እንደገለጹት ስብሃት ከተያዙ በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል። ስብሃት በተያዙበት ሰዓት ለከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች፣ “እኛ እኮ ከሞትን ቆይተናል“ የሚል አስተያየት እንደሰጡ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ስብሃት ከመያዛቸው አስቀድሞ “ቢያዙ ምን ይሉ ይሆን“ ብለው ጄነራሎቹ ይወያዩ እንደነበር የገለጹት ሌፍተናንት ጄነራል ባጫ “ግለሰቡ ቢያዙ ሕገ መንግሥቱ ጥሩ ነው ፤ ሕገ መንግሥቱ እንደዚህ ነው… ብለው ነው የሚያወሩት” የሚል ግምት በጄኔራሎቹ ሀሳብ … [Read more...] about ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው
Politics
የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል?
ከህወሀት መደምሰስ በኋላ የብልጽግና ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን ጥያቄ ኢትዮጵያውያን መጠየቅ የጀመሩት የአገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌን መቆጣጠሩን የሚያበስረው ዜና ከተሰማ ሰአት አንስቶ ነው። ከዚህ የድል ዜና በኋላ ብዙዎች የዜጎች መፈናቀል እና የፖለቲካ ትኩሳት የሚፈጥራቸው አሰቃቂ ክስተቶችን ከመስማት እንገላገላለን በሚል ተስፋ አድርገው ነበር። ለመሆኑ አገር እየመራ ያለው የቀድሞው ኢህአዴግ የአሁኑ ብልጽግና ፓርቲ ከህወሀት መደምሰስ በኋላ ፈተናዎቹ ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ኢትዮ ኤፍ ኤም በፖለቲካ ነክ ጉዳዮች ላይ ትንታኔ በመስጠት ከሚታወቁት ዶክተር አለማየሁ አረዳ ጋር ቆይታ አደርጓል። እንደ ዶ/ር አለማየሁ ገለጸ ህወሀት በአካል ቢወገድም የዘረጋው አጠቃላይ ስርአት፣አስተሳሰቡና የመንፈስ ልጆቹ የገዢው ፓርቲ ፈተና ይሆናሉ ብለዋል። ይህ … [Read more...] about የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል?
ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ
ጌታቸው ረዳና መሰል የህወሓት ጁንታዎች ይጠቀሙባቸው የነበሩ ከ40 በላይ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው መያዛቸው ተገለጸ። የጁንታው ቃል አቀባይ የሆነው ጌታቸው ረዳና መሰሎቹ ከመከላከያ ሰራዊት የተሰነዘረባቸውን ጥቃት ለማምለጥ ሲጠቀሙባቸው የነበሩት እነዚሁ ተሽከርካሪዎች በሀገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር መግባታቸውን የ32ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ አስታውቀዋል። እንደ ኮሎኔል ደጀኔ ገለጻ፤ ተሽከርካሪዎቹ የተያዙት ከማይጨው 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዴላ ወረዳ ነው። ተሽከርካሪዎቹ ውስጥ በተደረገው ፍተሻም የከሀዲው ቡድን አመራር አባላት መታወቂያ፣ ፓስፖርትና የተለያዩ የግል ሰነዶቻቸው መገኘታቸውን ኮሎኔል ደጀኔ አስታውቀዋል። የግል ሰነድ ከተገኘባቸው የጁንታው አባላት መካከል የቀድሞው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር … [Read more...] about ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ
“ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ
የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዳንሻ ከተማ በመሰባሰብ በአማራ ክልል የመስተዳደር ጥያቄያቸው አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኝ በህዝባዊ ሰልፍ ጠይቀዋል። የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዳንሻ ከተማ በመገኘት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ጥያቄያችን የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ አደባባይ በመውጣት ድምፃቸወን አሰምተዋል። ነዋሪዎቹ በህወሃት የግፍ አገዛዝ በጉልበት ወደትግራይ ክልል ተካለው ሲፈፀምባቸው የቆየው ግፍ ይበቃል ብለዋል። በዚህ የህልውና ጉዳይ በሆነው የህዝብ ትእይንት የተገኙት የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሠብሳቢ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መልእክት አስተላልፈዋል። ኮሎኔል ደመቀ ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጅ ሠጥተን አንጠይቅም ብለዋል። አሁንም ቢሆን በወልቃይት ጉዳይ ሌላ ጁንታ አይኖርም ብለን ሳንዘናጋ ሁላችንም … [Read more...] about “ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ
ፌዴራል ፖሊስ መቀሌ ገባ፤ በትግራይ ሰላም እያስጠበቀ ነው
የአክሱም ጽዮን ማሪያም ንግስ በዓልም በሰላም ተከናውኗል በጁንታው ላይ የተወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ በድል መጠናቀቁን ተከትሎ የፌዴራል ፖሊስ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ገብቶ የኅብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በማስከበር ላይ እንደሆነ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የጽዮን ማሪያም ንግስም በሰላም መከናወኑ ተገልጿል። ከሀዲው የህወሓት ቡድን የሀገር ሉዓላዊነትን በመዳፈር በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ በፈፀመው ጥቃት የተጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በድል መጠናቀቁን ያስታወሰው ኮሚሽሽኑ፤ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ የፌዴራል ፖሊስ ገብቶ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት እያስከበር ይገኛል። ህብረተሰቡም መደበኛ የዕለት ተዕለት ኑሮውን መጀመሩ ተገልጿል። ለተመሳሳይ የጸጥታ ማስከበር ስራ ወደ … [Read more...] about ፌዴራል ፖሊስ መቀሌ ገባ፤ በትግራይ ሰላም እያስጠበቀ ነው
ለደቡብ ሱዳን ሰላም ማጣት የስዩም መስፍን ሤራ
5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሰጡት ማብራሪያ፤ ከሀዲው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን በክልልና በዘር ከመከፋፈል አልፎ ጎረቤት ሀገራትን ጭምር በጎሳና በዘር ሲያባላ እንደነበር ተናግረዋል። “ሶማሊያ ስንሄድ እኛ እኮ እናንተን አናምናችሁም፤ በክልልና በጎሳ ከፋፍላችሁ የምታባሉን እናንተ ናችሁ፤ የእናንተ መንግስት ነው ይህን የሚያደርገን፤ በጣም ነው የምንጠላችሁ” በማለት ሳይደብቁ ኢትዮጵያን ይወቅሱ ነበር ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። “በተመሳሳይ ደቡብ ሱዳን ስንሄድም አሁን ላይ በሀገራችን እየተባላንበት ያለው ጉዳይ የእናንተው ውጤት ነው” በማለት ኢትዮጵያን እንደሚወቅሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ አብራርተዋል። “በኢጋድ ውስጥ ስዩም መስፍን የሚባለውን ሰውዬ መድባችሁ ከፋፍሎን አባልቶን … [Read more...] about ለደቡብ ሱዳን ሰላም ማጣት የስዩም መስፍን ሤራ
መለዮ ለባሾቹ የቁርጥ ቀን ልጆች
ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ የጦር ኃይሎች ዋና አዛዡ ዐቢይ አህመድ ጄኔራሎቻቸውን በቅጽል ስም በመጥራት ለኢትዮጵያ የሰሩትን ውለታ በዚህ መልኩ አወድሰዋል፤ 1. ድል ቁርሱ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ 2. ትንታጉ ሌ/ጀነራል አበባዉ ታደሰ 3. ነበልባሉ ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ 4. ሀገር ወዳዱ ሌ/ጀነራል ዮሃንስ ገብረመስቀል 5. የወገን አቅም ገንቢዉ ሌ/ጀነራል ሀሰን ኢብራሂም 6. ግስላዉ ሌ/ጀነራል ጌታቸዉ ጉዲና 7. አነፍናፊዉ ሌ/ጀነራል አስራት ዲናሮ 8. የጦርነት ሊቁ ሜ/ጀነራል አለምሸት ደግፌ 9. ሰዉ ሀይል አመጋጋቢ ሜ/ጀነራል ሀጫሉ ሸለማ 10. አይበገሬዉ ሜ/ጀነራል ዘዉዱ በላይ 11. ሳተናዉ ሜ/ጀነራል በላይ ሥዩም 12. ልበ ቆራጡ ሜ/ጀነራል መሰለ መሰረት 13. ሎጂስቲክስ አሳላጩ ሜጀር ጀኔራል አብዱራህማን … [Read more...] about መለዮ ለባሾቹ የቁርጥ ቀን ልጆች
ነቀርሳው ህወሓት ተነቀለ!
በትግራይ ክልል ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ ለ25 ቀናት በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቡድንና በመከላከያ ሠራዊቱ መካከል ሲደረግ የሰነበተው ውጊያ፣ ቅዳሜ ኅዳር 19 ቀን ከሰዓት በኋላ የመከላከያ ሠራዊቱ የክልሉ ዋና ከተማ መቀሌን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ(ዶ/ር) እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አረጋግጠዋል። መከላከያ ሠራዊቱ ባካሄደው ዘመቻ ንጹኃን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑና ቅርሶች ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አስታውቀዋል። ሠራዊቱ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዴት ከተማዋን መቆጣጠር ይቻላል በሚለው ላይ ኅዳር 18 ቀን ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጫቸው ያስታወሱት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ፣ … [Read more...] about ነቀርሳው ህወሓት ተነቀለ!
ጃዋር “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ”
በቅርቡ ጃዋር መሐመድን ማረሚያ ቤት ድረስ ሄደው ከጎበኙ መካከል አንደኛው ከጃዋር አንደበት የሰሙትን ማመን እንዳቃታቸው ይገልጻሉ። ጃዋር ያለፈበትን መንገድ እያሰላ በጸጸት ውስጥ ያለ ይመስላል። በአጭር ጉብኝታቸው “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ” በማለት ቅዝዝ ብሎ የነገራቸው ጠያቂው እሱን ከተሰናበቱ በኋላ ነበር ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ሁኔታውን ያጫወቱት። ለተለያዩ ሚዲያዎችና በጃዋር ዙሪያ ለነበሩ እንቅስቃሴዎች እንግዳ ያልሆኑት እኚሁ ሰው ለጎልጉል ዘጋቢ መነሻ ሃሳብ ከሰጡ በኋላ ዘጋቢያችን በርካታ መረጃዎችን አሰባስቦ የሚከተለውን ሪፖርት አዘጋጅቷል። በሪፖርቱ አስቀድሞ የተሰባሰቡና ጊዜ ሲጠብቁ የነበሩ መረጃዎች ተካተዋል። ሪፖርቱ አንባቢያን የራሳቸውን ስሌት እንዲያሰሉና አቅም ያላቸው ይበልጥ ጉዳዩን እንዲያጠኑት የሚያነሳሳ ይሆናል። ጃዋርና “የአንድነት ኃይሎች” የት፣ … [Read more...] about ጃዋር “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ”
በ96 የህወሃት ወንበዴዎች ላይ የፍርድ ቤት ማዘዣ ወጣባቸው
የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የጁንታው ሕወሓት ቡድን ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የጥፋት ቡድኑ አባላት ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች ፀረ-ሰላም ሃይሎች ጋር በመቀናጀትም ከተለያዩ ክልሎች አገርን የማፍረስ ተልዕኮ ያላቸውን ኃይሎች በመመልመል ትግራይ ክልል ድረስ በመውሰድ ለእኩይ ተልዕኮቸው ስኬት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን በማድረግ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ብሄርን ከብሄር በማጋጨት እና በሃይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በማድረግ በርካታ ንፅሁን ዜጎች እንዲገደሉ፣ በአካልና በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡ እነዚህ የሀገር ህልውናን አደጋ ላይ በመጣል እንዲሁም ህገ-መንግስቱንና … [Read more...] about በ96 የህወሃት ወንበዴዎች ላይ የፍርድ ቤት ማዘዣ ወጣባቸው










